×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 22462

      Sorry, pritning is not allowed

በዚህ ጉዳያ ቦርድን ስልጣን የሚመለኮ ለኢ
የሰበር መ / ቁ .22462
የካቲት 16 ቀን 1998 ዓ.ም ዳኞች፡- 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
2. አቶ አብዱልቃድር መሐመድ 3. አቶ ጌታቸው ምህረቱ 4. አቶ መስፍን ዕቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሰ አመልካች፡- የአዋሳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ / አ / ማ / ጠበቃው ቀርቧል መልስ ሰጭ፡- አቶ ደሳለው አሊ ቀረበ
ፍ ር ድ ለሰበር ችሎት የቀረበው ክርክር የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ
በመ /
ሰጭዎች በአሰሪና
ጉዳይ ክሱ የቀረበው የተመደብኩበት የስራ
መደብ ደረጃ ይስተካከል በሚል ነው ፡፡ አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ አሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ
ወሳኝ ቦርድ ክሱን ለማየት ስልጣን አለው በማለት የተሰጠ ነው ፡፡ አመልካች ውሳኔውን
በመቃወም ለዚህ ችሎት ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ጉዳዩ ለሰበር ችሎት
እንዲቀርብ በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት መ /
ሰጭ መልሱን አቅርቧል ፡፡
ችሎቱም በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ውሳኝ ቦርድ የስራ ክርክሮች ምን አይነት
ናቸው የሚለውን የህግ ነጥብ መሰረት በማድረግ አቤቱታ የቀረበለትን ውሳኔ አግባብነት
ካለው ህግ ጋር አገናዝቦ መርምሯል ፡፡ ይህ ችሎት በመ / ቁ .18180 አግባብነት ያላቸውን
የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ድንጋጌዎች በመተርጎም የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ
የማየት ስልጣን የተሰጠው የውል የስራ ክርክር ጉዳዮችን ነው ፤ አንድ የስራ ክርክር
ር ፡፡ _ከር
የወል የስራ ክርክር ነው የሚባለው ጉዳዩ የጋራ በሆነ የሰራተኞች መብትና ጥቅም ላይ
አሉታዊም ሆነ አወንታዊ ውጤት የሚያስከትል ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው ፤ በአንፃሩ አንድ
የስራ ክርክር የወል ሳይሆን የግል የስራ ክርክር ጉዳይ ነው የሚባለው የክርክሩ ውጤት
በተከራካሪው ሰራተኛ ሰራተኞች / ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሆኖ ሲገኝ ነው በማለት
የህግ ትርጉም ሰጥቷል ፡፡
መ / ሰጭ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ የተመደብኩበት የስራ መደብ ደረጃ
ይስተካከል በሚል ያቀረበው ክስ የጋራ በሆነ የሰራተኞች መብትና ጥቅም ላይ
አሉታዊም ሆነ አወንታዊ ውጤት የሚያስከትል ባለመሆኑ የወል የስራ ክርክር
አይደለም ፡፡ በመሆኑም ጉዳዩን ለማየት በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ስልጣን
አለው በማለት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል ፡፡
ው ሳ ኔ
የአሰሪና
ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ሃምሌ 8 ቀን 1997 ዓ.ም የሰጠው
ውሳኔና የፌዴራል
ፍርድ ቤት በመ / ቁ 41228 ታህሳስ 19 ቀን
1998 ዓ.ም ውሳኔ ተሽሯል ፡፡
ግራ ቀኙ በዚህ ችሎት ያወጡትን ወጭና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻሉ ፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል ፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመስ ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
12-3 -ዓን

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?