የሰበር መ / ቁ . 15410
ጥቅምት 1 ቀን 1998 ዓ.ም.
ዳኞች፡- 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
2. ኣቶ ፍስሐ ወርቅነህ
3. ወ / ሮ ስንዱ ዓለሙ
4. አቶ አሰግድ ጋሻው
5. ወ / ሮ ደስታ ገብሩ
አመልካች፡- ኣቶ ተሾመ ጅፋር
መልስ ሰጭ፡- የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን
ስለሥራ ክርክር
የሥራ ክርክር ችሎቶች
ስልጣን - የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ
ስልጣን፡- የአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁ . 42/85
አንቀጽ 147
አመልካች
የደመወዝ
ክፍያ ይፈጸመልኝ በማለት
ለአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ክስ ሲያቀርብም ቦርዱ ጉዳዩ
የሰጠውን
የፌዴራል
ከፍተኛ ፍ / ቤት ደመወዝ
አስመልክቶ የተሰጠ ውሣኔ የለም በማለት ሽሮ የደመወዝ ጭማሪውን
ጉዳይ የማየት ሥልጣን የቦርዱ ነው ከሚል እምነት በመነሳት ጉዳዩን
አይቶ እንዲወስን ለቦርዱ ሲመልስለት ቦርዱ በበኩሉ ጉዳዩን የማየት
ስልጣን የለኝም በማለት ወሰነ ፡፡ ከቦርዱ ውሣኔ ይግባኝ ለፌዴራል
ከፍተኛ ፍ / ቤት ቢቀርብም ፍ / ቤቱ በጉዳዩ ፍርድ የሰጠሁበት በመሆኑ
እንደገና ላየው የምችልበት ሥርዓት የለም በማለት ውድቅ ስላደረገው
የቀረበ አቤቱታ ፡፡
ው ሣ
የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤትና የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ
ቦርድ የሰጡት ውሣኔ ፀንቷል ፡፡
1. የአሰሪ አጠቃላይ የደመወዝ ጭማሪ አወሳሰን ሥርዓት ሕገ
ወጥ ነው በሚል የሚቀርብን ክስ የማየት ሥልጣን የአሰሪና
ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ነው ፡፡
2. የግል ጥቅምን መሠረት አድርጎ የሚቀርብን የደመወዝ
ጭማሪ ክሱ የማየት ስልጣን የሥራ ክርክር ችሎት ነው ::
ጥቅምት 1 ቀን 1998 ዓ.ም.
የመ.ቁ. 15410
ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
አቶ ፍስሐ ወርቅነህ
ወ / ሮ ስንዱ ዓለሙ
አቶ አሰግድ ጋሻው
ወ / ሮ ደስታ ገብሩ
አመልካች፡- አቶ ተሾመ ጅፋር
ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን - ግርማ ማርቆስ
ፍ ር ድ
በዚህ መዝገብ
መዝገብ የተያዘው የአመልካች እና የተጠሪ ክርክር
የደመወዝ ጭማሪ ጥያቄን የሚመለከት ነው ፡፡ አመልካች
የተጠቀሰውን ክፍያ ይክፈለኝ ሲል ከኣሰሪ እና ሠራተኛ ቦርድ ዘንድ ክስ
ይመሰርታል ፡፡ ቦርዱም በሁለቱ መካከል በነበረ ክርክር አስቀድሞ
የተሰጠ ፍርድ እንደነበር ጠቁሞ ይህም ጥያቄ አብሮ ፍርድ እንዳገኘ
የሚቆጠር ነውና በአፈፃፀም እንጂ በክስ '
በማለት ይወስናል ፡፡
ከዚህ ውሣኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት
ደግሞ የደመወዝ ጭማሪን አስመልክቶ የተሰጠ ፍርድ ስላሌለ ጥያቄው
