×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
አዋጅ ቁጥር ፫፻፳፱/፲፱፻፶፭ የንግድ አሠራር አዋጅ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ መሠረታዊ በሆኑ አንዳንድ የንግድ , ዳና አገልግሎቶች የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲ ሪፐብሊክ ዘጠነኛ ዓመት ቁጥር ፴፱ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አዲስ አበባ ሚያዝያ ፱ ቀን ፲፱፻፲፭ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ አዋጅ ቁጥር ፫፻፳፱ / ፲፱፻፶፭ ዓም የንግድ አሠራር አዋጅ ገጽ ፪ሺ፩፻፵፪ አዋጅ ቁጥር ፫፻፳፱ / ፲፱፻፲፭ የንግድ አሠራር አዋጅ የንግድ ሥራ አገሪቱ በምትከተለው የነፃ ገበያ ኢኮኖሚ ፖሊሲ መሠረት ተገቢውን አሠራር ተከትሎ መካሄድ ስላለበት ፣ ኢኮኖሚያዊ ቀልጣፋነትንና ማኅበራዊ ደኅንነትን ለማስፈን እና በነጋዴዎችም መካከል የሚደረጉትን ፀረ - ውድድር የሆኑ | conducive for the promotion of competitive environment , by ተግባራት በመቆጣጠር ለውድድር አመቺነት ያለው ሥርዓት | regulating anti - competitive practices in order to maximize ማሳደግ ኣስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፣ ላይ እጥረት በሚያጋጥምበት ወቅት በተጠቃሚው ላይ ጉዳት | and equitable distribution of certain basic goods and services እንዳይደርስ ዋጋን መቆጣጠርና ሥርጭቱንም ሥርዓት ማስያዙ | in times of irregular and short supply is necessary to safeguard አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት ፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፵፭ ( ፩ ) መሠረት የሚከተለው ታውጇል ። ክፍል አንድ ፩ . አጭር ርዕስ ይህ አዋጅ “ የንግድ አሠራር አዋጅ ቁጥር ፫፻፳፱ / ፲፱፻፲፭ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ የቃሉ አግባብ ሌላ ትርጉም የሚሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ ፤ ፩ . “ መሠረታዊ የንግድ ዕቃ ወይም አገልግሎት ” ማለት በገበያ ላይ ዕጥረት በመፈጠሩ ምክንያት ተገቢ ያልሆነ የንግድ ሥራሊያስከትል የሚችል ከሸማቹ የዕለትቁሳዊ ላጎትጋር የተገናኘ አይ አገልግሎት ነው ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ ፰ሺ፩ በማስወገድ የተጠቃ ” . ይህ አዋጅ በማንኛውም በንግድ ሥራ ላይ ቦታ , ገጽ ፪ሺ፩የሃ ፤ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፴፱ ሚያዝያ ፪ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓም ፪ . “ ሚኒስቴር ” ወይም “ ሚኒስትር ” ማለት የንግድና ኢን ዱስትሪ ሚኒስቴር ወይም ሚኒስትር ነው ። ፫ . “ አግባብ ያለው ባለሥልጣን ” ማለት የንግድና እንዱ ስትሪ ሚኒስቴር ወይም ክልል የሚመለከተው ቢሮ ነው ። ፬ . “ ተጠቃሚ ” ማለት ለራሱ ፍጆታ ከነጋዴ የንግድ ዕቃ ወይም አገልግሎት የሚገዛ ማናቸውም ሰው ነው ። ፭ ኮሚሽን ” ማለት በዚህ አዋጅ መሠረት በፌዴራል ደረጃ የሚቋቋም ኣካል ነው ። ፮ . “ የንግድ ዕቃ ” ማለት ለገንዘብነት ከሚውል ከወርቅ ገንዘብ ፣ ከማንኛውም ዓይነት ገንዘብ ፣ ከሌላ መገበያያ ገንዘብ ፣ ገንዘብነት ካላቸው ሰነዶችና ከግል መገልገያዎች በስተቀር የሚንቀሳቀሱ ዕቃዎች ማለት ነው ። ፯ . “ ሰው ” ማለት ማንኛውም የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው ። ፰ . “ አገልግሎት ” ማለት ደመወዝ ወይም የቀን ሙያተኛ ክፍያ ያልሆነ ገቢ የሚያስገኝ ማናቸውም አገልግሎት የመስጠት ንግድ ሥራ ነው ። ፱ . “ ጽሕፈት ቤት ” ማለት በሚኒስቴሩ መዋቅር ሥር ያለና ለዚህ አዋጅ አፈፃፀም ኃላፊነት የሚሰጠው መምሪያ ፲ . “ ነጋዴ ” ማለት የሙያ ሥራው አድርጎ ጥቅም ለማግኘት ሲል በንግድ ሕግ ቁጥር ፭ የተዘረዘሩትን ሥራዎች የሚሠራ ወይም አገልግሎት የሚሰጥ ወይም መንግሥት የንግድ ሥራ ነው ብሎ በሕግ የሚወስነውን ሥራ የሚሠራ ማንኛውም ሰው ነው ። ፲፩ . “ የንግድ ሥራ ” ማለት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) በተተረጎመው መሠረት ነጋዴ የሚሠራው ሥራ ነው ። ፫ ዓላማ ለነፃ ገበያ ውድድር እንቅፋት የሆኑ ድርጊቶችና ተገቢ ያልሆኑ የንግድ ሥራዎች እንዳይፈጸሙ በመከላከልና በማስወገድ ተገቢ ውድድር እንዲሰፍን ለማድረግ ፣ እና በንግድ ዕቃዎች እና አገልግሎቶች አቅርቦት እና ሥርጭት ላይ ገደብ የሚፈጥሩ ድርጊቶችን በመከላከልና ኅብረተሰብ ማስጠበቅ ነው ። ፬ የተፈፃሚነት ወሰን ሰው ላይ ተፈፃሚ ይሆናል ። ፭ ልዩ ሁኔታዎች የዚህ አዋጅ አንዳንድ ድንጋጌዎች ቀጥሎ በተመለከቱት ላይ ተፈጻሚ ስለማይሆኑበት ሁኔታ በኮሚሽኑ ሊወሰን ይችላል ። ፩ በኢንቨስትመንት አዋጁ መሠረት በመንግሥት ብቻ በሚካሄዱ የንግድ ሥራዎች ፤ ፪ • በመንግሥት ትኩረት ሊሰጣቸውና ዕድገታቸው እንዲበ ረታታ ለታቀዱ ለልማት ጉልህ አስተዋፅኦ ለሚያደርጉ ድርጅቶች ፣ እና ፫ . የዋጋ ቁጥጥር በሚደረግባቸው መሠረታዊ የንግድ ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች ። ክፍል ሁለት ፀረ ውድድር ስለሆኑ ተግባራት ፮ : ክልከላ ፩ . ማንኛውም ሰው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በማምረት ፣ በአቅርቦት ፣ በስርጭት ወይም ዕቃና አገልግ ሎትን በመገበያየት ሂደት ውስጥ የነፃ ገበያ ውድድርን የሚገድብ ፣ የሚቀንስ ፣ የሚከለክል ወይም በማንኛውም ሌላ መንገድ የሚጎዳ የጽሑፍ ወይም የቃል ስምምነት ማድረግ አይችልም ። ገጽ ፪ሺ፩፻፵፬ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፱ ሚያዝያ ፪ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓ.ም. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) አጠቃላይ አነጋር እንደተጠበቀ ሆኖ ቀጥሎ የተዘረዘሩት ድርጊቶች ፀረ ውድድር ስምምነቶች እንደሆኑ ይቆጠራሉ ፣ ሀ ) ዋጋን በጋራ የመወሰን ስምምነት ፣ ለ ) የገበያ ዋጋን ለመወሰን በሽርክና ለመጫረት የሚደረግ ስምምነት ፣ ሐ ) ገበያን ወይም ደንበኞችን መመደብ የመከፋፈል ስምምነት ፣ መ ) የምርትና ሽያጭ ቦታ ምደባ ስምምነት ፣ ሠ ) ላለመሸጥ ፣ አገልግሎት ላለመስጠትና ላለመደ ራደር በሕብረት አቋም መያዝ ። ፯ ስለመፍቀድ በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ ( ፩ ) የተደነገገው ቢኖርም ሚኒስቴሩ አስፈላጊውን ጥናት በማድረግ ስምምነቱ ከሚያደርሰው ጉዳት የላቀ ለአገሪቷየሚሰጠው ጥቅም የሚያመዝን መሆኑን በማረጋገጥ ተገቢውን ግዴታ አስገብቶ ስምምነቱ እንዲደረግ ሊፈቅድ ይችላል ። ፰ ምዝገባ በዚህ አዋጅ በአንቀጽ ፯ መሠረት የተፈቀደና በጽሑፍ የተደረገው ስምምነት ዝርዝር ጉዳይ በሚኒስቴሩ ውስጥ በሚገኝ ልዩ መዝገብ እንዲገባ ሆኖ ለሕዝብ ይፋ ይደረጋል ። ፬ ምዝገባን ስለመሰረዝ ስምምነቱ ከተፈጸመ በኋላ ለሀገሪቷ ከሚሰጠው ጥቅም ይልቅ | 9 Cancellation ጉዳቱ የሚያመዘን ከሆነ ወይም ተስማሚ ወገኖች በገቡት ግዴታ መሠረት ካልፈጸሙ ሚኒስቴሩ የሰጠውን ፈቃድ ሊሠረዝ ይችላል ። ፲ : ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር በንግድ ሥራ ሂደት ውስጥ በተለያዩ መንገዶች ተወዳ ዳሪን ለማጥፋት ያለመ ማንኛውም ድርጊት ወይም ተግባር ሁሉ ተገቢ ያልሆነ የንግድ ውድድር እንደሆነ ይቆጠራል ። ፪ በተለይም የሚከተሉት ድርጊቶች ተገቢ ያልሆኑ የንግድ ውድድሮች እንደሆኑ ይቆጠራሉ፡ በሌላው የንግድ ድርጅት ወይም በንግድ ድርጅቱ ተግባሮች ፣ በተለይም ድርጅቱ ከሚያቀርበው ምርት ወይም አገልግሎት ጋር በተገናኘ ሁኔታ ማደናገርን ያስከተለ ወይም ሊያስከትል የሚችል ማናቸውም ድርጊት ፣ ለ ) በሌላው ድርጅት መልካም ስም ወይም ዝና ላይ ሀሰት በሆነ አፈጻጸም ጉዳት ያደረሰ ወይም ሊያደርስ የሚችል ማናቸውም ድርጊት ፣ ሐ ) የአንድን ድርጅት ወይም የድርጅቱን ተግባሮች በተለይም ድርጅቱ ከሚያቀርበው ምርት ወይም አገልግሎት ጋር በተገናኘ ሁኔታ የሕዝብን ግንዛቤ ያዛባ ወይም ሊያዛባ የሚችል ማናቸውም ድርጊት ፣ መ ) ባለመብት ከሆነው የመረጃው ባለቤት ፈቃድ ውጭ ከሐቀኛ የንግድ አሠራር ተፃራሪ በሆነ ሁኔታ የሌላውን መረጃ የማውጣት የመያዝ ወይም የመቀጠም ማናቸውም ድርጊት ፣ ሠ ) የሌላውን የንግድ ድርጅት ወይም የድርጅቱን ተግባሮች በተለይም ድርጅቱ ከሚያቀርበው ምርት ወይም አገልግሎት ጋር በተገናኘ ሁኔታ ታማኝ ነትን ያሳጣ ወይም ሊያሳጣ የሚችል ማናቸውም ሀሰት የሆነ ወይም ማረጋገጫ የሌለው አገላለጽ ፣ ገጽ ፪ሺ፩፻፵፭ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፱ ሚያዝያ ፱ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓም : ረ ) ማናኛውም የንግድ ዕቃ በተወዳዳሪዎች እንዳይመረት ወይም እንዳይከፋፈል ወይም ማንኛውም አገልግሎት እንዳይሰጥ ለማድረግ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የመግታት ፣ የመከልከል ወይም የማዳከም ድርጊት ፣ ሰ ) ማናቸውም ዕቃ ወይም አገልግሎት ወቅታዊ ወይም ኢኮኖሚያዊ በሆነ መንገድ እንዳይመረት ወይም አገል ግሎት እንዳይሰጥ የመግታት ወይም የመከልከል ድርጊት ። ሸ ) በኢትዮጵያ ውስጥ የሚመረቱትን ዕቃዎች ለማጥፋት ወይም ለመጉዳት ወይም በነዚህ ዕቃዎች ላይ ያለውን ማንኛውንም የንግድ ክፍል ለመገደብ ወይም በሞኖፖል ለመያዝ በማሰብ የነዚህ ዓይነት ዕቃዎች በተሰሩበት አገር ዋና ገበያዎች ከሚሸጡበት የገበያ ወይም የጅምላ ዋጋ ባነሰ ዋጋ ወደ ኢትዮጵያ ማስገባት ፣ ቀ ) ሚኒስቴሩ ሳይፈቅድ በማንኛውም ሁኔታ ለዕርዳታ ዓላማ ወደ ሀገር ውስጥ በገቡ ዕቃዎች መነገድ ፣ ፲፩ ገበያን በበላይነት አለአግባብ ስለመጠቀም ፩ . ማንኛውም ሰው ዕቃዎችንና አገልግሎቶችን የገበያ ድርሻ በበላይነት ለመቆጣጠር የሚያስችል ወይም የሌሎችን የገበያ ድርሻ ሊቀንስ የሚችል ወይም በማን ኛውም ሁኔታ ነፃ ውድድርን በመገደብ በገበያ ዕድገት ላይ ጎጂ ተፅዕኖ ያደረሰ ወይም ሊያደርስ የሚችል የንግድ ሥራ መሥራት አይችልም ። ፪ . በተለይም የሚከተሉት ድርጊቶች ገበያን በበላይነት ያለአግባብ የመጠቀም ድርጊቶች እንደሆኑ ይቆጠራሉ፡ ሀ ) በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ተገቢ ያልሆነና እጅግ የናረ ወይም የወረደ የመሸጫ ወይም የአገል ግሎት ክፍያ ዋጋ መጠየቅ ወይም አቅርቦትን መገደብ ወይም ሌላውን ከንግድ ሥራ ለማገድና ላለማስገባት ተገቢ ያልሆነ የንግድ ሥራ መሥራት ፣ ለ ) በዕቃ ገዥዎች ወይም በአገልግሎት ተጠቃሚዎች ላይ ጉዳት ሊያመጣ የሚችል ወይም የገበያን ዕድገት የሚቀንስ ተግባር መፈጸም ፣ ሐ ) አንድ ዓይነት ዕቃዎችን ወይም አገልግሎቶችን ለተጠቃሚዎች እኩል ባልሆነ ድርድር መሸጥ ወይም ክፍያ መቀበል ፣ መ ) ኣንድ ዓይነት ዕቃዎችን ለነጋዴዎች እኩል ባልሆነ ድርድር መሸጥና አንዳንዶቹን የመወዳደር ችሎታቸው በሚቀንስበት ሁኔታ ላይ መጣል ፣ ሠ ) ኣንድን ዕቃ ወይም አገልግሎት ለመሸጥ ገዥው ያልፈለገውን ሌላ ዕቃ ወይም አገልግሎት አብሮ እንዲገዛ ማስገደድ ፣ ረ ) ስለንግድ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ጥራት ፣ ብዛት ፣ መጠን ፣ አሠራር ፣ ውሁድ ፣ ጥንካሬ ወይም ዕቃዎቹ ስለሠሩበት ወይም አገልግሎት ስለሚሰጡበት ጊዜና ቦታ ወይም በተመሳሳይ ሁኔታዎች ሀሰተኛ ወይም አሳሳች የንግድ መግለጫ ወይም ማስታ ወቂያ ማውጣት ፣ ሰ ) የንግድ ዕቃዎችን መደበቅ ፣ ወይም በመደበኛው የንግድ መስመር ለሕዝብ እንዳይሸጡ ማድረግ ወይም መያዝ ፣ ሽ ) በቂ ባልሆነ ምክንያት ማናቸውንም የንግድ ዕቃ ወይም አገልግሎት ለተጠቃሚዎች አልሸጥም ቀ ) ተገቢ ውድድር እንዳይኖር ለማድረግ የማምረቻ ወጪን በማይሽፍን ዋጋ መሸጥ ። ገጸ ፪ሺ፩፻፵፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፱ ሚያዝያ ፱ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም ክፍል ሦስት አጣሪ ኮሚሽን ፲፪ : ስለኮሚሽኑ መቋቋም ከዚህ በኋላ “ ኮሚሽን ” እየተባለ የሚጠራ ተጠሪነቱ ለሚኒ ስትሩ የሆነና በዚህ አዋጅ የተሰጠውን ሥልጣንና ተግባር በሥራ ላይ የሚያውል አጣሪ ኮሚሽን ተቋቁሟል ። ፲፫ ስለአባላቱ ኮሚሽኑ ከመንግሥት ፣ ከግል ድርጅቶች እና ከተጠቃ ሚዎች ማኅበር የተመረጡ አባላት ይኖሩታል ። የኮሚሽኑ አባላት ሰብሳቢውን ጨምሮ በሚኒስትሩ አቅራ ቢነት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሾማሉ ። ፲፬ ስብሰባ ኮሚሽኑ በወር አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል ። ሆኖም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በማንኛውም ጊዜ አስቸኳይ ስብሰባ ሊያደርግ ይችላል ። ፪ . በኮሚሽኑ ስብሰባ ላይ ከአባላቱ ከግማሽ በላይ ከተገኙ ምልዓተ ጉባዔ ይሆናል ። ፫ ኮሚሽኑ ውሳኔ የሚያሳልፈው በድምፅ ብልጫ ይሆናል ። ሆኖም ድምዕ እኩል ለእኩል ከሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምፅ ይኖረዋል ። ፲፭ የኮሚሽኑ ሥልጣንና ተግባር ፩ ኮሚሽኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል ። ሀ ) የዚህ አዋጅ ድንጋጌዎችን የመተላለፍ ደርጊት ተፈጽሟል ከሚል ማንኛውም ወገን የሚቀርቡ ለትን አቤቱታዎች መመርመር ፣ ለ ) የምርመራ ተግባሩን ለማከናወን አስፈላጊ ናቸው ያላቸውን መረጃዎችንና ሰነዶችን ማንኛውም ሰው እንዲያቀርብለት የማስገደድ ፣ ሐ ) ከጉዳዩ ጋር አግባብ አለው ተብሎ የሚገመተውን ማንኛውም ሰው የምስክርነት ቃሉን እንዲሰጥ የማድረግ ፣ መ ) የመሐላ ሥርዓት ወይም የማረጋገጫ ቃል የመቀ በልና በዚህም መሠረት ምርመራ የማድረግ ፣ ሠ ) በማንኛውም ድርጅት ውስጥ የኮሚሽኑን መታወ ቂያ በማሳየት በሥራ ሰዓት መግባትና ለምርመራ ሥራው አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችንና ሰነዶችን የመፈተሽ ፣ ረ ) አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ባለሙያዎች እንዲመደቡለት ወይም እንዲቀጠሩለት ሚኒስቴሩን በመጠየቅ ሙያዊ ጥናት የማድረግ ፣ ሰ ) የቀረቡለትን አቤቱታዎች መርምሮ እንደአግባቡ አስተዳደራዊ እርምጃዎች እና ወይም የቅጣት ውሳኔ የመስጠት ። ፪ • ኮሚሽኑ የወሰነው ማንኛውም አስተዳደራዊ እርምጃ ወይም የቅጣት ውሳኔ በሚኒስትሩ መዕደቅ አለበት ። ፫ : ሚኒስትሩ ከኮሚሽኑ የቀረበለትን ማንኛውንም አስተዳ ደራዊ እርምጃ ወይም የቅጣት ውሳኔ ሊያጸድቅ ፣ ሊያሻሽል ወይም እንደገና እንዲታይ ሊያደርግ ይችላል ። ፬ • ኮሚሽኑ ኃላፊነቱን በተሟላ ሁኔታ ለመወጣት በሚያስ ችለው መጠን ሥልጣንና ተግባሩን ከፊል በጽሕፈት ቤቱ አማካኝነት እንዲከናወን መወከል ይችላል ። ፲፮ የማስፈፀም ሥልጣን ፩ በኮሚሽኑ ተወስኖ በሚኒስትሩ የፀደቀውን አስተዳ ደራዊ እርምጃ እና ወይም የቅጣት ውሳኔ የማስፈፀም ሥልጣን በዚህ አዋጅ ለሚኒስቴሩ ተሰጥቷል ። ፪ . ሚኒስቴሩማንኛውንም የአስተዳደር እርምጃእና ወይም የቅጣት ውሳኔ ለማስፈጸም ፖሊስን ለማዘዝ ይችላል ። ድምፅ መጽደቅ አለባቸው ፣ ማ ) ገጽ ፪ሺ፩፻ : ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፱ ሚያዝያ ፱ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም : ፫ . ማንኛውም የአስተዳደር እርምጃ እና ወይም የቅጣት ውሳኔ ከመፈፀሙ በፊት ለሚኒስትሩ ቀርቦ አፈፃፀሙ እንዲቀጥል በጽሑፍ መፈቀድ አለበት ። በዚህ ኣንቀጽ በንዑስ አንቀጽ ( ፫ ) መሠረት የሚፃፈው ደብዳቤ ግልባጩ አፈፃፀሙ ለሚመለከተው ነጋዴ መስጠት አለበት ። ፩ . ማንኛውም አስተዳደራዊ እርምጃ እና ወይም የቅጣት ውሳኔ ላይ ቅሬታ ያለው ሰው ውሳኔው እንዲፈጸም መፈቀዱን ደብዳቤ ደርሶት ካወቀበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ፴ ቀናት ውስጥ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረብ ይችላል ። ፪ ሚኒስትሩ በዚህ አንቀጽ በንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) ከተወ ሰነው የይግባኝ ጊዜ በፊት የማንኛውንም ውሳኔ አፈፃፀም መጀመር አይችልም ። የጽሕፈት ቤቱ ተግባራት ፩ . ጽሕፈት ቤቱ የሚከተሉት ተግባራት ይኖሩታል ። ሀ ) በኮሚሽኑ የወጡትን መመሪያዎች በሥራ ላይ ያውላል ፣ ለ ) የአስተዳደር እና ወይም የቅጣት ውሳኔዎች ያስፈ ሐ ) የኮሚሽኑን ቃለ ጉባዔዎች ፣ ሪፖርቶች ፣ ውሳኔ ዎችና ሌሎች ሰነዶች ይይዛል ፣ መ ) የዚህን አዋጅ አፈፃፀም በተመለከተ የሕዝቡን ንቃተ ሕሊና ለማሳደግ የሚረዱ የተለያዩ መድረኮች ያዘጋጃል ። • በጽሕፈት ቤቱ አማካኝነት የሚከናወኑ ሌሎች ዝርዝር ተግባራት በኮሚሽኑ ይወሰናሉ ። ፲፱ የሥነ ሥርዓት ደንቦችና መመሪያዎች ፩ ኮሚሽኑ ሥልጣንና ተግባሩን በተገቢ ሁኔታ ለመፈጸም የሚያስችሉትን የሥነ - ሥርዓት ደንቦችና መመሪያዎች ያዘጋጃል ። ፪ ደንቦቹና መመሪያዎቹ በኮሚሽኑ አባላት ሁለት ሦስተኛ ክፍል አራት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ፳ የዕቃዎችን ዋጋ ስለማመልከት ማንኛውም ነጋዴ እንደአስፈላጊነቱ የንግድ ዕቃዎቹንና የአገልግሎቶቹን የዋጋ ዝርዝር በንግድ ቤቱ በግልጽ ሥፍራ በሚታይ ቦታ ማመልከት ወይም በንግድ ዕቃዎቹ ላይ መለጠፍ አለበት ። የዕቃው ወይም የአገልግሎቱ ዋጋ ቀረጥ ፣ ታክስ ወይም ሌላ ሕጋዊ ክፍያ ያካተተ ይሆናል ። ፳፩ ስለንግድ ዕቃዎች መግለጫ ማንኛውም ነጋዴ በሚሸጣቸው የንግድ ዕቃዎች ላይ እንደአስፈላጊነቱ መግለጫ መለጠፍ ወይም በተለየ ወረቀት ላይ ጽፎ ለገዢው መስጠት አለበት ። በንግድ ዕቃዎች ላይ የሚደረግ መግለጫ እንደአግባቡ የሚከተሉትን ዝርዝሮች የሚያመለክት መሆን ኣለበት፡ ሀ ) ዕቃዎቹ የተሠሩበት ወይም የመጡበትን አገር፡ ለ ) የዕቃዎቹን ክብደት ፣ መጠን እና ብዛት ፣ ሐ ) የዕቃዎቹን ጥራት ፣ መ ) ዕቃዎቹ ከምን እንደተመረቱ የሚያሳይ ዝርዝር ፣ ሠ ) ዕቃዎቹን የቴክኒክ ገዝርዝሮች ፣ የአሠራር ወይም የአጠቃቀም ዘዴ ፣ ገጽ ፪ሺ፩፻፵፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፵፱ ሚያዝያ ፩ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም ረ ) በዕቃዎቹ አጠቃቀም ወቅት ሊወሰዱ የሚገባቸውን የደኅንነት ጥንቃቄዎች ፣ ሰ ) ነጋዴው ስለዕቃው አገልግሎት ለገዢው የሚሰጠውን ዋስትና ፣ ሸ ) የኅብረተሰቡን ጥቅም ለመጠበቅ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ሚኒስቴሩ አግባብ ካለው ሌላ መሥሪያ ቤት ጋር በመመካከር በሕዝብ ማስታወቂያ የሚያወጣቸውን ሌሎች ዝርዝሮች ። ፫ በታሸገ ዕቃ ላይ የሚደረግ መግለጫ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፪ ) ከተገለጸው በተጨማሪ የሚከተሉትን ዝርዝሮች ማመልከት አለበት ። ሀ ) የዕቃው የተጣራ ክብደት ፣ ለ ) የፋብሪካው ወይም የአሻጊው ስምና አድራሻ ፣ ሐ ) ዕቃው አገልግሎት መስጠት የሚያበቃበትን ጊዜ ፣ እና መ ) ዕቃው የተመረተበትን ቀን ። ፳፪ የመሠረታዊ ንግድ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ዋጋ የመወሰን አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ሚኒስቴሩ የዋጋ ቁጥጥር ሊደረግባቸው የሚገቡ መሠረታዊ የንግድ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ላይ ያደረገውን ጥናት ለሚኒስትሮች ምክር ቤት አቅርቦ በማስ ፈቀድ ዝርዝራቸውንና ዋጋዎቻቸውን በሕዝብ ማስታወቂያ ሊያወጣ ይችላል ። ፳፫ ስለመሠረታዊ የንግድ ዕቃዎች ሥርጭት አግባብ ያለው ባለሥልጣን ከሚመለከታቸው ሌሎች መሥሪያቤቶች ጋር በመመካከር ዝርዝራቸውንና ዋጋዎ ቻቸው በሕዝብ ማስታወቂያ የተገለጹት መሠረታዊ የንግድ ዕቃዎች እና አገልግሎቶች ስለሚሠራጩበት ፣ ስለሚሸጡ በትና ከቦታ ቦታ ለሚዘዋወሩበት ሁኔታ ለመወሰንና እንደአስ ፈላጊነቱም ዕቃዎቹ ባለቁ ጊዜ እንዲተኩ ነጋዴውን ለማዘዝ ይችላል ። ፳፬ ደረሰኞችን ስለመስጠትና ስለመያዝ ፩ . ማንኛውም ነጋዴ ለሸጠው የንግድ ዕቃ ወይም አገል ግሎት ደረሰኝ የመስጠት ግዴታ አለበት ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) መሠረት ነጋዴው ለሸጣቸው የንግድ ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች የሰጣ ቸውን የደረሰኝ ቀሪዎች ወይም ለገዛቸው የንግድ ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶች የተቀበላቸውን ደረሰኞች ለአምስት ፭ ዓመት ላላነሰ ጊዜ መያዝ አለበት ። ፳፭ አስተዳደራዊ እርምጃ ኮሚሽኑ የዚህን አዋጅ ድንጋጌዎች ወይም አዋጁን ለማስ ፈጸም የወጡትን ደንቦች ፣ የሕዝብ ማስታወቂያዎች ወይም መመሪያዎች በተላለፈማንኛውም ሰው ላይ ቀጥሎ የተመለከ ቱትን ወይም ሌሎች አግባብነት ያላቸውን አስተዳደራዊ እርምጃዎች ለመውሰድ ይችላል ። ፩ አቤቱታ የቀረበበትን ድርጊት እንዲታገድ ፣ እንዲስተ ካከል ወይም ጨርሶ እንዲቋረጥ ማድረግ ፣ የንግድ ፈቃዱን ማገድ ወይም መሰረዝ ፣ ፫ የተጎጂውን የመወዳደር አቅም በነበረበት ለመመለስ የሚያስችል ተገቢ እርምጃ መውሰድ ፣ የዋጋ ቁጥጥር የሚደረግባቸው ዕቃዎች በሆኑ ጊዜ ዕቃዎቹ እንዲያዙና እንዲሸጡ በማድረግ ከሽያጩ ከተገኘው ገቢ ላይ ለሽያጩ ሂደት የወጣው ወጪ ተቀናሽ ሆኖ ቀሪው ለባለቤቱ እንዲመለስ ማድረግ ። ሆኖም ባለቤቱ ወለድ ወይም ሌሎች ክፍያዎችን መጠየቅ አይችልም ። ሚቃረን ማንኛውም ዓይነት ሕግ ገጽ ፪ሺ፩፻፷፱ ቁጥር ፵፱ ሚያዝያ ፱ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓም ፳፭ ቅጣት በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፳፭ መሠረት የሚወሰደው አስተዳደራዊ እርምጃ እንደተጠበቀ ሆኖ ኮሚሽኑየዚህን አዋጅ ድንጋጌዎች ወይም አዋጁን ለማስፈፀም የወጡትን ደንቦች የሕዝብ ማስታ ወቂያዎች ወይም መመሪያዎች በተላለፈ ማንኛውም ሰው ላይ ቀጥሎ የተመለከቱትን ቅጣቶች ሊወስን ይችላል ። በአማራጭ የአጥፊውን ጠቅላላ ንብረት ዋጋእስከ አስር በመቶ ወይም የአጥፊውን ዓመታዊ ጠቅላላ የሽያጭ ገቢ እስከ አስራ አምስት በመቶ ሊደርስ በሚችል የገንዘብ ፪ • በተከለከለው ማናቸውም ተግባር ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የማንኛውም ግለሰብ ተባባሪነት መኖር ከተረጋገጠ ጥፋት ባደረገው ሰው ላይ ከብር ፭ሺ ብር ( አምስት ሺህ ብር እስከ ፲ሺ ( ሃምሳ ሺህ ብር ) ሊደርስ በሚችል የገንዘብ መቀጫ ። ፳፯ ስለመቀጫ አወሳሰን የመቀጫውን ልክ ለመወሰን ኮሚሽኑ የተፈፀመውን ጥፋት ክብደት ፣ የደረሰውን ጉዳት የአጥፊውን የገበያ ተሳትፎ ፣ በድርጊቱ ጉዳት የደረሰበትን ገበያ መጠን እና የኣጥፊውን የገንዘብ አቋም ግምት ውስጥ ማስገባት አለበት ። ፳፰ የሕዝብ ማስታወቂያ ስለማውጣት አግባብ ያለው ባለሥልጣን ይህን አዋጅ ለማስፈጸም የሚያስ ፈልጉ የሕዝብ ማስታወቂያዎችን ሊያወጣ ይችላል ። . ፳፱ • ደንብ የማውጣት ሥልጣን እንደ ጉዳዩ አግባብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ወይም የክልል መስተዳድር ምክር ቤቶች ይህን አዋጅ ለማስፈጸም ደንብ ሊያወጡ ይችላሉ ። የተሻሩ ሕጐች የዚህን አዋጅ ድንጋጌዎች ወይም የተለመደ አሠራር ተፈጻሚነት አይኖርውም ። ፴፩ አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ ይህ አዋጅ ከሚያዝያ ፱ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓ.ም. ይሆናል ። አዲስ አበባ ሚያዝያ ፱ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም : ግርማ ወልደጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅትታተመ

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?