ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ርታማነት ለማሳደግ የተለያዩ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ስምንተኛ ዓመት ቁጥር ፴፮ አዲስ አበባ - ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፲፬ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፷፰ ፲፱፻፲፬ ዓም የብሔራዊ የግብርና ግብዓት ባለሥልጣን ማቋቋሚያ ገጽ ፲፱፻፯ አዋጅ ቁጥር ፪፻፳፰ ፲፱፻፲፬ ብሔራዊ የግብርና ግብዓት ባለሥልጣንን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ ለሀገሪቱ ዕድገትና ልማት መሠረት የሆነውን የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖሚ ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ፣ ኣርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ ከዚሁ ተጠቃሚ መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ በመሆኑ ፤ የግብርናውን ዘርፍ ምርትና የግብርና ግብዓቶችን በጥራት ፣ በዓይነትና በበቂ መጠን በማም ረትና ፣ በማቅረብ በዘርፉ ለተሰማራው ተጠቃሚ እንዲዳረስ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ ፤ በግብርና ግብዓት ማምረት ፣ ማቅረብ ፣ ሥርጭትና ንግድ ተግባር ላይ እንዲሳተፉ የግል ባለሀብቶች ፣ መንግሥታዊ ድርጅ ቶችና ሌሎችም አግባብ ያላቸውን በማበረታታት የዘርፉን የሥራ ሂደት ማጠናከር በማስፈለጉ ፤ የግብርናውን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ቀጣይነት ያለው ልማት በሀገሪቱ ለማረጋገጥ የግብርና ግብዓቶችን በሥርዓት አስተባብሮና አቀናጅቶ መምራት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፤ በአጠቃላይ የአገሪቱን ወቅታዊና ዘላቂ የግብርና ልማት ፍላጐት ለማሟላት የሚያግዙ የግብርና ግብዓቶች አግባብ ባላቸው ሕጎችና ደንቦች መሠረት ጥራታቸው ተጠብቆ በወቅቱ እንዲቀርቡ በመከታተልና ቴክኖሎጂዎችንም ለማስፋፋት የሚያስችል አቅምና ክህሎት የመገንባት ፍላጎት በመኖሩና ይህንንም ሥራ የሚያስተባብርና የሚከታተል ኣካል ማቋቋም በማስፈለጉ ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ / ፩ / መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ያ ሰዓት ባለሥልጣን ከዚህ በኋላ | 3. Establishment ገጽ ፩ሺ፪፻፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፫ ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም : ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የብሔራዊ የግብርና ግብዓት ባለሥልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፪፻፷፮ / ፲፱፻፲፬ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ፣ ፩ . “ የግብርና ግብዓት ” ማለት የግብርናውን ምርትና ምር ታማነት ለማሳደግ ለገበያ የሚቀርቡ የዕፅዋት ዘር ፣ ማዳበሪያና ፀረ ተባይ ናቸው ፣ ፪ . “ የዕፅዋት ዘር ” ማለት እውን ዘር ፣ አኩራች ፣ ቅጥፍ ተክል ፣ ወይም ለዕፅዋት ማራባት የሚያገለግል ማንኛውም የተክል ክፍል ወይም አካል ነው ፣ ፫ . “ ማዳበሪያ ” ማለት አንድ ወይም ከአንድ በላይ ለተክል ምግብነት የሚውሉ ንጥረ ነገሮችን የያዘ ፣ በተፈጥሮ የሚገኝ ወይም በፋብሪካ የተዘጋጀ የአፈርን ለምነት ለመጠበቅ ወይም ለማሻሻል የሚውል ቁስ ነው ፣ ፬ . “ ፀረ ተባይ ” ማለት ተዛማች ተባይን ሳይጨምር መደበኛ ተባይን ለመከላከል ፣ ወይም ለመቆጣጠር የሚውል የተቀመመ ነገር ፣ የዚሁ ድብልቅ ወይም ሕይወት ያለው የግብርና ግብዓት ነው ፣ ፭ “ ተባይ ” ማለት ጥገኛ በሆነና ባልሆነ መልክ የሚኖሩ ህይወት ያላቸው ነፍሳት ፣ አረምና እፅዋት በሽታ ሆነው በማምረት ፣ በማቀነባበር ፣ በማከማቻ ፣ በማጓጓዣና በግብይት