በህገ ወጥ መንገድ መሆኑ ተረጋግጦ
የሰበር መ / ቁ 24246
ቀን 28/9/98
ዳኞች፡- 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
2. አቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ
3. አቶ ጌታቸው ምህረቱ
4. አቶ መስፍን ዕቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሠ
አመልካች፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነፈጅ ቀርቧል ፡፡
መልስ ሰጭ፡- አቶ ዓለሙ ሻሎ ከጠበቃው ጋር ቀርቧል ፡፡
ፍ ር ድ
በዚህ ጉዳይ ለሰበር ችሎት የቀረበው ክርክር አንድ ሠራተኛ ከሥራ የተሰናበተው
ወደ ሥራ እንዲመለስ በአዋጁ ቁ . 42/85
መሠረት ሲወሰን ከሥራ ከተሰናበተበት ጊዜ ጀምሮ ወደ ሥራ እንዲመለስ ውሣኔ
እስከተሰጠበትና ሥራ ላልተሰራበት ጊዜ ያልተከፈለው ደመወዝ ሊከፈለው ይገባል ?
ወይስ አይገባም ? የሚለውን ነጥብ የሚመለከት ነው ።
ጉዳዩን በመጀመሪያ ያየው የሥር ፍ / ቤት መ /
ሰጭ ከሥራ የተሰናበተው በሕግ
ወጥ መንገድ በመሆኑ ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎ ወደ ሥራው እንዲመለስ የወሰነ ሲሆን
ውሣኔውን ይግባኝ ሰሚው ፍ / ቤትም አጽንቶታል ፡፡ አመልካች ይህን ውሣኔ በመቃወም
ለዚህ ችሎት ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ጉዳዩ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ
በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት መ /
ሰጭ መልሱን አቅርቧል ፡፡
ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትከል ልሳጭ
ችሎቱም አንድ ሠራተኛ ከሥራ የተሰናበተው በሕገ ወጥ መንገድ መሆኑ ተረጋግጦ ወደ ሥራ እንዲመለስ በአዋጅ ቁ . 42/85 መሠረት ሲወሰን ከሥራ ከተሰናበተበት ጊዜ ጀምሮ ወደ ሥራ እንዲመለስ ውሣኔ እስከተሰጠበትና ሥራ ላልተሰራበት ጊዜ ያልተከፈለው ደመወዝ ሊከፈለው ይገባል ? ወይስ አይገባም ? የሚለውን ነጥብ መሠረት በማድረግ አቤቱታ የቀረበበትን ውሣኔ አግባብነት ካለው ሕግ ጋር አገናዝቦ መርምሮታል ፡፡
ይህ ችሎት በመቁ . 17189 አግባብነት ያላቸውን የአዋጅ ቁ . 42 / 85 ን ድንጋጌዎች በመተርጎም ሕጉ ሥራ ላልተሰራበት ጊዜ ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፈል የሚፈቅድ አይደለም የሚል ውሣኔ ሰጥቷል ፡፡ በመሆኑም በዚህ ጉዳይ ለመ / ሰጭ ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፈል የተሰጠው ውሣኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል ፡፡
ው ሣ ኔ
ይህ ችሎት መ / ሰጭ
የፌ / ከፍተኛ ፍ / ቤት በመቁ . 38664 የካቲት 30 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው
ውሣኔ ተሻሽሏል ፡፡
ግራ ቀኙ በዚህ ችሎት ያወጡትን ወጭ የየራሳቸውን ይቻሉ ፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል ፡፡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።
ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ግልባጭ
You must login to view the entire document.