×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር 235/93 የፌዴራል የሥነ ምግባር እና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሰባተኛ ዓመት ቁጥር ፳፫ አዲስ አበባ ግንቦት ፲፮ ቀን ፲፱፻፶፫ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፪፻፴፭ / ፲፱፻፫ ዓም የፌዴራል የሥነ ምግባር እና የጸረ ሙስና ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ገጽ ፭ሺ፬፻፵፰ አዋጅ ቁጥር ፪፻፴፭ ፲፱፻፲፫ የፌዴራል የሥነ ምግባር እና የጸረ ሙስና ኮሚሽንን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝቦች ሙስና እና ብልሹ አሠራር የአንድን አገር ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ ዕድገት የሚገታ ተግባር መሆኑን የተገነዘቡ በመሆናቸው፡ አገሪቱ የተያያዘችውን የዕድገት ጎዳና እና የዲሞክራሲያዊ | development of any country ; ሥርዓት ግንባታ ለማፋጠንና ቀጣይነት ያለው እንዲሆን ሙስናን እና ብልሹ አሠራርን በቁጥጥር ሥር ማዋል አስፈላጊ በመሆኑ ሙስናን እና ብልሹ አሠራርን ለመሸከም የማይፈልግ እና ይህንኑ በብቃት ለመዋጋት ዝግጁ የሆነ ሕብረተሰብ መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ፡ ሙስናን እና ብልሹ አሠራርን ለመመርመር እና ለመክሰስ፡ ለመቆጣጠር እና ለመከላከል መልካም ሥነ ምግባር በኅብረተሰቡ ውስጥ እንዲስፋፋ በማድረግ ሙስናን እና ብልሹ አሠራርን መዋጋት የሚችል ነፃና ራሱን የቻለ መንግሥታዊ አካል ማቋቋም | impropriety through the promotion of ethical values in the አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፵፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የፌዴራል የሥነ ምግባር እና የጸረ ሙስና ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፪፻፴፭ / ፲፱፻፶፫ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ፡ ያንዱ ዋጋ 440 ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፴ሺ፩ ገጽ ፭ሺ፬፻፷፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፫ ግንቦት ፲፮ ቀን ፲፱፻፫ ዓም • ፩ . “ ኮሚሽን ” ማለት የፌዴራል የሥነ ምግባር እና የጸረ ሙስና ኮሚሽን ነው፡ ፪ . “ ኮሚሽነር እና ምክትል ኮሚሽነር ” ማለት እንደቅደም ተከተሉ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ወይም ምክትል ኮሚሽነር ፫ . “ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ” ማለት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በመንግሥት በጀት የሚተዳደር እና የፌዴራል መንግሥቱ ሥራዎች የሚከናወኑበት ማናቸውም መሥሪያ ቤት ነው ፥ ፬ . “ የመንግሥት ልማት ድርጅት ” ማለት የመንግሥት ባለቤትነት ድርሻ በሙሉ ወይም በከፊል ያለበት ማናቸውም የፌዴራል መንግሥት የልማት ድርጅት ወይም የአክሲዮን ኩባንያ ነው፡ ፭ “ የመንግሥት ባለሥልጣን ” ማለት በመንግሥት መሥሪያ ቤት ወይም ልማት ድርጅት ውስጥ በኃላፊነት እንዲያገለግል በመንግሥት ወይም በቦርድ የተሾመ፡ የተመደበ ፥ የተቀጠረ ወይም በሕዝብ የተመረጠ ማንኛውም ሰው ነው ፥ ፮ . “ የመንግሥት ሠራተኛ ” ማለት ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም በፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግ ወይም በአሠሪና ሠራተኛ ሕግ ወይም ራሱን በቻለ ሌላ ሕግ የሚተዳደርና በመን ግሥት መሥሪያ ቤት ወይም በመንግሥት ልማት ድርጅት ውስጥ ተቀጥሮ ወይም ተመርጦ የሚሠራ ማንኛውም ሰው ነው፡ ፯ . “ የሥነ ምግባር አውታሮች ” ማለት በመንግሥት አስተ ዳደር ውስጥ ምግባረ ብልሹ ባህርያትን በከፍተኛ ደረጃ ለመቀነስ እና ሙያዊ ብቃትን እና መልካም ሥነ ምግባርን ለማበረታታት የሚያገለግሉ ዘዴዎች፡ አካላት፡ ሥርዓቶች ወይም ኣስፈላጊ ሁኔታዎች እና የመሳሰሉት ፰ . “ ሰው ” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው ። ክፍል ሁለት ስለኮሚሽኑ መቋቋም እና ሥልጣንና ተግባር ፫ . የኮሚሽኑ መቋቋም ፩ . የፌዴራል የሥነ ምግባር እና የጸረ ሙስና ኮሚሽን | ከዚህ በኋላ “ ኮሚሽኑ ” እየተባለ የሚጠራ ራሱን የቻለ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤት ሆኖ በዚህ አዋጅ | 4. Independence of the Commission ተቋቁሟል ። ፪ • የኮሚሽኑ ተጠሪነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል ። ፬ . ስለኮሚሽኑ የአሠራር ነጻነት የዚህ አዋጅ አንቀጽ ፪ ንዑስ አንቀጽ / ፪ እና አንቀጽ ፬ ንዑስ አንቀጽ / ፪ / ሰ እና / ሸ ድንጋጌዎች ቢኖሩም ኮሚሽኑ ሥራውን በማከናወን ረገድ ከማንኛውም ሰው ጣልቃ ገብነት | 5 Head Office ወይም አመራር ነፃ ነው ። ዋና መሥሪያ ቤት የኮሚሽኑ ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ ይሆናል ። ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በየክልሉ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶችን ሊያቋቁም ይችላል ። የኮሚሽኑ ዓላማዎች ኮሚሽኑ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል ፤ የሥነ ምግባር እና የጸረ ሙስና ትምህርቶችን በማስ ፋፋት የነቃ እና ሙስናን ሊሸከም የማይችል ሕብረ ተሰብ እንዲፈጠር ጥረት ማድረግ ፣ የሙስና ወንጀልን እና ብልሹ አሠራርን መከላከል ፣ የሙስና ወንጀልን እና ብልሹ አሠራርን በማጋለጥ ፥ በመመርመር እና በመክሰስ በአገሪቱ ውስጥ ሐቀኛ የሕዝብ አገልግሎት እንዲሰፍን ጥረት ማድረግ ፣ ገጽ ፭ሺ፬፻፲ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፫ ግንቦት ፲፮ ቀን ፲፱፻፰ ዓም ፬ . ለመንግሥት ባለሥልጣኖች ለመንግሥት ሠራተኞች የሚያገለግሉ የሥነ ምግባር ደንቦች እንዲ ዘጋጁ ማድረግ ፣ ተፈጻሚነታቸውን መከታተል ' እና ሌሎች ለሚያዘጋጇቸው የሥነ ምግባር ደንቦች ሲጠየቅ ድጋፍ ማድረግ ። ፯ • የኮሚሽኑ ሥልጣንና ተግባር ኮሚሽኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፤ ስለሙስና ጎጂነት የሕዝቡ ንቃተ ሕሊና እንዲጎለብት በማስተማር እና መልካም ሥነ ምግባር በሕዝብ አገል ግሎት እና በኅብረተሰቡ ውስጥ እንዲስፋፋ በማድረግ ሙስናን እና ብልሹ አሠራርን መዋጋት ፣ ፪ • በመንግሥት መ / ቤቶች እና በመንግሥት ልማት ድርጅቶች ውስጥ ለሙስና የተጋለጡ የአሠራር ሥርዓ ቶችን በመመርመርና እንዲሻሻሉ በማድረግ ሙስናን የመከላከል ፣ በሌሎች ሰዎች ሲጠየቅ ተመሳሳይ ምክርና ድጋፍ የመስጠት ፣ ፫ በመንግሥት መ / ቤቶች እና በመንግሥት ልማት ድርጅቶች ውስጥ ከባድ የሥነ ምግባር መጣስ ስለመ ፈጸሙ ጥቆማ ሲደርሰው ወይም በቂ ጥርጣሬ ሲኖረው የማጣራት ወይም እንዲጣራ የማድረግ እና ተገቢው እርምጃ እንዲወስድ የመከታተል ፣ ፬ • በወንጀል ሕግ እና በሌሎች ሕጎች ውስጥ የተመለከቱ የሙስና ወንጀሎች በመንግሥት መ / ቤቶች ወይም በመን ግሥት ልማት ድርጅቶች ውስጥ ፣ ወይም የመንግሥት መ / ቤቶች ወይም የመንግሥት ልማት ድርጅቶች የተካፈ ሉበት በሆነ ጊዜ በግሉ ዘርፍ ፣ ወይም ፌዴራል መንግሥቱ ለክልሎች ከሚሰጠው ድጎማ በተያያዘ በክልል መ / ቤቶች ውስጥ ስለመፈጸማቸው ጥቆማ ሲደርሰው ወይም በቂ ጥርጣሬ ሲኖረው ምርመራ የማድረግ ወይም እንዲመረመር የማድረግ እና ክስ የመመሥረት ፣ ፭ የሙስና ወንጀሎችን በመመርመር ሂደት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ መሠረት ማንኛውንም ግቢ ፣ የሥራ ቦታ ፣ ተሽከርካሪ ወይም ማናቸውንም ሌላ ንብረት ፣ እንደአስፈላጊነቱ የመፈተሽ ፣ የመበርበር እና የመያዝ ፣ ፮ : በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ መሠረት በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ሰዎችን ከ፵፰ ሰዓት ላልበለጠ ጊዜ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ አሥሮ የማቆየት ፣ በሕግ መሠረት በዋስትና የመልቀቅ እና ተጠርጣሪዎችን የጣት አሻራና ፎቶግራፍ የመውሰድ ፣ ፯ . ለምርመራ አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ማንኛውንም ሰው በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግና በሌሎች ሕጎች መሠረት አስቀርቦ የመጠየቅ ፣ ቃል የመቀበል እና ከማን ኛውም ሰው ወይም መ / ቤት ማስረጃ እንዲቀርብለት የማዘዝ ፣ ፰ ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ የተገኘ እና በባንክ የተቀመጠ ገንዘብ ለመኖሩ በቂ ጥርጣሬ ወይም ማስረጃ ሲኖር በማናቸውም ባንክ የሚገኝ የተጠርጣሪዎችየባንክ ሂሳብ በኮሚሽነሩ ትዕዛዝ እንዲመረመር የማድረግ እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲከበር የማድረግ ፣ ፱ የመንግሥት ባለሥልጣኖችን እና በሕግ ሀብታቸውንና የገንዘብ ጥቅማቸውን እንዲያስመዘግቡ ግዴታ ያለባ ቸውን የመንግሥት ሠራተኞች ሀብትና የገንዘብ ጥቅሞች መዝግቦ የመያዝ ፣ ወይም ተመዝግበው እንዲያዙ የማድረግ ፣ ፲ ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ በምርመራ ላይ ያሉ ሰዎች ሀብት በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዳይንቀሳቀስ የማድረግ ፣ በሙስና ወንጀል የተገኘ ለመሆኑ የተረጋገጠን ማናቸ ውንም ንብረት ወይም ሀብት በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲወረስና በሐራጅ ተሸጦ ወይም ሳይሽጥ ለመንግሥት ገቢ እንዲሆን የማድረግ ፣ 3 ሱራዋና ዓለም ገጽ ፭ሺ፬፻፶፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፰ ግንቦት ፲፮ ቀን ፲፱፻፰ ዓም ፲፩ የሥነ ምግባር ደንቦችእና የጸረ - ሙስና ሕጎች መከበራ ቸውን የመከታተል እና የማረጋገጥ ፣ ስለአፈጻጸማቸው የምክር አገልግሎት የመስጠት ፣ ፲፪ ሥነ ምግባርን እና ሙስናን በተመለከተ ጥናትና ምርምር የማድረግ እና ተመሳሳይ ሥራዎችን የመደገፍ ፣ የኮሚ ሽኑን ዓላማዎች ለማራመድ የሚረዱ ሪፖርቶችን እና ቴክኒካዊ ጥናቶችን አሳትሞ የማሰራጨት ፣ ፲፫ የሥነ ምግባር ደንቦች እና ደንቦቹ ሲጣሱ የሚወሰዱ እርምጃዎች የተጣጣሙ እንዲሆኑ ሌሎች የሥነ ምግባር አውታሮችን የማስተባበር ፣ ፲፬ • የሕግ አውጭና የዳኝነት አካላትን ሳይጨመር ለመን ግሥት መሥሪያ ቤቶችና ለመንግሥት