መልስ ለፊቴ በዚህ ጉዳይ ለሰበር ችሎ 8
የሰበር መ / ቁ . 21956
ሚያዝያ 4/1998 ዓ.ም. ዳኞች፡- 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
2. አቶ አብዱልቃድር መሐመድ 3. አቶ ጌታቸው ምህረቱ 4. አቶ መስፍን ዕቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሰ አመልካች፡- አብክመ ገጠር መንገዶች ባለስልጣን የጎጃ / ገ / መ / ጥ / ጽ / ቤት
እነ ብርሃኑ አንቴ / 33 ሰዎች /
ፍ ር ድ የቀረበው ክርክር ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠርኩ / ን /
ይወስንልኝ / ን / የሚል ዳኝነት በመጠየቅ የሚቀርብ ክስ የክስ ምክንያት / Cause of
action / አለው ? ወይስ የለውም ? ጉዳዩንስ ለመዳኘት የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ
ቦርድ ስልጣን አለው ? ወይስ የለውም ? የሚለውን የህግ ነጥብ የሚመለከት ነው ፡፡
የም / አማራ አሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ተጠሪዎች ላልተወሰነ ጊዜ
እንደተቀጠርኩ / ን / ይወሰንልኝ / ን / በማለት ያቀረቡትን ክስ በመቀበል አከራክሮ ውሣኔ
ሰጥቷል ፡፡ በውሣኔው ላይ ይግባኝ የቀረበለት ይግባኝ
ፍ / ቤትም ከላይ
የተመለከተውን የህግ ነጥብ ሳይመረመር አልፎታል ፡፡
አመልካች በዚህ ችሎት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ጉዳዩ ለሰበር
ችሎት እንዲቀርብ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ተጠሪዎች ቀርበው መልስ ሰጥተዋል ፡፡
ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ግልባጭ
[ 0 ዓ \ x
ችሎቱም ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠርኩ / ን / ይወስንልኝ / ን / የሚል ዳኝነት
በመጠየቅ የሚቀርብ ክስ የክስ ምክንያት / cause of action / አለው ? ወይስ የለውም ?
የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሣኝ ቦርድ ጉዳዩን አይቶ ለመወሰን ስልጣን አለው ? ወይስ
የለውም ? የሚለውን የህግ ነጥብ መሰረት በማድረግ አቤቱታ የቀረበበትን ውሣኔ
መርምሯል ፡፡
ይህ ችሎት በመቁ . 16273 ጥቅምት 22 ቀን 1998 በሰጠው ውሣኔ አግባብነት
ያላቸውን የህጉን ድንጋጌዎች በመተርጎም አንድ ሠራተኛ ከውሉና ከአሰሪና ሠራተኛ
ሕጉ አንፃር ሊያገኘው የሚገባና የቀረበት ጥቅም ካለ የቀረበት ጥቅም እንዲሰጠው
መጠየቅ / ክስ ማቅረብ / የሚችል ሲሆን ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠርኩ ይወሰንልኝ
በሚል ብቻ የሚቀርብን ክስ የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድም ሆነ የሥራ ክርክር
ችሎት ተቀብለው
ሊያዩ የሚችሉበት የሕግ ምክንያት የለም በማለት የሕግ ትርጉም
ሰጥቷል ፡፡
በሌላም በኩል ቢሆን በመ / ቁ . 18180 አግባብነት ያላቸው የአሰሪና ሠራተኛ
አዋጅ ድንጋጌዎችን በመተርጎም የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ የማየት ስልጣን
የተሰጠው የወል የሥራ ጉዳዮችን ነው ፡፡ አንድ የሥራ ክርክር የወል የሥራ ክርክር ነው
የሚባለው ጉዳዩ የጋራ በሆነ የሠራተኞች መብትና ጥቅም ላይ አሉታዊም ሆነ
አዎንታዊ ውጤት የሚያስከትል ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው ፡፡ በአንፃሩ አንድ የሥራ ክርክር
የወል ሳይሆን የግል የሥራ ክርክር
ጉዳይ ነው የሚባለው የክርክሩ ውጤት
በተከራከረው ሠራተኛ ሠራተኞች / ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሲገኝ ነው በማለት የህግ
ትርጉም ሰጥቷል ፡፡
በዚህ ጉዳይም የም / አማራ አሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ተጠሪ ዎች
ያቀረቡት ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠርኩ / ን / ይወስንልኝ / ን / በማለት ያቀረቡትን ክስ የክስ
ተን } 6 51 &
ምክንያት የሌለው ከመሆኑም በአሻገር
የጋራ በሆነ የሠራተኞች መብትና ጥቅም ላይ
አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ውጤት የሚያስከትል ባለመሆኑ የወል የሥራ ክርክር
አይደለም ። በመሆኑም በሁለቱም ምክንያቶች የቀረበውን ክስ ውድቅ ማድረግ ሲገባው
ጉዳዩን አከራክሮ በመወሰኑ መሠረታዊ የህግ ስህተት ፈጽሟል ፡፡
ው ሣ ኔ
- የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ በመቁ .
በግንቦት 29 ቀን 1997
ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ እና የአማራ ጠቅላይ ፍ / ቤት በመ / ቁ . 06938 በጥቅምት
22 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል ፡፡
- ግራ ቀኙ በዚህ ችሎት ያወጡትን ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻሉ ፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል ፧ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ፡፡
ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ኣክል ግልባጭ
You must login to view the entire document.