ሰክስ እንጂ በአፈፃፀም ሊጠየቅ አይገባም በማለት የቦርዱን ውሣኔ
ሳይቀበለው ቀርቷል ፡፡ እንደዚሁም ቦርዱ የደመወዝ ጭማሪውን ክርክር
አይቶ ውሣኔ ይሰጥበት ዘንድ ጉዳዩን መልሶለታል ፡፡ ጉዳዩን ወደ ቦርድ
የመለሰውም ይህን ክርክር የመዳኘት ስልጣን ያለው ቦርድ እንጂ ፍ / ቤት
አይደለም በሚል እምነት መሆኑን በውሣኔው አመላክቷል ፡፡
በመቀጠል ጥያቄው በቀጥታ ክስ አይነት ለአሰሪ እና ሠራተኛ
ጉዳይ ወሣኝ ቦርድ ቀርቦለታል ፡፡ ቦርዱም ግራ ቀኙን ከአከራከረ በኋላ
ጉዳዩን ለመዳኘት ስልጣን የለኝም ሲል መዝገቡን ዘግቶታል ፡፡ የፌዴራል
ከፍተኛ ፍ / ቤት ደግሞ አስቀድሜ ፍርድ የሰጠሁበት ጉዳይ ስለሆነ
ደግሜ ላየው የምችልበት ሥርዓት የለም በማለት በአሁን አመልካች
የቀረበለትን ይግባኝ ውድቅ አድርጎታል ፡፡
ይህም ችሎት በግራ ቀኙ የቀረበለትን ክርክር መርምሯል ፡፡
ምላሽ ሊያገኝ የሚገባው የጉዳዩ ጭብጥም ቦርድ ይህን የደመወዝ
ጭማሪ ክርክር ለመዳኘት ሥልጣን አለው ? ወይስ የለውም ? የሚለው
መሆኑን ተገንዝቧል ፡፡
ከመዝገቡ መረዳት እንደሚቻለው የአመልካች የደመወዝ ጭማሪ
ይገባኛል ክርክር ተጠሪው በዚህ ረገድ የወሰደው አጠቃላይ እርምጃ
የሠራተኞች መብትና ጥቅም
የሚጎዳ ነው የሚል ይዘት ያለበት
አይደለም ፡፡ አሊያም የተጠሪው የደመወዝ ጭማሪ አወሳሰን ሕገ ወጥ
ነውና ሊስተካከል ይገባዋል በሚል አይነት የቀረበ አይደለም ፡፡ ይልቁንም
የግል ጥቅምን ወይም መብትን ከማስከበር አኳያ የቀረበ
መሆኑን በግልጽ መረዳት የሚቻል ነው ፡፡ ይህም ይህ ችሎት በመ.ቁ.
18180 ለግል እና ለወል የሥራ ክርክር አይነቶች ከሰጠው ትርጉም
አኳያ ሲታይ የግል እንጂ የወል
የሥራ ክርክር የሚሰኝ አይደለም ፡፡
ጉዳዩን የመዳኘት ሥልጣንም የፍ / ቤት እንጂ የአሰሪ እና ሠራተኛ ጉዳይ
ወሣኝ ቦርድ አይሆንም ፡፡
ስለሆነም ቦርዱ ጉዳዩን ለመዳኘት ሥልጣን የለኝም የሚል ውሣኔ መስጠቱ የሚነቀፍ አይደለም ፡፡ በተጨማሪም የፌዴራል ከፍተኛ
ፍ / ቤት ጉዳዩን ወደ ቦርድ ሲመልሰው ክርክሩን የመዳኘት ሥልጣን
ያለው ቦርድ ነው በሚል እምነት እንጂ ይህን ነጥብ በጭብጥነት ይዞ
ፍርድ ያልሰጠበት መሆኑን ከውሣኔው መገንዘብ ስለሚቻል ቦርዱ
የሥልጣኑን ጥያቄ በጭብጥነት ይዞ ፍርድ መስጠቱ ጉዳዩን እንዲዳኝ
ከመለሰለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት ፍርድ ጋር አይጣጣምም ወይም
ይቃረናል ሊያሰኘው የሚችል አይሆንም ፡፡ እንዲሁም ለሁለተኛ ጊዜ
ይግባኝ የቀረበለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት ጉዳዩን እንደገና እንዳይ
የሚፈቅድልኝ ሥርዓት የለም ሲል የሰጠው ምክንያት የሕግ መሠረት
ሆኖ ባይታይም ይግባኙን ውድቅ በማድረጉ ግን የፈፀመው
መሠረታዊ የሆነ የሕግ ሥህተት የለም ፡፡
ው ሣ ኔ
የአሰሪ እና ሠራተኛ ጉዳይ ወሣኝ ቦርድ ሰመቁ .14 / 01 / 93
የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት ደግሞ ሰመ ቁ . 21501 የሰጡት ውሣኔ
ፀንቷል ፡፡
You must login to view the entire document.