×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 15493

      Sorry, pritning is not allowed

• መንግሥት ጠቅላይ ፍ / ቤት ሰበር ችሎት አመልካች የፌዴራ a m ቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት
የመ / ቁ . 15493 ዳኞች : - አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
አቶ ፍስሐ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ ወ / ሮ ስንዱ አለሙ
ወ / ሪት ሂሩት መለሰ አመልካች : - አቶ ጳውሎስ ሩምቾ መልስ ሰጭ፡
ጫልቱ መርዳሳ ውል የግዴታዎች መቅረት ስለ ይርጋ - የውልን ጉዳይ ስለሚመለከት ማስረጃ ገንዘቡ እንደተከፈለ የሚያስቆጥሩ የህሊና ግምቶች - የፍትሐ ብሔር ህግ ቁጥሮች 1845 ፣ 2024
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ እንዲከፈለው የጠየቀው የጥብቅና አበል በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 2024 ( ለ ) መሠረት እንደተከፈለ ስለሚቆጠር የሥር ተከሣሾች በአመልካች የተጠየቀውን ገንዘብ ሊከፍሉ አይገባም በማለት ሌሎች ፍ / ቤቶች የሰጡትን ውሳኔ በመሻሩ
የቀረበ አቤቱታ
ውሳኔ፡ - የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ / ቤት ሰበር ችሎት የሰጠው ውሳኔ ጸንቷል ::
1. የሕሊና ግምት ድንጋጌዎች ከይርጋ ደንብ ድንጋጌዎች የተለዩ ናቸው ::
2. በፍ / ብ / ሕ / ቁ 2024 በተደነገገው የሕግ ግምት ተጠቃሚ ያልሆነ ወገን ( ተከሣሽ
ክፍያው በከፊል መክፈሉ ግምቱን በፍ / ብ / ሕ / ቁ 2025 ( 1 ) መሠረት ቀሪ አያደርግም ::
ኣቦር አቤቱታ የቀረበው የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ የተጠየቀውን ገንዘብ ሊከፍሉ አይገባሃ
ሐምሌ 29 ቀን 1997 ዓ.ም
የመዝገብ ቁ .15493 ዳኞች መንበረፀሐይ ታደሰ
ፍሥሐ ወርቅነህ አብዱልቃድር መሐመድ ስንዱ ዓለሙ
ሂሩት መለሰ አመልካች አቶ ጳውሎስ ሩምቾ መልስ ሰጪ ወ / ሮ ጫልቱ መርዳሳ
በዚህ መዝገብ ፍ / ቤት ሰበር ችሎት አመልካች እንዲከፈለው የጠየቀው የጥብቅና አበል በፍትሀብሄር ሕግ ቁጥር 2024 ( ለ ) መሠረት እንደተከፈለ ስለሚቆጠር የሥር ተከሣሾች በአመልካች
በማለት ሌሎች ፍ / ቤት የሰጡትን ውሣኔ በመሻሩ
አመልካች ባቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻነት ጉዳዩ ለሰበር ችሎት ቀርቦ እንዲታይ በመወሰኑ መልስ ሰጪም በጉዳዩ ላይ ያላትን የጽሁፍ መልስ አቅርባለች ::
አመልካች የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ / ቤት ሰበር ችሎት መሠረታዊ የሕግ ስህተት ፈጽሟል የሚለው ( 1 ) ከጥብቅና አበሉ ውስጥ የመጨረሻ ክፍያ የተፈፀመው ሰኔ 1990 ዓ.ም በመሆኑ ክስ እስከቀረበበት ታህሣሥ 18 ቀን 1992 ዓ.ም በፍትሐብሄር ሕግ ቁ .2024 ( ለ ) የሚጠቅሰው የሁለት ዓመት የጊዜ ገደብ አላለፈም ( 2 ) መልስ ሰጪዎች ከፊል ዕዳውን በመፈፀማቸው ዕዳውን እንዳመኑ ስለሚቆጠር በ 2024 የተቀመጠው የህግ ግምት በ 2025 ( 1 ) መሠረት ቀሪ ሆኖአል ፡፡ ( 3 ) የጥብቅና ውሉ በጽሁፍ የተደረገ በመሆኑ የይርጋ ጊዜው መታሰብ ያለበት በ 1 ዐ ዓመት እንጂ በ 2 ዐ 24 መሠረት በሁለት ዓመት አይደለም የሚሉትንና ሌሎችንም ተመሳሳይ ክርክሮች በማቅረብ ነው :: መልስ ሰጪዋ ጥቅምት 2 ቀን 1997 የተጻፈ ዝርዝር መልስ በማቅረብ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ / ቤት ሰበር ችሎት የሰጠው ውሣኔ እንዲፀናላት ጠይቃለች ::
