* ናብሊክ ሕገ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አሥረኛ ዓመት ቁጥር ፲፫ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ADDIS ABABA - 23 December , 2003 አዲስ አበባ - ታህሣሥ ፲፫ ቀን ፲፱፻፮ ዓ.ም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፫፻፷፮ / ፲፱፻፶፮ ዓ.ም የኢትዮጽያ ዜግነት አዋጅ ገጽ ፪ሺ፭፻፭ አዋጅ ቁጥር ፪ ስለኢትዮጵያ ዜግነት የወጣ አዋጅ ከሕገ መንግሥቱ ድንጋጌዎች ጋር የተጣጣመና የተሟላ አዲስ የዜግነት ሕግ ማውጣት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፤ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ / ፩ / መሠረት የሚከተለው ታውጇል ፡፡ ክፍል አንድ ፩ አጭር ርእስ ይህ አዋጅ ' የኢትዮጵያ ዜግነት አዋጅ ቁጥር ፫፻፸፰ / ፲፱፻፮ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ፡፡ ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስ ተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ፤ ፩ / “ የውጭ አገር ሰው ” ማለት የኢትዮጵያ ዜጋ ያልሆነ ማንኛውም ሰው ነው ፤ ፪ / “ መደበኛ መኖሪያ ቦታ ” ማለት በኢትዮጵያ የፍትሐ ብሔር ሕግ አንቀጽ ፩፻፴፫ የተደነገገውን ትርጓሜ የሚያሟላ የአንድ ሰው መኖሪያ ቦታ ነው ፤ ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣ.ቁ ፭ ሺ ፩ … .ይም የኢት ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፫ ታህሣሥ ፲፫ ቀን ፲፻፯ ዓ.ም ፫ / “ ልጅ ” የሚለው ቃል ጉዲፈቻ የተደረገ ልጅንም ይጨምራል ፤ ፬ / “ ለአካለ መጠን ያላደረሰ ” ማለት በኢትዮጵያ የፍትሐ ሕግ መሠረት በዕድሜው ለአካለ ያላደረሰ ሰው ነው ፤ ፭ / “ ባለሥልጣን ” ማለት የደህንነት ፣ የኢምግሬ ሽንና የስደተኞች ጉዳይ ባለሥልጣን ነው ፡፡ ክፍል ሁለት የኢትዮጵያን ዜግነት ስለማግኘት ፫ . በትውልድ ስለሚገኝ ዜግነት ፩ / ወላጆቹ ወይም ከወላጆቹ አንዱ ኢትዮጵያዊ የሆነ ሰው ፣ በትውልድ የኢትዮጵያ ዜጋ ነው ፣ ፪ / በኢትዮጵያ ውስጥ የተገኘ ወላጆቹ ያልታወቁ ሕፃን የውጭ አገር ዜግነት ያለው መሆኑ ካልተረጋገጠ በስተቀር ከኢትዮጵያዊ እንደተወለደ ተቆጥሮ የኢት ዮጵያ ዜጋ ይሆናል ፡፡ ፬ . በሕግ ስለሚገኝ ዜግነት አንድ የውጭ አገር ሰው በዚህ አዋጅ ከአንቀጽ ፭ - ፲፪ 4. Acquisition By Law በተመለከቱት ድንጋጌዎች የኢትዮጵያን ዜግነት ሕግ ሊያገኝ ይችላል ፡፡ ጅ መሟላት ስለሚገባቸው ሁኔታዎች የኢትዮጵያ ዜግነት በሕግ ለማግኘት የሚያመለክት የውጭ አገር ሰው የሚከተሉትን ማሟላት አለበት ፣ ፩ / በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት ለአካለ መጠን ያደረሰና በሕግ ችሎታ ያለው መሆን ፤ ፪ / መደበኛ መኖሪያውን በኢትዮጵያ ውስጥ መመስረትና ማመልከቻውን እስካቀረበበት ቀን ድረስ ባሉት አምስት ዓመታት ውስጥ በድምሩ ቢያንስ ለአራት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ ፫ / ከአገሪቱ ብሔር / ብሔረሰቦች ቋንቋዎች ባንዱ መግባባት መቻል ፤ ፬ / እራሱንና ቤተሰቡን ለማስተዳደር የሚያስችል ሕጋዊ የገቢ ምንጭ ያለው መሆን ፤ ፭ መልካም ሥነ - ምግባር ያለው መሆን ፤ ፮ በወንጀል