×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፮ ፲፱፻፲፮ ዓ.ም የኅብረት ሥራ ማኅበራት አዋጅ ቁጥር ፩፻፯/፲፱፻፵፩ ለማስፈጸም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፮/፲፱፻፮ ዓም

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አሥረኛ ዓመት ቁጥር ፵፯ አዲስ አበባ- ሰኔ ፳፩ ቀን ፲፱፻፲፮ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፮ ፲፱፻፲፮ ዓ.ም የኅብረት ሥራ ማኅበራት አዋጅ ቁጥር ፩፻፵፯ / ፲፱፻፲፩ ለማስፈጸም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፮ / ፲፱፻፶፮ ዓም ገጽ ፪ሺ፮፻፴፩ ሰው የኅብረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፮ / ፲፱፻፲፮ ስለኅብረት ሥራ ማኅበራት አዋጅ አፈጻጸም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሥራ ማኅበራት አዋጅ ቁጥር ሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፷፯ አንቀጽ ፭ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የኅብረት ሥራ ማኅበራት አዋጅ ቁጥር ፩፻፵፯ ፲፱፻፲፩ ለማስፈጸም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፮ / ፲፱፻፲፮ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በቀር በዚህ | 2. Definition ደንብ ውስጥ፡ ፩ ) “ አዋጅ ” ማለት የኅብረት ሥራ ማኅበራት አዋጅ ቁጥር ፩፻፵፯ / ፲፱፻፲፩ ነው ። ፪ ) “ መደበኛ ስብሰባ ” ማለት በአዋጅ ቁጥር ፩፻፵፯ / ፲፩ አንቀጽ ፳፪ ንዑስ አንቀጽ ፩ መሠረት የሚደረግ ጠቅላላ ጉባዔ ማለት ነው ። ፫ ) “ የኅብረት ሥራ ማኅበር ” ማለት በአዋጁ አንቀጽ ፪ ( ፪ ) የተጠቀሰው ትርጉም ይኖረዋል ። ያንዱ ዋጋ 340 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ : ፰ሺ፩ ገጽ ፪ሺ፮፻፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፯ ሰኔ ፳፩ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓ.ም. ፬ ) “ አግባብ ያለው ባለሥልጣን ” ማለት በአዋጅ ቁጥር ፪፻ሮ፬ ፲፱፻፬ አንቀጽ ፪ ( ፩ ) መሠረት የተቋቋመ የኅብረት ሥራ ኮሚሽን እና በየክልሉ የተቋቋሙ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ማደራጃና ማስፋፊያ ቢሮዎችና ጽሕፈት ቤቶችን ይጨመራል ። ፭ ) “ ኅብረት ” ( ዩኒየን ) ማለት ከአንድ በላይየሆኑተመሳሳይ ዓላማ ያላቸው መሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ኅብረት ነው ። ፮ ) “ ፌዴሬሽን ” ማለት ከአንድ በላይ የሆኑ ተመሳሳይ ዓላማ ያላቸው ኅብረቶች ( ዩኒየኖች ) እና የሕብረት ሥራ ማኅበራት ስብስብ ነው ። ፯ ) “ ሊግ ” ማለት የኅብረት ሥራ ማኅበራት በአገር አቀፍ ደረጃ የሚመሠርቱት