የሰበር መ / ቁ 20517
መጋቢት 22 ቀን 1998 ዓ.ም
ዳኞች 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
2. አቶ አብዱልቃድር መሐመድ
3. አቶ ጌታቸው ምህረቱ
4. አቶ መስፍን ዕቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሰ
አመልካቾች ፦ 1. ወ / ሮ አልማዝ ገ / መስቀል
2. ወ / ሮ መሠረት ገ / መስቀል 3. ወ / ሮ ተናኜ ገ / መስቀል 4. ወ / ሮ በልዩ ገ / መስቀል 5. ወ / ሮ ጌራ ገ / መስቀል
6. ወ / ሮ ምስጋና ገ / መስቀል መልስ ሰጪ ሼል ኢትዮጵያ ሊሚትድ
ፍ ር ድ
በዚህ ጉዳይ የቀረበው ክርክር የተከሣሽን መልስ ለመቀበል ፍ / ቤቱ በወሰነው ቀነ ቀጠሮ
የከሣሽ አለመቅረብ የሚኖረውን ሕጋዊ ውጤት የሚመለከት ነው ። በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ
ፍ / ቤት አመልካቾች በመ / ሰጭ ላይ ባቀረቡት ክስ መ / ሰጭ መልስ እንዲሰጥ በተቀጠረበት ቀን
አመልካቾች አለመቅረባቸውንና መ / ሰጭም ቀርቦ ክሱን መካዱን መሠረት በማድረግ ፍ / ቤቱ
መዝገቡን በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕ / ቁ 73
መሠረት ዘግቶታል ፡፡ በቀጠሮው
ቀን ያልቀረብነው
ጠበቃችን ይቀርባል በሚል በመሆኑ የተዘጋው መዝገብ ተከፍቶ ክርክሩ እንዲቀጥል አመልካቾች
ለፍ / ቤቱ ያቀረቡትን ጥያቄ ፍ / ቤቱ ምክንያቱ በቂ አይደለም በሚል ውድቅ ያደረገው ሲሆን
ይግባኝ የቀረበለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤትም ትዕዛዙን አጽንቶታል ። አመልካቾች ይህንን
ትዕዛዝ በመቃወም ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ጉዳዩ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ
በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት መ / ሰጭ ቀርቦ ግራ ቀኙ ክርክራቸውን በቃል ለችሎቱ አሰምተዋል ፡፡
ችሉቱም ክሱ ለመልስ በተቀጠረ ቀን የከሳሽ አለመቅረብ የሚኖረው ሕጋዊ ውጤት
ምንድነው ? የሚለውን የሕግ ነጥብ መሠረት በማድረግ ጉዳዩን መርምሯል ፡፡
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት በመ / ቁ 04103 ጥቅምት 17 ቀን 1997 ዓ.ም
ይህ ችሎት በመ / ቁ 14184 ሐምሌ 29 ቀን 1997 ዓ.ም በሰጠው ውጭ ከላይ የተመለከተውን የሕግ ነጥብ በሚመለከት የሕግ ትርጉም ሰጥቷል ፡፡ በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕ / ቁ 73 መሠረት ፍ / ቤቱ መዝገቡን በመዝጋት ተከሣሹን የሚያሰናብተው ጉዳዩን ለመስማት ፍ / ቤቱ ቀጠሮ በያዘበት ቀን ከሳሹ ያልቀረበ እንደሆነና ተከሣሹ ክሱን የካደ እንደሆን ነው :: ጉዳዩ የተከሳሹን መልስ ለመቀበል በተቀጠረ ቀን ከሳሹ ባይቀርብ ግን ከሳሹ እንዲፈጽመው የታዘዘው ነገር ስለሌለ ቀጣዩን ክንውን አስመልክቶ ትዕዛዝ ከመስጠት ውጭ ድንጋጌው የከሣሽን መዝጋት የሚያስችል አይደለም ፡፡ በመሆኑም የተከሳሽን መልስ ለመቀበል ቀጠሮ በተያዘበት ቀን ከሳሹ ያልቀረበ እንዲሆን ፍ / ቤቱ የተከሳሽን የጽሁፍ መልስ ከመዝገቡ ጋር አያይዞ ጉዳዩን የሚሰማበትን ቀነ ቀጠሮ ወስኖ ለዚሁ አስፈላጊ ትዕዛዞች መስጠት አለበት እንጂ መዝገቡን መዝጋት የለበትም ፡፡
ስለሆነም በዚህ ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት አመልካቾች ባቀረቡት ክስ መ / ሰጭ መልስ እንዲሰጥ ቀጠር በተያዘበት ዕለት አመልካቾች ሳይቀርቡ ሲቀሩና ተከሳሹ ክሱን ሲክድ ፍ / ቤቱ ዝገቡን በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕ / ቁ 73 በመዝጋት የሰጠው ትዕዛዝ ችሉቱ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግዋቶታል ፡፡
ው ሣ ኔ
የሰጠው ትዕዛዝ ፤ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት በመ / ቁ 34545 ግንቦት 8 ቀን 1997
ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ ተሽሮሯል ፡፡
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት የአመልካቾችን የክስ መዝገብ ከፍቶ ክርክሩ
እንዲቀጥል እንዲያደርግ ታዟል ፡፡ ይፃፍ ።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል ።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ፡፡
ፊር 11
You must login to view the entire document.