×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 15747

      Sorry, pritning is not allowed

የመ / ቁ 15747
ጥቅምት / 3 ቀን 1999 ዓ / ም
ዳኞች፡- 1. ኒን ና ስ n ይ c
2 ታ - » ያ * : 1
1 ► ን ! ? ? - 1 ፈ ሩ ነ -
አመልካች - ወ / ሮ ዘነበች ደምሴ መልስ ሰጭ - አቶ ልብስነህ ረዳ
ጉዳዩ ለዚህ ችሎት የቀረበዉ በአመልካችና በመልስ ሰጭ መካከል የነበረዉ ጋብቻ ከፈረሰ በኋላ የንብረት ክፍፍሉን በሚመለከለት አመልካች ከመልስ ሰጭ ብር 18,000 ( አስራ ስምንት ሽህ ብር ) ተቀብላ ሌላ ንብረት ላትጠየቅ የፈረመችው ስምምነት ሽማግሌዎች አሳስተዉኝ የፈረምኩት በመሆኑ ልገደድበት አይገባም ፤ የጋራ ንብረታችንን እኩል እንካፈል በማለት አመልካች ያቀረበችዉ ክርክር በቤተሰብ ሽማግሌዎች ፣ በምስራቅ ጎጃም መስተዳድር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንዲሁም በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተቀባይነት በማጣቱ አመልካች ለዚህ ችሎት አቤቱታ በማቅረቧ ነዉ ፡፡ አመልካች ያቀረበችዉ የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ጉዳዩ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ በተሰጠዉ ትዕዛዝ መሰረት ግራ ቀኙ ክርክራችዉን ለችሎቱ በጽሁፍ አቅርበዋል ፡፡
ችሎቱም አመልካች የጋራ ንብረት ክፍፍሉን በሚመለከለት መልስ ሰጭ አመልካች ከመልስ ሰጭ ብር 18,000 ( አስራ ስምንት ሽህ ብር ) ተቀብላ ሌላ ንብረት ላትጠየቅ የፈረመችው ዉል የሚፈርስበት ህጋዊ ምክንያት አለ ? ወይስ የለም ? የሚለዉን የህግ ነጥብ መሰረት በማድረግ ጉዳዩን መርምሯል ፡፡
በህግ አግባብ የተቋቋሙ ዉሎች ባቋቋሟቸዉ ሰዎች ላይ ህግ እንደሆኑ የፍ / ብ / ህ / ቁ 1731 ( 1 ) ይደነግጋል ፡፡ በመሆኑም ዉሎች በህግ በተቀመጡት ሁኔታዎች ካልፈረሰ በቀር በተዋዋዮቹ ላይ አስገዳጅ ናቸዉ ፡፡ በህግ ከተቀመጡት ዉል ከሚፈርስባቸዉ ምክንያቶች አንዱ በፍ / ብ / ህ / ቁ / 1710 ( 2 ) የተመለከተዉ ለአንደኛዉ ተዋዋይ ወገን የበለጠ ጥቅም ለሚሰጥ ዉል የሌላኛዉ ወገን ፈቃድ የተገኘዉ ችግሩን ፧ የመንፈስ ቀላልነቱን ፧ መጃጀቱን ፤ በዕድሜ መግፋቱን ወይም በንግድ ግልጽ የሆነ የልምድ ዕዉቀት የሌለዉ መሆኑን በመደገፍ እንደሆነና በህሊናም ግፍ መስሎ ሲታይ ነዉ ፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሰረት አንድ ዉል ከተዋዋይ ወገኖች ለአንደኛዉ ወገን ከሌላኛዉ ወገን የበለጠ መብት የሚሰጥ ከሆነና የሌላኛዉ ወገን ፈቃድ የተገኘዉ በድንጋጌዉ ከተመለከቱት ሁኔታዎች ቢያንስ በአንዱ ምክንያት ከሆነና ሌላኛዉ ወገን የተጎዳዉ በግፍ ሆኖ ከተገኘ ዉሉ ሊፈርስ ይችላል ፡፡
