×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 14637

      Sorry, pritning is not allowed

የሰ / መ / ቁ 14637
ኀዳር 21/1999 ዓ.ም.
ዳኞች 1. አቶ ከማል በድሪ
2. አቶ ፍስሐ ወርቅነህ
3. አቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ
4. አቶ መስፍን እቁበዮናስ
5. ወ / ት ሒሩት መለሠ
አመልካች ፦ ወ / ሮ እታገ ሁ ግዛው ጠ / ቶሎሣ ወልዴ ቀረቡ ።
ተጠሪዎች ፦ 1. ወ / ሮ አስራት ዮሴፍ ቀረቡ ።
2. ወ / ት ንጋቷ ዮሴፍ ወኪል አስራት ዮሴፍ ቀረቡ ፡፡
3. ወ / ሮ ውዴ ተ / ጊዮርጊስ ቀረቡ ።
ፍ ር ድ
ለዚህ የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው የአሁኑ ተጠሪዎች በፌ / መ / ደረጃ ፍ / ቤት
ያቀረቡት አቤቱታ ነው ::
ተጠሪዎች በመሠረቱት ክስ አውራሻቸውና አቶ ዮሴፍ ጅሉ ባልና ሚስት በነበሩበት
ወቅት ያፈሩትን የጋራ ንብረት የሆነውን ቤት አውራሻቸው ሲሞቱ አቶ ዮሴፍ የራሣቸው
ያልሆነውን ንብረት ጭምር አጠቃለው
ለአመልካች ስለሸጡ የሽያጩ
ይፍረስልን
በማለት ጠይቀዋል ፡፡ ፍ / ቤቱም የተጠሪዎችን ጥያቄ ተቀብሉ ውሉ እንዲፈርስ የወሰነ ሲሆን
ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው የፌ / ከፍተኛ ፍ / ቤትም የይግባኝ ቅሬታውን ሣይቀበለው
ቀርቷል ፡፡
የአሁኑ አቤቱታ የቀረበውም በዚህ ውሣኔ ላይ ሲሆን ይህ ችሎትም ውሉ ሊፈርስ
ይገባል የተባለበትን የሕግ አግባብ ለመመርመር አቤቱታው ለሠበር ችሎት እንዲቀርብ
አድርጓል ፡፡ ግራ
ቀ ም ክርክራቸውን
አቅርበዋል ፡፡ ይህ ችሎትም ጉዳዩን
እንደሚከተለው መርምሯል ፡፡
የሚችለው ውሉ በተደረገ ጊዜ ፈቃዱን ያልሰጠው
ወገን የውሉ ' , ወይም ኢሞራላዊ ሲሆን ወይም ውሉ በሕጉ የተመለከተውን የአፃፃፍ
ተጠሪዎች በሥር ፍ / ቤት በመሠረቱት ክስ የጠየቁት በአቶ ዮሴፍ ጅሎ እና በተጠሪ መሃከል የተደረገው እንዲፈርስ በመሆኑ 3 ኛ ወገን በሌሎች ተዋዋይ ወገኖች የተደረገውን ውል እንዲፈርስ ሊጠይቁ የሚችሉበትን የሕግ መሠረት መመርመሩ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል ። ስለግዴታ መቅረት የሚመለከተው የፍትሐብሔር ሕጉ ውስጥ አንድ ውል ስለሚፈርስበትና ስለሚሠረዝበት ሁኔታ ተደንግጎ እናገኛለን ፡፡ በዚህም መሠረት አንድ ውል የተደረገበት ጉዳይ ወይም ምክንያት ከሕግ ውጪ ወይም ለሕሊና ተቃራኒ ወይም ለውሉ አፃፃፍ የተደነገገውን ፎርም ያልጠበቀ የሆነ እንደሆነ ከተዋዋዮቹ አንዱ ወይም ማንኛውም ጥቅም ያለው እንዲሰረዝ ለመጠየቅ እንደሚችል በፍ / ሕ / ቁ 1808 / 2 / ሥር ተመልክቷል ። በዚህ ድንጋጌ መሠረት ከተዋዋዮቹ በተጨማሪ ሌላ 3 ኛ
መፍረስ ለመጠየቅ የሚችለው ውሉ የተደረገበት ጉዳይ / Object of the contract / ሕገ ወጥ
ፎርም ሣይከተል ሲቀር ነው ። በሌላ በኩል ግን በፈቃድ ጉድለት ወይም በችሎታ ማጣት
የተነሣ ውሉ እንዲፈርስ መጠየቅ
ወይም ችሎታ ያልነበረው ተዋዋይ ወገን ብቻ ለመሆኑ የፍ / ሕ / ቁ 1808 / 1 / ያመለክታል ።
ወደተያዘው ጉዳይ ስንመለስ የሥር ፍ / ቤት ውሉ እንዲፈርስ የወሰነው አቶ ዮሴፍ
የጋራ የሆነውን ንብረት ክፍፍል ሣይደረግበት አጠቃለው መሽጣቸው ውሉን ሕገወጥ
ያደርገዋል በሚል ነው :: ነገር ግን ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ውል የተደረገበት ጉዳይ
ወይም ምክንያት የቤት ሽያጭ ነው :: ይህ ደግሞ ሕገ ወጥ ጉዳይ ነው የሚባል አይደለም
ውሉ የተደረገበት ጉዳይም ሕገወጥ ባለመሆኑ 3 ኛ ወገኖች ውሉ እንዲፈርስ የሚጠይቁበት
ምክንያት አይኖርም ፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በፈቃድ ጉድለት ምክንያት ውሉ እንዲፈርስ መጠየቅ የሚችለው
ይኸው ፈቃዴን አልሠጠሁም ወይም ችሎታ አልነበረኝም የሚለው ተዋዋይ ወገን ብቻ
በመሆኑና ተጠሪዎችም ተዋዋይ ወገኖች ያልነበሩ ወይም ከተዋዋይ ወገኖች አንደኛውን
የሚወክሉ
ወይም የሚተኩ ባለመሆናቸው
ውሉ እንዲፈርስ ለመጠየቅ በሕጉ መብት
አልተሰጣቸውም ። በመሆኑም ፍ / ቤቶች በተጠሪዎች ጥያቄ ውሉ እንዲፈርስ በመወሰናቸው
የሕግ ስህተት ፈጽመዋል ፡፡
ው ሣ ኔ
1 / የፌ / መ / ደረጃ ፍ / ቤት በመ / ቁ 313 በ 05 / 05 / 95 የሰጠው ውሣኔ እና የፌ / ከፍተኛ
ፍ / ቤት በመ / ቁ 18052 በ 16 / 03 / 96 የሰጠው ትዕዛዝ ተሽሯል ፡፡
2 / ተጠሪዎች ክርክር የተነሣበት ውል እንዲፈርስ ለመጠየቅ የሚያስችል መብት የላቸውም ፡፡
3 / ወጪና ኪሣራ ግራ ቀ ይቻቻሉ ፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል ፡፡ ወደ መ / ቤት ይመለስ ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?