ልማት ድርጅቶች የሚያገለግሉ የሥነ ምግባር ደንኮች መዘጋጀታቸውን ማረጋገጥ ወይም ማዘጋጀት እና አፈጻጸማቸውን የመከ ታተል ፣ ከሕግ አውጭ እና ከዳኝነት አካላት ጥያቄ ሲቀርብለት በሥነ ምግባር ደንብ አዘገጃጀት ረገድ ምክር የመስጠት ፣ ፲፭ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና የመንግሥት ልማት ድርጅቶች የሥነ ምግባር መጣስና የሙስና ወንጀል የተፈጸመ ለመሆኑ ጥርጣሬ ሲኖራቸው በራሳቸው ተነሳ ሽነት ምርመራማካሄድ ይችላሉ ። በከባድ የሥነ ምግባር መጣስና በሙስና ወንጀል ጉዳይ ግን ውሳኔ ላይ ከመድረ ሳቸው በፊት በምርመራ ያገኙትን ውጤት ለኮሚሽኑ ሪፖርት የማድረግ ግዴታ አለባቸው ፣ ፲፮ ለጠቋሚዎች እና ለምሥክሮች የአካልና የሥራ ዋስትና ጥበቃ የመስጠት ፣ ፲፯ ሙስናን በመታገል እና በመከላከል ረገድ ጥሩ ውጤት ያስገኙ ሰዎችን እና መ / ቤቶችን አወዳድሮ ለሽልማት የሚበቁበትን ሥርዓትና መለኪያ የመዘርጋት፡ ተግበራዊ የማድረግ ፣ ፲፰ . ለክልሎች አስፈላጊውን የምክርና የድጋፍ አገልግሎት የመስጠት ፣ ፲፱ . ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸው አገራዊ ፣ አቀፋዊ አካላት ጋር ግንኙነትና ትብብር የመፍጠር ፣ ፳ • የንብረት ባለቤት የመሆን ፣ ውል የመዋዋል ፣ በራሱ ስም የመክሰስና የመከሰስ ፣ ፳፩ . በሕግ የሚሰጡትን እና ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን የማከናወን ። ፰ የኮሚሽኑ አቋም ኮሚሽኑ ፣ ፩ በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በተወካዮች ምክር ቤት የሚሾሙ አንድኮሚሽነርእና አንድምክትል ኮሚሽነር ፣ ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ ሠራተኞች ፣ ይኖሩታል ። ፱ • የኮሚሽነሩ ሥልጣንና ተግባር ፩ ኮሚሽነሩ የኮሚሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን የኮሚሽኑን ሥራዎች ያደራጃል ፣ ይመራል ፣ ያስተዳ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) አነጋገር እንደተጠበቀ ሆኖ ከሚሽነሩ ፣ ገጽ ፭ሺ፬፻፲፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፬ ግንቦት ፲፮ ቀን ፲፱፻፫ ዓ.ም ሀ ) በዚህ አዋጅ በአንቀጽ ፯ የተዘረዘሩትን የኮሚሽኑን ሥልጣንና ተግባራት በሥራ ላይ ያውላል ፣ ለ ) የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግ አጠቃላይ መርሆ ዎችን መሠረት በማድረግ በሚያወጣው ደንብና የኮሚሽኑን ሠራተኞች ይቀጥራል ፣ ያስተዳድራል ፣ ያሰናብታል ፣ ሐ ) የኮሚሽኑን ዓመታዊ የሥራ ፕሮግራም እና የአምስት ዓመት በጀት ያዘጋጃል ፣ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል ፣ ለኮሚሽኑ በተፈቀደለት በጀት እና ፕሮግራም መሠረት የፋይናንስ ሕግን ተከትሎ ገንዘብ ወጪ ያደርጋል ፤ ሠ ) በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩ ወይም ጥፋተኛ ሆነውየተገኙሰዎችን የኮሚሽኑሠራተኞች በሕግ መሠረት ለመመርመር ወይም ለማሰር እንዲችሉ ሥልጣን ይሰጣል ፤ ረ ) ምርመራው በመከናወን ላይ ላለ ጉዳይ አግባብነት ያለው በሆነ ጊዜ የማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት የባንክ ሂሳብ እንዲፈተሽ እና አስፈላጊው መረጃ እንዲሰበሰብ ትዕዛዝ ለመስጠት ይችላል ፤ ሰ ) የኮሚሽኑን ጠቅላላ የአሰራር ሂደት ፣ የሥራ ግምገማ ውጤትና አስተያየት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቀርባል ፤ ሸ ) እንደአግባቡ ለቦርዱ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ያስተላልፋል ፤ ቀ ) ኮሚሽኑ ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በሚያደርጋቸው ግንኙነቶች ኮሚሽኑን ይወክላል ። ፫ ኮሚሽነሩ ለኮሚሽኑ ሥራ ቅልጥፍና በሚያስፈልግ መጠን ሥልጣንና ተግባሩን በከፊል ለኮሚሽኑኃላፊዎች እና ሠራተኞች በውክልና ሊያስተላልፍ ይችላል ። ፲ የኮሚሽነሩ የሥራ ዘመንና ከሥራ መነሳት ፩ . የኮሚሽነሩ የሹመት ዘመን ለ፮ ዓመት ይሆናል ፤ ሆኖም አስፈላጊ ሲሆን በተወካዮች ምክር ቤት ተቀባይነት ሲያገኝ በድጋሚ ሊሾም ይችላል ። ፪ • ኮሚሽነሩ የሹመት ዘመኑ ከማለቁ በፊት ከዚህ በታች በተመለከቱት ምክንያቶች ካልሆነ በስተቀር ከሥራው አይነሳም ፤ ሀ ) በወንጀል ተከሶ ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት ጥፋተኛ መሆኑ ሲረጋገጥ ፤ ለ ) በአእምሮ ወይም በአካል ሕመም ምክንያት ተግባሩን በተገቢው ሁኔታ ማከናወን ሲሳነው ፤ ፲፩ . የምክትል ኮሚሽነሩ ሥልጣንና ተግባር ምክትል ኮሚሽነሩ ተጠሪነቱ ለኮሚሽነሩ ሆኖ ፤ ሀ ) ኮሚሽነሩ በማይኖርበት ጊዜ ወይም የኮሚሽነሩ ቦታ ክፍት በሚሆንበት ጊዜ ኮሚሽነሩን ተክቶ ይሰራል ፤ ለ ) የምርመራ መምሪያን በዳይሬክተርነት ይመራል ፤ ሐ ) በኮሚሽነሩ የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል ፤ ፲፪ • የምክትል ኮሚሽነሩ የሥራ ዘመንና ከሥራ መነሳት የምክትል ኮሚሽነሩ የሹመት ዘመን ለ፮ ዓመት ይሆናል ፤ ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝና በተወካዮች ምክር ቤት ተቀባይነት ሲያገኝ በድጋሚ ሊሾም ይችላል ። ፪ • ምክትል ኮሚሽነሩ የሹመት ዘመኑ ከማለቁ በፊት ከዚህ በታች በተመለከቱት ምክንያቶች ካልሆነ በስተቀር ከሥራው አይነሳም ፤ ሀ ) በወንጀል ተከሶ ሥልጣን ባለው ፍርድ ቤት ጥፋተኛ መሆኑ ሲረጋገጥ ፤ ለ ) በአእምሮ ወይም በአካል ሕመም ምክንያት ተግባሩን በተገቢው ሁኔታ ማከናወን ሲሳነው ። ገጽ ፭ሺ፬፻፰ ፈዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር፳፫ግንቦት ፲፱ ቀን ፲፱፻፰ ዓም : ፲፫ ስለኮሚሽኑ ሠራተኞች ቅጥር ሁኔታ ፩ ኮሚሽነሩ በዚህ አዋጅ ለኮሚሽኑ የተሰጡትን ሥልጣንና ተግባራት ለማከናወን በሚያስፈልግ መጠን ችሉታን እና መልካም ሥነ ምግባርን መሠረት አድርጎ ሠራተኞችን ይቀጥራል ። ጀ • ኮሚሽነሩ ከአማካሪ ቦርዱ ጋር በመመካከር የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግን አጠቃላይ መርሆዎች መሠረት በማድረግ የኮሚሽኑን የሠራተኞች አስተዳደር ደንብና ሁኔታ አዘጋጅቶ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲጸድቅ በሥራ ላይ ያውላል ፤ በአስተዳደር ደንቡ መሠረት ከሥራ ያሰና ፲፬ በጀት መንግሥት የኮሚሽኑን የአምስት ዓመት በጀት ይመድባል ። ይኸውም እንደገና በኮሚሽኑ ዓመታዊ የሥራ ፕሮግራም መሠረት ተዘርዝሮ ይፈቀዳል ። ፲፭ የሂሳብ መዛግብት ፩ ኮሚሽኑ የተሟሉ እና ትክክለኛ የሂሳብ መዛግብት ይይዛል ። ፪ የኮሚሽኑ የሂሳብ መዛግብት እና ገንዘብ ነክ ሰነዶች | 16. Establishment of Advisory Board በፌዴራሉ ዋና ኦዲተር በየዓመቱ ይመረመራል ። ክፍል ሦስት ስለአማካሪ ቦርድ ፲፮ : የአማካሪ ቦርድ መቋቋም ፩ የሚከተሉት አባላትየሚኖሩት አንድአማካሪ ቦርድ ( ከዚህ በኋላ “ ቦርዱ ” እየተባለ የሚጠራ ) ይቋቋማል ፤ ሀ ) ኮሚሽነሩ ፤ ለ ) የኮሚሽኑ ልዩ ልዩ መምሪያዎች ዳይሬክተሮች ፤ ሐ ) ዋናው ኦዲተር ወይም