የመ / ቁ .19966
ቀን ሚያዚያ 4/1998
ዳኞች፡- 1- አቶ መንበረፀሀይ ታደሰ
2- አቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ
3- አቶ ጌታቸው ምህረቱ
4- አቶ መስፍን አቁበዮናስ
5- ወ / ት ሂሩት መለሠ
አመልካች ፦ አምቦ ማዕድን ውሃ ፋብሪካ
ተጠሪ ፦ እነ ኢቲቻ ቃበታ / 23 ሠዎች /
ፍ ር ድ
በዚህ ጉዳይ ለሰበር ችሎት የቀረበው ክርክር ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠርኩ / ን
ይወስንልኝ / ን የሚል ዳኝነት በመጠየቅ በሚቀርብ ክስ
የክስ ምክንያት / cause of action /
አለው ? ወይስ የለውም ? ጉዳዩንስ ለመዳኘት የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ስልጣን
አለው ? ወይስ የለውም ? የሚለውን የህግ ነጥብ የሚመለከት ነው ።
የአሠሪና
ሠራተኛ ወሣኝ
ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠረኩ / ን
ይወሰንልኝ / ን በማለት የቀረቡትን ክስ በመቀበል አከራክሮ ውሳኔ ሰጥቷል ፡፡ በውሳኔው ላይ
ይግባኝ የቀረበለት ይግባኝ ሰሚው ፍ / ቤትም ከላይ የተመለከተውን የህግ ነጥብ ሳይመረምር
አልፎታል ፡፡
ኣመልካች በዚህ ችሎት ያቀረበው የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ጉዳዩ ለሰበር ችሉት
እንዲቀርብ በተሰጠው ትእዛዝ መሰረት ተጠሪዎች ቀርበው መልስ ሠጥተዋል ፡፡
ችሎቱም ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠርኩ / ን ይወሰንልኝ / ን የሚል ዳኝነት በመጠየቅ
የሚቀርብ ክስ የክስ ምክንያት / cause of action / አለው ? ወይስ የለውም ? የአሰሪና ሰራተኛ
ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ጉዳዩን አይቶ ለመወሰን ስልጣን አለው ? ወይስ የለውም ? የሚለውን
የህግ ነጥብ መሰረት በማድረግ አቤቱታ የቀረበበትን ውሳኔ መርምሯል ፡፡
ይህ ችሉት በመ / ቁ .16273 ጥቅምት 22 ቀን 1998 በሰጠው ውሳኔ አግባብነት
ያላቸውን የህጉን ድንጋጌዎች በመተርጎም አንድ ሰራተኛ ከውሉና ከአሰሪና ሰራተኛ ህጉ
አንፃር ሊያገኘው የሚገባና የቀረበት ጥቅም ካለ የቀረበት እንዲሰጠው መጠየቅ / ክስ
ፌዴራል ( B ቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ግልባጭ
በመሆኑም በሁለቱም ምክንያቶች የቀረበው . ማቅረብ / የሚችል ሲሆን ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠርኩ ይወሰንልኝ በሚል ብቻ የሚቀርብን ክስ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድም ሆነ የስራ ክርክር ችሎት ተቀብለው ሊያዩ የሚችሉበት የህግ ምክንያት የለም በማለት የህግ ትርጉም ሰጥቷል ፡፡
በሌላም በኩል ቢሆን በመ / ቁ 18180 አግባብነት ያላቸው የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ድንጋጌዎችን በመተርጎም የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ የማየት ስልጣን የተሰጠው የወል የስራ ጉዳዮችን ነው አንድ የስራ ክርክር የወል የስራ ክርክር ነው የሚባለው ጉዳዩ የጋራ በሆነ የሰራተኞች መብትና ጥቅም ላይ አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ውጤት የሚያስከትል ሆኖ ሲገኝ ብቻ ነው ፡፡ በአንጻሩ አንድ የስራ ክርክር የወል ሳይሆን የግል የስራ ክርክር ጉዳይ ነው የሚባለው የክርክሩ ውጤት በተከራከረው ሰራተኛ / ሰራተኞች / ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሲገኝ ነው በማለት የህግ ትርጉም ሰጥቷል ።
በዚህም ጉዳይ የም / ኦሮሚያ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሣኝ ቦርድ ተጠሪያዎች ያቀረቡት ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠርኩ / ን ይወሰንልኝ / በማለት ያቀረቡትን ክስ የክስ ምክንያት የሌለው ከመሆኑም በአሻገር የጋራ በሆነ የሰራተኞች መብትና ጥቅም ላይ አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ውጤት የሚያስከትል ባለመሆኑ የወል የስራ ክርክር አይደለም ።
ክስ ውድቅ ማድረግ ሲገባው ጉዳዩን አከራክሮ በመወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ፈጽሟል ፡፡
ው ሳ ኔ
1. የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሣኝ ቦርድ በመ / ቁ ጂ.ቢ.ኤም 9-24 / 1778
በመጋቢት 16 ቀን 1997 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ / ቤት
ፍ / ቤት በመ / ቁ .24769 በሚያዚያ 7 ቀን 1997 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ
ተሽሯል ፡፡
2. ግራ ቀኙ በዚህ ችሎት ያወጡትን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻሉ ፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል ፡፡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
You must login to view the entire document.