ሂደት በግብርና ምርቶችና ውጤቶች ላይ ጉዳት በማድረስ ምርቱና ጥራቱ እንዲቀንስ ምክንያት የሚሆኑ ሕይወት ያላቸው ነገሮች ናቸው ፣ ፮ . “ ባለሥልጣን ” ማለት ብሔራዊ የግብርና ግብዓት ባለሥ ልጣን ነው ፣ ፯ . “ ሚኒስቴር ” ማለት የገጠር ልማት ሚኒስቴር ነው ። ፫ . መቋቋም ፩ . ብሔራዊ የግብርና “ ባለሥልጣኑ ” እየተባለ የሚጠራ የሕግ ሰውነት ያለው ራሱን የቻለ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል ፣ ፪ . የባለሥልጣኑ ተጠሪነት ለገጠር ልማት ሚኒስቴር ይሆናል ። ዋና መሥሪያ ቤት የባለሥልጣኑ ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ ሆኖ እንደአስፈላ ጊነቱ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች ይኖሩታል ። ፭ ዓላማ የባለሥልጣኑ ዓላማ የሀገሪቱ የግብርና ግብዓቶች ምርት ፣ አቅርቦት ፣ ሥርጭትና ግብይት ቀልጣፋና ውጤታማ በሆነ መንገድ መከናወኑን ማረጋገጥ ፣ በዘርፉም የአቅም ግንባታ ሥራን በመሥራት አምራቹንና ሸማቹን ኅብረተሰብ ተጠቃሚማድረግ ይሆናል ። ፮ . የባለሥልጣኑ ሥልጣንና ተግባር ባለሥልጣኑ ቀጥሎ የተመለከቱት ሥልጣንና ተግባራት | 6 . Powers and Duties of the Authority ይኖሩታል ፣ ፩ . የአገሪቱን የገጠር ልማት ፖሊሲዎችንና እስትራቴጂ ዎችን መሠረት በማድረግ የግብርና ግብዓት ፖሊሲና እስትራቴጂአዘጋጅቶያቀርባል ፣ ሲጸድቅም አፈፃፀሙን ይከታተላል ፣ ፪ አግባብነት ካላቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር ግንኙነት በመፍጠር የግብርና ግብዓት ሕጎች ተግባር ላይ እንዲውሉ ያደርጋል ፣ ፩ . በመንግሥት የሚሾም አንድ ዋና ሥራ አስኪያጅ \ ገጽ ፩ሺ፪፻፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፮ ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም • ፫ ለግብርና ግብዓት ግምገማና ማጽደቅ የሚረዱ መመሪያ ዎችንና የአሠራር ሥርዓቶችን ያወጣል ፣ ሥራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል ፣ የሀገሪቱን የልማት ፍላጎት መሠረት ያደረጉ የግብርና ግብዓት ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች እንዲዘጋጁ የሚያ ስችሉ መመሪያዎችና የአሠራር ሥርዓት ያወጣል ፣ ኣግባብነት ያላቸው ሕጐች እንደተጠበቁ ሆነው ፣ ወደ ሀገር ውስጥ ለሚገቡም ሆነ ወደ ውጭ ለሚላኩ የግብርና ግብዓቶች ይለፍ ፈቃድ ይሰጣል ፣ ፮ • የግብርና ግብዓት ጥራቱ ተጠብቆ ለተጠቃሚው መሠራ ጨቱን ያረጋግጣል ፣ የግብርና ግብዓት ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ እንዲረዳ የገበያ ፍላጎት ትንበያ ጥናት ያካሂዳል ፣ ፰ የግብርና ግብዓቶች ዋጋን ለማረጋጋት የሚጠቅሙ ጥናቶችን በማካሄድ በመንግሥት መወሰድ ስለሚገ ባቸው እርምጃዎች የውሳኔ ሐሳብ ያቀርባል ፣ የግብርና ግብዓት ምርት ፡ አቅርቦትን ፣ ሥርጭትንና ግብይትን አቅም ለመገንባት አስፈላጊውን እገዛ ያደርጋል ፣ ፲ የግብርና ግብዓት ኢንዱስትሪውን ልማት ለማፋጠን እንዲረዳ በሕዝቡ ዘንድ ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲኖር አስፈላጊውን ያደርጋል ፣ ፲፩ ባለሀብቶች በግብርና ግብዓቶች ምርትና ሥርጭት ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ያበረታታል ፣ ፲፪ የግብርና ግብዓቶችእጥረትን ለመሸፈን እንዲረዳ አግባብ ካላቸው መ / ቤቶች ጋር በመተባበር የአቅርቦቱን አስተማ ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ያመቻቻል ፣ ፲፬ . ውል ይዋዋላል ፣ ይከሳል ፣ ይከሰሳል ፣ የንብረት ባለቤት ይሆናል ፣ ፲፭ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት ለሚሰጠው አገል ግሎት ክፍያ ይሰበስባል ፣ ፲፮ • ዓላማውን ከግብ ለማድረስ አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራትን ያከናውናል ፯ ድርጅታዊ አቋም ፪ አስፈላጊ ሠራተኞች ፣ ይኖሩታል ። የዋና ሥራ አስኪያጁ ሥልጣንና ተግባር የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስኪያጅ በመንግሥት የሚሾም ሆኖ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፤ ፩ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ( ፪ ) ላይ የተጠቀሱትን የባለሥል ጣኑን ሥልጣንና ተግባራት በበላይነት ይመራል ፣ ይፈጽማል ፣ ፪ የባለሥልጣኑን ዓመታዊ የሥራ ፕሮግራምና በጀት በማዘጋጀት ለገጠር ልማት ሚኒስቴር ያቀርባል ፣ ፫ በመንግሥት የፀደቀው በጀት በሥራ ላይ መዋሉን ይከታተላል ፣ ያረጋግጣል ፣ በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕጎች መሠረት የባለሥል ጣኑን ሠራተኞች ይቀጥራል ፣ ያስተዳድራል ፣ ያሰና ብታል ፣ ፭ ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ባለሥል ጣኑን ይወክላል ፣ ፮ : ለባለሥልጣኑ በተፈቀደለት በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፣ ፯ እንደአስፈላጊነቱ ለሌሎች የባለሥልጣኑ ሠራተኞች ውክልና ይሰጣል ፣ ገጽ ፩ሺ፪፻፲ ፌዴራል ነጋሪት ቁጥር ፴ ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም የባለሥልጣኑ የሥራ አፈጻጸምና የሂሣብ ሪፖርት አጠናቅሮ ለሚኒስቴሩ ያቀርባል ፣ ፱ ከሚኒስቴሩ የሚሰጡ ሌሎች ተጨማሪ ተግባራትን ያከናውናል ። ፱ . በጀት የባለሥልጣኑ በጀት ከሚከተሉት ምንጮች የሚገኝ ይሆናል ፣ ፩ ከመንግሥት የሚመደብ በጀት ፣ ፪ ከተለያዩ ምንጮች ከሚገኙ ዕርዳታዎችና ስጦታዎች ። ፲ ስለሂሣብ መዛግብት ፩ . ባለሥልጣኑ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት ይይዛል ፣ ባለሥልጣኑየሂሣብ መዛግብትን ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ በዋናው ኦዲተር ወይም ዋናው ኦዲተር በሚሰ ይመው ሌላ ኦዲተር እንዲመረመሩ ያደርጋል ። ፲፩ . የተሻሩና ተፈጻሚነት ስለማይኖራቸው ሕጎች ፩ . የሚከተሉት ሕጐች በዚህ አዋጅ ተሽረዋል ፤ ሀ ) የብሔራዊ የዕፅዋት ዘር ኢንዱስትሪ ድርጅት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፵፯ / ፲፱፻፳፯ እንደተ ሻሻለ / ። ለ ) የብሔራዊ የማዳበሪያ ኢንዱስትሪ ኤጀንሲ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፩፻፮ / ፲፱፻፷፯ / እንደተ ሻሻለ / ። ፪ ይህን አዋጅ የሚቃረን ማንኛውም ሕግ ወይም መመሪያ በዚህ አዋጅ ውስጥ የተካተቱ ጉዳዮችን በሚመለከት ተፈጻሚነት አይኖረውም ። ፲፪ ስለመብትና ግዴታ መተላለፍ ፩ . በአዋጅ ቁጥር ፵፯ / ፲፱፻፷፭ / እንደተሻሻለ / ተቋቁሞ የነበረው ብሔራዊ የዕፅዋት ዘር ኢንዱስትሪ ድርጅት መብትና ግዴታ እንዲሁም በዕፅዋት ዘር አዋጅ ቁጥር ፪፻፮ / ፲፱፻፶፪ ለድርጅቱ ተሰጥቶ የነበረው ሥልጣንና ኃላፊነት በዚህ አዋጅ መሠረት ለባለሥልጣኑ ተላልፋል ፣ ፪ በአዋጅ ቁጥር ፩፻፮ / ፲፱፻፷፯ / እንደተሻሻለ / ተቋቁሞ የነበረው የብሔራዊ የማዳበሪያ ኢንዱስትሪ ኤጀንሲ መብትና ግዴታእንዲሁም በማዳበሪያማማረትና ንግድ አዋጅ ቁጥር ፩፻፴፯ / ፲፱፻፵፩ ለኤጀንሲው ተሰጥቶ የነበረው ሥልጣንና ኃላፊነት በዚህ አዋጅ መሠረት ለባለሥልጣኑ ተላልፋል ። ፲፫ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሰኔ ፴ ቀን ፲፱፻፶፬ ዓም ግርማ ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ማረሚያ ቁጥር ፩ / ፲፱፻፲፬ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር ፪፻፷፮ / ፲፱፻፲፬ የሚከተሉት እርማቶች ተደርገውበታል ፤ አንቀጽ ፲፫ ፤ ( መ ) ከገቢ ” ከሚለው ቀጥሉ “ ግብር ” የሚል ቃል ተጨምሮ ይነበብ ። አንቀጽ ፳፯ከንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) ( ሀ ) ቀጥሎ ፤ “ ለ ) ፳ ሺ ብር ” የሚል ተጨምሮ ይነበብ ። ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅትታተመ