የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ሁለተኛ ዓመት ቁጥር ፪ አዲስ አበባ ጥር ፳፰ ቀን ፲፱፻፰፰ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፲፮ / ፲፱፻፳፰ ዓም የሰንደቅ ዓላማና አርማ አዋጅ . ገጽ ፲፬ አዋጅቁጥር ፲፮ / ፲፱፻፰ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሰንደቅ ዓላማና ዓርማ አዋጅ ስለ ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማና ዓርማ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፪ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እና ( ፪ ) የተደነገገ በመሆኑ ፤ ለሕገ መንግሥቱ ድንጋጌ አፈጻጸም ሰንደቅ ዓላማንና ዓርማን የሚመለከቱ ዝርዝር ጉዳዮችን የሚወስን ሕግ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፤ | በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ | መንግሥት አንቀጽ ፵፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የሰንደቅ ዓላማና ዓርማ አዋጅ ቁጥር ፲፮ | ፲፱፻ጅቷ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ክፍል ሁለት ስለ ሰንደቅ ዓላማና ብሔራዊ ዓርማ ፪ : የሰንደቅ ዓላማ ምንነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሰንደቅ ዓላማ ( ከዚህ በኋላ “ ሰንደቅ ዓላማው ” እየተባለ የሚጠራ ) የሪፐ ብሊኩ ሉዓላዊነትና የሕዝቦች በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ አንድነት መግለጫ ነው ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ• ቸሺ፩ ገጽ ፲፭ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፬ ጥር ፳፰ ቀን ፲፱፻ዥ፰ ዓ•ም• _ Negarit Gazeta - No . 4 6 February 1996 Page 95 ፫ የሰንደቅ ዓላማው ቀለማትና ቅርጽ ፩ ሰንደቅ ዓላማው ከላይ አረንጓዴ ፡ ከመሃል ቢጫ ፡ ከታች ቀይ ሆኖ በመሃሉ ክብ በሆነ ሰማያዊ መደብ ላይ የተቀረጸ ብሔራዊ አርማ ይኖረዋል ። ፪ ቀለማቱ ብሩህና መሠረታዊ ይሆናሉ ። ፫ ቀለማቱ ኣግድም የተዋቀሩና እኩል ስፋት የሚኖራቸው ይሆናሉ ፤ የሰንደቅ ዓላማው ወርድ የቁመቱ እጥፍ ይሆናል ። ፬ . የዓርማው ቅርጽ ክብ በሆነ ሰማያዊ መደብ ላይ ፦ ሀ ) ከየአቅጣጫው መጥተው የሚገናኙ ቀጥታና እኩል የሆኑ ቢጫ መስመሮች ይኖረዋል ። ለ ) ቀጥታና እኩል ከሆኑት መስመሮች የተዋቀረ ኮከብ ይኖረዋል ። ሐ ) ቀጥታና እኩል በሆኑት መስመሮች መጋጠሚያ ላይ የሚፈነጠቅ ቢጫ ጨረር ይኖረዋል ። ፩ የሰንደቅ ዓላማው ቀለማት ትርጉም የሰንደቅ ዓላማው ቀለማት የሚከተለው ትርጉም ይኖራቸዋል ፤ | ፩ አረንጓዴው የሥራ ፡ የልምላሜና የዕድገት ምልክት ነው ፤ | 2 ) the yellow for hope , justice and equality , and . ፪• ቢጫው የተስፋ ፡ የፍትሕና የእኩልነት ምልክት ነው ፤ ፫ ቀዩ ለነጻነትና ለእኩልነት መስፈን የሚደረግ የመስዋዕት ነትና የጀግንነት ምልክት ነው ። ፬ ፡ የዓርማው ትርጉም : ክብ ሰማያዊ መደብ ፡ ሰላምን ያመለክታል ። ፭ የዓርማው ትርጉም ፩ : ቀጥታና እኩል የሆኑት መስመሮች ፤ . የብሔሮች ፡ የብሔረሰቦችና የሕዝቦች እንዲሁም የሃይማ ንፍ ኖቶችን እኩልነት ያመለክታሉ ። ። ፪ ቀጥታና እኩል ከሆኑት መስመሮች የተዋቀረው ኮከብ ፣ የኢትዮጵያ ብሔሮች ፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በመፈ ቃቀድ የመሰረቱትን አንድነት ያመለክታል ። ። ፫ ቢጫ ጨረር ፤ በመፈቃቀድ አንድነት ለመሠረቱት ብሔር ፣ ብሔረሰቦች | የፈነጠቀውን ብሩህ ተስፋ ይጠቁማል ። ማን ፮ ፡ የሰንደቅ ዓላማው ስዕላዊ መልክ የሰንደቅ ዓላማው ስዕላዊ መልክ እንደሚከተለው ነው ፡ ገጽ ፲፮ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፬ ጥር ፳፰ ቀን ፲፱፻፳፰ ዓ . ም . Negarit Gazeta - No . 4 6 February 1996 – Page 96 ፯ የሰንደቅ ዓላማ አወጣጥ የሰንደቅ ዓላማውን መውለብለብ የሚያግድ ከአቅም በላይ | . የሆነ ምክንያት ካላጋጠመ በስተቀር ፤ ፩ . በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሚኒስትሮችምክር ቤት ከላይ እስከ ታች ባሉ የክልል የሥልጣን ኣካላት ጽሕፈት ቤቶች ' በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ፡ በሌሎች ኣስፈጻሚ አካላት ጽ / ቤቶች ፡ በፍርድ ቤቶች ፡ በትምህርት ቤቶች ፡ በመከላከያ ድርጅቶች ፡ በፖሊስና ፡ በጠረፍ ጥበቃ ተቋሞች በሪፐብሊኩ ኤምባሲዎችና በአምባሳደሮች መኖሪያ ቤት ሕንጻዎች ሰንደቅ ዓላማ በየቀኑ ይወጣል ፤ ጀ የሪፐብሊኩ የንግድ መርከቦች እና ጀልባዎች በየቀኑ ሰንደቅ ዓላማ ያወጣሉ ፤ ፫ . በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ያልተመለከቱ የመን ግሥት መሥሪያ ቤቶች በብሔራዊ በዓል ቀን ሰንደቅ ዓላማ ያወጣሉ ፤ ሰንደቅ ዓላማ የሚወጣው በሚከተሉት ሥፍራዎች ይሆናል ፤ . ሀ ) በፌዴሬሽን ምክር ቤት በቅጥር ግቢው ኣደባባይ ለ የሪፐብሊኩ ርዕሰ ብሔርና ርዕሰ መስተዳድር በጽሕ ፈት ቤቱና በመኖሪያ ቤቱ ሕንጻዎች ላይ ፤ ሐ የሪፐብሊኩ ርዕሰ ብሔርና ርዕሰ መስተዳድርና አም ባሳደሩ የሚጓዝበት ተሽከርካሪ ፡ አውሮፕላንና 8 . Size of the Flag ተንሳፋፊ ላይ ፧ ፰ የሰንደቅ ዓላማው መጠን በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፫ ( ፫ ) የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ፡ ሰንደቅ ዓላማው የሚከተለው መጠን ይኖረዋል ፤ ፩ በከፍተኛ አደባባይ የሰንደቅ ዓላማው መጠን ፪፻፲ በ፬፻፳ ሴሜ ፡ የሰንደቁ ቁመት ከ፲፭ እስከ ፲፰ ሜትር ፡ ፪ በመካከለኛ አደባባይ የሰንደቅ ዓላማው መጠን የፃ በ፫፻ ሴሜ ፡ የሰንደቁ ቁመት ከ፬ እስከ ፲፭ ሜትር ፤ ፫ በመሥሪያ ቤቶች በከፍተኛ የትምህርት ተቋሞችና ድርጅቶች አደባባይ የሠንደቅ ዓላማው መጠን ፳፻፴፭ በ፪፻ኛ ሴሜ • የሰንደቁ ቁመት ከ፫ እስከ ፲፪ሜትር ፤ ፩ በትልልቅ የመንግሥት ህንጻዎች ላይ የሰንደቅ ዓላማው መጠን ፩፻፴፭ በ፪፻ኛ ሴሜ• የሰንደቁ ቁመት ፭ ማትር ! ኛ በትልልቅ ሕንጻዎች ምድር ቤት ውስጥ የሚገኙ ድርጅ ቶችና የንግድ ቤቶች የሠንደቅ ዓላማው መጠን ፳፻፭ በ፪፻፲ ሴሜ ፡ የሰንደቁ ቁመት ማትር ! ፮ በከፍተኛ መርከቦች ላይና በሰልፍ ጊዜ በክብር ዘብ የሚያዘው የሠንደቅ ዓላማው መጠን ፳፭ ባ፪፻፲ ሌማ የሠንደቁ ቁመት ፪፻፴ ሴማ ፤ ፯ ለውጭ ሀገር እንግዳ አቀባበልና ለበዓላት በየመንገዱ ለሚውለበለብ የሠንደቅ ዓላማው መጠን ¶ ሰ፳፻፰ ሴሜ ፡ የሰንደቁ ቁመት ፪ ሜትር ፤ ፰ በመካከለኛ መርከቦች ላይ የሠንደቅ ዓላማው መጠን በ፩፻ዊ ሴሜ ፡ የሰንደቁ ቁመት ፪ ሜትር ፤ ፱ በርእሰ ብሔር በርእሰ መስተዳድሩና በአምባሳደሮች ጽሕፈት ቤት ጠረጴዛ ላይ የሰንደቅ ዓላማው መጠን ፳፩ በ፵፪ ሲሜ ፡ የሰንደቁ ቁመት ፵ ሌማ ! ፲ . ርእሰ ብሔር ' ርእሰ መስተዳድሩና አምባሳደሮች በሚጓ | ዙበት መኪና ላይ የሚውለበለበው ሰንደቅ ዓላማ ! የቁመቱና የወርዱቅንብርሴሾ ) ፫ላ፬ሆኖብ በኋላ ና | . ገጽ ፲፯ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፩ ጥር ፳፰ ቀን ፲፱፻ዥ፰ ዓም• _ Negarit Gazeta - No . 