በስም በአመልካች መ / ቤት ያላግባብ የተሠናበቱ በመሆኑ
የሰበር መዝ / ቁ 19850
ዳኞች፡- 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
2. አቶ ፍስሐ ወርቅነህ 3. አቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ 4. አቶ ጌታቸው ምህረቱ
5. ወ / ት ሂሩት መለሠ አመልካች፡- የደብረብርሃን ከተማ አገልግሎት ጽ / ቤት ተጠሪ፡- አቶ መኰንን አሠፋ
የግራ ቀኙ የቃል ክርክር የተሠማ ሲሆን ፍ / ቤቱም ከዚህ የሚተለውን ፍርድ ሠጥቷል ፡፡
ፍ ር ድ
አቤቱታው የቀረበው ተጠሪ
የ 3 ወር ደመወዝ ኪሣራ እንዲከፈላቸው በመወሠኑ ነው ፡፡
ተጠሪ ሥራ አስኪያጅ ሆነው ከሚሠሩበት ከአመልካች መ / ቤት በመሠናበታቸው
ወደ ሥራ ለመመለስ በደብረ ብርሃን ወረዳ ፍ / ቤት ክስ መስርተው ጉዳዩን ለማየት
ፍ / ቤቱ ሥልጣን የለውም በማለት የወሠነ ሲሆን ይግባኝ የቀረበለት ለሠሜን ሸዋ
መስተዳድር ዞን ከፍተኛ ፍ / ቤት ግን የክልሉን ማዘጋጃ ቤት ለማቋቋም በወጣው አዋጅ
ቁጥር 91/96 መሠረት የማዘጋጃ ቤት ሠራተኞች ቅሬታቸውን ለማቅረብ የሚችሉት
መስተዳድር
በሚያወጣው
እንደሆነ
ቢያመለክትም ይህ ደንብ ባለመውጣቱ የመንግስት ሠራተኛ አዋጅ ሆነ የአሠሪና
ፈይራሩ ጨቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ልዩ
25 ነፃ
የተጠሪ ክርክር ግብት የአመልካች
መ / ቤት የመንግስት መ f ዴት “ ሌ en ያያታ
ጦ / ቤት መሆኑን ፣
ሠራተኛ አዋጅ በዚህ ጉዳይ ተፈፃሚነት የሌላቸው በመሆኑ ጉዳዩ መታየት ያለበት
በፍ / ሕጉ በመደበኛ ፍ / ቤት ነው በማለት የተጠሪ ስንብት ህገ ወጥ በመሆኑ በፍ / ህ / ቁ .
2573 እና 2583 መሠረት የ 3 ወር ደመወዝ ይከፈላቸው በማለት ወስኗል ፡፡
የአሁኑ የሠበር አቤቱታ የቀረበውም ይህ ውሣኔ የሕግ ስህተት አለው በማለት
ሲሆን ተጠሪ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ሥራ አስኪያጅ ሆነው የተሾሙ
በመሆኑ ከሹመታቸው የመነሣታቸው ጉዳይ በፍ / ሕጉ መሠረት የሚዳኝ ነው ወይስ
አይደለም የሚለውን ነጥብ ለመመርመር ተጠሪን በማስቀረብ የግራ ቀኙን ክርክር
ሠምቷል ፡፡
ተጠሪ በደብረ ብርሃን ከተማ አገልግሎት ጽ / ቤት ሥራ አስኪያጅ ሆነው
እንዲያገለግሉ በክልሉ መንግስት የተሾሙ መሆኑን በቃል ክርክር ወቅት አምነዋል ፡፡
ጉዳያቸው በፍ / ሕጉ
አለበት በማለት ነው ፡፡ ነገር ግን የደብረ ብርሃን አገልግሎት
ጽ / ቤት የመንግስት ግብር በመሠብሠብ ፣ መሬት ለሕዝብ በመስጠት እና የመሣሠሉትን
የከተማው አስተዳደር ሥራ የሚሠራ
ተጠሪነቱም ለከተማው
አስተዳደር መሆኑን በቃል ክርክር ጊዜ ተጠሪ ገልፀዋል ፡፡ እንግዲህ የአመልካች መ / ቤት
ከሚያከናውነው ተግባር አኳያ የመንግሥት የሥራ አስፈፃሚ መ / ቤት መሆኑን መረዳት
ይቻላል ፡፡ በአጠቃላይ ተጠሪ በሥራ አስፈፃሚ መ / ቤት ለማስተዳደር በክልሉ መንግስት
የተሾሙ ሥራ አስኪያጅ መሆናቸውን ፍ / ቤቱ ተረድቷል ፡፡ የመንግስት ሹመኞች
ከመንግስት ጋር ያላቸው የሥራ ግንኙነት ደግሞ በፍትሐብሔር ሕጉ የማይዳኝ መሆኑ
ከፍ / ህ / ቁ . 2513 / 1 / መገንዘብ ይቻላል ፡፡ በመሆኑም የሰ / ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ / ቤት
የመንግስት ተሿሚ የሆኑትን የተጠሪን ጉዳይ በፍ / ሕጉ መሠረት በመዳኘት ውሣኔ
መስጠቱ የሕግ ስህተት መሆኑን ተረድተናል ፡፡
ፌዴራል ጠቅላይ ይቅ
ትክክል ግልባጭ
-s ] ን ናሪ
ው ሣ ኔ
1 / ተጠሪ በመንግስት የተሾሙ ባለሥልጣን በመሆናቸው ጉዳያቸው በፍ / ብሔር ሕጉ
ሊዳኝ አይገባም ፡፡
2 / የሰ / ሸዋ ዞን መስተዳድር ዞን ከፍተኛ ፍ / ቤት በመ / ቁ . 5004 በ 18 / 3 / 94 እና የክልሉ
ጠቅላይ ፍ /
ቤት በመ / ቁ .134 / 97 በ 6 / 7 / 97 በሠጡት ውሣኔ ተሽሯል ፡፡
3 / ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ ይቻቻሉ ፡፡
የማይነበብ የሦስት ዳኞች ፊርማ አለበት ፡፡
ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ግልባጭ
3 ሉ / 144