የሰ / መ / ቁ . 15672
ዳኞች፡- 1. አቶ ከማል ሰድሪ
2. አቶ ፍስሓ ወርቅነህ
3. አቶ አብዱልቃድር መሐመድ
4. አቶ አሰግድ ጋሻው
5. አቶ መስፍን እቁበዮናስ
አመልካች፡- አቶ ታደለ ገስቻ
ተጠሪ፡- አቶ ውድመጣስ ነሮ
ስለ ንብረት ሽያጭ - ንብረት እንደገና በሐራጅ ስለሚሸጥበት ሁኔታ ስለ ሐራጅ አሸናፊ ክፍያ መፈፀሚያ ወቅት - የፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕ / ቁ .442
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁን ተጠሪ ባለቤት የሆነ ንብረት በሐራጅ ተሽጦ ዕዳ እንዲከፈል በማድረግ ሁለት ተጫራቾች በተለያየ ጊዜ አሸንፈው በህጉ መሠረት በ 15 ቀን ውስጥ ገቢ ስላላደረጉ ድረጅቱን ባለመብቱ በንብረቱ ግምት ይረከቡት በማለት የከፍተኛው ፍርድ ቤት
የሰጠውን ትዕዛዝ በማፅናቱ የቀረበ አቤቱታ ፡፡
ዉሳኔ ፡- የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ከፍተኛ ፍርድ ቤት በጉዳዩ
የሰጡት ውሳኔ ተሽሯል ፡፡
1. የፍ / ብ { ሥ ሥ / ሕ / ቁ 442 ላይ ንብረቱ ለምን ያህል ጊዜ በድጋሚ
እንዲሸጥ በፍ / ቤቱ እንደሚታዘዝ ሳይደነግግም ንብረቱ ገዢ አያገኝም
ወደሚል መደምደሚያ አያደርስም ፡፡
2. ሁለት ጊዜ ሃራጅ ሽያጭ ወጥቶ አሽናፊዎች ካልከፈሉ 3 ኛ ጊዜ
ሃራጅ ወጥቶ ቤቱ ሊሸጥ ይገባል ፡፡
የሰ / መ / ቁ . 15672
27/04 ቀን 1998 ዓ.ም
ዳኞች፡- 1. ኣቶ ከማል ሰድሪ
2. ኣቶ ፍስሓ ወርቅነህ 3. አቶ አብዱልቃድር መሐመድ 4. አቶ አሰግድ ጋሻው
5. ኣቶ መስፍን እቁበዮናስ አመልካች፡- አቶ ታደለ ገለቻ - ታዬ ባንጃው ጠበቃ ቀርቧል ፡፡ ተጠሪ፡ ኣብ ውድመጣስ ኑሮ - አልቀረበም ፡፡
ው ሣ ኔ ይህ የአፈፃፀም ክርክር ለዚህ ሰበር ችሎት ሊቀርብ የቻለው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ / ቤት 1 ኛ ፍትሐብሔር ቀጥታ ክስ ችሎት መጋቢት 29 ቀን 1996 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ አመልካች ቅር በመሠኘታቸው ነው ፡፡
ለጉዳዩም መነሻ በሆነው በአመልካችና በተጠሪ መካከል በነበረው የአፈፃፀም ክርክር ተጠሪ ( የፍርድ ባለመብት ) የነበሩ ሲሆን አመልካች ደግሞ የፍርድ ባለዕዳ ነበሩ አመልካች የሚሉትም የእኔ ባለቤት ከወ / ሮ ይችዓለም ለገ ገዝታው ስሙ ያልተዛወረ « ሠላም የህፃናት ልብስ
መደብር ። የተባለው ተሽጦ : ለዕዳዬ እንዲውል የፌ / ከ / ፍ / ቤት ውሣኔ ሠጥቶ የፍርድ አፈፃፀም መምሪያ ድርጅቱን አስገምቶ ፍ / ቤቱም ድርጅቱን ለሐራጅ ጨረታ እንዲቀርብ አድርጓል ሆኖም ግን ሁለት ተጫራቾች
ተጫራቾች በተለያየ ጊዜ ተጫርተው ያሸነፉ ቢሆንም ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት በ 15 ቀን ጊዜ ውስጥ ገንዘቡን ገቢ ሊያደርጉ አልቻሉም በዚህም መሠረት የከ / ፍ / ቤት ቀጥታ ክስ ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕ / ቁ 442 መሠረት ንብረቱ በጨረታ እንዲሸጥ ትዕዛዝ የሚሠጠው ለምን ያህል ጊዜ እንደሆነ የተገለፀ ነገር የለም ፣ ነገር ግን አፈፃፀሙ ተግባራዊ መሆን ስላለበት ላልተወሠነ ጊዜ ትዕዛዝ ሲሰጥ መቆየት የለበትም ፣ በመሆኑም ንብረቱ ለሁለተኛ ጊዜ ተጫራች ባለመቅረቡ
