×
ያስሱ ምርቶች ስለ እኛ ይግቡ / ይመዝገቡ አግኙን English
African Law Archive
Logo
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፲፩/፲፱፻፲፭ የከፍተኛ ትምህርት የወጪ መጋራት የሚነስ ትሮች ምክር ቤት ደንብ

      ይቅርታ፣ ማተም አይፈቀድም።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ዘጠነኛ ዓመት ቁጥር ፳፭ አዲስ አበባ - ነሐሴ ፴ ቀን ፲፱፻፶፭ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፲፩ / ፲፱፻፶፭ ዓም የከፍተኛ ትምህርት የወጪ መጋራት የሚኒስትሮች ምክር ቤት | Higer Education Cost - sharing Council of Minsiters የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፲፩ ፲፱፻፲፭ ስለ የከፍተኛ ትምህርት የወጪ መጋራት በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣ ደንብ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራ | This regulation is issued by the Council of Ministers pursuant ሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬ / ፲፱፻፷፯ አንቀጽ ፭ እና በከፍተኛ | Executive Organs of the Federal Democratic Republic of ትምህርት አዋጅ ቁጥር ፫፻፶፩ / ፲፱፻፲፭ መሠረት የሚከተለውን | Ethiopia Proclamation No. 4/1995 and the Hihger Education ደንብ አውጥቷል ። ፩ . አጭር ርዕስ ይህ ደንብ “ የከፍተኛ ትምህርት የወጪ መጋራት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፲፩ / ፲፱፻፲፭ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል ። ፪ . ትርጓሜ በዚህ ደንብ ውስጥ ፩ . “ ሚኒስቴር ” እና “ ሚኒስትር ” ማለት እንደቅደም ተከተ ላቸው የትምህርት ሚኒስቴር እና የትምህርት ሚኒስትር ፪ . “ ተቋም ” ማለት በመንግሥት አካል ሥር የሚተዳደር ከሁለተኛ ደረጃ በላይ ትምህርት የሚሰጥበትና በማን ኛውም ክልል ወይም በአዲስ አበባና ድሬዳዋ ውስጥ የሚገኝሆኖ ከፌዴራል መንግሥት በሚመደብለት በጀት የሚተዳደር ተቋም ነው ። ያንዱ ዋጋ ነጋሪት ጋዜጣ ፖሣቁ : ፰ሺ፩ ገጽ ፪ሺ፫፻፴፮ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፭ ነሐሴ ፴ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ.ም ፫ “ አሠሪ ” ማለት የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተመራቂን ቀጥሮ የሚያሠራ ማንኛውም የመንግሥት መሥሪያ ቤት ፣ የግል ወይም መንግሥታዊ ያልሆነ ተቋምና ዓለም አቀፍ ወይም አህጉር አቀፍ ድርጅት ሲሆን በሙያው በግሉ ሥራ የተሠማራ ሰውን ይጨምራል ። ፬ . “ ሰው ” ማለት የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው ። ፭ “ ተጠቃሚ ” ማለት ማንኛውም በመንግሥት ተቋም ለመማር እና የሚፈለግበትን ወጪ ለመክፈል ከተቋሙ ጋር ውለታገብቶ የከፍተኛ ትምህርት ወይም ሥልጠና የሚከታተል ተማሪ ነው ። ፮ “ ወጪ መጋራት ” ማለት የከፍተኛ ትምህርት ተጠቃሚ እና መንግሥት ለትምህርትና ሌሎች አገልግ ሎቶች የሚያወጣውን ወጪየሚጋሩበት ሥርዓት ነው ። – “ ከምረቃ በኋላ ከገቢ ተከፋይ ” ማለት ማንኛውም ተጠቃሚ በገባው ውለታመሠረት የሚጋራውን የወጪ መጠን ከወርሃዊ ገቢው በታክስ መልክ እየቀነሰ የሚከ ፍልበት ሥርዓት ነው ። ፫የደንቡ ተፈፃሚነት ይህ ደንብ ከ፲፱፻፲፮ የትምህርት ዘመን ጀምሮ ወደ ተቋማት በሚገቡ አዲስ ተማሪዎች ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ እንዲሁም የሁለተኛ ዓመትና ከዚያ በላይ በሆኑ ነባር ተማሪዎች ላይ ካሉበት ዓመት ጀምሮ ተፈፃሚ ይሆናል ። ፬ • የተጠቃሚው ድርሻና ኣፈጸጸም ፩ . መንግሥት ለምግብና ለመኝታ የሚያወጣውን ወጪ ሙሉ በሙሉና ፣ ለትምህርት ከሚወጣው ወጪ ለመነሻ ከ፲፭ ፐርሰንት ያላነሰ ተሰልቶ ተጠቃሚዎች እንዲጋሩ ይደረጋል ። ይህም ድርሻ በየተቋሙና በየመርሐ ግብሩ በሚወጣው ወጪ ላይ ተመስርቶ በትምህርት ዘመኑ መጀመሪያ ላይ በቅድሚያ ለተጠቃሚው መገለጽ አለበት ። በዚህ አንቀጽ በንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተገለጸውን መጠን ለመክፈል እያንዳንዱ ተጠቃሚ በትምህርት ዘመኑ መጀመሪያ ላይ ከተቋሙ ጋር የጽሑፍ ውል በማድረግ ፣ ትምህርቱን እንዲከታተል ይደረጋል ። ይህ የውለታ ሠነድ በሕግ ፊት የፀና ይሆናል ። ፫ . ተጠቃሚው ትምህርቱን ካቋረጠ ወይም ካጠናቀቀ መክፈል የሚገባውን መጠን የሚያሳይ መረጃ በተቋሙ ይሰጠዋል ። ይህ መረጃ የተጠቃሚውን ሙሉ ስም ፣ አድራሻ ፣ ፎቶና ሌሎች አስፈላጊ ጉዳዮችን የያዘ ይሆናል ። ለተማሪው ትምህርትና ሥልጠና የሚወጣው ወጪ መጠን ቢያንስ በየሦስት ዓመቱ የሚከለስ ይሆናል ፣ ለዚሁም ሚኒስቴሩ መመሪያ ያወጣል ። ፭ ) በታሳቢ ተምሮ ከምረቃ በኋላ ከገቢው ተከፋይ በሆነ መልክ እየተቀነሰ በገንዘብ ወይም በአገልግሎት የሚከፍል ተጠቃሚ በዜግነት ኢትዮጵያዊ መሆን ይኖር በታል ። ፭ ማበረታቻዎች በየዓመቱ የሚፈለግባቸውን መጠን ሙሉ በሙሉ | 5. Incentives በቅድሚያ በግል ወይም በድርጅቶች ድጋፍ ለሚከፍሉ ተጠቃሚዎች እስከ ፭ ፐርሰንት የሚደርስ ቅናሽ እንዲ ያገኙ ይደረጋል ፣ ፪ • ከተመረቁ በኋላ የሚፈልግባቸውን መጠን ሙሉ በሙሉ በተመረቁ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከፍለው ለሚጨርሱ ተጠቃሚዎች እስከ ፫ ፐርሰንት የሚደርስ ቅናሽ ይደረጋል ። ገጽ ፪ሺ፫፻፴፯ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፭ ነሐሴ ፴ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም ፫ ሚኒስቴሩ በየጊዜው በሚያወጣው መመሪያ መሠረት በተመረጡ መስኮች ለመሠልጠን ፈቃደኛ የሆነ ተማሪ ከምረቃ በኋላ መንግሥት በሚመድበው ቦታ ሁሉ ቢያንስ ለሠለጠነበት ዓመት ሦስት እጥፍ ጊዜ ለማገ ልገል ውል እየፈረመ እንዲማርና ከተማረ በኋላ በገባው ግዴታ መሠረት አገልግሎት እንዲሰጥ ይደረጋል ። ውል አፍርሰው የአገልግሎት ግዴታቸውን ያልተወጡ ተጠቃሚዎችትምህርቱየፈጀውን ወጪ በጊዜው ሥራ ላይ ባለው የድርሻ ክፍፍል ( % ) የሚጠበቅባቸውን ከነወለዱ ቢበዛ በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ አጠናቀው እንዲከፍሉ ይገደዳሉ ። ፮ : የወጪ ድርሻ አከፋፈል ፩ . ተጠቃሚው ከምረቃ በኋላ ሥራ ከጀመረ ጊዜ ጀምሮ | 6 Mode of Repayment of Shared Costs በስድስት ወር ውስጥ ወይም ከምረቃ በኋላ ከአንድ ዓመት በኋላ የሚፈለግበትን ክፍያ ተቀጣሪ ከሆነ ከወር ገቢው በየወሩ ቢያንስ ፲ ፐርሰንት ከገቢ ተከፋይ በሆነ መልክእየቀነሰ ወይም በሙያው በግሉ የተሠማራ ከሆነ ከዓመት ገቢው በዓመቱ የሚፈለግበት መጠን ተሠልቶ መክፈል አለበት ። ተጠቃሚው የሚፈለግበት ጠቅላላ መጠን የአገል ግሎት ክፍያ ወይም ወለድ የሚከፈልበት ሆኖ ውለታ በተገባበት ወቅት በሀገሪቱ የሚሠራበት የተቀማጭ ወለድ መጠን ይሆናል ። ፫ . ተጠቃሚው ያለበትን የክፍያ ግዴታ እንደ ትምህርት መርሃ ግብሩ ርዝመትና ዓይነት ከ፲፭ ዓመት ባልበለጠ ጊዜ ማጠናቀቅ ይኖርበታል ። ፬ . ተጠቃሚው ትምህርቱን ሳይጨርስ በማንኛውም ምክንያት ቢያቋርጥም እስካቋረጠበት ጊዜ የሚፈለግ በትን ክፍያ መክፈል ይኖርበታል ። ሆኖም ትምህርቱን ያቋረጠው በሀገራዊ ጥሪዎችና ተልዕኮዎች ከሆነ ክፍያው መሠረዝ ይኖርበታል ። ፭ ተጠቃሚው ተቀጥሮ የሚሠራ ሲሆን ክፍያው በአሠሪው አማካኝነት በየወሩ ከደመወዙ እየተቀነሰ ለመንግሥት ገቢ ይደረጋል ። ሆኖም ይህ ተቀናሽ በማናቸውም ጊዜ ተጠቃሚው በዚህ ደንብ በአንቀጽ ፰ ( ፩ ) ( ሐ ) መሠረት ከፍ ካላደረገው በስተቀር ከገቢ ተከፋይ ተቀናሹ መጠን ከተጠቃሚው የወር ደመወዝ ፩ / ፫ኛ ሊበልጥ አይገባም ። ፮ ተጠቃሚው በውጭ ቅጥር ወይም በግል ሥራምክንያት በውጭ ሀገር የሚኖር ከሆነ ፣ ክፍያው የፌዴራል ሀገር ውስጥ ገቢዎች ባለሥልጣን በሚያወጣው የአፈጻጸም መመሪያ መሠረት ይፈጸማል ። ፯ . አንድ በታሳቢ የተማረ ተጠቃሚየሚፈለግበትን ክፍያ ሳያጠናቅቅ ከስድስት ወር በላይ ለሆነ ጊዜ ለመቆየት ወደ ውጭ አገር መሄድ ቢፈልግ ላልተከፈለው መጠን ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል ። ፯ የአሠሪዎች ግዴታ ፩ . ይህ ደንብ ተግባራዊ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ የከፍተኛ | 7 . Obligations of Employers ትምህርት የተከታተለን ሰው የሚቀጠር ማንኛውም አሠሪ የሚከተሉትን ግዴታዎች ይኖሩበታል ። ሀ ) ተቀጣሪው ከተማረበት ተቋም የተሰጠውን የሚፈ ለግበትን ክፍያ መጠን የሚገልጽ መረጃና በየወሩ ከደመወዙ እየተቀነሰ ገቢ ሊደረግ የሚገባውን የገንዘብ መጠን የሚገልጽ የተሰጠማስረጃ እንዲያ ቀርብ የመጠየቅ ፣ ለ ) የተቀጣሪዎችን ዝርዝር በ፫ ወር ጊዜ ውስጥ ለፌዴራል ሀገር ውስጥ ገቢዎች ባለሥልጣን በጽሑፍ የማሳወቅ ፣ በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር ፪፻፷፮ / ፲፱፻፲፬ ፣ በቀረ በለት መረጃ እና በዚህ ደንብ በአንቀጽ ፰ ( ፩ ) ( ሐ ) መሠረት ከተቀጣሪው ደመወዝ በየወሩ እየቀነሰ የማስተላለፍ ፣ ተጠያቂ ይሆና► y ረት ግዴታውን በፊት በጡረታ ቢገለል ወይም ቢሞ " ር . ገጽ ፪ሺ፫፻፴፰ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፭ ነሐሴ ፴ ቀን ፲፱፻፲፭ ዓም መ ) ተቀጣሪው በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ፩ ( ሀ ) የተጠቀሰውን መረጃ ወይም ከዕዳ ክፍያ ነፃ መሆኑን የሚገልጽ ከፌዴራል ሀገር ውስጥ ገቢዎች ባለሥልጣን የተሰጠ መረጃ ካላቀረበ የተቀጣሪውን የወር ደመወዝ ፩፫ኛ በመያዝ ሁኔታወን የማሳወቅና በፌዴራል ሀገር ውስጥ ገቢዎች ባለሥልጣን በሚያገኘው መግለጫ መሠረት ከሦስት ወር ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ መፍትሔ መስጠት ይኖርበታል ። ፪ ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከቱትን ግዴታዎች ያልተወጣ ማንኛውም አሠሪ ሳይሰበሰብ በቀረው ክፍያ መጠን እና ባልተከፈለባቸው ወራት በገቢ ግብር አዋጅ መሠረት በኃላፊነት ተጠያቂ ይሆናል ። ፰- የተጠቃማው ግዴታ በዚህ ደንብ አንቀጽ ፮ ( ፩ ) የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ ተቀጣሪው በማናቸውም አሠሪ ተቀጥሮ ሲሠራ የሚከ ተለው ግዴታ ይኖርበታል ፦ ሀ ) የሚሠራበትን ሙሉ አድራሻ ፣ እንዲሁም ከዚህ በፊት በሌላ ቦታ ሠርቶ ከሆነ ይህንኑ መረጃ ለአሠሪው በመስጠት በአሠሪው አማካኝነት ለፌዴራል ሀገር ውስጥ ገቢዎች ባለሥልጣን የማሳወቅ ፣ ለ ) የሚፈለግበትን ክፍያ በየወሩ ከምረቃ በኋላ ከገቢ በተከፋይ መልክ ተቀናሽ በማድረግ መክፈል የመጀመር ፣ ሐ ) በዚህ ደንብ አንቀጽ ፬ ( ፪ ) የገባውን የውለታ ሠነድ ለአሠሪውየመስጠትና አሠሪውተገቢውን መጠን በየወሩ እየቀነሰ ለመንግሥት እንዲያስገባ የማድረግ ፣ ይህ መጠን በዚህ ደንብ አንቀጽ ፮ ( ፩ ) ከተገለጸው ማነስ አይችልም ። በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ ( ፩ ) እንዲሁም በዚህ ደንብ አንቀጽ ( ፩ ) የተመለከቱትን ግዴታዎች ያልተወጣ ማንኛውም ተጠቃሚ በገቢ ግብር አዋጅ መሠረት ፬ . ዕዳን ስለመሠረዝ ተጠቃሚው ሳያጓድል ክፍያውን ሲፈጽም ቆይቶ ጠቅላላ ክፍያው ከመጠናቀቁ ቀሪው ብድር ይሠረዛል ። ፲ • የትምህርት ሚኒስቴር ሥልጣንና ኃላፊነት በዚህ ደንብ ሌሎች ኣንቀጾች የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የትምህርት