×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 28130

      Sorry, pritning is not allowed

4 , ቃድ በገንዘብ ተለውጦ እንዲከፈላቸው
የሰ / መ / ቁ 28130
ዳኞች 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
2. አቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ 3. አቶ ጌታቸው ምህረቱ 4. አቶ መስፍን እቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሠ አመልካች የወረዳ 10 ቀበሌ 15 ህብረት ሱቅ ። አቶ ብርሃኑ ተሠማ
ፍ ር ድ አቤቱታ የቀረበው የፌ / መ / ደረጃ ፍ / ቤት አመልካች ለተጠሪ የ 12
ዓመት የአመት
በመወሠኑና ይህንኑ ውሣዔ
የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት በማጽናቱ ነው ።
ተጠሪ በፌ / መ / ደ ፍ / ቤት
ባቀረቡት ክስ አመልካች የሥራ ውላቸውን ከሕግ
ውጪ በማቋረጡ ወደ ሥራ እንዲመልሣቸው የማይመልሣቸው ከሆነም የ 12
የአመት ፈቃድን
የተለያዩ ክፍያዎች ተከፍሏቸው እንዲሰናበቱ ጠይቀዋል ።
ፍ / ቤቱም ጉዳዩን መርምሮ ስንብቱ ሕጋዊ መሆኑን አረጋግጦ 12 ዓመት የአመት ፈቃድ
በገንዘብ ተለውጦ እንዲሁም ሌሉች ይገባቸዋል ያለውን ክፍያዎች ወስኗል ፡፡ የፌ / ከፍተኛ
ፍ / ቤትም ለተጠሪ የ 12 ዓመት የአመት ፈቃድ እንዲከፈል የተሰጠውን ውሣ አጽድቋል ።
የሰበር አቤቱታውም የቀረበው ይህንኑ ውጭ በመቃወም ሲሆን ተጠሪ ቀርበው
ችሎቱ የግራ ቀኙን የጽሁፍ ክርክር መርምሯል ።
በዚህም ጉዳይ አከራካሪ የሆነው አንድ ሠራተኛ 12 ዓመት የተጠራቀመ የአመት
ፈቃድ ሊጠይቅ ይችላል ወይ ? የሚለው ነው ::
ዴራል ቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ግልባጭ
• ፈቁት በላይ የሆነውን የአመት ፈቃድ ሠራተኛው አንድ ሠራተኛ የአመት ፈቃድ ከክፍያ ጋር የማግኘት መብት ያለው መሆኑ በአዋጅ ቁጥር 42/85 አንቀጽ 77 / 1 / ሥር ተመልክቷል ፡፡ ሠራተኛውም ይህንን የአመት ፈቃድ በየአመቱ የማግኘት መብት ያለው መሆኑም በአዋጁ አንቀጽ 78 / 1 / መረዳት ይቻላል ። ነገር ግን ምንም እንኳን ሠራተኛው በየአመቱ የአመት ፈቃድ የማግኘት መብት ያለው ቢሆንም ከአሠሪው ጋር በመስማማት ወይም አሠሪው የሥራ ሁኔታ ሲያስገድደው የሠራተኛው የአመት ፈቃድ ወደ ሌላኛው አመት ሊተላለፍ የሚችል መሆኑ በአንቀጽ 79 / 2 / እና / 3 / ሥር ተመልክቷል ። በሌላ በኩል ግን በነዚህ ንዑስ ቁጥሮች ሥር በተመለከቱ ሁኔታዎች የአመት ፈቃድ ሊተላለፍ የሚችል ቢሆንም የተላለፈው የአመት ፈቃድ ከሚቀጥለው ሁለት ዓመት በላይ ሊራዘም የማይችል ለመሆኑ አንቀጽ 79 / 5 / ያመለክታል ። በመሆኑም የአንድ ሠራተኛ የአመት ፈቃድ ሊተላለፍ የሚችለው ቢበዛ አስከ ሁለት ዓመት ድረስ ብቻ ነው ። ስለሆነም ሠራተኛው የአመት ፈቃዱን እስከ ሁለት ዓመት ድረስ ካልጠየቀ ከዚያ በኋላ ሊጠይቅ የሚችልበት የሕግ መሠረት የለውም ።
ወደተያዘው ጉዳይ ስናመራ ተጠሪ የጠየቁት የ 12 ዓመት የአመት ፈቃድ ሲሆን ፍ / ቤቱም ጥያቄያቸውን እንዳለ ተቀብሎ ወስኖላቸዋል ፡፡ ከፍ ሲል እንደተገለፀው ግን በአ / ቁ 42/85 መሠረት ከሁለት
የማግኘት መብት የሌለው በመሆኑ የፍ / ቤቱ ውሣኔ የአዋጁን ድንጋጌ የሚቃረን ነው ።
ው ሣ ኔ
1. የፌ / መ / ደረጃ ፍ / ቤት በመ / ቁ 2469 በ 14 / 04 / 96 እንዲሁም የፌ / ከፍተኛ
ፍ / ቤት በመ / ቁ 30960 በ 12 / 11 / 96 አመልካች ለተጠሪ የ 12 ዓመት የአመት
ፈቃድ እንዲከፈል የሠጡት የውጭ ክፍል ተሻሽሏል ፡፡
2. ተጠሪ ከሥራ ከመሠናበታቸው በፊት የነበራቸው የመጨረሻው ሁለት ዓመት
የአመት ፈቃድ በገንዘብ ተለውጦ ይከፈላቸው ::
3. ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻሉ ። መዝገቡ ስለተዘጋ ይመለስ ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ፡፡
ፍራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክል ገልባኝ

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?