ምክንያት የባለዕዳውን ንብረት , ባለገንዘቡ እንደሚረከበው ሁሉ ድርጅቱን
ባለመብቱ በንብረቱ ግምት መሠረት ይረከቡት የሚል ትዕዛዝ ሠጥቷል ፡፡
አመልካችም በዚህ ትዕዛዝ ቅር በመሠኘት ለፌ / ጠ / ፍ / ቤት ይግባኝ የጠየቁ ሲሆን ፍ / ቤቱም ጉዳዩን ኣይቶ የከ / ፍ / ቤት የሠጠው ትዕዛዝ ጉድለት የሌለው ነው በማለት ወስኗል ፡፡ አመልካች
ፍ / ቤቶች
መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አለበት በማለት ለዚህ ሰበር ችሉ ይግባኛቸውን አቅርበዋል ፡፡ የይግባኛቸውም መሠረታዊ የፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕግ ቁጥር 442 ፍ / ቤቱ ንብረቱ እንደገና እንዲሸጥ ትዕዛዝ እንጅ በመነሻው ግምት የፍርድ ባለመብቱ፡ ( ተጠሪ ) ይረከበዋል አይልም የሚል ሲሆን ተጠሪም በዚሁ መሠረት መልሱን ይዞ የቀረበ ሲሆን አመልካችም የበኩሉን የመልስ መልስ አቅርቦ ከመዝገቡ ጋር ተያይዟል ፡፡
ይህ የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍ / ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም ጉዳዩን ከተገቢው የሕግ ድንጋጌ ጋር መርምራል ። እንደመረመረውም ክርክሩ የቀረበበትን ድርጅት ለመሸጥ ሁለት ጊዜ የሐራጅ ማስታወቂያ ወጥቶ ፣ በሁለቱም ሐራጅ የሐራጁ አሸናፊዎች ሐራጁ በተደረገ በ 15 ቀኖች ውስጥ የንብረቱን ዋጋ በሙሉ ኣልከፈሉም ተብሎ የፍርድ ባለመብቱ ማለትም ተጠሪ ንብረቱን በግምቱ እንዲረከብ መባሉ አግባብ መሆን አለመሆኑን አይቷል ፡፡ የፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕግ እንደተመለከተው የጨረታ አሸናፊ የሆነው ሰው በ 15 ቀን ጊዜ ውስጥ የንብርቱን ዋጋ ሳይከፍል የቀረ እንደሆነ ፍ / ቤቱ ንብረቱን እንደገና እንዲሸጥ ትዕዛዝ ይሰጣል የሚል ተመልክቷል ፡፡ ምንም እንኳን እዚህ ላይ በሕጉ ውስጥ ይህ አይነት ሁኔታ የተከሠተበት ንብረት ለምን ያህል ጊዜ በድጋሚ እንዲሽጥ በፍ / ቤቱ እንደሚታዘዝ ያልተመለከተ ቢሆንም ንብረቱ ከነአካቴው ገዥ አያገኝም ወደሚል መደምደሚያ የሚያስደርስ አይሆንም ፡፡ ስለሆነም በተያዘው ጉዳይ ላይ የጨረታው አሸናፊዎች ገንዘቡን አልከፈሉም ማለት ሌላ ገዥ የለም ማለት አይደለም ፡፡ በዚህም መሠረት የከ / ፍ / ቤት ክርክር የተነሣበትን ድርጅት ባለመብቱ በንብረቱ ግምት መሠረት እንዲረከቡት በማለት የሠጠው ትዕዛዝና የጠ / ፍ / ቤቱም የሠጠው ይህንኑ የሚያፀና ውሳኔ አግባብ አይደለም በማለት ሽረን ክርክር የተነሣበት ድርጀት በሐራጅ ይሸጥ
ሲል ይህ ሰበር ሰሚ ችሎት ወስኗል ። ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻሉ
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ፡፡
You must login to view the entire document.