አመልካች በመልስ ሰጪ ላይ ጥር 1 ቀን 1992 ዓ.ም ክስ የመሰረተው ጥቅምት 7 ቀን 1988 ዓ.ም በአመልካችና በመልስ ሰጪ መካከል የተመሰረተውን የጥብቅና አገልግሎት ውል መሠረት በማድረግ ነው :: የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ / ቤት ሰበር ችሎት ተዋዋዮቹ በውላቸው ላይ ለጥብቅና ውል ምክንያት የሆነው ቤት ለመልስ ሰጪ በገባ በሁለት ወር የጥብቅና ክፍያ መጠናቀቅ እንዳለበት ስለሚገልጽና ቤቱ ሕዳር 1988 መልስ ሰጪ እጅ የገባ በመሆኑ ክስ የቀረበበት የገንዘብ መጠን ክስ በቀረበበት ጊዜ ከሁለት ዓመት በላይ ስለሆነው በ 2024 መሠረት እንደተከፈለ ይቆጠራል ብሏል ::
ለዚህ ለሰበር ለቀረበው ጉዳይ ምክንያት የሆነው ዕዳ መከፈል ከነበረበት ሁለት ዓመት በላይ እንደሆነው ቤት ተረጋግጦአል :: ለጉዳዩ አግባብነት ያለው የፍ / ብ / ሕ / ቁ . 2024 ሲሆን በዚህ ድንጋጌ መሠረት በሁለት ዓመት ውስጥ ያልተከፈለ ዕዳ እንደተከፈለ እንደሚቆጠር በዚህ ሰበር ችሎት በመቁ .17068 ትርጉም ተሰጥቶበታል :: የጥብቅና አበል ክፍያን የሚመለከተው የፍ / ብ / ሕ / ቁ .2024 ( ለ ) ም አንዱ የድንጋጌው አካል በመሆኑ በተጠቀሰው ትርጓሜ ውስጥ የሚካተት ነው :: የጥብቅና ክፍያው በሁለት ዓመት ውስጥ ያልተጠየቀ በመሆኑም ለድንጋጌው በተሰጠው ትርጓሜ መሠረት እንደተከፈለ የሚቆጠር ነው :: ስለዚህ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ /
ቤት በዚህ ረገድ የፈፀመው የህግ ስህተት የለም :: አመልካች የሕግ ግምትና የይርጋ ህግን በማመሳሰል ጉዳዩ በፍ.ብ.ሕ.ቁ .1845 እንዲታይለት ቢጠይቅም የተያዘው ጉዳይ የክፍያ ግምት እንጂ የይርጋ ጉዳይ ባለመሆኑ ቅሬታው ተቀባይነት የለውም :: የክፍያ ግምት ውሉ በጽሁፍ የተደረገ ሲሆን ተፈጻሚ አይሆንም የሚል ህግ ባለመኖሩ አመልካች ውላችን በጽሁፍ ስለሰፈረ በ 2 ዐ 24 ( ለ ) ተፈጻሚነት ሊሆንብኝ አይገባም ያለው ተቀባይነት የለውም :: መልስ ሰጪ በከፊል የጥብቅና አበል መክፈላቸውም ቢሆን አሁን ክስ የቀረበበትን ቀሪውን የጥብቅና አበል ማመናቸውን አያመለክትም ፡፡ በመሆኑም የሕጉን ግምት ተፈጻሚነት በ 2025 ( 1 ) መሠረት ቀሪ ለማድረግ በቂ ምክንያት አይደለም :: በመሆኑም የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ / ቤት ክስ የቀረበበት ብር 71,000 ( ሰባ አንድ ሺህ ) ሁለት ዓመት ካለፈው በኋላ የተጠየቀ ስለሆነ በፍ.ብ.ሕ.ቁ .2 ዐ 24 ( ለ ) መሠረት እንደተከፈለ ይቆጠራል በማለት የሥር ፍ /
ቤቶችን ውሣኔ ሕጉን በትክክል ማድረጉን እንጂ የህግ ስህተት መፈፀሙን አያመለክትም ::
( 1 ) የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ / ቤት ሰበር ችሎት በመዝገብ ቁ.ዐዐ 253 በ 2 ዐ / 7 / 96 የሰጠው
ውሣኔ ፀንቷል :: ( 2 ) ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻሉ ፡፡

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?