የእርሱ ምክትል ፤ መ ) የፍትሕ ሚኒስትር ወይም የእርሱ ምክትል ፤ ሠ ) የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ወይም የእርሱምክትል ፤ ረ ) የደህንነት ኢሚግሬሽንና ስደተኞች ጉዳይ ባለሥ ልጣን ኃላፊ ወይም የእርሱ ምክትል ፤ ሰ ) የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር ወይም የእርሱ ምክትል ፤ ሸ ) በተወካዮች ምክር ቤት እና በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባዔዎች የሚመረጡና የየምክር ቤቶቹን ይሁንታ ያገኙ፫የፓርላማ አባላት ፣ ፪ከተወካዮች ፣ ፩ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ቀ ) መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፩ ተወካይ ፤ በ ) የተደራጀው የንግድ ኅብረተሰብ ፩ ተወካይ ፤ ተ ) የመንግሥትና የግል መገናኛ ብዙኀን ፪ ተወካዮች ፤ ት ) የሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን ፪ ተወካዮች ፤ ኀ ) የሴቶች ማህበር ፩ ተወካይ ነ ) የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፩ ተወካይ፡ ን ) ከዕንባ ጠባቂ ተቋም ፩ ተወካይ አ ) ከሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ፩ ተወካይ፡ ከ ) በየስድስት ወሩ የሚለወጡ የኃይማኖት ተቋማት ፪ ተወካዮች ኸ ) በየስድስት ወሩ የሚለወጡ የክልል የሥነ ምግባርእና የጸረ ሙስና አካላት ፪ ተወካዮች ። ገጽ ፩፬፻፲፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፫ ግንቦት ፲፮ ቀን ፲፱፻፶፫ ዓም • ቦርዱ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ( ሀ ) እና ( ለ ) ከተመለከቱት ውጪ ካሉት ኣባላቱ መካከል የራሱን ሰብሳቢ ይመርጣል ፤ ጸሐፊው ግን የኮሚሽኑ የአስተዳደር መምሪያ ዳይሬክተር ይሆናል ። ፫ የቦርዱ ተጠሪነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል ። ፲፯ . የቦርዱ ሥልጣንና ተግባራት ቦርዱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡ ፩ ሙስናን እና ብልሹ አሠራርን በመዋጋት ረገድ የቅድሚያ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ተግባራትን በመለየት እና የሥነ ምግባር ትምህርትን በማስፋፋት ረገድ ኮሚሽነሩን የማማከር፡ ፪ • የኮሚሽኑን የአሠራር፡ የሠራተኛ አቀጣጠር እና አስተዳ ደራዊ ፖሊሲዎች እና ስትራቴጂዎች የማጥናት እና ስለሚሻሻሉበት ሁኔታ ኮሚሽነሩን የማማከር፡ ፫ በኮሚሽኑ ሠራተኞች ላይ በሚቀርቡ አቤቱታዎች ላይ የተወሰዱ የዲሲፕሊን እርምጃዎችን በሚመለከት በየጊዜው በኮሚሽነሩ የሚቀርብለትን ሪፖርት ተቀብሎ አስፈላጊውን ምክር የመስጠት፡ በምርመራ ላይ ያለ ሰው ወይም ድርጅት የባንክ ሂሳብ እንዲፈተሽና መረጃ እንዲሰበሰብ በኮሚሽነሩ የተሰጡ ትዕዛዞችን ተገቢነት በሚመለከት በየጊዜው ከኮሚሽነሩ ሪፖርት የመቀበል እና አስፈላጊ የመሰለውን ምክር የመስጠት፡ የቦርዱን ሥራ ለማከናወን አስፈላጊ የሆኑ ልዩ ልዩ ኮሚቴዎችን ከአባላቱ መካከል የማቋቋም እና ከነዚሁ ኮሚቴዎች በየጊዜው እንዲቀርብለት የማድረግ፡ ፮ ለሥራው አስፈላጊ የሆኑ ባለሙያዎችን በአስረጅነት የመጥራት ። ሙስናን በመታገል እና በመከላከል ጥሩ ውጤት ያስገኙ ግለሰቦችን እና መ / ቤቶችን አስቀርቦ በውድድር ስለሚሸ ለሙበት ሁኔታ ኮሚሽኑን የማማከር፡ ስለሥራው እንቅስቃሴ በተለይም ለኮሚሽነሩ የተሰጡ ማናቸውንም ምክሮች የሚያሳይ ፡ የተሠሩ ሥራዎችን የሚገልጽ ጠቅለል ያለ መግለጫን የያዘ እና ችግሮችን ለይቶ የሚያመለክት እናችግሮቹን ለማስወገድ ሊወስዱ የሚገባቸውን እርምጃዎች የሚጠቁም ሪፖርት በየስ ድስት ወሩ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የማቅረብ፡ ፱ ከኮሚሽነሩ የሚመሩለትን ሌሎች ተመሳሳይ ተግባራት የማከናወን ። የቦርዱ የስብሰባ ሥርዓት ቦርዱ በየሦስት ወሩ አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያካሂዳል፡ ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የቦርዱ ሰብሳቢ በራሱ ተነሳሽነት ወይም በኮሚሽነሩ ሲጠየቅ በማና ቸውም ጊዜ አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል ። ከቦርዱ አባላት ከግማሽ በላይ በስብሰባው ከተገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይሆናል ። የቦርዱ ውሳኔዎች በድምጽ ብልጫ ያልፋሉ ፥ ሆኖም ድምጽ እኩል በእኩል በተከፈለ ጊዜ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ይኖረዋል ። የቦርዱ የስብሰባ ቦታ በኮሚሽኑ ዋና ጽሕፈት ቤት ይሆናል ። የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። ክፍል አራት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፲፱ : ስለኮሚሽኑ የፖሊስነትና እና የዐቃቤ ሕግነት ሥልጣን ስለመመርመርና ስለመከሰስ በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ሥነ ሥርዓትና በሌሎች ሕጎች ለፖሊስና ለዐቃቤ ሕግ የተሰጠ ሥልጣን በዚህ አዋጅ ውስጥ የተመለከቱ ጉዳዮችን በሚመ ለከት ለኮሚሽኑ ተሰጥቷል ። ገጽ ሺ፩ሺ፪፻፲፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፫ ግንቦት ፲፮ ቀን ፲፱፻፫ ዓም • የሥነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች መቋቋም ፩ በየደረጃው በሚገኙ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እና የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ውስጥ የሥነ ምግባር ሁኔታን የሚያስተባብሩ እና ለየመሥሪያ ቤቶቹ የበላይ ኃላፊዎች የሚያማክሩ የሥነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች ይቋቋማሉ ። ፪ የሥነ ምግባር መከታተያ ክፍል ተጠሪነቱ ለመሥሪያ ቤቱየበላይኃላፊይሆናል ። ሆኖም ከኮሚሽኑጋርየሥራ ትብብር ይኖረዋል ። የመተባበር ግዴታ ማንኛውም ሰው ከኮሚሽኑ ሥልጣንና ተግባር ጋር በተያያዘ ለሚጠየቀው ትብብርና ድጋፍ የመተባበር ግዴታ አለበት ። በሌላ ሕግ የበለጠ የሚያስቀጣ ካልሆነ በስተቀር ማንኛውም ሰው ለኮሚሽኑ ፣ ለፍትሕ አካላት ወይም ለመንግሥት መሥሪያ ቤት ኃላፊ ወይም ለመንግሥት ልማት ድርጅት ኃላፊ ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ መረጃ ወይም ማስረጃ በሰጠ ሰው ላይ ተጽዕኖ ለማድረግ ወይም ጉዳት ለማድረስ የሞከረ ወይም ያደረሰ ወይም ይህንኑ ሰው ለመቅጣት የሞከረ ወይም የቀጣ እንደሆነ ከሦስት ዓመት በማያንስ ከአሥራ አምስት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እሥራት እና ከስድስት ሺህ ብር በማያንስ ከሃያ አምስት ሺህ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ። ማንኛውም የኮሚሽኑ ኃላፊ ወይም ሠራተኛ በሕግ የተሰጠውን ሥልጣንና ኃላፊነት ያለአግባብ የተገለገ ለበት እንደሆነ ፣ በዚያም የተነሳ ያገኘው ጥቅም መወረሱ እንደተጠበቀ ሆኖ ፤ ከአምስት ዓመት በማያንስ ከአሥራ አምስት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እሥራት እና ከሦስት ሺህ ብር በማያንስ፡ ከአሥር ሺህ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ። ማንኛውም ሰው ሆን ብሎ ኮሚሽኑን ለማሳሳት ወይም ሌላውን ሰው ለመጉዳት ሐሰተኛ ሪፖርት ፡ ጥቆማ ወይም መረጃ ለኮሚሽኑ ያቀረበ እንደሆነ ከአንድ ዓመት በማያንስ ከአምስት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እሥራት እና ከሦስት ሺህ ብር በማያንስ ' ከአሥር ሺህ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ። ማንኛውም ሰው የኮሚሽኑ ሠራተኛ መስሎ በመቅረብ የማታለል ሥራ የፈጸመ እንደሆነ ከሁለት ዓመት በማያንስ ከሰባት ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እሥራት እና ከአምስት ሺህ ብር በማያንስ ፣ ከአሥራ አምስት ሺህ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ። ማንኛውም ሰው በዚህ አዋጅ በአንቀጽ ፳፩ በተደነ ገገው መሠረት ኮሚሽኑን ለመተባበር እንቢተኛ የሆነ እንደሆነ ከስድስት ወር በማያንስ ከአራት ዓመት በማይበልጥ እሥራት እና ከአንድ ሺህ ብር በማያንስ ከአምስት ሺህ ብር በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ። ማንኛውም ሰው የኮሚሽኑን ሥራ ያደናቀፈ ወይም ለማደናቀፍየሞከረእንደሆነ ከሁለት ዓመት በማያንስ ከአሥር ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እሥራት እና ከአምስት ሺህ ብር በማያንስ ከሃያ ሺህ ብር በማይ በልጥ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል ። ወንጀሉ የተፈ ጸመው ኃይልን በመጠቀም የሆነ እንደሆነ ቅጣቱ በዚሁ ንዑስ አንቀጽ የተደነገገው ከፍተኛ ቅጣት ይሆናል ። በዚህ አንቀጽ በንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ፣ ( ፫ ) ፣ ( ፬ ) ፣ ( ፭ ) እና ( ፮ ) የተመለከቱት ወንጀሎች የሕግ ሰውነት ባለው ድርጅት በተፈጸሙ ጊዜ የገንዘብ ቅጣቱ አምስትእጥፍ ይሆናል ። የመሸጋገሪያ ድንጋጌ ይህ አዋጅ በሥራ ላይ ከመዋሉ በፊት ተፈጽመው ምርመ ራቸው በጅምር፡ ወይም በሂደት ላይ ያለም ሆነ ፣ የተጠናቀቁ ወይም በፍርድ ቤት በመታየት ላይ ያሉ የሙስና እና ከሙስና ጋር የተያያዙ የወንጀል ጉዳዮች በነበሩበት ሁኔታ ቀጥለው ውሳኔ ያገኛሉ ። ገጽ ፭ሺ፬፻ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፯ ግንቦት ፲፮ ቀን ፲፰ ዓም • ደንብና መመሪያ የማውጣት ሥልጣን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም ደንብ ሊያወጣ ይችላል ። ፪ ኮሚሽኑ ይህንን አዋጅና በዚህ አዋጅ መሠረት የሚወ ጣውን ደንብ ለማስፈጸም መመሪያ ሊያወጣ ይችላል ። ፳፭ ተፈጻሚነት ስለማይኖራቸው ሕጎች ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረኑማናቸውም ሌሎች ሕጎች በዚህ አዋጅ ውስጥ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖራ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከግንቦት ፲፮ ቀን ፲፱፻፫ ዓ.ም. ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ግንቦት ፲፮ ቀን ፲፱፻፵ ዓም : ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?