×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 5/1988 የኢትዮጵያ የሰላምና የልማት ዓለም አቀፍ ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ነጋሪት ጋዜጣ ሁለተኛ ዓመት ቁጥር ፲፰ አዲስ አበባ የካቲት፲፬ ቀን ፲፱፻፵፰ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻ዥ፰ ዓም : የኬሚካል ጦር መሣሪያዎችን ዝግጅት፡ መመረት ፡ ክምችትና በጥቅም ላይ መዋል ለመከልከልና የተመረቱትንም ለማስ ወገድ የተደረገውን ኮንቬንሽን ለማጽደቅ የወጣ ገጽ ፻፵፱ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፭ / ፲፱፻፷፰ ዓም የኢትዮጵያ የሰላምና የልማት ዓለም አቀፍ ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ገጽ ፻፰ አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻ T ፰ የኬሚካል ጦር መሣሪያዎችን ዝግጅት፡ መመረት፡ ክምችትና በጥቅም ላይ መዋል ለመከልከልና የተመረቱትንም ለማስወገድ የተደረገውን ኮንቬንሽን ለማጽደቅ የወጣ አዋጅ የኬሚካል ጦር መሣሪያዎችን ዝግጅት፡ መመረት፡ ክምችትና በጥቅም ላይ መዋል ለመከልከልና የተመረቱትንም ለማስወገድ እ.ኤ.አ ጃንዋሪ ፲፫ ቀን ፲፱፻፫ ዓ.ም በፓሪስ የተደረገውን | Convention on the Prohibition of the Development Produc ኮንቬንሽን ከፈረሙት አገሮች ኢትዮጵያ አንዷ በመሆኗ ፤ ይህንኑ ኮንቬንሽን የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ | Destruction , done in Paris on the 13 day of January , 1993 ; ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የካቲት ፲፬ ቀን ፲፱፻፴፭ | ratified said convention at its session held on the 22 day of ዓም . ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው ስለሆነ ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ( ፩ ) እና ( ፲፪ ) መሠረት የሚከተለው | and ( 2 ) of the Constitution of the Federal Democratic ታውጇል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ « የኬሚካል ጦር መሣሪያዎችን ዝግጅት መመረት ክምችትና በጥቅም ላይ መዋል ለመከልከልና የተመረቱትንም ለማስወገድ የተደረገውን ኮንቬንሽን ማጽደቂያ የወጣ አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፰፰ » ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፴ሺ፩ ገጽ ፻፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፰ የካቲት ፲፬ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ • ም • ፪ ኮንቬንሽኑ ስለመጽደቁ የኬሚካል ጦር መሣሪያዎችን ዝግጅት፡ መመረት፡ ክምችትና በጥቅም ላይ መዋል ለመከልከልና የተመረቱትንም ለማስ ወገድ እ.ኤ.አ ጃንዋሪ ፲፫ ቀን ፲፱፻፫ ዓ ም በፓሪስ የተደ ረገው ኮንቬንሽን ጸድቋል ። ፫ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሥልጣን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ኣግባብ ካላቸው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ጋር በመተባበር ይህን የኬሚካል ጦር መሣሪ ያዎች ዝግጅት፡ መመረት፡ ክምችትና በጥቅም ላይ መዋል ለመከልከልና የተመረቱትንም ለማስወገድ የተደረገውን ኮንቬ ንሽን በሥራ ላይ እንዲውል የማድረግ ሥልጣን በዚህ አዋጅ ተሰጥቶታል ። ፬ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከየካቲት ፲፬ ቀን ፲፱፻፰፰ ዓም ጀምሮ የጸና ይሆናል ፡፡ ኣዲስ ኣበባ የካቲት ፲፬ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፭ / ፲፱፻፷፰ የኢትዮጵያ የሰላምና የልማት ዓለም አቀፍ ኢንስቲትዩትን ለማቋቋም የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ | ters pursuant to Article 5 of the Definition of Powers and ሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን | Duties of the Executive Organs of the Federal Democratic በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፴፯ አንቀጽ ፭ መሠረት ይህን ደንብ | Republic of Ethiopia Proclamation No. 4/1995 . አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የኢትዮጵያ የሰላምና የልማት ዓለም አቀፍ ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፭ / ፲፱፻፷፰ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ ደንብ ውስጥ “ ሚኒስቴር ” ማለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ነው ። ፫ . መቋቋም ፩ የኢትዮጵያ የሰላምና የልማት ዓለም አቀፍ ኢንስቲትዩት ( ከዚህ በኋላ “ ኢንስቲትዩቱ ” እየተባለ የሚጠራ ) በሕግ የሰውነት መብት ያለው ራሱን የቻለ ኢንስቲትዩት ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ። ፪ ኢንስቲትዩቱ ተጠሪነቱ ለሚኒስቴሩ ይሆናል ። ገጽ ደ፳፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፰ የካቲት ፲፬ ቀን ፲፱፻ቸ፰ ዓም ፬ ዋና መሥሪያ ቤት የኢንስቲትዩቱ ዋና መሥሪያ ቤት በአዲስ አበባ ሆኖ በማና ቸውም ሥፍራ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤት ሊኖረው ይችላል ። ፭ ዓላማ ኢንስቲትዩቱ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል ፤ ፩ ኢትዮጵያ በሕገ መንግሥቱ እውን ያደረገችው የሁሉም ዜጐችዲሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብቶች መከበር ይበልጥ ሥር እንዲሰድ ፣ የተገኘው ሰላምና መረጋጋት ይበልጥ እንዲጐለብትና የኢኮኖሚና የሶሻል እድገት እንዲፋጠን ሀገሪቱ ከዓለም አቀፍ ኅብረተሰብ ጋር የምታደርገውን ትብብርና የምትመሠርተውን ቅንጅት ለማሳካት የሚረዳ ጥናት ፣ ምርምርና ሥልጠናማካሄድ ፤ ፪ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ሀገሮች መካከል በመተማመን ፣ በመከባበር ፣ በጋራ ፍላጐትና ጥቅም ላይ የተመሠረተ ግንኙነት እንዲጠናከር የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረግ ፤ ፫ : የምርምር ተግባሮችን በማበረታታትና በመርዳት እንዲሁም በማያቋርጥ የሥልጠናፕሮግራም አማካይነት የጽንሰ ሃሳብና ተግባራዊ ድጋፍ በመስጠት የኢትዮጵያንና የአፍሪካ ቀንድ አካባቢን የወደፊት ደኅንነት ፣ መረጋጋት እና የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማትን ለማፋጠን የሚያ ስችሉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ፤ ፩ የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ሀገሮች በክልሉ ዘላቂ ሰላምና ልማት እንዲረጋገጥ ለሚያደርጉት ትግል የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ድጋፍና ትብብር እንዲጠናከርና ከሌሎች ሪጅኖች ጋር በሚደረገው ግንኙነት በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ ቅንጅት እንዲፈጠርና እንዲዳብር ማበረ ታታት ። ፮ . ሥልጣንና ተግባር ኢንስቲትዩቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ ከሰላምና ከልማት ጥያቄዎች ጋር የተዛመዱ የፖሊሲ አማራጭ ጥናቶችን ማካሄድና ማሰራጨት ፤ ፪ ከዲሞክራሲያዊ ተቋማት ግንባታና የሰብዓዊ መብት መከበር ፣ ከሰላምና ጸጥታ መረጋገጥ ፣ ከውጭ ግንኙነትና ትብብር፡ እንደዚሁም ከኢኮኖሚና ሶሻል ግንባታ ጋር የተሳሰሩ ፖሊሲዎችና መርሆዎችን አፈጻጸም መገም ገምና አማራጭ የአፈጻጸም ስልቶችን በጥናት ላይ ተመርኩዞ ማቅረብናማሰራጨት ፤ ፫ የዲሞክራሲ ባህል እንዲዳብርና ልዩነቶች ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ ትግል እንዲካሄድባቸው ፣ የሰብዓዊ መብቶች መከበር ሥር እንዲሰድ ፣ ተጠያቂነት፡ ግልጽነትና የሕዝብ አመኔታያለው የአስተዳደር ሥርዓት እንዲጠናከር ፣ የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ተቋሞችእንዲስ ፋፉና እንዲጠናከሩ የሚያግዝ ጥናት ፣ ምርምርና ሥልጠናማካሄድ ፤ ፩ ከሰላምና ከልማት ጥያቄዎች ጋር የተያያዙ መረጃዎችን መሰብሰብ መተንተንና ለሚመለከታቸው አካላት ማሰራጨት ፭ በብሔራዊና በአካባቢው ደረጃ የሚከሰቱ አለመግባባ ቶችን በሰላማዊ መንገድ በመፍታት ረገድ አስተዋጽኦና ድጋፍማድረግ ፮ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ የሚረዱ በተለይም አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ በማስወገድናሰላምን በማስፈን ስልቶች ላይ ያተኮሩ የሥልጠና ፕሮግራሞችን ማካሄድ ፣ ‹ ድቃል ፣ ተግባራዊነ ገጽ ፻፳፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፰ የካቲት ፲፬ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ • ም • ፯ ሴሚናሮችን ፣ ወርክሾፖችን ፣ ሲምፖዚየሞችን ፣ ጉባዔዎ ችንና የመሳሰሉ የዕውቀትና የልምድ ልውውጥ መድረ ኮችን ማዘጋጀት ፤ ፰ ከመንግሥታዊ ፣ ከዓለም አቀፍና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶችና ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸው ተቋሞች ጋር የትብብር ግንኙነት መመሥረት ፤ ፱ የጥናትና የምርምር ውጤቶችን ማሳተምናማሠራጨት ፤ ፲ ዓላማውን ለማስፈጸም የሚረዳ ዕርዳታና ስጦታ መቀበል ፤ ፲፩ ለሚሰጠው አገልግሎት እንደአስፈላጊነቱ የአገልግሎት ዋጋ መወሰንናማስከፈል ፤ ፲፪ የንብረት ባለቤት መሆን ፣ ውል መዋዋል ፣ በስሙ መክሰስና መከሰስ ፤ ፲፫ ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚያስፈልጉ ሌሎች ተግባ ሮችን ማከናወን ። ፯ የኢንስቲትዩቱ አቋም ኢንስቲትዩቱ ፤ ፩ . የባለ አደራ ቦርድ ( ከዚህ በኋላ “ ቦርዱ ” እየተባለ የሚጠራ ) ፣ ፪ በሚኒስቴሩ የሚሾሙ አንድዲሬክተርና ምክትል ዲሬክተር ፣ ፫ አስፈላጊው ሠራተኞች ይኖሩታል ። ፰ የቦርዱ አባላት የቦርዱ ሰብሳቢና አባላት በሚኒስቴሩ ይሰየማሉ ። ፱ የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ፩ የኢንስቲትዩቱን ሥራዎች በበላይነት ይመራል ፣ ይቆጣ ጠራል ፤ ፪ የኢንስቲትዩቱን የጥናት ፣ የምርምርና የሥልጠና ፕሮግ ራሞች መርምሮ ያጸድቃል ፤ ተግባራዊነታቸውን ይከታ ፫ የኢንስቲትዩቱን ዓመታዊ በጀት ቱንም ይቆጣጠራል ፤ ፬ • የኢንስቲትዩቱን የውስጥ ደንቦች ያጸድቃል ፣ ተግባራዊነ ታቸውንም ይከታተላል ፤ ፭ በኢንስቲትዩቱ ዲሬክተር በሚቀርቡለት ሌሎች የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ይመክራል ፣ ይወስናል ፤ ፮ . የኢንስቲትዩቱን የሥራ አፈጻጸም ይገመግማል ፤ ለሚኒስ ቴሩም ከአስተያየቱ ጋር ያስተላልፋል ። ፲ የቦርዱ ስብሰባ ፩ ቦርዱ ለሥራው ባስፈለገ መጠን ይሰበሰባል ። ፪ በቦርዱ ስብሰባ ላይ አብዛኞቹ አባላት ከተገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይሆናል ። ፫ የቦርዱ ውሳኔ የሚተላለፈው በስብሰባው በተገኙ አባላት በኣብዛኛው ድምጽ ሲደገፍ ነው ፤ ሆኖም ድምጹ እኩል በእኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል ። ፬ ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። ፭ ለቦርድ አባላት ሊከፈል የሚገባው አበል በቅድሚያ የሚኒስቴሩን ፈቃድ በማግኘት በኢንስቲትዩቱ የውስጥ ደንብ ይወሰናል ። ሆኖ የኢንስቲትዩቱን ዓላማዎች ለማስፈጸም ) ገጽ ፻፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፰ የካቲት ፲፬ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓም : ፲፩ . የዲሬክተሩ ሥልጣንና ተግባር ፩- ዲሬክተሩ የኢንስቲትዩቱ ዋና አስፈጻሚ ሆኖ ቦርዱ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የኢንስቲት ዩቱን ሥራዎች ይመራል ፣ ያስተዳድራል ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው አጠቃላይ ኣነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ዲሬክተሩ ፤ ሀ ) በዚህ ደንብ አንቀጽ ፭ የተመለከቱትን የኢንስቲት ዩቱን ሥልጣንና ተግባሮች በሥራ ላይ ያውላል ፤ ለ ) የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕጐችን መሠረታዊ ዓላማ በመከተል ቦርዱ የሚያጸድቀውን የውስጥ ደንብ መሠረት በማድረግ የኢንስቲትዩቱን ሠራተኞች ይቀጥራል ፣ ያስተዳድራል ፤ ሐ ) የኢንስቲትዩቱን ፕሮግራሞችና በጀት አዘጋጅቶ ለቦርዱ ያቀርባል ፣ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፤ መ ) ለኢንስቲትዩቱ በተፈቀደለት በጀትና የሥራ ፕሮግራም መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፤ ሠ ) ከስተኛ ወገኖች ጋር በሚደረጉ ግንኙነቶች ሁሉ ኢንስቲትዩቱን ይወክላል ፤ ረ ) የኢንስቲትዩቱን የሥራ አፈጻጸምና የሂሳብ ሪፖርት አዘጋጅቶ ለቦርዱ ያቀርባል ። ፫ ዲሬክተሩ ለኢንስቲትዩቱ የሥራ ቅልጥፍና ባስፈለገ መጠን ከሥልጣንና ተግባሩ በከፊል ለምክትል ዲሬክ ተሩና ለኢንስቲትዩቱ ሌሎች ሠራተኞች በውክልና ሊያስ ተላልፍ ይችላል ። ፲፪ በጀት ፩ . የኢንስቲትዩቱ በጀት ከሚከተሉት ምንጮች የተውጣጣ ይሆናል ፤ ሀ ) በፌዴራሉ መንግሥት ከሚመደብለት ድጐማ ፤ ለ ) ከሚያገኘው ማንኛውም ስጦታና እርዳታ ፤ ሐ ) ከሚሰበስበው የአገልግሎት ክፍያ ፤ እና መ ) ከማናቸውም ሌላ ምንጭ ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከተው ገንዘብ በኢንስቲትዩቱ ስም በሚከፈት የባንክ ሂሳብ ተቀማጭ ይሆናል ። ፲፫ • የሂሳብ መዛግብት ፩ ኢንስቲትዩቱ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሳብ መዛግብት ይይዛል ። ፪ . ለዋናው ኦዲተር በሕግ የተሰጠው ሥልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ ፣ የኢንስቲትዩቱ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች ቦርዱ በሚሰይመው የውጭ ኦዲተር በየዓመቱ ይመረመራሉ ። ፲፬ ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል ። አዲስ አበባ የካቲት ፲፬ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ.ም መለስ ዜናዊ የኢትየጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?