×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 20070

      Sorry, pritning is not allowed

የሰበር መ / ቁ 20070
ግንቦት 04 ቀን 1998 ዓ.ም
ዳኞች፡- 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
ዓብዱልቃድር መሐመድ
ጌታቸው ምህረቱ
መስፍን እቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሠ
አመልካች የጉጉማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤ / ክርስትያን ሠበካ ጉባዔ
ተጠሪ መምሬ አንዳርጌ አበጀ
ፍ ር ድ
በዚህ ጉዳይ ለሰበር ችሎት የቀረበው ክርክር የኃይማኖት ወይም የመንፈሣዊ
አገልግሉት የሚሰጡ ሰራተኞች ከኃይማኖት ድርጅቱ ጋር ያላቸው የስራ ግንኙነት በአሰሪና
ሰራተኛ አዋጅ የሚሸፈን መሆን አለመሆኑን የሚመለከት ነው ።
መልስ ሰጪ በአመልካች ቤ / ክርስትያን መንፈሣዊ አገልግሎት የሚሰጡ ሲሆኑ
በአዋሣ ዙሪያ ወረዳ ፍ / ቤት ባቀረቡት ክስ ቤ / ክርስትያንዋ ያላግባብ ከስራ ስላሰናበተቻው
ውዝፍ ደሞዝ ተከፍሏቸው ወደ ስራቸው እንዲመለሱ ጠይቀዋል ።
ፍ / ቤቱም የቀረበለትን ጉዳይ በአዋጅ ቁጥር 42/85 መሠረት መርምሮ ተጠሪ
ውዝፍ ደሞዝ ተከፍሏቸው ወደ ስራ እንዲመለሱ ወስኗል ፡፡
የደቡብ ብ / ሕ / ክ / መ.ጠቅላይ ፍ / ቤት ሰበር ችሉት ከላይ የተመለከተውን የሕግ
ነጥብ ሣይመረምር አልፎታል ፡፡
አመልካች በዚህ ችሎት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታም ተመርምሮ ጉዳዩ ለሰበር ችሎት
እንዲቀርብ በተሰጠው ትእዛዝ መሠረት መ / ሰጪ ቀርበው መልስ ሰጥተዋል ፡፡
ይህ ችሉትም የኃይማኖት ወይም የመንፈሣዊ አገልግሎት የሚሰጡ ሰራተኞች
ከኃይማኖት ድርጅት ጋር ያላቸው የስራ ግንኙነት በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ይሸፈናል ? ወይስ
ፈዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ገልባጭ
ውሣኔና የደ / ብ / ብ / ክ / መ.ጠቅላይ ፍ / ቤት ሰበር ችሎት በመ / ቁ 65o , ' አይሸፈንም ? የሚለውን የሕግ ነጥብ መሠረት በማድረግ አቤቱታ የቀረበበትን ውጭ መርምሯል ፡፡
ይህ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 18419 ግንቦት 4 ቀን 1998 በሰጠው ውሣ አግባብነት ያላቸውን የሕጉን ድንጋጌዎች በመተርጉም አንድ የኃይማኖት አገልግሎት የሚሰጥ ሰራተኛ ከኃይማኖት ድርጅቱ ጋር ያለው የስራ ግንኙነት በአሰሪ እና ሰራተኛ አዋጅ የሚሸፈን አለመሆኑ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል ፡፡
በመሆኑም በዚህ ጉዳይ አዋሣ ዙሪያ ወረዳ ፍ / ቤት መልስ ሰጪ ያቀረቡትን ጥያቄ በአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ የሚሸፈን አይደለም በማለት ውድቅ ሊያደርገው ሲገባ ጉዳዩን በዚህ ሕግ መሠረት አይቶ መወሰኑ የሕግ ስህተት አለበት ።
ው ሣ ኔ 1. የአዋሳ ዙሪያ ወረዳ ፍ / ቤት በመ.ቁ
በህዳር 13 ቀን 1995 ዓ.ም የሰጠው
በየካቲት
06 ቀን 1997 ዓ
ዓም የተሰጠው ውሣኔ ተሽሯል ፡፡ የአዳማ ዞን ከፍተኛ ፍ / ቤት
መጋቢት 20/1996 የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል ።
2. ወጪና ኪራሣ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ ።
3. መዝገቡ ተዘግቷል ። ይመለስ ፡፡
ፈደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ልባት
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
ተ.ወ ] ፊርማ
ቀን < ///

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?