በዚህ ጉዳይ በአመልካችና በመልስ ሰጭ መካከል ያጋራ ንብረት ክፍፍልን በሚመለከት የተደረገዉ ዉል አመልካች ከመልስ ሰጭ ላይ ብር 18,000 ( አስራ ስምንት ሽህ ብር ) ተቀብላ ሌላ ንብረት ላትጠየቅ የተስማማች መሆኑን ይደነግጋል ። በውሉ መሰረት የጋራ ንብረታቸዉ ምንም ያህል ከፍተኛ ግምት ቢኖረዉ አመልካች መልስ ሰጭ ከሰጣት ብር 18,000 ( አስራ ስምንት ሽህ ብር ) በተጨማሪ ከጋራ ንብረቱ ምንም እንዳትጠይቅ ይከለክላታል ፡፡ አመልካች በአዲስ አበባ ከተማ ብር 500,000 ( አምስት መቶ ሽህ ብር ) የሚገመት የጋራ ሴት አለን በማለት የምትከራከር ሲሆን መልስ ሰጭ በበኩሉ ቤቱን የሰራሁት ከአመልካች ጋር ከተለያየን በኋላ የሰራሁትና የአመልካች አስተዋጽኦ የሌለበት ነዉ ፧ ብር 500,000 ( አምስት መቶ ሽህ ብር ) አያወጣም በማለት ተከራክሯል ፡፡ መልስ ሰጭ ቤቱን ተለያይተን መኖር ከጀመርን በኋላ የሰራሁት ነዉ እንጅ ጋብቻዉ ከፈረሰ በኋላ የሰራሁት ነዉ በማለት አልተከራከረም ፡፡ በጋብቻ . ዉስጥ የተፈራ ንብረት የአንደኛዉ ተጋቢ የግል ንብረት መሆኑ ካልተረጋገጠ በቀር የተጋቢዎች የጋራ ንብረት አንደሆነ ህግ ይደነግጋል ፡፡ ቤቱ ጋብቻዉ ከመፍረሱ በፊት የተሰራ ቢሆንም መልስ ስጭ የግል ንብረቴ እንደሆነ ያቀረበዉ ክርክር የለም ፡፡ ስለሆነም ቤቱ የጋራ ንብረት እነደሆነ ግምት እንዲወሰድ ይደነግጋል ፡፡ ጋብቻዉ በሚፈርስበት ወቅትም የጋራ ንብረታቸዉን በህጉ መሰረት ተጋቢዎቹ እኩል መካፈል ይኖርባቸዋል ፡፡
ከላይ የተጠቀሰዉ ዉል አመልካች ከዚህ የጋራ ቤት ላይ ምንም ጥያቄ እንዳይኖራት ፧ መልስ ሰጭ የቤቱ ብቸኛ ባለመብት በማድረግ ለመልስ ሰጭ የበለጠ ጥቅም የሚሰጥ ነዉ ፡፡ ማንም ሰዉ የመንፈስ ቀላልነት ወይም በሌላ ምክንየት በትክክል ማሰብ የማይችል ሰዉ ካልሆነ በቀር ከጉዳት በቀር ምንም ጥቅም በማያገኝበት ሁኔታ መብቱን አሳልፎ የሚሰጥ ዉል አይፈርምም ተብሎ ይገመታል ፡፡ አመልካች ከላይ የፈረመችዉ ዉል ብር 18,000 ( አስራ ስምንት ሽህ ብር ) ተቀብላ ከፍተኛ ብልጫ ያለዉን የጋራ ንብረት ግማሽ ድርሻዋን ላለመጠየቅ ግዴታ የገባችበት ነዉ ፡፡ ከላይ በተመለከተዉ ምክንያት ይህ ችሎት ዉሉ የተፈረመዉ የአመልካችን የመንፈስ ቀላልነት በመጠቀም እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል ፡፡ በዚህ ሁኔታ በተፈረመ ዉል አመልካች ከፍተኛ ግምት ካለዉ የጋራ ንብረት እንዳትካፈል መደረጉ ግፍ መስሎ የሚታይ ነዉ ፡፡ በመሆኑም ዉሉ በፍ / ብ / ህ / ቁ 1710 ( 2 ) መሰረት ሊፈርስ የሚገባዉ ነዉ ፡፡ የስር ፍርድ ቤቶች ይህን ዉል ተፈጻሚ በማድረግ የሰጡት ዉሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል ፡፡
አመልካችና መልስ ሰጭ ሚያዝያ 1995 ዓ / ም ያደረጉት ዉል በፍ / ብ / ህ / ቁ 1710 ( 2 ) መሰረት እንዲፈርስ ተወስኗል ፡፡ አመልካችና መልስ ሰጭ የጋራ ንብረታቸዉን በህጉ በተመለከተዉ መሰረት እኩል እንዲካፈሉ ተወስኗል ፡፡ የምስራቅ ጎጃም መስተዳድር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፍ / ይ / መ / ቁ 05378/95 ሰኔ 10 ቀን 1995 ዓ / ም የሰጠዉ ብይንና የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፍ / ይ / መ / ቁ 2676 የካቲት 16 ቀን 1996 ዓ / ም የሰጠዉ ትዕዛዝ ተሽረዋል ። አመልካችና መልስ ሰጭ በዚህ ችሎት ያወጡትን ወጭና የደረሰባቻን ኪሳራ
የየራሳቸዉን ይቻሉ ። መገዝገቡ ተዘግቷል ፡፡

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?