የኢትዮጵያ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ሊግ ነው ። ክፍል ሁለት ስለ ኅብረት ሥራ ማኅበራት አመሠራረት ፫ የመሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማኅበራት አመሠራረት ፩ ) መሠረታዊ ማኅበር በተወሰነ ኣካባቢ በሚኖሩ ወይም በሚሠሩ ወይም በተወሰነ ሙያ በተሰማሩ ፈቃደኛ ግለሰቦች ይቋቋማል ። የመሥራች አባላት ቁጥር ከአሥር ኣያንስም ። አግባብ ያለው ባለሥልጣን ከኢኮኖሚያዊ ብቃት አኳያ ተመልክቶ የአባላትን መነሻ ቁጥር ለመወሰን የአፋጻጸም መመሪያ ያወጣል ። ፪ ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ መሠረት የሚመሠረት መሠረታዊ ማኅበር የሥራ ክልል በአንድ ክልል ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ክልሎችን የሚሸፍን ሊሆን ይችላል ። ፫ ) በዚህ አንቀጽ በንዑስ አንቀጽ ፪ በተመለከተው የሥራ ክልል ውስጥ ከአንድ በላይየተለያዩ ዓይነቶች መሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ሊመሠረቱ ይችላሉ ። የኅብረት ሥራ ኅብረት ( ዩኒየን ) አመሠራረት ፩ ) የዚህ ሕግና ሌሎች የኅብረት ሥራ ማኅበራትን የሚመ ለከቱ ሕጎች ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ተመሣሣይ ዓላማ ያላቸው መሠረታዊ ማኅበራት የሕብረት ሥራ ኅብረት ( ዩኒየን ) ሊመሠረቱ ይችላሉ ። ፪ ) በዚህ ሕግና በሌሎች ሕጎች የተደነገገው እንደተጠበቁ ሆነው ከኅብረቱ ጋር ተመሣሣይ ተግባር የሚያከናውንና የማኅበሩን መርሆች የተቀበለ ግለሰብ የኅብረቱ ( ዩኒየን ) አባል ሊሆን ይችላል ። የኅብረት ሥራ ፌዴሬሽን አመሠራረት ፩ ) የዚህ አና የሌሎች ሕጎች ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ተመሣሣይ ዓላማ ያላቸው ኅብረቶች በፌዴራል ደረጃ ፌዴሬሽን ሊመሠርቱ ይችላሉ ። ፪ ) የዚህ እና የሌሎች ሕጎች ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ከፌዴሬሽኑ ጋር ተመሣሣይ ተግባር የሚያከናውን የሕብረት ሥራ ማኅበር እና ግለሰብ አባል ሊሆን ይችላል ። ፮ የኅብረት ሥራ ሊግ አመሠራረት ፩ የዚህ እና የሌሎች ሕጎች ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነውመሠረታዊ ኅብረት ሥራማኅበራት ፣ ኅብረቶችእና ፌዴሬሽኖች በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ማኅበራትን የሚወክል ሊግ ሊመሠርቱ ይችላሉ ። 7 ያከናውን የኅብረት ገጽ ፪ሺ፮፻ሣ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፯ ሰኔ ፳፩ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓም : ፪ ) በዚህ አንቀጽ በንዑስ አንቀጽ ፩ መሠረት የሚመሠረት ሊግ ቁጥር ከአንድ ሊበልጥ አይችልም ። ፯ . የሥራ ክልል ፩ ) በዚህ ደንብ አንቀጽ ፬ ወይም ፭ የተመሠረተማንኛውም ኅብረት ወይም ፌዴሬሽን የሥራ ክልል በኅብረቱ ወይም በፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ይወሰናል ። ፪ ) የሊጉ የሥራ ክልል በአገር አቀፍ ደረጃ ይሆናል ። ክፍል ሦስት የኅብረት ሥራ ማኅበራት ተግባራትና ዓይነቶች ፰ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ተግባራት ማናኛውም የኅብረት ሥራ ማኅበር የማምረት ወይም አገል | 8. Functions of Cooperative society ግሎት የመስጠት ወይም የማምረትና አገልግሎት የመስጠት ተግባራት ሊኖሩት ይችላሉ ። ፱ • የማምረት ተግባር የሚያከናውን የኅብረት ሥራ ማኅበር የማምረት ተግባር የሚያከናውን የኅብረት ሥራ ማኅበር በማምረት ሥራ ላይ የተሰማራ ወይም ጥሬ ዕቃ ወደ አላቂ ዕ . የሚቀይር ወይም በከፊል የተሠሩትን ወደ አላቂ ምርትነት የሚቀይር ይሆናል ። ፲ የአገልግሎት ተግባር የሚያከናውን የኅብረት ሥራ ማኅበር የአገልግሎት ተግባር የሚያከናውን የኅብረት ሥራ ማኅበር ለአባላት የተለያዩ አገልግሎቶችን የሚሰጥ ወይም እንዲያገኙ የሚያደርግ ይሆናል ። ፲፩ : የማምረትና የአገልግሎት ተግባር የሚያከናውን የኅብረት ሥራ ማኅበር የማምረትና የአገልግሎት ተግባር ሥራ ማኅበር በዚህ ደንብ በአንቀጽ ፬ እና ፲ የተመለከቱትን ተግባራት በጣምራ የሚያከናውን ይሆናል ። ፲፪ • የኅብረት ሥራ ማኅበራት ዓይነቶች ፩ ) የተለያዩ የኅብረት ሥራ ዓይነቶች ሀገሪቱ በሚኖራት ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ የሥራ ዘርፎች ውስጥ ሊደራጁ ይችላሉ ። ፪ ) የኅብረት ሥራ ማኅበራት ዓይነተኛ መለያ ባሕሪያቸው ፣ በሚሠሩት የሥራ ኣካባቢ ፣ በአመሠራረታቸው ፣ በተግባ ራቸውና በሚኖራቸው የሕጋዊ ሰውነት የሚለይ ይሆናል ። ፫ ) ስለኅብረት ሥራ ማኅበራት ዓይነተኛ ባሕሪያት አግባብ ያለው ባለሥልጣን መመሪያ ያወጣል ። ክፍል አራት ስለ ኅብረት ሥራ ማኅበራት ምዝገባ እንቅስቃሴ • ምዝገባ ፩ ) ሊጉን እና ፌዴሬሽኑን ጨምሮ በብሔራዊ ደረጃ የሚቋቋ ሙትን ዩኒየኖች የኅብረት ሥራ ኮሚሽን ይመዘግባል ። ፪ ) በዚህ ደንብ መሠረት የተመዘገበ ማንኛውም ማኅበር ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ ሕጋዊ ሰውነት ያገኛል ። ፩ ) ማንኛውም አባል ለገዛ . ገጽ ፪ሺ፮የሣባ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ሣጊ ሰኔ ፳፩ ቀን ፲፱የን፮ ዓም ፲፬ . የኅብረት ሥራ ማኅበር መተዳደሪያ ደንብ ስለሚይዛቸው ዝርዝሮች በአዋጁ አንቀጽ ፲፩ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የማን ኛውም የኅብረት ሥራ ማኅበር መተዳደሪያ ደንብ የሚካተ ሉትን መያዝ አለበት፡ ( ሀ ) የማኅበሩን ዓላማ ፡ የኅብረት ሥራ እሴቶችና መርሆች፡ የማኅበሩን አስተዳደራዊ መዋቅር ፧ የማኅበሩን የበጀት ዓመት ፧ ( መ ) የማኅበሩን ገንዘብ አያያዝና አጠቃቀም ፣ የማኅበሩን ብድር አወሳሰን ፤ ( ረ ) አባላት ከማኅበሩ ሲለቁ፡ ሲሰናበቱ ወይም በሞት ሲለዩ ተፈጸሚ የሚሆን ሥርዓት ፧ ( ሰ ) የማኅበሩ የስብሰባ ሥነ ሥርዓትና ለአባላት የሚሰጥ ማስታወቂያ ፣ ( ሸ ) የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ እንዲሁም ሌሎች ኃላፊዎች የሚቀጠሩበት፡ የሚመረጡበት ሥርዓት፡ ሥልጣንና ተግባራቸው እንዲሁም የሥራ ዘመናቸው ፧ የማኅበሩ ሠራተኞች አስተዳደር ፣ ( በ ) ልዩ ውሣኔና የምልዓተ ጉባዔ ውሣኔ የሚያስፈለጋቸው ጉዳዮች፡ የማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብ ለማሻሻል ተፈጻሚ የሚሆን ሥርዓትን ማኅበሩ ሲከፈል፡ ሲፈርስ ወይም ከሌሎች ማኅበራት ጋር ሲዋሃድ ተፈጻሚ የሚሆን ሥርዓት፡ ( ቸ ) ሌሎች አግባብነት ያላቸው ጉዳዮች ። ፲፭ የኅብረት ሥራ ማኅበር አባላት የዕጣ ሰርተፊኬት ሙሉየዕጣ መጠን ሰርተፊኬት ይሰጠዋል ። ፪ ) የዕጣ ሰርተፊኬቱ በምስጢር የሚታተም ሆኖ የሚከተ ሉትን መያዝ አለበት ( ሀ ) የማኅበሩ ስም ፣ ኣድራሻና ዓርማ ፤ ( ለ ) ማኅበሩ የተመዘገበበት ቀንና የምዝገባ ( ሐ ) የዕጣ ሰርተፊኬት መለያ ቁጥር ፣ ( መ ) የአንድ ዕጣ ዋጋ ፣ ( ሠ ) የአባሉ ስም ፣ የአባልነት መለያ ቁጥር ፣ ( ረ ) የገዛው የዕጣ መጠንና ዋጋ ፣ ( ሳ ) ማኅበሩን ለመምራት ሥልጣን ያለው ሰው ፊርማ ፣ ( ሸ ) የማኅበሩ ማኅተም ፣ ( ቀ ) ሰርተፊኬቱ የተሰጠበት ቀን ፡ ወርና ዓመተ ምህረት ፣ ፫ ) የኅብረት ሥራ ማኅበሩ ዕጣ ከአንድ የማኅበሩ አባል ወደ ሌላ አባል ወይም ከአንድ የማኅበሩ አባል ወደ ሦስተኛ ወገን ሊተላለፍ አይችልም ። ፲፮ የሕብረት ሥራ ማኅበር አባላት ስለሚሰናበቱበት ሁኔታ ፩ ) ግዴታውን ያልተወጣ አንድ አባል ከማኅበሩ ይሰና በታል ። አባሉ ግዴታውን እንዳልተወጣ የሚቆጠረው፡ ( ሀ ) በተወሰነው የጊዜ ገደብ የዕጣ ክፍያን ያላጠናቀቀ እንደሆነ ፣ ( ለ ) በማኅበሩ በሚሰጠው የሥራ ዘርፍ ከሁለት ጊዜ በላይ ግዴታውን ያልተወጣ ፣ ( ሐ ) ማኅበሩ በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ወይም ግብይቶች ለአንድ ዓመት ያልተሳተፈ ፣ ገጽ ፪ሺ፯፻፵፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፯ ሰኔ ፳፩ ቀን ፲፱፻፮ ዓም : ( መ ) ያለበቂ ምክንያት ለሁለት ተከታታይ ጊዜ በመደበኛ ስብሰባዎች ላይ ይልተሳተፈ እንደሆነ ፪ ) ጥፋት የፈጸመ አንድ አባል ከማኅበሩ ይሰናበታል ። አባሉ ጥፋት እንደፈጸመ የሚቆጠረው፡ ( ሀ ) ከማኅበሩ ዓላማ ጋር የሚጻረር ተግባር የፈጸመ፡ ( ለ ) በማኅበሩ ንብረቶች ላይ ሆነ ብሎ አደጋ ያደረሰ ወይም እንዲደርስ ያደረገ፡ ( ሐ ) በተለያየ ምክንያት በእጁ የገባውን የማኅበሩን ንብረት ለግል ጥቅሙ ያዋለ፡ ( መ ) የማኅበሩን ገንዘብ ሆነ ብሎ ያጎደለ ወይም ሁኔታ ዎችን ያመቻቸ፡ ( ሠ ) በማኅበሩ ስም መደለያ ወይም ጉቦ የሰጠ ወይም የተቀበለ፡ ( ረ ) በማኅበሩ የሚገዙ ወይም የሚሸጡ ንብረቶችን ጥቅም ለማግኘት ሲል ከገበያ ዋጋ በታች የሸጠ ወይም ከገበያ ዋጋ በላይ የገዛ ወይም እንዲሸጥ ወይም እንዲገዛ ያደረገ፡ ( ሰ ) ለማኅበሩ የሚያቀርበውን ምርት ወይም አገል ግሎት ዋጋ እንዳያገኝ ጥራቱን ያጓደለ ወይም መጠኑን የቀነሰ እንደሆነ ነው ። ፲፯ : ስለ ክፍያ ማንኛውም ኅብረት ሥራ ማኅበር የምስክር ወረቀት ለማውጣት ወይም ምትክ የምስከር ወረቀት ለማግኘት ከዚህ ደንብ ጋር ተያይዞ በሚገኘው ሠንጠረዥ ላይ የተመለከተውን ክፍያ ለመንግሥት ይከፍላል ። ፲፰ ምትክ የምስክር ወረቀት ስለመስጠት ፩ ) የተሰጠው የምስክር ወረቀት የጠፋበት ማንኛውም ኅብረት ሥራ ማኅበር ምትክ የምስክር ወረቀት እንዲ ሰጠው አግባብ ያለውን ባለሥልጣን ሊጠይቅ ይችላል ። ፪ ) አግባብ ያለውን ባለሥልጣን ጥያቄው በቀረበለት በ፲ ቀን ጊዜ ውስጥ ምትክ የምስክር ወረቀቱን ይሰጣል ። ፫ ) አግባብ ያለው ባለሥልጣን ስለ ምትክ የምስክር ወረቀት አሰጣጥ ዝርዝር መመሪያ ያወጣል ። ፲፬ ምዝገባ ስለሚከለከልበት ሁኔታ ማንኛውም ኅብረት ሥራ ማኅበር፡ ፩ ) አስቀድሞ ከተመዘገበ ማኅበር ጋር ተመሣሣይ ስምና ዓርማ ያለው ከሆነ፡ ፪ ) የራሱ የሆነ የፕሮጀክት ጥናት የሌለው ከሆነ ፥ ፫ ) በዚህ ደንብ እና በአዋጁ መሠረትለምዝገባ የሚያስፈልጉ ሁኔታዎችን ያላሟላ ከሆነ፡ ፬ ) ዓላማው ይህን ደንብ ፡ አዋጅ ወይም አግባብ ባለው ባለሥልጣን የወጡ መመሪያዎችን የሚፃረር ከሆነ ፤ ተመዝግቦ የምስክር ወረቀት ማግኘት ኔይችልም ። ክፍል አምስት ስለ ኅብረት ሥራ ማኅበሩ ስብሰባዎች ፳ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ፩ ) ማንኛውም የኅብረት ሥራ ማኅበር ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ያደርጋል ። ፪ ) ከጠቅላላ ጉባዔው አባላት ከግማሽ በላይ ሲገኙ ምንዓተ ጉባዔ ይሆናል ። ገጽ ፪ሺ፮፻፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፯ ሰኔ ፳፩ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓም ፫ ) መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ተጠርቶ ምልዓተ ጉባዔው ካልተሟላ በ፲፭ ቀናት ውስጥ ሁለተኛ ጠቅላላ ጉባዔ ይጠራል ። ለሁለተኛ ጊዜ የተጠራው መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ምልዓተ ጉባኤ ካልተሟላ በተገኙት አባላት መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ይካሄዳል ። ፬ ) በዚህ አንቀጽ በንዑስ አንቀጽ ፫ መሠረት ምልዓተ ጉባዔ ሳይኖር የተካሄደ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ የሚያሳልፋቸው ውሣኔዎች ሁሉም የጉባዔው አባላት በተገኙበት እንደተ ላለፈ ይቆጠራል ። ፳፩ : አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ፩ ) በአዋጁ አንቀጽ ፳፪ መሠረት የተጠራው አስቸኳይ | 21. Emergency meeting of the General Assembly ጠቅላላ ጉባዔ ምልዓተ ጉባኤው ካልተሟላ በ፲፭ ቀናት ውስጥ የሥራ አመራርኮሜቴው ለሁለተኛ ጊዜ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ይጠራል ። ለሁለተኛ ጊዜ የተጠራው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ምልዓተ ጉባዔ ካልተሟላ አግባብ ያለው ባለሥልጣን ጥሪ የማድረግ ሥልጣን ይኖረዋል ። ፪ ) ከጠቅላላው አባላት ሁለት ሦስተኛው ሲገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይሆናል ። ፳፪ ጥሪ ስለማድረግ በዚህ አዋጅ መሠረት አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ከመደረጉ ከ፲፭ ቀን በፊት የማኅበሩ የሥራ አመራር ለአባላቱ ሀገር አቀፍ ሥርጭት ባለው ጋዜጣ ወይም አመቺ ሆኖ በተገኘው መንገድ ጥሪማድረግ አለበት ። ፳፫ • የሕብረት ሥራ ማኅበር የድምጽ አሰጣጥ ሥርዓት ፩ ) በማኅበሩ መተዳደሪያ ደንብ በተለየ ሁኔታ ካልተገለጸ በቀር በመደበኛ ወይም በአስቸኳይ ጉባዔው የሚተላለፉ ውሣኔዎች በአባላቱ የአብላጫ ድምጽ ይሆናል ። ፪ ) የድምጽ አሰጣጥ እኩል በኩል የተከፈለ ሲሆን የጉባዔው ሰብሳቢ ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል ። ክፍል ስድስት ስለ ሕብረት ሥራ ማኅበር ንብረትና ገንዘብ ፳፬ . የተጣራ ትርፍ አደላደል ፩ ) ከማኅበሩ የተጣራ ትርፍ ላይ ፴ በመቶ እየተቀነሰ በመጠባበቂያ ሂሣብ ይቀመጣል ። የመጠባበቂያ ሂሣቡ የሚቀመጠው ከማኅበሩ ካፒታል ፴ በመቶ እስከሚደርስ ብቻ ነው ። ፪ • በየዓመቱ ከማኅበሩ የተጠራ ትርፍ ውስጥ እየተቀነሰ በመጠባበቂያ የሚመደበው ገንዘብ በማኅበሩ ስም የቁጠባ ሂሣብ ተከፍቶለት ይቀመጣል ። ስለአጠቃቀሙ አግባብ ያለው ባለሥልጣን መመሪያ ያወጣል ። ፳፭ ስለሕብረት ሥራ ማኅበር የማይከፋፈል ንብረት ማንኛውም የማኅበሩ ንብረት፡ ( ሀ ) በመጠባበቂያ ሂሣብ ውስጥ የተመዘገበ ከሆነ፡ ( ለ ) በስጦታ ወይም በውርስ የተገኘ ከሆነ የወል ንብረት ይሆናል ። ፳፮ የሕብረት ሥራ ማኅበር ሲፈርስ ስለሚኖረው ንብረት | 26. Distribution of Assets of Dissolved Cooperative society . አከፋፈል ማንኛውም ኅብረት ሥራ ማኅበር በሕግ መሠረት ሲፈርስ በአዋጁ አንቀጽ ፵፬ ንዑስ አንቀጽ ፬ መሠረት ሕብረት ሥራ ለ ሃኅበሩ ገንዘብ ጠያቂዎች ተከፍሎ የሚቀረው ንብረት ሕብረት ሥራ ማኅበሩ ሲፈርስ ለነበሩ ኣባላት ፡ ሕብረት ሥራ ማኅበሩ ከመፍረሱ በፊት ያለጥፋት ለተሰናበቱ አባላትና ለሟች አባላት ተተኪዎች እንደየድርሻቸው ይከፋፈላል ። ስለአከፋፈሉ አግባብ ያለው ባለሥልጣን መመሪያ ያወጣል ። 1 ጽ ፪ሺ፰፻፵፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፯ ሰኔ ፳፩ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓም ፳፯ የተሻሩ ሕጎች ይህን ደንብ የሚቃረን ማንኛውም ደንብ ወይም መመሪያ ተፈጻሚነት የለውም ። ፳፰ መመሪያ የማውጣት ሥልጣን ኣግባብ ያለው ባለሥልጣን ይህን ደንብ ለማስፈጸም መመሪያ ሊያወጣ ይችላል ። ፳ሀ • ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ሰኔ ፳፩ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓ.ም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የኅብረት ሥራ ኮሚሽን የምስክር ወረቀት አገልግሎት ክፍያ ሠንጠረዥ [ ተ.ቁ የምስክር ወረቀቱ ዓይነት መጠን ብር አዲስ ምዝገባ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?