ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ተግባር ለመወሰን ባወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ሥ * \ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እሥረኛ ዓመት ቁጥር ፪ አዲስ አበባ - ሰኔ ፲፯ ቀን ፲፱፻ጥ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፫ / ፲፱፻፮ ዓ.ም በልማት ወደ ኋላ ለቀሩ ክልሎች ልዩ ድጋፍ የሚያደርግ የፌደራል ቦርድ ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ገጽ ፪፭፻፴፬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፪ / ፲፱፻፲፯ በልማት ወደኋላ ለቀሩ ክልሎች ልዩ ድጋፍ የሚያደርግ የፌዴራል ቦርድ ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ፭ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል ፡፡ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ “ ደንብ በልማት ወደኋላ ለቀሩ ክልሎች ልዩ ድጋፍ የሚያደርግ የፌዴራል ማቋቋሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፩፻፫ / ፲፱፻ ¥ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ ፤ በዚህ ደንብ ውስጥ ፧ ፩ . " በልማት የአፋር ፣ የሶማሌ ፣ የጋምቤላና የቤኒሻንጉል / ጉሙዝ / ክልሉች ማለት ሲሆን ፤ በኦሮሚያና በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች የሚገኙትን የአርብቶ አካባቢዎችንም ያካትታል ፡፡ ፪ . " ልዩ ድጋፍ ማለት በዋነኛነት የዕቅድ ዝግጅትና አፈጻጸምን በሚመለከት የሚደረግ የክልሉቹን ፍላጎት መሠረት ያደረገ እና አቅማቸውን በሚገነባ መንገድ ቀጣይነት ያለው የተቀናጀ እገዛ ነው ፡፡ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖ.ሣ.ቁ. ሺ 1 ገጽ ፪ሺ፮፻፴፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፬ ሰኔ ፲፯ ቀን ፲፱፻፮ ዓ.ም. ፫ መቋቋም ፩ / በልማት ወደኋላ ለቀሩ ክልሎች ልዩ ድጋፍ የሚያደርግ ፌዴራል ቦርድ / ከዚህ በኋላ ቦርዱ እየተባለ የሚጠራ / የሕግ ሰውነት ያለው ሆኖ በዚህ ደንብ ተቋቁሟል ፡፡ ፪ / የቦርዱ ተጠሪነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል ፡፡ ፬ ዓላማ የቦርዱ ዓላማ ፤ ፩ . የፌዴራል መንግሥቱ አካላት በልማት ወደኋላ ለቀሩ ክልሎች የሚሰጡትን ድጋፍ ማቀናጀት ፣ ፪ . ክልሎቹ በራእይና በእቅድ ላይ የተመሰረተ ቀጣይ ልማት የማስፈጸም አቅም ግንባታና የዲሞክራታ ይዜሽን ሥራ ለማከናወን ለሚያደርጉት ጥረት ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ ፡፡ ፭ . የቦርዱ ኃላፊነትና ተግባር ፤ ቦርዱ የሚከተሉት ኃላፊነትና ተግባራት ይኖሩታል ፤ የዕቅድ ሃሣብ ያመነጫል ፤ በዕቅድ አዘገጃጀትና አፈጻጸም የተቀናጀ ቀጣይ እገዛ ይሰጣል ፤ ራሳቸውን የሚያስችል ቀጣይ የአቅም ግንባታ እገዛ ለክልሎቹ ያደርጋል ፤ ፫ . በልማትና በመልካም አስተዳደር ለክልሎቹ የሚደረገውን ሁሉንም የፌዴራል እገዛ ያቀናጃል ፤ ፮ . የቦርዱ ኣባላት ቦርዱ የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል፡ ፩ . የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ................... ሰብሳቢ ፪ . የግብርና እና የገጠር ልማት ሚኒስቴር ........ አባል ፫ የትምህርት ሚኒስቴር ፬ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ፭ . የወሃ ሀብት ሚኒስቴር ፮ . የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ፯ . የገቢዎች ሚኒስቴር ፰ የመሠረተ ልማት ሚኒስቴር ፯ . የቦርዱ ስብሰባ ፩ . ቦርዱ በሦስት ወር አንድ ጊዜ ይሰበሰባል ፤ ሆኖም አስፈላጊ በሰብሳቢው በማናቸውም ጊዜ ሊሰበሰብ ይችላል ፡፡ ፪ . ከቦርዱ አባላት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በስብሰባ ላይ ከተገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይሆናል ፡፡ ፫ . ቦርዱ ውሣኔ የሚያሳልፈው በድምጽ ብልጫ ይሆናል ፤ ሆኖም ድምጹ እኩል ከሆነ ሰብሳቢው የደገፈው ሀሣብ የቦርዱ ውሣኔ ይሆናል ፡፡ ፬ . የዚህ ኣንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ፡፡ ፰ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ኃላፊነትና ተግባር ሚኒስቴሩ የሚከተሉት ኃላፊነቶችና ተግባሮች ይኖሩታል ፤ ገጽ ፪ሺ፮፻፴፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፬ ሰኔ ፲፯ ቀን ፲፱፻፮ ዓ.ም. ጽ / ቤትና የፌዴራል እገዛውን የሚያቀናጅ ማእከል ሆኖ ያገለግላል ፤ የቦርዱን ውሣኔ አፈጻጸም ይከታተላል ፤ ኣጎራባች የሚሠጡትን እገዛ ያቀናጃል ፡፡ ፫ . አግባብ ያላቸው ሚኒስቴር መ / ቤቶችና ክልሎቹ የሚሰተፉበት ዓመታዊ ስብሰባ ይጠራል ፤ ፬ ቦርዱን በመወከል ከሦስተኛ ወገኖች ጋር ግንኙነት ያደርጋል ፡፡ ፬ . ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ ይህ ደንብ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል ፡፡ መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ደሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