ተከስሶ ያልተቀጣ መሆን ፤ ፯ የቀድሞ ዜግነቱን የተወ መሆኑን ዮጵያን ዜግነት ቢያገኝ የቀድሞ ዜግነቱን ለመተው የሚችል መሆኑን ወይም ዜግነት የሌለው ሰው መሆኑን ማስረዳት መቻል ፤ እና ፰ / በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፪ የተመለከተውን ቃለ መሐላ መፈጸም ፡፡ K የጋብቻ ሁኔታዎች ከኢትዮጵያ ዜጋ ጋር የፀና ጋብቻ ያለው የውጭ ፩ / ጋብቻው በኢትዮጵያ ሕግ መሠረት የተፈጸመ ከኢትዮጵያ ውጭ ከተደረገ በዚያን አገር ሕግ መሠረት የተፈጸመ ከሆነ ፤ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፫ ታሣሥ ፫ ቀን ፲፱፻፲ ዓ.ም ፪ / ጋብቻው ከተፈጸመ ቢያንስ ሁለት ዓመት የሞላው ፫ / ማመልከቻውን እስከአቀረበበት ቀን ድረስ ቢያንስ ለአንድ ዓመት በኢትዮጵያ ውስጥ የኖረ ከሆነ ፤ ፬ / በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፭ ንዑስ አንቀጽ / ፩ / ፣ / ፯ / እና I ፰ / የተደነገጉትን ሁኔታዎች የሚያሟላ ከሆነ ፤ የኢት ዮጵያ ዜግነት በህግ ሊሰጠው ይችላል ። ፯ . የጉዲፈቻ ሁኔታዎች በኢትዮጵያ ዜጋ ጉዲፈቻ የተደረገ ሰው ፤ ፩ / ለአካለ መጠን ያላደረሰ ከሆነ ፤ ፪ / ከጉዲፈቻ አድራጊ ወላጁ ጋር በኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖር ከሆነ ፤ ፫ / ከጉዲፈቻ ወላጆቹ አንዱ የውጭ አገር ሰው ከሆነ ለልጁ የኢትዮጵያ ዜግነት እንዲሰጠው የተስማማ ስለመሆኑ በጽሑፍ ከገለጸ ፤ እና ፬ / በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፭ / የተደነገገው ሁኔታ ከተሟላ ፣ የኢትዮጵያ ዜግነት ይችላል ፡፡ ፰ . ልዩ ሁኔታዎች ለኢትዮጵያ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተ የውጭ አገር ሰው በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፭ ንዑስ አንቀጽ / ፪ / እና / ፫ / የተመለከቱትን ሁኔታዎች ባያሟላም የኢትዮጵያ ዜግነት በህግ ሊሰጠው ይችላል ። ፱ . በሕግ ዜግነት ስለተሰጠው ሰው ልጆች የኢትዮጵያ የተሰጠው በኢትዮጵያ ውስጥ አብሮት ለሚኖር ለአካለ መጠን ያላደረሰ ልጁ የኢትዮጵያ ዜግነት እንዲሰጠው ሊጠይቅ ይችላል ፡፡ ሆኖም የኢትዮጵያ ዜግነት በህግ የተሰጠው ከወላጆች ለአንደኛው ለልጃቸው የኢትዮጵያ ዜግነት እንዲሰጥ የሁለቱም ስምምነት ያስፈልጋል ፡፡ አንቀጽ / ፩ / መሠረት የኢትዮጵያ ዜግነት እንዲሰጠው ጥያቄ የቀረበለት ልጅ የቀድሞ ዜግነቱን የተወ ወይም ለመተው አመልካቹ ማስረዳት ከቻለ የኢትዮጵያ ዜግነት በህግ ይሰጠዋል ፡፡ በሕግ ዜግነት ለማግኘት ስለሚቀርብ ማመልከቻ ፩ / የኢትዮጵያ ዜግነት በሕግ እንዲሰጥ የሚቀርብ ማመልከቻ አግባብነት ካላቸው ማስረጃዎች ጋር ተያይዞ ለባለሥልጣኑ መቅረብ አለበት ፤ የኢትዮጵያ ዜግነት እንዲሰጥ የተጠየቀው ኣካለ መጠን ላላደረሰ ልጅ ከሆነ ማመልከቻው በወላጆቹ መቅረብ አለበት ፡፡ ፲፩ ማመልከቻን ስለማጣራትና ስለመወሰን ፩ / የኢትዮጵያ እንዲሰጥ ማመልከቻ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፳፫ መሠረት በተቋቋመ የዜግነት ጉዳይ ኮሚቴ ይጣራል ፡፡ ፪ / ኮሚቴው የቀረበለትን ማመልከቻና ማስረጃዎች ከመረመረና አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘም ተጨማሪ ማስረጃዎች እንዲቀርቡለት በማድረግ ካጣራ በኋላ ለባለሥልጣኑ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል ፡፡ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲፫ ታህሣሥ ፲፫ ቀን ፲፱፻፮ ዓ.