×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 19958

      Sorry, pritning is not allowed

በመውጣቱና በዋስትና ያልተያዙ ቤቶች ጭምር በጨረታ እንዲሸጡ ማስታወቂያ በመውጣቱ ጨረታው እንዲቆም ክስ ኦዩ ሇ
የሰበር መ / ቁ 19958
ግንቦት 4/1998 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
ዓብዱልቃድር መሐመድ ጌታቸው ምህረቱ መስፍን ዕቁበዮናስ
5. ወ / ሂሩት መለሠ አመልካች፡- አቶ አስፋው ማናዬ ተጠሪ፡- የኢት / ንግድ ባንክ ጊምቢ ቅርንጫፍ
ፍ ር ድ ለሠበር መነሻ የሆነው ጉዳይ የጀመረው በም / ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍ / ቤት ሲሆን አመልካች ከተጠሪ ባንክ ለተበደሩት ብድር ያስያዙት ቤት ከግምቱ በታች ለመሸጥ ጨረታ
ጉዳዩን ያየው ከፍተኛ ፍ / ቤትም የቀረበውን ክስ ባለመቀበል ጨረታው እንዲቀጥል
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ / ቤትም የከፍተኛ ፍ / ቤቱን
ውሣኔ አጽንቷል ።
የአመልካች አቤቱታም የቀረበው በዚህ ውሣ ላይ ሲሆን ተጠሪ በዋስትና ከያዘው
ቤት ውጪ አመልካች ለተበደሩት ብድር መክፈያ ሌሉች ቤቶችን በአዋጅ ቁጥር 97/90
በጨረታ እንዲሸጡ
ማስታወቂያ
በአግባቡ
አለመሆኑን
ለማጣራት አቤቱታው ለሰበር ቀርቦ ችሎቱ የግራ ቀኙን የቃል ክርክር ሠምቷል ።
በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሠረት የሚንቀሣቀስ ወይም የማይንቀሣቀስ ንብረት
በዋሰትና የያዘ ባለገንዘብ ባንክ የሚፈልገው እዳ በተወሰነው ጊዜ ካልተከፈለው ማስጠንቀቂያ
ለባለዕዳው በመስጠት በመያዣ የያዘውን ንብረት በሀራጅ ለመሽጥ ይችላል :: / አንቀጽ 3
ይመለከታል / በመሆኑም በዚህ አዋጅ መሠረት ባንክ ላልተከፈለው እዳ ንብረት ሊሸጥ
የሚችለው ቀድሞውኑ ንብረቱን ለብድሩ በዋሰትና ወይም በመያዣ የያዘው ከሆነ ነው ።
መሆኑን ለምር / ቤቶች ተጠሪው የቤ / ቁ / 465 እና 480 በመያዣ የያዘው መሆኑን
ያወጣው ጨረታ እንዲቀጥል መወሰናቸው ህጉን ያልተከተለ በተያዘው ጉዳይ ተጠሪ ለአመልካች ላበደረው ብድር በአዋጁ መሠረት ጨረታ ያወጣው በአራት ቤቶች ላይ ማለትም በቤ / ቁ / 418 ፣ 468 ፣ 465 ፣ እና 480 ላይ ነው : የአመልካች ዋነኛ ክርክር የቤ / ቁ / 465 እና 480 ለበድሩ በዋስትና የተሰጡ አይደሉም የሚል ነው ። በዚህም መሠረት ይህ ችሉት ባንኩ እነዚህን ክርክር የተነሣባቸውን ቤቶች በመያዣ የያዘው መሆኑን ለማረገገጥ የማያዣ ውሉን ተመልክቷል ፡፡ በዚህም መሠረት ባንኩ ለአመልካች ለሰጠው ብድር በመያዝ የያዘው ባባለቤትነት ማረጋገጫ ሠነድ ቁጥር 02/86 የተመዘገቡትን የቤት ቁጥር 418 ፣ እና 468 ብቻ ነው :: ከዚህ ውጪ የቤት ቁጥር 465 እና 480 በመያዣ የተያዙ ለመሆኑ በሥር ፍ / ቤቶችም ቢሆን የተረጋገጠ ፍሬ ነገር የለም ። በመሆኑም ባንኩ በአ / ቁ / 97 / 90 መሠረት ራሱ ጨረታ በማውጣት ንብረት ሊሰጥ የሚችለው ፣ ከላይ እንደተገለፀው ፣ ንብረቱን ለሰጠው ብድር በመያዣ ይዞታ ከሆነ ብቻ ነው ፡፡ የማይንቀሳቀስ ንብረት የመያዣ ውል ደግሞ በጽሁፍ መሆንና መመዝገብ ያለበት በመሆኑ ( የፍ / ህ / ቁ / 1723 እና 3045 ይመለከታል ) ተጠሪ ቤቶቹን በመያዣ የያዘ
በጽሁፍ የተደረገና የተመዘገበ የመያዣ ውል ማቅረብ ይጠበቅበታል ፡፡ ነገር ግን በሥር ሣያረጋግጡ ቤቶቹ ላይ
መሆኑን ተረድተናል ፡፡
1 / የም / ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍ / ቤት በመ / ቁ / 184/94 በ 24 / 2 / 96 እንዲሁም የኦሮሚያ
ጠቅላይ ፍ / ቤት በመ / ቁ / 02605 በ 20 / 7 / 97 የሰጡት ውሣ ተሻሽሏል ፡፡
2 / ተጠሪ ጨረታውን ለቤ / ቁ / 418 እና 468 ላይ ብቻ እንዲቀጥል ። በመያዣ ያልተያዙት
ቤቶች ላይ ማለትም ከቤ / ቁ / 465 እና 480 በጨረታ ሊሸጡ አይገባም ።
3 / ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራቸውን ይቻሉ ::
መዝገቡ ተዘግቷል ይመለስ ።
ፌዴራል ቃላ ናርጅ ት
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
ቀን / 3 / 2 /

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?