የሰበር መ / ቁ 21008
ቀን 25/9/98
ዳኞች፡- 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
2. አቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ
3. አቶ ጌታቸው ምህረቱ
4. አቶ መስፍን ዕቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሠ
አመልካች የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ድርጅት ነ / ፈጅ ቀርቧል ፡፡
መልስ ሰጭ፡- 1. አቶ ስንታየሁ ታደሰ
ቀርበዋል ፡፡
2. አቶ ደገፋው ዳምጠው
ፍ ር ድ
በዚህ ጉዳይ ለሰበር
የቀረበው ክርክር የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሣኝ
ቦርድን ስልጣን የሚመለከት ነው ፡፡
በመ / ሰጭ በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ክሱ የቀረበው ቋሚ እንድንሆን ይወስንልን
እና ጥቅማ ጥቅም ከልክሎናል በሚል ነው ፡፡ አቤቱታ የቀረበበት ውሣኔ አሰሪና ሠራተኛ
ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ክሱን ለማየት ሥልጣን አለው በማለት የተሰጠ ነው ፡፡ አመልካች
ውሣኔውን በመቃወም ለዚህ ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ጉዳዩ ለሰበር ችሎት
እንዲቀርብ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት መ / ሰጭ መልሱን አቅርቧል ፡፡
ችሎቱም በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሣኝ ቦርድ የሥራ ክርክሮች ምን አይነት
ናቸው የሚለውን የሕግ ነጥብ መሠረት በማድረግ አቤቱታ የቀረበለትን ውሣኔ
አግባብነት ካለው ሕግ ጋር አገናዝቦ መርምሯል ፡፡
ፌዴራል ስቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ግልባጭ
ክርክር አይደለሃል የተሰጠው ውሣኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ
ይህ ችሎት በመ / ቁ . 18180 አግባብነት ያላቸውን የአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ ድንጋጌዎች በመተርጎም የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ የማየት ስልጣን የተሰጠው የውል የሥራ ክርክር ጉዳዮችን ነው ፤ አንድ የሥራ ክርክር የወል የሥራ ክርክር ነው የሚባለው ጉዳዩ የጋራ በሆነ የሠራተኞች መብትና ጥቅም ላይ አሉታዊም ሆነ አወንታዊ ውጤት የሚያስከትል ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው ፤ በአንፃሩ አንድ የሥራ ክርክር የወል ሳይሆን የግል የሥራ ክርክር ጉዳይ ነው የሚባለው የክርክሩ ውጤት በተከራካሪው ሠራተኛ / ሠራተኞች / ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሆኖ ሲገኝ ነው በማለት የሕግ ትርጉም ሰጥቷል ።
መ /
ሰጭ በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ቋሚ እንድንሆን ይወሰንልን እና ጥቅማ ጥቅም ከልክሎናል በሚል ያቀረበው ክስ የጋራ በሆነ የሠራተኞች መብትና ጥቅም ላይ አሉታዊም ሆነ አወንታዊ ውጤት የሚያስከትል ባለመሆኑ የወል የሥራ
በመሆኑም ጉዳዩን ለማየት በአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ
ስልጣን አለው በማለት
ተገኝቷል ።
የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ በመቁ . 180/01/96 ጥር 03 ቀን 1997
ዓ / ም የሰጠው ውሣኔና የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ / ቁ . 36671
ሐምሌ 5 ቀን 1997 የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል ፡፡
ግራ ቀኙ በዚህ ችሎት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻሉ ፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል ፧ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ፡፡
ፌዴራል :: ትላይ ፍርድ ቤት
ትክል ግልባጭ
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ፡፡
ፊርማ --------
You must login to view the entire document.