የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ አራተኛ ዓመት ቁጥር ፲ አዲስ አበባ ታህሣሥ ፲፩ ቀን ፲፱፻፲ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፳፬ / ፲፱፻፲ ዓም የገምሩክ መጋዘን ስራ ፈቃድ የሚሰጥበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ . ገጽ ፮፻፰ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፳፬ / ፲፱፻፲ የጉምሩክ መጋዘን ሥራ ፈቃድ የሚሰጥበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ ፲፱፻፴፯ አንቀጽ ፭ እና የጉምሩክ ባለሥልጣንን እንደገና ለማቋቋምና አሰራሩን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፰ ፴፬ አንቀጽ ፵ ( ) እና አንቀጽ ፴፬ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ። ፩ ኣጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የጉምሩክ መጋዘን ስራ ፈቃድ የሚሰጥበትን ሁኔታ ለመወሰን የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፳፬ / ፲፱የኝ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ ደንብ ውስጥ ፤ ፩ . “ የተፈቀደ የጉምሩክ መጋዘን ” ማለት የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት ያልተፈፀመባቸው ዕቃዎች እንዲከማቹበት በጉምሩክ ባለሥል ጣን ፈቃድ የሚቋቋም የጠቅላላ ወይም የግል ዕቃ መጋዘን ነው ፤ ፪ “ ፈቃድ ” ማለት በዚህ ደንብ መሠረት የጉምሩክ መጋዘን ለማቋቋም የሚሰጥ ፈቃድ ነው ፤ ፫ “ የጠቅላላ ዕቃ የጉምሩክ መጋዘን ” ማለት የተለያዩ አስመጪ ዎች ወይምላኪዎችዕቃ ላይ የጉምሩክ ሥነ ሥርዓትእስከሚፈጸ ምበት ጊዜ ድረስ የሚቀመጡበት መጋዘን ነው ፤ ፬ . “ የግል ዕቃ የጉምሩክ መጋዘን ” ማለት ማንኛውም ሰው በስሙ ለሚያስመጣቸው ወይም ለሚልካቸው ዕቃዎች የጉምሩክ ሥነ ሥርዓት እስከሚጠናቀቅለት ድረስ የሚከማቹበት መጋዘን ነው ፤ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ገጽ ፮፻፳፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲ ታህሣሥ ፲፩ ቀን ፲፱፻፶ ዓም ፭ “ ሰው ” እና “ ባለሥልጣን ” ማለት የጉምሩክ ባለሥልጣንን እንደገና ለማቋቋምና አሠራሩን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፰ ፳፬ የተሰጣቸው ትርጓሜ ይኖራቸዋል ። ፫ በፈቃድ የሚቋቋሙ የመጋዘን ዓይነቶች በባለስልጣኑ በሚሰጥ ፈቃድ የሚቋቋም የጉምሩክ መጋዘን በተለያዩ ሰዎች ስም የመጣን ወይም የሚላክን ዕቃ ለማኮማ ቸት የሚያገለግል የጠቅላላ ዕቃ የጉምሩክ መጋዘን ወይም ባለፈቃዱ በራሱ ስም ያመጣውን ወይም የሚልከውን ዕቃ ለማከማቸት የሚያገለግል የግል ዕቃ መጋዘን ተብሎ በሁለት ይመደባል ። ፪ . የጠቅላላ ዕቃ ማከማቻ እና የግል ዕቃ ማከማቻ የጉምሩክ መጋዘን ፈቃድ ለመስጠት የሚያበቁት መስፈርቶች በፌዴ ራል መንግሥት የገቢዎች ቦርድ በሚወጣ መመሪያ ይወሰ ናል ። ቦርዱ የሚያወጣው መመሪያ ለሕዝብ ይፋ ይደረጋል ። ፈቃድ ስለመስጠት ፩ . የጉምሩክ ባለስልጣንን እንደገና ለማቋቋምና አሰራሩን ለመወ ሰን በወጣው አዋጅ እና በአዋጁ መሠረት በወጡ መመሪያ ዎች ውስጥ የተመለከቱትን ድንጋጌዎች ለሚያሟላ ማንኛ ውም የጉምሩክ መጋዘን ፈቃድ ጠያቂ ባለስልጣኑ የመጋዘን ፈቃድ ይሰጣል ። ፪ . ባለሥልጣኑ የመጋዘን ሥራ ፈቃድ መጠየቂያ ማመልከቻ ውን በተቀበለ በ፴ ቀናት ውስጥ የሥራ ፈቃድ ለመስጠት ወይም ለመከልከል ያሳለፈውን ውሣኔ ለአመልካቹ በጽሑፍ ማሳወቅ አለበት ። ፭ የጉምሩክ መጋዘን የሚቋቋምባቸው ቦታዎች ፩ የጉምሩክ መጋዘን የጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያዎችን በመከ ተል በአገሪቷ የአየር ፡ የየብስና የውሃ ላይ ማጓጓዣዎች መግቢያና መውጫ በሆኑ የጉምሩክ ወደቦች ወይም የመተላለ ፊያ መንገዶች ላይ የሚቋቋም ይሆናል ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ላይ የተመለከተው እንደተ ጠበቀ ሆኖ ቦርዱ ሲያምንበት በሌሎች በማናቸውም ሥፍራ መጋዘን እንዲቋቋም ሊፈቅድ ይችላል ። ፮ የተፈቀደ የጉምሩክ መጋዘን ስራ ቀንና ሰዓት ፩ የተፈቀደ የጉምሩክ መጋዘን በህግ በተወሰነው መደበኛ የስራ ቀንና ሰዓት ዕቃ ለማስገባትና ለማስወጣት ክፍት ይሆናል ። ፪ ከመደበኛ የስራ ቀንና ሰዓት ውጭ ዕቃ ወደ መጋዘን ለማስገባትና ከመጋዘን ለማስወጣት ቢያስፈልግ ባለሥልጣ ኑን በጽሁፍ መጠየቅና ፈቃድ ማግኘት ያስፈልጋል ። ፯ ለባለሥልጣኑ ስለሚከፈል የአገልግሎት ክፍያ ፩ በፈቃድ የተቋቋመ የጉምሩክ መጋዘንን የሚቆጣጠር የጉም ሩክ ሹም ባለሥልጣኑ ይመድባል ። ፪ . በፈቃድ ለተቋቋመ መጋዘን ቁጥጥርና ባለሥልጣኑየሚያወጣ ውን ጠቅላላ ወጭ መሠረት በማድረግ ባለፈቃዱ በየዓመቱ ለባለሥልጣኑ ገቢ የሚያደርገው የአገልግሎት ክፍያ መጠን በቦርዱ ይወሰናል ። የፈቃድና የዕድሣት ክፍያ ፩ የጉምሩክ መጋዘን ፈቃድ የሚሰጠው ማንኛውም ሰው ከዚህ እንደሚከተለው የፈቃድና የዕድሣት ክፍያ ይከፍላል ፤ 5 ሳለጫ ሰነዶች ገጽ ፮፻፷፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲ ታህሣሥ ፲፩ ቀን ፲፱፻፲ ዓም ሀ ) ለጠቅላላ ዕቃ የጉምሩክ መጋዘን ፈቃድ ብር ፩ሺህ፪፻፶ ብር ፭፻ ለ ) ለግል ዕቃ የጉምሩክ መጋዘን ፈቃድ ብር ፩ሺህ፪፻፶ ለዕድሳት ብር ፭፻ ይከፈላል ። ፱ ፈቃዱ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ፩ . በዚህ ደንብ በአንቀጽ ፲ መሠረት በተዘረዘሩት ምክንያቶች ፈቃዱ ካልተሠረዘ በስተቀር የተሰጠ የመጋዘን ፈቃድ ለአንድ የበጀት ዓመት የፀና ይሆናል ። ፪ • የጉምሩክ መጋዘን ፈቃድ በየበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ከሐ ምሌ ፩ እስከ ሐምሌ ፴ ባለው ጊዜ ውስጥ በዚህ ደንብ አንቀጽ ፰ መሠረት ተገቢው ክፍያ ተፈጽሞ መታደስ አለበት ። ፫ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) መሠረት በተመለከተው ጊዜ ውስጥ ፈቃድ ያላሳደሰ ከነሐሴ ፩ እስከ ነሐሴ ፴ ባለው ጊዜ የማደሻውን ፻ ፐርሰንት ቅጣት በመክፈል ያሳድሳል ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) እና ( ፫ ) በተመለከተው ጊዜ ውስጥ የጉምሩክ መጋዘን ፈቃድ ሳያሳድስ ከቀረ የተሰጠው የመጋዘን ፈቃድ ይሰረዛል ። ፲ ፈቃዱን የሚያሰርዙ ምክንያቶች ባለሥልጣኑ በዚህ ደንብ መሠረት የሰጠውን ፈቃድ በሚከተሉት ምክንያቶች ሊሰርዝ ይችላል ። ፩ . ያለማስጠንቀቂያ ፡ ሀ ) በጉምሩክ መጋዘን ውስጥ ያልተመዘገበ ወይም ፈቃድ ያልተሰጠው ዕቃ በመጋዘኑ እንዲገባ ወይም እንዲወጣ ያደረገ ፡ ወይም ለ ) የጉምሩክ ሥነ - ሥርዓት ያልተፈፀመበት ዕቃ ከመጋዘን እንዲወጣ ያደረገ ፡ ወይም ፤ ሐ ) ስለዕቃ የሚገልጹ ሠነዶችን የሰረዘ ወይም የደለዘ ወይም መ ) በመጋዘን ያልገባን ዕቃ እንደገባ አስመስሎ የሀሰት ማስረጃ የሰጠ ፡ ወይም ሠ ) ወደ መጋዘን ለመግባት በመጣው ዕቃ ላይ የሰፈረው መረጃ ወደ መጋዘን ለመግባት ከመጣው ዕቃ በዓይነት ወይም በብዛት ፡ በመጠን ፡ በክብደት የማይመሳሰሉ መሆናቸው ወይም በሰነድ ውስጥ ያልተገ ለጹ ዕቃዎች መኖራቸውን እያወቀ ለጉምሩክ ያልገለጸ ረ ) ወደ መጋዘኑ በገቡ ዕቃዎች ላይ ስርቆት የፈፀመ ፤ መሆኑ ሲረጋገጥ ያለቅድሚያ ማስጠንቀቂያ የመጋዘን ፈቃዱ ይሰረዛል ። ፪- በማስጠንቀቂያ ከዚህ በታች ለተገለጹት ምክንያቶች በባለሥልጣኑ በቅድ ሚያ የሰባት ቀን ማስጠንቀቂያ በመስጠት የመጋዘን ፈቃድ ይሰረዛል ሆኖም በማስጠንቀቂያው ውስጥ የተገለጸው ሁኔታ እንዲስተካከል ከተደረገ የፈቃዱ መሠረዝ ይቀራል ፤ ሀ ) በህግ ወይም ባለስልጣኑ ባወጣቸው መመሪያዎች ውስጥ የተደነገጉትን የሚጥስ ተግባር መፈጸም ፣ ወይም ፤ ገጽ ፮፻፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲ ታህሣሥ ፲፩ ቀን ፲፱፻፶ ዓም ለ ) የባለሥልጣኑኃላፊዎችና ሠራትኞች የዕለት ተግባራቸውን እንዲፈጽሙ ትብብር አለማድረግ ፡ ወይም ሐ ) በጥንቃቄ ጉድለት በዕቃዎች ላይ ጉዳት ማድረስ ፣ ወይም መ ) የጉምሩክ ፎርማሊቲ ያልተፈፀመባቸው ወይም በባለቤቱ . ' { ት የተተዉ ወይም በፍ / ቤት ትዕዛዝ የታገዱ ፡ የተወረሱ እና የመሳሰሉት ዕቃዎች ወደ ባለሥልጣኑ መጋዘን በወቅቱ አለማስተላለፍ ፡ ወይም ፡ ሠ ) ለተፈቀዱ ምክንያቶች ናሙና አለመስጠት ፡ የተሰጡ ናሙናዎችን ተከታትሎ አለማስመለስ ፤ በወቅቱ ሪፖርት አለማድረግና በሌሎች ተመሳሳይ ምክንያቶች ለባለእቃ ውና ለባለሥልጣኑ ሹሞች ቀና አገልግሎት አለመስጠት ፣ ወይም ረ ) እነዚህን የመሳሰሉ ሌሎች ድርጊቶችን መፈጸም ። ፲፩ . ስለፈቃድ መሠረዝና ስለ ቅጣት , ፩ ከዚህ በላይ በተመለከቱት አንቀጽ ፬ ንዑስ አንቀጽ ( ፰ ) እና አንቀጽ ፬ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( g ) ላይ በተገለጹት ምክንያቶች የመጋዘን ፈቃድ ሲሰረዝ በመጋዘኑ ውስጥ tu ያሉትን እቃዎች ባለፈቃዱ በራሱ ወጪና ኪሳራ ወደ ባለሥልጣኑ መጋዘን እንዲገቡ ያደርጋል ። ፪ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ዕቃው ወደ ባለሥልጣኑ መጋዘን እስከሚዛወርበት ጊዜ ድረስ መጋዘኑ በጉምሩክ ቁልፍ ታሽጐ እንዲቆይ ይደረ ፫ • በዚህ ደንብ አንቀጽ ፲ የተመለከቱትን ፈቃድ የሚያሰርዙ ድርጊቶችን ለመፈጸሙ ሲረጋገጥ በተፈጸመው ድርጊት 1. በጉምሩክ ሕግና አግባብ ባለው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ መሠረት ተገቢው ቅጣት ይፈጸማል ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) የተመለከተው እንደተጠ በቀ ሆኖ በአንቀጽ ፬ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) እና በአንቀጽ ፲ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፱ ላይ በተመለከቱት ምክንያቶች ፈቃዱ የተሰረዘበትበድጋሚየመጋዘን ሥራፈቃድአይሰጠ ውም ። ፲፪ የተሻሩ ደንቦችና መመሪያዎች ፩- የ፲፱፻፴፮ ዓም • የጉምሩክ ( መጋዘን ) ደንቦች ቁጥር ፯ / ፴፮ ፪ ይህን ደንብ የሚቃረን ሌላ ማንኛውም ደንብ ፡ መመሪያ ' ወይም የአሠራር ልምድ በዚህ ደንብ ውስጥ በትመለከቱት ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም ። ፲፫ ደንቡየሚፀናበት ጊዜ ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስአበባታህሣሥ ፲፩ ቀን ፲፱፻፶ ዓም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት