×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር ፫፻ሮ/ ፲፱፻፲፭ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የጋራ ሕንፃ ቤት ባለቤትነት ኣዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ዘጠነኛ ዓመት ቁጥር ፲፭ ኣዲስ አበባ ጳጉሜ ፮ ቀን ፲፱፻፶፭ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ • አዋጅ ቁጥር ፫፻፪ / ፲፱፻፲፭ ዓም የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የጋራ ሕንጻ ቤት ባለቤትነት አዋጅ ገጽ ፪ሺ፫፻፲፭ አዋጅ ቁጥር ፫፻፭ / ፲፱፻፶፭ የጋራ ሕንፃ ባለቤትነት አዋጅ በከተሞች ያለውን የቤት አቅርቦትና የቤት ፍላጐት አለመ ጣጣም ለመቀነስ የከተማ ቦታን በግል ከመሸንሸን በተጨማሪ ሌሎች የከተማ ቦታ አጠቃቀም አማራጮችን ጐን ለጐን ተግባራዊ | alternatives of urban land use in addition to plots basis urban ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ የከተማ ቦታን ወደላይ ወይም ጐን ለጐን የተሠሩ ቤቶችን ለሚይዝ የጋራ ሕንፃ ግንባታ ማዋል አነስተኛ የከተማ ቦታ የብዙ | land to a high rise or a row of houses condominium building ሰዎች የጋራ ይዞታ እና መጠቀሚያ እንዲሆን በማድረግ የከተማ | will contribute to maintain the beauty of the urban areas and to ቦታ አጠቃቀምንና የቤት አቅርቦትን በማሻሻል እንዲሁም የከተ | the improvement of urban land use and supply of housing ሞችን ውበት በመጠበቅ ረገድ የሚኖረውን ድርሻ በመረዳት ፣ የግል አልሚዎችና የኅብረት ስራ ማኅበራት በጋራ ሕንጻ ግንባታ ለሚኖራቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ እና የጋራ ሕንጻ ቤት ለሚገዙ ወይም ለሌሎች በጋራሕንጻው ላይ ባለመብትለሆኑ ሰዎች | condominium to create favorable conditions , to private ምቹ ሁኔታ መፍጠር ለጋራ ሕንጻ ግንባታ ወሳኝ በመሆኑ ፣ ለዚህም በኢትዮጵያ ፌዴራላዊዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) በተደነገገው መሠረት | related to the condominium ; ይህ አዋጅ ታውጇል ። ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ኣዋጅ “ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የጋራ ሕንጻ ቤት ባለቤትነት አዋጅ ቁጥር ፫፻፪ / ፲፱፻፲፭ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ ጳጉሜ ፮ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓ.ም. Federal Negarit Gazeta ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፭ ክፍል ዘጠኝ የጋራ ሕንጻ ለመሥራት ስለሚደራጅ የመኖሪያ ቤት የኅብረት ሥራ ማኅበራት ፴፱ አደረጃጀት የመኖሪያ ቤት የኅብረት ሥራ ማኅበራት የጋራ ሕንጻ በመሥራት ዓላማ ሊደራጁ ይችላሉ ። – የሕብረት ሥራ ማኅበራት አዋጅ ቁጥር ፻፵፯ ፲፩ ተፈጻሚነት ፩ የጋራ ሕንጻ ለመሥራት ለሚደራጁ የሕብረት ሥራ ማኅበራት ስለመኖሪያ ቤት የሕብረት ሥራ ማኅበራት በአዋጅ ቁጥር ፻፵፯ ፲፩ ዓም የተደነገገው ተፈጻሚ ይሆናል ፣ ሆኖም ሕንጻው በዚህ አዋጅ መሠረት ሲመዘገብ ይህ አዋጅ ተፈጻሚ ይሆናል ። ፴፩ : ሕንጻ ስለማስመዝገብ ፩ የጋራ ሕንጻው ግንባታ ሲጠናቀቅ የኅብረት ሥራማኅበሩ የሥራ አመራር ኮሚቴ ሕንጻውን በዚህ አዋጅ መሠረት ያስመዘግባል ፣ በዚህ አንቀጽ መሠረት ሕንጻውን ያስመዘገበው የሥራ አመራር ኮሚቴ የባለቤቶች ማኅበር የመጀመሪያ ቦርድ በመሆን በዚህ ሕግ ለቦርዱ የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ፣ ፫ . በአዋጅ ቁጥር ፪፯ ፲፩ መሠረት የተመረጠው የቁጥጥር ኮሚቴ በዚህ አዋጅ መሠረት ኦዲተር ሆኖ ይሠራል ፣ ሕንጻው በተመዘገበ በ፲ ቀናት ውስጥ የቤት ባለቤቶች አዲስ የዳይሬክተሮች ቦርድና ኦዲተር ሊሰይሙ ይችላሉ ክፍል አሥር ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፴፪ ደንብ ስለማውጣት የከተማ አስተዳደሮቹ ይህን አዋጅ ለማስፈጸም የሚረዳ ደንብ ለማውጣት ይችላሉ ። • ስለ ሌሎች ሕጐች ተፈጻሚነት ፩ በ፲፱፻፶፪ ዓም የወጣው የኢትዮጵያ ፍትሐ ብሔር ሕግ ከቁጥር ፩ሺ፪፻ T ፩ እስከ ቁጥር ፩ሺ፫፻፰ ያሉ ድንጋጌዎች | 43. Applicability of Other Laws በዚህ አዋጅ መሠረት በሚተዳደር የጋራ ሕንጻ ላይ ተፈጻሚነት አይሆኑም ፣ ፪ . ማንኛውም ሕግ ፣ ልማድ ወይም አሠራር በዚህ አዋጅ በተደነገጉ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም ። አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ የፀና ይሆናል ። አዲስ አበባ ጳጉሜ ፮ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም ግርማ ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ገጽ ፪ሺ፫፻፲፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፭ ጳጉሜ ፮ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. ፪ . ትርጓሜ በዚህ አዋጅ ውስጥ፡ ፩ ) “ የጋራ ሕንጻ ” ማለት ከመሬት ወደላይ ወይም ጐን ለጐን የተሠሩ በተናጠል የሚያዙ አምስትና ከአምስት በላይ ቤቶች እና በጋራ ባለቤትነት የሚያዙ የጋራ መጠቀሚ ያዎች ያሉት ለመኖሪያ ወይም ለሌላ አገልግሎት የሚውል ግንባታ ሲሆን ሕንጻውያረፈበትን የቦታ ይዞታ ይጨምራል ፣ ፪ ) “ የጋራ መጠቀሚያ ” ማለት በተናጠል ከተያዙት ቤቶች ውጭ ያለ ማናቸውም የሕንጻው አካል ነው ፣ ፫ ) “ የጋራ ወጪ ” ማለት የባለቤቶች ማህበርን አላማ እና ግዴታ ለማስፈጸም የሚደረግ ማናቸውም ወጪ እና በዚህ አዋጅ ፣ በሕንጻው ማሳወቂያ የጋራ ወጪ ተብሎ የተደነ ገገው ነው ፣ ፬ ) “ የጋራ ትርፍ ” ማለት የባለቤቶች ማህበር ከሚሰበስበው ገቢ ወጪው ተቀንሶ የሚገኘው ውጤት ነው ፣ ፭ ) “ አስመዝጋቢ ” ማለት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፫ መሠረት ሕንጻ ያስመዘገበ ነው ፣ ፮ ) “ የሕንጻ ማሳወቂያ ” ማለት የቤት ባለቤቶች ማኅበርን እና የእያንዳንዱን የቤት ባለቤት መብትና ግዴታዎች የሚወስን ሰነድ ሲሆን ማንኛውንም የሕንፃ ማሳወቂያ ማሻሻያ ይጨምራል ፣ – “ የሕንጻ መግለጫ ” ማለት የጋራ ሕንፃውን ስምና አድራሻ ፣ የቤቶችንና የጋራ መጠቀሚያዎችን ወሰኖች ፣ እንደዚሁምከጋራ ሕንጻው አንፃርየጋራ መጠቀሚያዎች እና የእያንዳንዱ ቤት የሚገኝበትን ትክክለኛ ቦታ የሚያሳይ ሰነድ ሲሆን ፣ ማንኛውም የሕንፃ መግለጫ ማሻሻያ ይጨምራል ፣ ፰ ) “ ለተወሰነ ቤት የተመደበ የጋራ መጠቀሚያ ” ማለት ከጋራ መጠቀሚያ ውስጥ ለአንድ ወይም ለተወሰኑቤቶች አገልግሎት ብቻ የተመደበ የህንፃው አካል ነው ። ፱ ) “ የቤት ባለቤቶች ማህበር ” ማለት በዚህ አዋጅ መሠረት የተቋቋመ የጋራ ሕንጻ ቤት ባለቤቶች ማህበር ነው ፣ ፬ ) “ ሰው ” ማለት ማንኛውም የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው ፣ ፲፩ ) “ መዝጋቢ አካል ” ማለት በዚህ አዋጅ መሠረት የምዝገባ ተግባር ለማከናወን የሚሰየም አስፈጻሚ ኣካል ፲፪ ) “ ቤት ” ማለት በሕንፃ ማሳወቂያና መግለጫ ለአንድ ለተወሰነ አገልግሎት የተመደበ አንድ ወይም ከኣንድ በላይ ክፍሎች ያሉት የሕንጻው አካል ነው ፣ ፫ . የተፈጻሚነት ወሰን ይህ አዋጅ በአዲስ አበባና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል ። ክፍል ሁለት የጋራ ሕንጻ ምዝገባና የምስክር ወረቀት ፬ . የጋራ ሕንጻ ምዝገባ ፩ ) የዚህ አዋጅድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነውማንኛውም የሕንጻ ባለቤት ወይም ወኪሉ ህንጻው በዚህ አዋጅ እንዲገዛ ፍላጐቱን በጽሁፍ ለመዝጋቢው አካል በመግለጽ የሕንጻ ማሳወቂያና መግለጫ ፣ መተዳደሪያ ደንብና ውስጠ ደንብ ሲያቀርብ ሕንጻው ይመዘገባል ፣ ፪ ) የሕንጻ ማሳወቂያና መግለጫ ፣ የመተዳደሪያ ደንብ እና ውስጠ ደንብ ይዘት ይህንን አዋጅ ለማስፈጸም በሚወጣ ደንብ ይወሰናል ፣ ፫ ) የሕንጻማሳወቂያና መግለጫ ፣ መተዳደሪያደንቡናውስጠ ደንቡ በመዝጋቢው አካል መጽደቅና መመዝገብ አለበት ። የምዝገባ የምስክር ወረቀት በዚህ አዋጅ መሠረት ሕንጻው ሲመዘገብ ለአስመዝጋቢው የምስክር ወረቀት ይሰጠዋል ። ፪ሺ፫፻፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፭ ፮ • የምዝገባ ውጤት ሕንጻው ፣ ሕንጻው ያረፈበት ቦታና ከዚሁ ጋር የተያያዙ መብቶች ፣ ጥቅሞችና ግዴታዎች በዚህ አዋጅ መሠረት ይገዛሉ ፣ ፪ ) በህንጸ መግለጫ ላይ የተገለጸው ሕንጻ በቤቶችና በጋራ መጠቀሚያዎች ይከፋፈላል ፣ ፫ ) የቤት ባለቤቶች ማኅበር የሕግ ሰውነት ያለው አካል ሆኖ ይቋቋማል ። ፯ የሕንጻ ማሳወቂያና መግለጫ ፣ መተዳደሪያ ደንብና ውስጠ ደንብ ስለማሻሻል የሕንጻማሳወቂያናመግለጫ ፣ መተዳደሪያ ደንብና ውስጠ ደንብ መሻሻል በቤት ባለቤቶች ፪ / ፫ኛ ድምጽ መጽደቅ አለበት ፣ ፪ ) በክፍል ባለቤቶች የጸደቀው የሕንጻ ማሳወቂያና መግለጫ ፣ መተዳደሪያ ደንብና ውስጠ ደንብ ማሻሻያ ተግባራዊ የሚሆነው ለመዝጋቢው አካል ቀርቦ ሲመዘ ግብና ለዚሁም የምዝገባ የምስክር ወረቀት ለማህበሩ ሲሰጠው ነው ። ክፍል ሦስት ስለ ባለቤትነት ፰ ስለ ቤት ባለቤትነት ፩ ) በዚህ አዋጅ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የማናቸውም ቤት ባለቤት በቤቱ ላይ የባለቤትነት መብት ይኖረዋል ፣ ፪ ) በዚህ አዋጅ መሠረት የሚተዳደር የጋራ ሕንጻ አባል የሆነ ቤት በተናጠልማናቸውም ሕጋዊ ተግባር የሚከናወ ንበት ነው ። ስለ ጋራ መጠቀሚያዎች ፩ ) በዚህ አዋጅ ፣ በጋራ ሕንጻ ማሳወቂያ ፣ በመተዳደሪያ ደንብና በውስጠ ደንብ የተወሰኑ ገደቦች እንደተጠበቁ ሆነው ማንኛውም የጋራ ሕንጻ የቤት ባለቤት የጋራ መጠቀሚያዎችን አግባብ በሆነ መንገድ የመጠቀም መብት አለው ፣ ፪ ) በጋራ መጠቀሚያዎች የመጠቀም መብት የማይከፋፈል እና ከእያንዳንዱ ቤት የባለቤትነት መብት ጋር የማይነ ጣጠል ነው ፣ ፫ ) የእያንዳንዱ ቤት የባለቤትነት መብት በጋራ መጠቀሚያ ላይ የሚያስገኘው የማይከፋፈል መብት ድርሻ መቶኛ በሕንጻ ማሳወቂያ ይወሰናል ፣ ፬ ) የእያንዳንዱ ቤት የባለቤትነት መብት በጋራ መጠቀሚያ ላይ የሚያስገኘው መብት ድርሻ የእያንዳንዱ ቤት አካል ሆኖ የሚታይና በቤት ላይ የሚፈጸመው ማናቸውም ሕጋዊ ተግባር የሚመለከተው ነው ፣ ፭ ) በዚህ አዋጅ መሠረት ካልሆነ በቀር የጋራ መጠቀሚ ያዎች ሊከፋፈሉ አይችሉም ። ክፍል አራት ስለ የቤት ባለቤቶች ማህበር ስለማኅበሩ የቤት ባለቤቶች ማኅበር ትርፍ ለማግኘት ወይም ለመከፋፈል ሣይሆን ለአባላቱ የጋራ ጥቅም የተቋቋመ ማኅበር ነው ። ፲፩ . ዓላማ የቤት ባለቤቶች ማህበር የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል፡ ፩ ) የቤት ባለቤቶችን በመወከል የጋራ ሕንጻውን ማስተ ፪ ) የጋራ ሕንጻውን ነዋሪዎች ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ ፣ ፫ ) የቤት ባለቤቶች ፣ ቤቶችን የያዙ ሰዎች ፣ መጠቀሚያ ተከራዮች ፣ ይህንን አዋጅ ፣ የሕንጻ ማሳወ ቂያና መግለጫውን ፣ መተዳደሪያ ደንቡንና ውስጠ ደንቡን ማክበራቸውን ማረጋገጥ ፣ ፬ ) የቤት ባለቤቶችን የጋራ ጥቅም በመወከል አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች ተግባራትን መፈጸም ። በዳይሬክተሮች ቦርድ በሚቀርብሶ በሰባ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፭ ጳጉሜ ፮ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓ.ም. Federal Negarit Gazeta No.95 ፲፪ . የማኅበር አባልነት ማንኛውም የጋራ ሕንጻ ቤት ባለቤት የቤት ባለቤቶች ማኅበር አባል ይሆናል ። ፲፫ . የማኅበሩ ሥልጣንና ተግባር የቤት ባለቤቶች ማኅበር የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ። ፩ . የሕንጻ ማሳወቂያና መግለጫ ፣ መተዳደሪያ ደንብና ውስጠ ደንብ ማውጣት ፣ ማሻሻል ፣ ፪ • በጀት መወሰን ፣ ማሻሻል ፣ የጋራ መጠቀሚያዎችን አጠቃቀም መወሰን ፣ ፬ • የጋራ መጠቀሚያዎችን ማከራየት ፣ በዋስትና ማስያዝ ፣ ማስተላለፍ ፣ ቅጣት መዋጮና የአገልግሎት ክፍያዎችን መወሰን ፣ ፮ ሠራተኞች መቅጠር ፣ ማስተዳደር ፣ ማሰናበት ፣ ፯ የንብረት ባለቤት መሆን ፣ በዋስትና ማስያዝ ፣ ማስተ ውል መዋዋል ፣ መክሰስ ፣ መከሰስ ፣ ፲፬ • የማኅበሩ ጠቅላላ ስብሰባ ሥልጣንና ተግባር የቤት ባለቤቶች ማኅበር ጠቅላላ ስብሰባ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባር ይኖሩታል ፡ ፩ የሕንጻ ማሳወቂያና መግለጫ እንዲሁም ማሻሻያ ማጽደቅ ፣ ፪ መተዳደሪያ ደንብና ውስጠ ደንብ እንዲሁም ማሻሻያ ዎቹን ማጽደቅ ፣ ፫ • የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን መምረጥ ፣ መሻር ፣ የማኅበሩን የሥራክንውንና የሂሣብ ምርመራ ሪፖርቶች መስማትና ውሳኔ መስጠት ፣ በዚህ አዋጅ መሠረት የቤት ባለቤቶች ማኅበር ከሌላ የቤት ባለቤቶች ማኅበር ጋር እንዲዋሀድ ወይም ሕንጻው በዚህ አዋጅ መሠረት መተዳደሩ እንዲያበቃ መወሰን ፣ ፮ : ዓመታዊ የሥራ ዕቅድና በጀት ማጽደቅ ፣ ማናቸውም ጉዳይ ላይ ውሣኔ መስጠት ፣ ፲፭ የቤት ባለቤቶች ማኅበር ስብሰባ ፩ • የቤት ባለቤቶች ማኅበር ዓመታዊ ጠቅላላ ይኖረዋል ፣ የቤት ባለቤቶችማኅበር ፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ በሚያደ ርገው ጥሪ መሠረት ሌሎች ስብሰባዎችን ያደርጋል ፣ ፫ ፳፭ ፐርሰንት ( ሃያ አምስት በመቶ ) የሆኑትን ቤቶች የያዙ የቤት ባለቤቶች የባለቤቶች ስብሰባ እንዲደረግ ከጠየቁ የዳይሬክተሮች ቦርድ የቤት ባለቤቶች ስብሰባ መጥራት አለበት ፣ ፬ . በማንኛውም ስብሰባ ከጋራ ሕንጻው ቤት ባለቤቶች ፱ ፐርሰንት ሲደመር ፩ ( ሃምሳ በመቶ ሲደመር ፩ ) እና በላይ ከተገኙ ምልዓተ ጉባኤ ይሆናል ፣ የቤት ባለቤቶች በቀጥታ ወይም በወኪል አማካኝነት ድምጽ ሊሰጡ ይችላሉ ፤ ፮በዚህ አዋጅ በሌላ ሁኔታ ካልተደነገገ በቀር የቤት ባለቤቶች ማኅበር ውሣኔ የሚያስተላልፈው በድምጽ ብልጫ ይሆናል ። ፲፮ • የዳይሬክተሮች ቦርድ ፩ የዳይሬክተሮች ቦርድ የቤት ባለቤቶች ማኅበር የአመራር አካል ነው ፣ ፪፡ የመጀመሪያው ዳይሬክተሮች በአስመዝጋቢው የሚሰ የሙ መሆናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ዳይሬክተሮች ከቤት ባለቤቶች መካከል በባለቤቶች ይመረጣሉ ። የቤት ባለቤቶች ማኅበር መብ ” ገጽ ፪ሺ፫፻፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፭ ጳጉሜ ፮ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. Federal Negarit Gazeta ፲፯ . የመጀመሪያው የዳይሬክተሮች ቦርድ ፩ የጋራ ሕንጻው በዚህ አዋጅ መሠረት ከተመዘገበ በኋላ አስመዝጋቢው የመጀመሪያውን የዳይሬክተሮች ቦርድ መሰየም አለበት ፣ ፪ የቤት ባለቤቶች በአስመዝጋቢው በተሰየሙት የቦርድ አባላት ተጨማሪየሚሆኑ አባላት ወይም ተተኪ የዳይሬ ክተሮች ቦርድ ሊመርጡ ይችላሉ ፣ ፫ . በዚህ አንቀጽ መሠረት ምር ሚከናወንበት ጊዜ ፣ እና በመጀመሪያ የዳይሬክተሮች ቦርድ እና በተተኪው የዳይሬክተሮች ቦርድ መካከል ስለሚደረገው የሥልጣን ሽግግር ይህንን አዋጅ ለማስፈጸም በሚወጣ ደንብ ይወሰናል ። ፲፰ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሥልጣንና ተግባር የዳይሬክተሮች ቦርድ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባር ይኖሩታል ፦ 3 • በዚህ አዋጅ መሠረት የማኅበሩን ጠቅላላ ስብሰባ መጥራት ፣ የስብሰባውን ቃለ ጉባዔ በጽሑፍ መያዝ ፣ የሕንጻ ማሳወቂያና መግለጫ ፣ መተዳደሪያ ደንብና ውስጠ ደንብ ማሻሻያማዘጋጀት ፣ ሲጸድቅም በሥራ ላይ ማዋል ፣ ዓመታዊ የሥራ ዕቅድና በጀት ማዘጋጀት ፣ ሲጸድቅም በሥራ ላይ ማዋል ፣ የማኅበሩን መዛግብትና ሂሣብ መያዝ ፣ ፭ የቤት ባለቤቶች ማኅበር ጠቅላላ ስብሰባ ውሣኔዎችን ማስፈጸም ፣ ፮ : የማኅበሩን የሥራ እንቅስቃሴ በሚመለከት ለጠቅላላ ስብሰባ ሪፖርት ማቅረብ ፣ ፯ ሌሎች በጠቅላላ ስብሰባ የሚሰጡትን ተግባራት ማከናወን ፣ ፲፱ : ስለ መተዳደሪያ ደንብና ውስጠ ደንብ ደንብና ውስጠ ደንብ ፳ ( ኦዲተር ፩ የቤት ባለቤቶች ማኅበር ኦዲተር ይኖረዋል ፣ ፪ . የኦዲተርአሰያየም ፣ ብዛት ፣ ተፈላጊችሎታ ፣ ተግባራትና ስንብት በደንብ ይወሰናል ። ክፍል አምስት የጋራ ሕንጻ ቤትን ስለመሸጥና ማከራየት ፳፩ . በአስመዝጋቢው የሚደረግ ሽያጭ ፩ . በዚህ አዋጅ መሠረት ሕንጻው ከመመዝገቡ በፊት ወይም ከተመዘገበ በኋላ የጋራ ሕንጻ ቤት ሽያጭ ውል ለመዋዋል ይቻላል ፣ ፪ : ሕንጻው ከመመዝገቡ በፊትም ሆነ በኋላ ከአስመዝ ጋቢው ላይ የጋራ ሕንጻ ቤት ለሚገዛ ማንኛውም ሰው አስመዝጋቢው መረጃ መስጠት አለበት ፣ ፫ አስመዝጋቢው ለገዥው መረጃ እስከሚሰጠው ድረስ ገዥው በቤት ሽያጭ ውሉ አይገደድም ፣ መረጃ ከአስመዝጋቢው የደረሰው ገዥ የባለሀብትነት ስም በስሙ ከመዛወሩ በፊት ለአስመዝጋቢው በጽሑፍ የውሉን መሠረዝ መግለጽ ይችላል ፣ በመረጃ በተገለጹ ጉዳዮች ላይ መሠረታዊ ለውጥ ሲኖር አስመዝጋቢው በተሻሻለ መረጃ ለውጡን ለገዥው መግለጽ አለበት ። በተሻሻለ መረጃ መሠረታዊ ለውጥ መኖሩን ሲገልጽለት ወይም ገዢው በራሱ መሠረታዊ ለውጥ መኖሩን ተረድቶ አስመዝጋቢው በተሻሻለ መረጃ ሳይገለጽለት ከቀረ ገዥው ለአስመዝጋቢው በጽሑፍ የውሉን መሠረዝ መግለጽ ይችላል ። ፪ሺ፬፻ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፭ ጳጉሜ ፮ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓ.ም. ሕንጻው ከመመዝገቡ በፊት የቤት ሽያጭ ውል የተዋዋለ አስመዝጋቢ በውሉ የተመለከተውን ሕንጻ ግንባታ ሳይዘገይ የማጠናቀቅና ሕንጻውን የማስመዝገብ ግዴታ አለበት ። ፳፪ ቤቶችን ስለማከራየት ፩ . ማንኛውም የቤት ባለቤት ሲያከራይ ወይም የቤት ኪራይ ውል ሲያድስ ለቤት ባለቤቶች ማኅበር በጽሑፍ መግለጽ እና የኪራይ ውሉን ሰነድ ወይም የኪራይ ውሉን ማደሻ ሰነድ አባሪ አድርጐ መስጠት አለበት ፣ ፪ . ማንኛውም የቤት ባለቤት የቤት ኪራይ ውል በማና ቸውም ምክንያት ሲቋረጥ የውሉን መቋረጥ የሚያስረዳ ማስረጃ አባሪ በማድረግ የውሉን መቋረጥ ለቤት ባለቤቶች ማኅበር መግለጽ አለበት ፣ ፫ . ማንኛውም የቤት ባለቤት የቤት ኪራይ ውል ሲዋዋል ለተከራዩ የጋራ ሕንጻውን ማሳወቂያና መግለጫ መተዳ ደሪያ ደንብና ውስጠ ደንብ ቅጂ መስጠት አለበት ። ኀበ አስቀድሞ ወደ ቤት ስለመግባት የሕንጻው ማሳወቂያና መግለጫ ከመመዝገቡና የቤት ባለቤ ትነት ስም ለገገርው ከመዛወሩ በፊት ገዥው ወደ ገዛው ቤት ስለመግባቱ ፣ በዚህም ጊዜ ገዥው ስለሚከፍለው ክፍያ እና ስለአስመዝጋቢው ግዴታ በቤት ሽያጭ ውል ላይ ስምምነት ሊደረግ ይችላል ። ክፍል ስድስት ስለ ጋራ ወጪዎችና ትርፍ ፳፬ በባለቤቶች የሚደረግ መዋጮ የዚህ አዋጅ ሌሎች ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው የቤት ባለቤቶች የጋራ ወጪዎችን ለመሽፈን ፣ በጋራ መጠቀሚያዎች ላይ ካላቸው የማይከፋፈል ጥቅም ጋር የሚመጣጠን መዋጮ ይከፍላሉ ፣ ፪ የቤት ባለቤቱ በጋራ መጠቀሚያዎች ላለመጠቀም የወሰነ ቢሆንም ፣ ወይም በማኅበሩ ላይ የይገባኛል ጥያቄ ያለው ቢሆንም ወይም በቤት ባለቤቶች ማኅበር ፣ በመተዳደሪያ ደንብ ወይም በውስጠ ደንብ በጋራ መጠቀሚያዎች የመጠቀም መብቱ በከፊል ወይም በሙሉ የተገደበ ቢሆንም የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ተፈጻሚ ይሆናል ። ፳፭ : የመያዣ መብት ፩ የቤት ባለቤት የጋራ መዋጮጮውን በማይከፍልበት ጊዜ ማኅበሩ በባለቤቱ ቤትና በጋራ ጥቅሞች ድርሻው ላይ ባልተከፈለው መዋጮ መጠን የመያዣ መብት ይኖረዋል ። ይህ የገንዘብ መጠን ክፍያው በተወሰነለት ጊዜ ባለመከፈሉ ምክንያት የሚኖረውን ወለድ እና ወጪዎችን ይጨምራል ፣ ፪ • የቤት ባለቤት መዋጮውን መክፈል ከነበረበት ጊዜ አንስቶ ባለው የሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ማኅበሩ በዚህ አዋጅ መሠረት በንብረቱ ላይ አለ የሚለውን የመያዣ መብቱን የሚያረጋግጥለት ምስክር ወረቀት ማግኘት አለበት ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፪ መሠረት ያልተመዘገበ እንደሆነ የማኅበሩ በመያዣ መብት የሦስት ወር ጊዜው ካለቀ በኋላ ተፈጻሚ አይሆንም ፣ ፬ . የማኅበሩን የመያዣ መብት ለማረጋገጥ የሚሰጠው የምስክር ወረቀት የቤት ባለቤቱ ያልከፈለውን የመዋጮ መጠን እና መዋጮውን ለማስከፈል ሲባል ማኅበሩ ያወጣቸውን ልዩ ልዩ ወጪዎች ለይቶ ማመልከት ይኖርበታል ፣ ማኅበሩ የመያዣውን መብት ከማስመዝገቡ በፊት ለሚመለከታቸው የቤት ባለቤቶች የ፲፭ ቀናት የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ መስጠት አለበት ፣ ገጸ ፪ሺ፬፻፩ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፭ ጳጉሜ ፮ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም የቤት ባለቤቱ በዚህ አንቀጽ የሚፈልግበትን ክፍያከፍሎ ሲያጠናቅቅ ማኅበሩ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ማስረጃ እንዲ መዘገብ በማድረግ ለቤት ባለቤቱ ሊሰጠው ይገባል ፣ ፯ በዚህ አንቀጽ የተመለከተው የማኅበሩ የመያዣ መብት ከመንግሥት ግብርና ቀረጥ በስተቀር ከሌሎች የተመዘ ያልተመዘገቡ መያዣዎች ቅድሚያ ይኖረዋል ። ፳፮ የጋራ ትርፍ ፩ . ማኅበሩ የሚያገኘው ማንኛውም ትርፍየጋራ ወጪዎችን ለመሽፈን ይውላል ወይም በልዩ ተቀማጭ ሂሣብ ውስጥ ይቀመጣል ፣ ፪ : ማኅበሩ ካልፈረሰ በስተቀር ይህ ትርፍ በቤት ባለቤቶች መካከል አይከፋፈልም ። ፳፯ : ስለጥገናና ዕድሣት በአደጋ ምክንያት የሚደርስ ጉዳትን ስለመጠገን ፦ ሀ ) በአደጋ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን ቤቶች ፣ የጋራ መጠቀሚያዎችን እና የማኅበሩ ንብረቶች ማኅበሩ ማስጠገን አለበት ፣ ለ ) በአደጋ ምክንያት የሚደረግ ጥገናጉዳት የደረሰበትን መጠገንን መተካትን ይጨምራል ። ሆኖም በቤቶች ላይ የተደረገ ተጨማሪ ሥራ ላይ የሚደርስ ጉዳትን መጠገንን አይጨምርም ሐ ) ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም በአንድ ቤት ላይ የተደረገ ተጨማሪ ሥራ ዓይነትና መጠን የሚወሰነው በሕንጻ ማሳወቂያ በተቀመጠው የቤቶች ደረጃ የሚመለከተው ቤት ከተመደበበት የክፍል ደረጃ ጋር በማወዳደር ይሆናል ፣ መ ) የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ ( ለ ) ቢኖርም ሕንጻው ከመመዝገቡ በፊት በቤቶች ላይ የተደረገ ተጨማሪ ሥራዎች ቢኖሩ ማኅበሩ የማስጠገን ኃላፊነት ይኖርበታል ። ስለ ዕድሣት፡ ማኅበሩ የጋራ መጠቀሚያዎችን የማደስ ኃላፊነት አለበት ፣ ለ ) እያንዳንዱን ቤት የማደስ ኃላፊነት የቤቱ ባለቤት ነው ፣ ሐ ) ለተወሰኑ ቤቶች የተመደቡ የጋራ መጠቀሚያዎችን ማደስ ፣ የጋራ መጠቀሚያዎቹ የተመደቡላቸው ቤቶች ባለቤቶች ኃላፊነት ነው ፣ መ ) የማደስ ኃላፊነት በመደበኛ የንብረት አጠቃቀም የሚመጣን ማርጀት ወይም አገልግሎት መቀነስ ማስተ ካከልን ይመለከታል ፣ ፫ • ለክፍል ባለቤቶች የሚደረግ ዕድሣት ፣ ሀ ) የጋራ መጠቀሚያን ወይም ቤትን የማደስኃላፊነት የቤት ባለቤት ከሆነና የቤት ባለቤቱ በቂ በሆነ የጊዜ ገደብ ውስጥ ይህንን ኃላፊነቱን ባይወጣ ማኅበሩ ዕድሳቱን በራሱ ሊያከናውን ይችላል ፣ ለ ) በዚህ ንዑስ አንቀጽ መሠረት ማኅበሩ ዕድሳት ሲያከ ናውን ወጪው ኃላፊነቱን ያልተወጣው የቤት ባለቤት የጋራ ወጪ ተጨማሪ ድርሻው ሆኖ ይታሰባል ። ፳ A : ስለ ልዩ ተቀማጭ ገንዘብ ማኅበሩ ለጥገናና እድሳት ራሱን የቻለ የተለየ ገንዘብ ማስቀመጥ እና ሲያስፈልግ ወጪ ማድረግ አለበት ፣ ለዚህ ተቀማጭ ገንዘብ ማኅበሩ ከክፍል ባለቤቶች መዋጮ ይሰበስባል ፣ በዚህ አንቀጽ የተመለከተው ተቀማጭ ገንዘብ የማኅበሩ ሀብት ነው ። በዚህ አዋጅ መሠረት ካልሆነ በቀር ለቤት ባለቤቶች አይከፋፈልም ። ፪ሺ፬፻፪ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፭ ጳጉሜ ፮ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ.ም. Federal Negarit Gazeta No. 95 11 September , 2003- ~ Page 2402 ክፍል ሰባት ስለ ማኅበራት ውህደት ፳፱ : ስለ ምዝገባ ፩ የዚህ ኣዋጅ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ የቤት ባለቤቶች ማኅበራት የተዋሃደ የሕንጻ ማሳወቂያና መግለጫ ፣ መተዳደሪያ ደንብና ውስጠ ደንብ ለመዝጋቢው አካል በማስመዝገብ ሊዋሃዱ ይችላሉ ፣ ውህደቱ ከመመዝገቡ በፊት በእያንዳንዱ ማኅበር የቤት ባለቤቶች ቼ ፐርሰንት ድምፅ መጽደቁና ማኅበራቱን ለመወከል ሥልጣን ባላቸው ሰዎች መፈረሙ መረጋገጥ አለበት ፣ ስለ ውህደቱ በሚጠራው ጠቅላላ ስብሰባ ለሚዋሃደው ማህበር የሚያገለግሉት የሕንጻ ማሳወቂያና መግለጫ ፣ መተዳደሪያ ደንብና ውስጠ ደንብ በውህደቱ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለሚጠራው ጠቅላላ ስብሰባ ቀርበው መጽደቅ ኣለባቸው ፣ ፬ . የሚዋሀዱት ማህበራት የመጨረሻ ዓመት የኦዲት ሪፖርት በንዑስ አንቀጽ ፫ ላይ በተጠቀሰው ስብሰባ ላይ ለአባላት መገለጽ አለበት ። ፴ ምዝገባው የሚያስከትለው ውጤት ውህደቱን የመሠረቱት ማኅበራት በሙሉ ተዋህደው የተዋሀደ አንድ የቤት ባለቤቶች ማኅበር ይመሠረታል ፣ ፪ • ከውህደት በፊት የነበሩት ቤቶች እና የጋራ መጠቀሚ ያዎች የተዋሀደው ማኅበር ሴቶችና የጋራ መጠቀሚ ያዎች ሆነው ይቀጥላሉ ፣ ፫ ከውህደቱ በፊት የነበሩት የእያንዳንዱ ማኅበር የሕንጻ ማሳወቂያና መግለጫ ፣ መተዳደሪያ ደንብና ውስጠ ደንብ ተፈጻሚነታቸው ይቀራል ፣ የዚህ አዋጅ አንቀጽ ፴፩ እንደተተጠበቀ ሆኖ ፣ ከውህደቱ በፊት የነበሩት የእያንዳንዱ ማኅበር ዳይሬክተሮች በአንድ ላይ የተዋሀደው ማኅበር የመጀመሪያ ዳይሬክ ተሮች ይሆናሉ ፣ ፭ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፴፩ መሠረትምርጫ እስከሚከናወን የሚያገለግሉ አንድ ወይም ከአንድ በላይ ኦዲተሮች በአባላት ይሰየማሉ ፣ ፮ : በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፳፬ መሠረት ለጠቅላላ ስብሰባ ቀርበው የጸደቁትና የተመዘገቡት የሕንጻ ማሳወቂያና መግለጫ የመተዳደሪያ ደንብ እና ውስጠ ደንብ የተዋ ሀደው ማኅበር የሕንጻ ማሳወቂያና መግለጫ መተዳደሪያ ደንብ እና ውስጠ ደንብ ሆነው ይቀጥላሉ ፣ ውህደቱን የመሠረተው የእያንዳንዱ ማኅበር መብትና ግዴታዎች ለተዋሐደው ማኅበር ይተላለፋሉ ። ፴፩ ዳይሬክተሮችንና ኦዲተሮችን ስለመምረጥ የተዋሀደው ማኅበር የሕንጻ ማሳወቂያና መግለጫ ፣ መተዳ ደሪያ ደንብና ውስጠ ደንብ በተመዘገበ በ፵ ቀናት ውስጥ የተዋሀደው ማኅበር የቤት ባለቤቶች በጠቅላላ ስብሰባ ለተዋ ሐደው ማኅበር የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትና ኦዲተሮች መምረጥ አለባቸው ። ክፍል ስምንት የጋራ ሕንጻ በዚህ አዋጅ መሠረት መተዳደሩ ስለሚያበቃበት ሁኔታ ፴፪ • የቤት ባለቤቶች ፈቃድ ድምፅ በሚሰጥበት ጊዜ ቢያንስ ፳ ፐርሰንት የሆኑት ቤቶች | 32 . ባለቤቶች የጋራ ሕንጻው በዚህ አዋጅ መሠረት መተዳደሩ እንዲያበቃ በማለት ድምጽ ከሰጡ ማኅበሩ ይህንኑ የሚገልጽ የጽሁፍ ማስታወቂያ ለመዝጋቢው አካል ማቅረብ አለበት ። ፪ሺ፬የ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፭ ጳጉሜ ፮ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓ.ም Federal Negarit Gazeta – No. 95 12 September , 2003- ~ Page 2403 ፴ • ከፍተኛ ውድመት ፩ . ቦርዱ በጋራሕንጻው ላይ ከፍተኛ ውድመት ደርሷል ብሎ በሚወሰንበት ጊዜ ጉዳዩን ለቤት ባለቤቶች ጠቅላላ ስብሰባ በማቅረብ ስለውድመቱ መጠን እና ከውድመቱ በኋላ ሕንጻው በዚህ ሕግ መገዛቱን ያቆም እንደሆነ ማስወሰን አለበት ፣ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ መሠረት በሚደረገው የባለቤቶች ስብሰባ ከ፳ ፐርሰንት በላይ የሆኑት ቤቶች ባለቤቶች ሕንጸው በዚህ ሕግ መገዛቱ እንዲያበቃ ከወሰኑ ቦርዱ ይህንኑ የሚገልጽ የጽሁፍ ማስታወቂያ ለመዝ ጋቢው አካል ማቅረብ አለበት ፣ ፫ የቤቶች ባለቤቶች በዚህ አንቀጽ በተገለጸው ድምጽ መጠን ሕንጻው በዚህ ሕግ መገዛቱን እንዲያቆም በማለት ካልወሰኑ ቦርዱ በቂ በሆነ ጊዜ ውስጥ ውድመቱ እንዲ ጠገን ማድረግ አለበት ። ፴፬ ስለ ሽያጭ ፩ የጋራ ሕንጻው ወይም የተወሰነው የጋራ መጠቀሚያ በሚሸጥበት ጊዜ ይህ ሕግ በተሸጠው ሕንጻ ወይም የጋራ መጠቀሚያ ላይ ተፈጻሚ መሆኑ ያበቃል ፣ ማኅበሩ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ በተደነገገው መሠረት ሽያጭ ለማከናወን ፣ ሀ ) ድምጽ በተሰጠበት ዕለት ፳ ፐርሰንት የሚሆኑትን የቤት ባለቤቶች የአዎንታ ድምጽ እና ፣ ለ ) ሽያጩ ለተወሰኑ ቤቶች አገልግሎት ተለይተው የተሰጡ የጋራ መጠቀሚያዎችን የሚጨምር ከሆነ በተጨማሪ የጋራ መጠቀሚያው ተለይቶ የተሰ ጣቸው ቤቶች ባለቤቶችን የእያንዳንዳቸውን ፈቃደ ኝነት በጽሁፍ ማግኘት አለበት ። ፴፭ ለሕዝብ ጥቅም ንብረት ስለመውሰድ በሕግ መሠረት ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የተወሰደ የጋራ ሕንጻ ወይም የጋራ መጠቀሚያ በዚህ ሕግ መገዛቱ ያበቃል ። ፴፮ ከሽያጭና ከንብረት መወሰድ ስለሚገኝ ጥቅም ፩ . በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፴፬ ወይም አንቀጽ ፴፭ መሠረት የጋራ ሕንጸው ወይም የተወሰነው የጋራ መጠቀሚያ በመሸጡ ወይም በመወሰዱ የሚገኘው ጥቅም በጋራ መጠቀሚያዎች ላይ ባላቸው የመቶኛ ጥቅም ጋር ተመጣጣኝ በሆነ መጠን ለቤት ባለቤቶች ይከፋፈላል ፣ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ ቢኖርም የተሸጠው ወይም የተወሰደው ለተወሰኑ ቤቶች መጠቀሚያነት ብቻ ተለይቶ የተተወ የጋራ መጠቀሚያ በሆነ ጊዜ ጥቅሙ የሚከፋፈለው የጋራ መጠቀሚያው ተለይቶ በተሰ ጣቸው ቤቶች መካከል ብቻ ይሆናል ። ፴፯ ስለ ምዝገባ ፩ መዝጋቢው አካል በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፴፪ ወይም ፴፫ መሠረት የሚቀርብለትን ማስታወቂያ መርምሮ በመመ ዝገብ የምስክር ወረቀት ይሰጣል ፣ ፪ የምስክር ወረቀቱ እንደተሰጠ ይህ አዋጅና አዋጁን ለማስፈጸም የሚወጡ ሌሎች ሕጐች በሕንጻው ላይ ተፈጻሚነታቸው ያበቃል ። ፴፰ ስለሀብት ክፍፍል የጋራ ሕንጻው በዚህ አዋጅ መገዛቱ ሲያበቃ ፣ ፩ የቤት ባለቤቶች ማህበር ሀብት በማኅበሩ ላይ የሚነሱ የገንዘብ ጥያቄዎችን ለመክፈል ይውላል ፣ ፪ ቀሪው የማኅበሩ ሃብት በጋራ ጥቅማቸው መጠን ለቤት ባለቤቶች ይከፋፈላል ።

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?