ም ፫ / የኢትዮጵያ ዜግነት በሕግ እንዲሰጥ ኮሚቴው ያቀረበው የውሳኔ ሃሳብ በባለሥልጣኑ ተቀባይነት ካገኘ አመልካቹ በኮሚቴው ዘንድ ቀርቦ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፪ የተመለከተውን ቃለ መሐላ እንዲፈጽም ተደርጐ በሕግ የኢትዮጵያ ዜግነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ይሰጠዋል ፡፡ ፲፪ የታማኝነት ቃለ መሐላ የኢትዮጵያ ዜግነት በሕግ የሚሰጠው ማንኛውም ለአካለ መጠን ያደረሰ ሰው የሚከተለውን ቃለ መሐላ መፈጸም አለበት ፣ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ታማኝ ዜጋ ለመሆንና ለአገሪቱ ሕገ - መንግሥት ተገዥ ለመሆን ቃል እገባለሁ ፡፡ ” ፲፫ ስለዜግነት መታወቂያ ወረቀት ፩ / ማንኛውም ለአካለ መጠን ያደረሰ የኢትዮጵያ ዜጋ የዜግነት መታወቂያ ወረቀት ይሰጠዋል ፡፡ ፪ / ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች በወላጅ መታወቂያ ወረቀት ላይ መመዝገብ አለባቸው ፡፡ ፫ / የዜግነት መታወቂያ መረቀት የሚሰጠው በባለሥል ጣኑ ወይም በባለሥልጣኑ ውክልና በተሰጠው መሥሪያ ቤት ይሆናል ፡፡ ክፍል ሦስት የዜግነት መብቶች ፲፬ ስለመንግሥታዊ ጥበቃ ፩ / መንግሥት ለዜጎች መብቶችና ሕጋዊ ጥቅሞች ጥበቃ ያደርጋል ፡፡ ፪ / መንግሥት በውጭ አገር የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዜጎች መብቶችና ሕጋዊ ጥቅሞች የሚጠበቁበትን ሁኔታ ለማረጋገጥ የሚያስችሉ እርምጃዎችን ይወስዳል ፡፡ ፲፭ . ለሌላ መንግሥት ተላልፎ ስለአለመሰጠት ማንኛውም ኢትዮጵያ ዜጋ ለሌላ መንግሥት ተላልፎ እንዲሰጥ አይደረግም ፡፡ ፲፮ . ዜግነትን ስለመለወጥ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የዚህ ኣዋጅ ኣንቀጽ ፲፱ ዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ዜግነቱን የመለወጥ መብት ይኖረዋል ፡፡ ፲፯ . ዜግነትን ስለአለመገፈፍ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፱ ወይም ፳ በተደነገገው መሠረት ኢትዮጵያዊ ዜግነቱን ካላጣ በስተቀር በማንኛውም መንግሥታዊ ዜግነቱ አይገፈፍም ፡፡ ፲፰ . የዜጎች እኩልነት ሁሉም የኢትዮጵያ ዜጎች ዜግነታቸውን ያገኙበት ሁኔታ ከግምት ውስጥ ሳይገባ እኩል የዜግነት መብትና ግዴታ ይኖራቸዋል ፡፡ ዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር w ሥ 1 ቀን ፲ ዓ.ም ክፍል አራት የኢትዮጵያ ዜነትን ስለማት ፲፬ . የኢትዮጵያ ዜነትን ስለመተው ፩ / የሌላ አገር ዜግነት ያገኘ ወይም ሊሰጠው ቃል የተገባለት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜግነቱን የመተው መብት አለው ፤ ፪ / በዚህ ዜግነቱን ለመተው የፈለገ ኢትዮጵያዊ ባለሥልጣኑ በሚወስነው ቅጽ መሠረት አስቀድሞ ለባለሥልጣኑ ማሳወቅ አለበት፡ ፫ / ለአካለ መጠን ያላደረሰ ሰው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፩ / መሠረት ዜግቱን ለመተው የሚችለው በወላጆቹ የጋራ ውሳኔ ወይም ከወላጆቹ አንዱ የውጭ አገር ሰው ከሆነ ኢትዮጵያዊ በሆነ ወላጁ ውሳኔ ይሆናል ፤ ፪ ዜግነቱን ለመተው መፈለጉን ያላወቀ ኢትዮጵያዊ የሚፈለጉበት ብሔራዊ ግዴታዎች ካሉ እነዚህኑ ከመወጣቱ ወይም ለ / በወንጀል ተከስሶ ወይም ተፈርዶበት ከሆነ ከክሱ ነፃ ከመደረጉ ወይም የተወሰነበትን ከመፈጸሙ ፤ የዜግነት መልቀቂያ አይሰጠውም ፡፡ ኙ ባለሥልጣኑ የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች መሟላታ ቸውን ካረጋገጠ በኋላ ዜግነቱ የሚቋረጥበትን ቀን የሚገልጽ የዜግነት መልቀቂያ የምስክር ወረቀት ለባለጉዳዩ ይሰጠዋል ፤ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፩ / መሠረት የዜግነት መልቀቂያ የምስክር ያልተሰጠው ማንኛውም ባለጉዳይ ሥልጣን ላለው ፍርድ ቤት ይግባኝ የማቅረብ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡ ፩ . የሌላ አገር ዚነት ቡት የኢትዮጵያ ዜነት ስለሚያርበት ሁኔታ ፩ / የዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፬ / ፬ / ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በራሱ ፍላጎት የሌላ ዜግነት ካገኘ ዜግነቱን እንደተወ ይቆጠራል ፪ / ከወላጆቹ አንዱ የውጭ አገር ዜጋ በመሆኑ ወይም በውጭ አገር በመወለዱ የሌላ አገር ዜግነት ያገኘ ኢትዮጵያዊ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፲፪ / ፫ / መሠረት ኢትዮጵያዊ ዜግነቱን አስቀድሞ እንዲተው ካልተደረገ በስተቀር ለአካለ መጠን ካደረሰ በኋላ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የሌላ አገር ዜግነቱን ትቶ በኢትዮጵያዊነቱ ብቻ ለመቀጠል መምረጡን ለባለሥልጣኑ ካላሳወቀ ዜግነቱን በፈቃዱ እንደተወ ይቆጠራል ፫ / ራሱ ጠይቆ ሳይሆን በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፪ / ከተመለከተው ውጭ በማናቸውም ሌላ ምክንያት ላይ ተመሥርቶ በሕግ ድንጋጌዎች ተፈጻሚነት የተነሳ የሌላ አገር ዜግነት ያገኘ ኢትዮጵያዊ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፫ ታህሣሥ ፲፫ ቀን ፲ቅደ፮ ዓ.ም ሀ / ባገኘው የሌላ አገር ዜግነት መብቶች መጠቀም ከጀመረ ወይም በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ያገኘውን የሌላ አገር ዜግነት ትቶ በኢትዮጵያዊነቱ ብቻ ለመቀጠል መምረጡን ለባለሥልጣኑ ካላሳወቀ ዜግነቱን እንደተወ ይቆጠራል ፡፡ ፬ / ከኢትዮጵያ ዜግነቱ በተጨማሪ የሌላ አገር ዜግነት ይዞ የተገኘ ሰው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፪ / ወይም ፫ / ድንጋጌዎች መሠረት የኢትዮጵያ ዜግ ቀሪ እስከሚሆን ድረስ የኢትዮጵያ ዜግነት ብቻ እንዳለው ሆኖ ይቆጠራ ፡፡ ፳፩ . ዜግነትን ማጣት በተጋቢና በልጆች ዜግነት ላይ የሚያስከትለው ውጤት የኢትዮጵያ ዜግነትን ማጣት በዚያ ሰው የትዳር ኛና ልጆች ዜግነት ላይ የሚያስከትለው ውጤት | 22 ReAdmission to Ethiopian Nationality አይኖርም ፡፡ ፳፪ . የኢትዮጵያ ዜግነትን መልሶ ስለማግኘት ፩ / አስቀድሞ ኢትዮጵያዊ የነበረና በሕግ የሌላ አገር ዜግነት ያገኘ ሰው ፤ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ በመምጣት መደበኛ መኖሪያውን በኢትዮጵያ ውስጥ ከመሠረተ ፤ ለ / ይዞት የነበረውን የሌላ አገር ዜግነት ከተወ ፤ እና ሐ / ዜግነቱ እንዲመለስለት ለባለሥልጣኑ ካመለ ( ከተ ፤ የኢትዮጵያ ዜግነቱን መልሶ ያገኛል ፡፡ ፪ / የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ / ፩ / ድንጋጌ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፳ / ፪ / መሠረት የኢትዮጵያ ዜግነቱን አጥቶ ለነበረ ሰውም ተፈጻሚ ይሆናል ፡፡ ክፍል አምስት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፳፫ ስለዜግነት ጉዳይ ኮሚቴ ፩ / የሚከተሉትን አባላት የያዘ የዜግነት ጉዳይ ኮሚቴ ይቋቋማል ፤ ሀ / የባለሥልጣኑ ተወካይ- ......... ለ / የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካይ ....... አባል ሐ / የፍትህ ሚኒስቴር ተወካይ መ / የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ተወካይ --- “ ሠ / የባለሥልጣኑ ተወካይ .... አባልና ፀሐፊ ፪ / ኮሚቴው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩ ሀ / የኢትዮጵያ ዜግነት በሕግ ለማግኘት የሚቀርቡ ማመልከቻዎችን የመመርመር ፤ ለ / በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፳ መሠረት የኢትዮጵያ ዜግነቱን በፈቃዱ እንደተወ የሚቆጠር ሰው የሚያቀርባቸውን ተቃራኒ ማስረጃዎች የመመ የኢትዮጵያ ዜግነትን መለሶ ለማግኘት ማመ ልከቻ ሲቀርብ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፳፪ የተ ደነገጉት ሁኔታዎች መሟላታቸውን የማረጋ የ 6 ዓ.ም ጀምሮ ራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፲ ታሥ ፫ ቀን ፲፰ ዓ.ም ፫ / ኮሚቴው በዚህ አንቀጽ አንቀጽ / ፪ / መሠረት አንድን ጉዳይ የሚያየው በባለሥልጣኑ ሲመራለት የደረሰበትንም ግኝትና የውሳኔ ሃሳብ ለባለሥልጣኑ ያቀርባል ፤ ፬ / ኮሚቴው ለሥራው ባስፈለገ መጠን ይሰበስባል ፤ ፭ / ከኮሚቴው አባላት ኵግማሽ በላይ ከተገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይኖራል ፤ የኮሚቴው ያልፋል ፣ ሆኖም ድምጽ እኩል በእኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ድምጽ የሰጠበት ወገን ሃሳብ የኮሚቴው ሃሳብ ሆኖ ያልፋል ፤ ፯ የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ኮሚቴው የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ሊያመጣ ይችላል ። ፳፬ . ደንብና መመሪያ የማውጣት ሥልጣን ፩ / ይህን አዋጅ በሚገባ ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ ደንቦችን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሊያወጣ ይችላል፡ ይህን አዋጅ በሚገባ ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን ባለሥልጣኑ ይችላል ። ፳፩ . የተሻረ ሕግ የ፲፱፻፶፪ የኢትዮጵያ ዜግነት ሕግ / እንደተሻሻለ / በዚህ አዋጅ ተሽሯል ። ፳፮ የመሸጋገሪያ ድንጋ ይህ አዋጅ እስከጸናበት ቀን ድረስ በቀድሞው የዜግ ነት ሕግ መሠረት የኢትዮጵያ ዜጋ የነበረ ማንኛውም ሰው የኢትዮጵያ ዜጋ እንደሆነ ይቀጥላል ። ፳፯ እየሄ የሚናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከታህሣሥ ፫ ቀን የጸና ይሆናል ፡፡ አዲስ አበባ ታህሣሥ ፫ ቀን ፲፱፻፯ ግርማ ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት