×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 18940

      Sorry, pritning is not allowed

ያለአግባብ ከሥራ ቸው
የሰ / መ / ቁ 18940
ግንቦት 4/1998
ዳኞች፡- 1. አቶ መንበረፀሓይ ታደሰ
ዓብዱልቃድር መሐመድ
ጌታቸው ምህረቱ
መስፍን እቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሠ
አመልካች፡- የኢት / ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን
ተጠሪ ፦ ወ / ሮ ኃይማኖት ገ / መድህን
ተጠሪ ለቀረበው የሠበር አቤቱታ መልስ አልሰጥም በማለታቸው መዝገቡን
መርምረን ተከታዩን ውጭ ሰጥተናል ፡፡
ፍ ር ድ
ተጠሪ በፌ / መጀመሪያ ደረጃ
ፍ / ቤት በመሠረቱት ክስ አመልካች
ደሞዝ ተከፍሏቸው ወደስራቸው
እንዲመለሱ ጠይቀዋል ፡፡ አመልካችም ተጠሪ ለተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ ሠራተኛ ናቸው
በማለት የተከራከረ ቢሆንም ፍ / ቤቱ ግን የአመልካችን ክርክር ባለመቀበል ተጠሪ የ 3 ወራት
ደሞዝ ተከፍሏቸው ወደ ስራቸው እንዲመለሱ ወስኗል ፡፡ ጉዳዩ በይግባኝ የቀረበለት
የፌ / ከፍተኛ ፍ / ቤትም ይግባኙን ባለመቀበል መዝገቡን ዘግቶታል ።
የአሁኑም የሠበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውጭ ላይ ሲሆን ተጠሪ በወቅቱ
በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት የጥበቃ ሃይሉን ለማጠናከር ለተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ
ሠራተኛ በመሆናቸው
የሥር ፍ / ቤት ውሣኔ ሊሻርልን ይገባል በማለት ጠይቀዋል ፡፡
ተጠሪም ለቀረበው የሠበር አቤቱታ መልስ እንዲሰጡ ተጠርተው ቀርበው መልስ መስ
ጠት እንደማይፈልጉ ገልፀዋል ።
ፊያፈራል ጠቅላይ ፍርድ ሊቅ
ትክክል ግልባጭ
279 - s
የተደረገ መሆኑን .
ይህ ችሉትም ተጠሪ ለተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ ሠራተኛ መሆን አለመሆናቸውን
ከአ / ቁ .42 / 85 አንቀፅ 9 እና 10 አኳያ እንደሚከተለው መርምሯል ፡፡
አንድ የስራ ውል የሚቆይበትን ጊዜ በተመለከተ አጠቃላይ መርሁ በአዋጅ ቁጥር
42/85 አንቀጽ 9 ሥር ተቀምጧል ። በዚህም መሠረት በማንኛውም የሥራ ውል ጊዜ
በአንድ አሠራር ሠራተኛ መሃከል የተደረገ የሥራ ውል ላልተወሰነ ጊዜ እንደተደረገ የሥራ
ውል ሊቆጠር እንደሚገባ ሕጉ ግምት ይወስዳል ፡፡ ነገር ግን ይህን የሕግ ግምት ፈራሽ
ለማድረግና ሠራተኛው ለተወሰነ ጊዜ የተቀጠረ መሆኑን ለማሣየት በአዋጁ አንቀፅ 10 ሥር
የተመለከቱት ሁኔታዎች
መኖራቸው
ሊረጋገጥ ይገባል ፡፡ በመሆኑም አንድ ሠራተኛ
ላልተወሰነ ጊዜ የተቀጠርኩ ነኝ ሲል ለማስረዳት የሥራ ውል መኖሩን ብቻ ማስረዳት
ሲጠበቅበት አሠሪው ደግሞ ለተወሰነ ጊዜ የተቀጠረ መሆኑን ለማሣየት የሥራ ውሉ
የተደረገው በአንቀፅ 10 ሥር ከተመለከቱት ምክንያቶች ውስጥ በአንዱ ወይም በሌላኛው
ማስረዳት መቻል አለበት ፡፡ በተያዘው ጉዳይ አመልካች ተጠሪን የቀጠረው
የነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት የጥበቃ ኃይሉን በማጠናከር በማስፈለጉ
እንደነበረና አሁን ግን የፀጥታው ሁኔታ ሲሻሻልና ከተጠሪም ጋር የተደረገው የሥራ ውል
ጊዜው በማለቱ ተጠሪን ማሠናበቱን ገልጿል ። ተጠሪም በዚህ ችሎት ቀርበው አመልካች
ያቀረበውን አቤቱታ አላስተባበሉም ፡፡ በመሆኑም ተጠሪ የተቀጠሩት በወቅቱ በነበረው
የፀጥታ ችግር ምክንያት የስራውን ጫና ለማቅለል በመሆኑና ይህም በአዋጁ አንቀፅ 10 ሥር
ከተመለከቱትና ለተወሰነ ጊዜ የሚደረጉ የሥራ ውሉች ከተቀመጠው መስፈርት አንዱ
በመሆኑ የተጠሪ የሥራ ውል ሲጠናቀቅና የነበረው የፀጥታ ችግርም በመሻሻሉ አመልካች
የተጠሪን የሥራ ውል ማቋረጡ በአዋጁ አንቀፅ 24 ( 1 ) መሠረት ሕጋዊ ነው :: ከዚህም
በተጨማሪ በአ / ቁ 42/85 መሠረት ውዝፍ ደሞዝ ሊ
ገባ መሆኑ ከአዋጁ
አንቀፀ 54 ( 1 ) መገንዘብ ይቻላል ፡፡
በአጠቃላይ የሥር ፍ / ቤቶች ተጠሪ ወደ ስራቸው እንዲመለሱና የ 3 ወር ውዝፍ
ደሞዝ እንዲከፈላቸው የተሰጠው ውጭ የሕግ ሥህተት የተፈፀመበት ነው ፡፡
2-9 ና S
ው ሣ ኔ
1. የፌ / መ / ደረጃ ፍ / ቤት በመ / ቁ .09962 ህዳር 8/1997 ዓ.ም እንዲሁም የፌ /
ከፍተኛ ፍ / ቤት በመ / ቁ .35179 ታህሣሥ 26 ቀን 1997 ዓ.ም የሰጡት ውጫዎች
ተሽረዋል ።
2. ተጠሪ ለተወሰነ ጊዜ የተቀጠሩ ሰራተኛ በመሆናቸው የሥራ ውሉ የተደረገበት ጊዜ
በማብቃቱ መሠናበታቸው ሕጋዊ ነው ።
3. ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ ።
ፈዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
አከከል ልባች
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?