×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 20678

      Sorry, pritning is not allowed

የሰ / መ / ቁ 20678
ቀን ሰኔ 12 ቀን 1998 ዓ.ም
ዳኛች ፦ 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
2. አቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ
3. አቶ ተኔ ጌታነህ
4. አቶ መስፍን ዕቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሰ
አመልካች ፦ ወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ነ / ፈጅ ቀርቧል ።
መልስ ሰጭ፡ 1. የአቶ ከበደ ደሳለኝ ወራሾች ቀርባለች ፡፡
2. አቶ ኤርከኖ አቤ ቀርቧል ፡፡
አቶ ማማሬ በጅጋ ቀርቧል ፡፡
ፍ ር ድ
በዚህ ጉዳይ ለሰበር ችሎት የቀረበው ክርክር አንድ ሰራተኛ ከሥራ የተሰናበተው
በሕገወጥ መንገድ መሆኑ ተረጋግጦ
ሥራ እንዲመለስ በአዋጅ ቁ 42/85 መሠረት
ሲወሰን ከሥራ ከተሰናበተበት ጊዜ ጀምሮ ወደ ሥራ እንዲመለስ ውሣ እስከተሰጠበትና
ሥራ ላልተሰራበት ጊዜ ያልተከፈለው ደመወዝ ሊከፈለው ይገባል ? ወይስ አይገባም ?
የሚለውን ነጥብ የሚመለከት ነው ።
ጉዳዩን በመጀመሪያ ያየው የሥር ፍ / ቤት መ / ሰጭ ከሥራ የተሰናበተው በሕገወጥ
መንገድ በመሆኑ
ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎ ወደ ሥራው እንዲመለስ የወሰነ ሲሆን
ውጫውን ይግባኝ ሰሚው ፍ / ቤትም አጽንቶታል ፡፡ አመልካች ይህን ውሣ በመቃወም
ለዚህ ችሎት ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ጉዳዩ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ
በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት መ / ሰጭ መልሱን አቅርቧል ፡፡
ችሎቱም አንድ ሰራተኛ ከሥራ የተሰናበተው በሕገወጥ መንገድ መሆኑ ተረጋግጦ
ወደ ሥራ እንዲመለስ በአዋጅ ቁ 42/85 መሠረት ሲወሰን ከሥራ ከተሰናበተበት ጊዜ
ፌዴራል በኃላይ ፍርድ i ኔት
ት i ል ግን
ጀምሮ ወደ ሥራ እንዲመለስ ውሣኔ እስከተሰጠበትና ሥራ ላልተሰራበት ጊዜ ያልተከፈለው
ደመወዝ ሊከፈለው ይገባል ? ወይስ አይገባም ? የሚለውን ነጥብ መሠረት በማድረግ አቤቱታ
የቀረበበትን ውጭ አግባብነት ካለው ሕግ ጋር አገናዝቦ መርምሮታል ፡፡
ይህ ችሉት በመ / ቁ 17189 አግባብነት ያላቸውን የአዋጅ ቁ .42 / 85 ን ድንጋጌዎች
በመተርጎም ሕጉ ሥራ ላልተሰራበት ጊዜ ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፈል የሚፈቅድ አይደለም
የሚል ውጭ ሰጥቷል ። በመሆኑም በዚህ ጉዳይ ለመ / ሰጭ ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፈል
የተሰጠው ውሣኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል ፡፡
ው ሣ ኔ
ይህ ችሎት መ / ሰጭ ውዝፍ ደመወዙ ሊከፈል አይገባም
በማለት ወስኖ
የኦሮሚያ ጠ / ፍ / ቤት ሰበር ችሎት በመ / ቁ 06360 ሰኔ 27 ቀን 1997 ዓ.ም
የሰጠው ውሣ ተሻሽሏል ፡፡
ግራ ቀኙ በዚህ ችሎት ያወጡትን ወጭ የየራሳቸውን ይቻሉ ፡፡
ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ፡፡
ፌዴራል ጠቅላይ ፍረድ ቤት
ትክክል ግልባጭ

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?