ሚኒስቴር የሚከተለው ሥልጣንና ኃላፊነት ይኖረዋል ። ሀ ) ይህ ደንብ ሥራ ላይ መዋሉን የመከታተልና የማረ ለ ) የከፍተኛ ትምህርት ተቋሞች ከተጠቃሚዎች የሚጠይ ቁትን የክፍያ ተመን የማጽደቅ ፣ ሐ ) ለዚህ ደንብ አፈጸጸም የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን የማውጣት ፣ መ ) የውለታ ሠነዶችን ይዘት የመወሰን ፣ ሠ ) የወጪ መጋራቱ ከገንዘብ በተለየ መልኩ በአገልግሎት የሚፈጸምበትን መስኮችና ዝርዝር መመሪያዎች የማወጣት ፣ ፲፩ . የፌዴራል ሀገር ውስጥ ገቢዎች ባለሥልጣን ሥልጣንና ኃላፊነት በዚህ ደንብ ሌሎች ኣንቀጾች የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ባለሥልጣኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ኃላፊነት ይኖረዋል ። ሀ ) ከእያንዳንዱ ተጠቃሚ የሚፈለገውን መጠንና ወርሀዊ ክፍያውን ለተጠቃሚውና ቀጣሪዎች የማሳወቅ ፣ ለ ) ኣጠቃላይ ክፍያውን የመሰብሰብ ፣ የመከታተልና የመ ቆጣጠር ፣ ገጽ ፪ሺ፫፻፴፱ ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ቁጥር ፳፭ ነሐሴ ፴ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓም . ለዚሁ ተፈጻሚነት አስፈላጊውን ሥርዓትና ድርጅት የመፍጠርና ተግባራዊ የማድረግ ፣ መ ) የሚፈለግበትን ክፍያ ላጠናቀቀ ተጠቃሚ ተገቢ መረጃ ሠርቲፊኬት የመስጠት ፣ ለእያንዳንዱ ተጠቃሚየግብር ክፍያ መለያ ቁጥር የመስጠት ፣ ረ ) በክልሎች ውስጥ ከሚቀጠሩተጠቃሚዎችየሚፈ ለገው ተቀናሽ መጠን ለመንግሥት ገቢ የሚሆን በትን ሁኔታ የማመቻቸት ፣ ፲፪ • የተቋማት ሥልጣንና ኃላፊነት በዚህ ደንብ ሌሎች አንቀጾች የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ተቋማት የሚከተሉት ሥልጣንና ኃላፊነት ይኖራቸዋል ። ሀ ) የሥርዓቱን ተፈጸሚነት የመከታተል ፣ ለ ) በየትምህርት ዘመኑ መጀመሪያ ላይ ተጠቃሚው እንዲጋራ የሚጠበቀውን ወጪ አስልቶ የመግለጽ ፣ ተጠቃሚውን በተመለከተ ተገቢውን መረጃ አደራጅቶ የመያዝ ፣ ሐ ) ከተጠቃሚዎቹ የሚፈለገውን ወጪ አጠናቅሮ ተጠቃሚው ከተቋሙ ሲለቅ አስፈላጊ የመስጠት ። ፲፫ : ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ ይህ ደንብ ከመስከረም ፩ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓ.ም. ጀምሮ የፀና አዲስ አበባ ነሐሴ ፴ ቀን ፲፱፻፶፭ ዓ.ም መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር

ሙሉውን ሰነድ ለማየት መግባት አለብዎ

ለመግባት የኢሜል አድራሻዎን እና የይለፍ ቃልዎን ያስገቡ።
እባክህን ትክክለኛ ኢሜል አስገባ
እባክህ የኢሜል አድራሻህን አስገባ
እባክህ የይለፍ ቃልህን አስገባ
የይለፍ ቃል ቢያንስ 8 ቁምፊዎች መሆን አለበት።
የሚስጥራዊውን ቁጥር ረሳህው?