ሠላሳ አንደኛ ዓመት ቍጥር ፳፬
ነጋሪት ጋዜጣ ።
የጋዜጣው ፡ ዋጋ ፤
ባገር ውስጥ
ባመት $ 6 በ፮ ወር ' $ 3
ለውጭ አገር እጥፍ ' ይሆናል "
ማ ው ጫ ። ፲፱፻፷፬ ዓ. ም.
የሕግ ክፍል ማስታወቂያ ቍጥር ፬፻፳፩፲፱፻፷፬ ዓ. ም.
ለመታሰቢያ የሚወጣ የብር ገንዘብ ደንብ ገጽ ፩፻፸፮ ዓ. ም.
የሕግ ክፍል ማስታወቂያ ቍጥር ፬፻፳፪ / ፲፱፻፷፫ ለመታሰቢያ የሚወጣ ገንዘብ ደንብ.
ገጽ ፩፻፸፯
ማረሚያ ቍጥር ፸፮ ፲፱፻፷፬ ዓ. ም.
በኢትዮጵያ ንጉሠ ' ነገሥት ፡ መንግሥት ፡ በጽሕፈት ፡ ሚኒስቴር ፡ ተጠባባቂነት የቆመ ።
የአማርኛ መርሐ ልሳን የተቋቋመበትን ትእዛዝ ቍጥር ለማረም
ገጽ ፩፻፹፩
የሕግ ክፍል ማስታወቂያ ቍጥር ፬፻፳፩ ፲፱፻፷፬ ዓ. ም. በ፲፱፻፶፭ ዓ. ም. የወጣውን የገንዘብና የባንክ ሥራ አዋጅ መሠረት በማድረግ የወጣ ደንብ ።
፩ ፤ አውጭው ባለሥልጣን ፤
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በ፲፱፻፶፭ ዓ. ም. በቍጥር ፪፻፮ በወጣው የገንዘብና የባንክ ሥራ አዋጅ (እንደተሻሻለ) በአንቀጽ ፱ በንዑስ አንቀጽ ፫ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ፪ ፤ አጭር አርእስት ፤
ይህ ደንብ « በ፲፱፻፷፬ ዓም ለመታሰቢያ ገንዘብ ደንብ » ተብሎ ሊጠቀስ ይቻላል
፫ ፤ ዩ q ታሰቢያ ገንዘብ ማውጣት ፤
ባንኩ የሚያወጣው ልዩ የመታሰቢያ የብር ገንዘብ (ከዚህ በኋላ በ፲፱፻፷፬ ዓ. ም. ለመታሰቢያ የሚወጣ ገንዘብ እየተባለ የሚጠራው) የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ክብር መታሰቢያ ነው ። ፤ ቅርጽና ጽሑፍ ፤
በ፲፱፻፷፬ ዓ.ም. ለመታሰቢያ የሚወጣው የብር ገንዘብ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ቅርጽና ጽሑፍ የያዘ ይሆናል " ፩ በስተፊቱ ላይ ፤
ሀ በመካከሉ የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ብሩህ ገጽ ምስል ይገኝበታል ፤
ለ ዙሪያ ክብነቱን ተከትሎ በላይኛው ጠርዝ ላይ በአንድ (፩) መሥመር ፤
« ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ » የሚሉት ቃላት በአማርኛ ቋንቋና ፊደል ይጻፋሉ ፤
ሐ ዙሪያ ክብነቱን ተከትሎ በስተግርጌ በኩል በአ ንድ (፩) መሥመር
ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ » የሚሉት ቃላት በእንግ
ሊዝኛ ቋንቋና በላቲን ፊደል ይጸፋሉ 3
አዲስ አበባ ሐምሌ ፲፫ ቀን ፲፱፻፷፬ ዓ. ም.
ቢያንስ ' በወር ' አንድ ' ጊዜ ' ይታተማል
የፖስታ ▪ ሣጥን ቍጥር º ፩ሺ፫፻፰፬ (1364)