6February 1996 Page 97 ፱• የሰንደቅ መትከያ ሥፍራ በአደባባይ የሚውለበለብ ሰንደቅ ዓላማ የሚተከለው በተቻለ መጠን ከመሥሪያ ቤቱ ህንጻ ፊት ለፊትና መሃል ለመሃል ይሆናል ። ፲ . የሰንደቅ ልሣን የማናቸውም ሰንደቅልሣን ( ጫፍ ) የጦርአምሳልይኖረዋል ። ፲፩ : ሰንደቅ ዓላማው የሚወጣበትና የሚወርድበት ጊዜ ፩ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) እና የተመለከቱት እንደተጠበቁ ሆነው በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፯ ( ፩ ) በተጠ ቀሱት መሥሪያ ቤቶች እንዲሁም በመርከቦችና ጀልባዎች ላይ ሰንደቅ ዓላማው ከጠዋቱ በ፲፪ ሰዓት ወጥቶ ከምሽቱ ፲፪ ሰዓት ይወርዳል ። ሆኖም የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ በታወጀባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የመከ ላከያ ሠራዊት አሀዶች ሁኔታው እስካልተለወጠ ድረስ መደበኛውን ሰዓት ጠብቅው ሰንደቅ ዓላማውን ማውጣትና ማውረድ አይገደዱም ። . ፪ በትምህርት ቤቶች ሰንደቅ ዓላማው የሚወጣው ጠዋት ተማሪዎች ተሰልፈው ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ይሆናል ፤ የሚወርደውም የቀኑ ትምህርት ሲያበቃ ይሆናል ። ፫ በበዓላት ወቅት ሰንደቅ ዓላማው በዋዜማው ወጥቶ በበዓሉማግስት ይወርዳል ። ፲፪ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሰንደቅ ዓላማ | ከዚህ በላይ በተደነገጉት አንቀጾች መሠረት አረንጓዴ ቢጫ ቀይና ክብ ሰማያዊ ቀለማት ኖሮት በመሀከሉ በዚህ አዋጅ የተዘረዘረው ዓርማ ያለው ብቻ ነው ። ፲፫ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ይህንን የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሰንደቅ ዓላማ የሚገባውን ክብር | የመስጠትና የማክበር ኃላፊነትና ግዴታ አለበት ። ክፍል ሦስት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፲፬ ደንብ የማውጣት ሥልጣን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይህን አዋጅ ተግባራዊ ለማድረግ አስፈላጊ የሆነ ደንብ ለማውጣት ይችላል ። ፲፭ መመሪያ ስለማውጣት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፬ መሠረት የሚወጣውን ደንብ ተከትለው የሚከተሉት መሥሪያ ቤቶች የአፈጻጸም መመሪ ያዎች ለማውጣት ይችላሉ ፤ ፩ . የመከላከያ ሠራዊት አሀዶችን በሚመለከት የሀገር | መከላከያ ሚኒስቴር ፡ ፪ የንግድ መርከቦችንና ጀልባዎችን በሚመለከት የትራንስ ፖርትና መገናኛሚኒስቴር ፫ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኤምባሲ ዎችንና ቆንስላዎችን በሚመለከት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ። ገጽ ፲፮ ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፬ ጥር ፳፰ ቀን ፲፱፻፰፰ ዓ - ም ፲፮• የተሻሩ ሕጎች የሚከተሉት ሕጎች በዚህ ኣዋጅ ተሽረዋል ፤ ፩ . የሰንደቅ ዓላማ አዋጅ ቁጥር ፫ ፲፱፻፫ ፣ እና ፪ : የሪፐብሊኩ ዓርማ አዋጅ ቁጥር ፬ ፲፱፻ዥ ። ፲፯ አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከጥር ፳፰ ቀን ፲፱፻T፰ ዓም ጀምሮ የጸና | ይሆናል ። አዲስ አበባ ፣ ጥር ፳፰ ቀን ፲፱፻ዥ፰ ዓም ዶ / ር ነጋሶ ጊዳዳ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ታተመ