' ን'በመሻር የወጣያ «
የሰበር መ.ቁ 22262
የካቲት 22 ቀን 1998 ዓ.ም
ዳኞች፡- 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
አብዱልቃድር መሐመድ
ጌታቸው ምህረቱ
4. .. መስፍን ዕቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሰ
አመልካች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጠበቃው ቀርቧል ፡፡
መልስ ሰጭ፡- ካፕቴን ግርማ አዱኛ ጠበቃው ቀርቧል ፡፡
ፍ ር ድ
በዚህ ጉዳይ የቀረበው ክርክር የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 42/85
የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 በፀናበት ጊዜ ለስራ
ክርክር ሰሚ አካል ያልቀረበ የስራ ክርክር ፍፃሜ የሚገኘው በአዋጅ ቁ 42/85 ነው ?
ወይስ በአዋጅ ቁ .377 / 96 የሚለውን ነጥብ የሚመለከት ነው ።
መ / ሰጭ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት ስራ ክርክር ችሉት መጋቢት 7 ቀን
1996 ከስራዬ በፈቃዴ እንደለቀቅኩ የሚገልጽ የምስክር ወረቀት እንዲሰጠኝ እንዲሁም
የተጠራቀመ የዓመት እረፍት ቀናት በገንዘብ ተለውጦ ከሌሎች ክፍያዎች ጋር እንዲከፈለኝ
ይወሰንልኝ በማለት ባቀረቡት ክስ ፍ / ቤቱ አመልካች ለመ / ሰጭ የምስክር ወረቀት እንዲሰጥ
ወስኖ የዓመት እረፍት ፈቃድ ቀናት በገንዘብ ተለውጦ ይከፈለኝ እና ሌሉች ክፍያዎች
እንዲከፈለኝ በማለት ያቀረቡትን ጥያቄ ግልጽነት የጎደለው ነው በማለት አልፎታል ፡፡ ጉዳዩ
በይግባኝ የቀረበለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት በበኩሉ የስራ ውሉ በተቋረጠበት መስከረም
4 ቀን 1996 ዓም በስራ ላይ በነበረው አዋጅ ቁ 42/85 ድንጋጌዎችና በሕብረት
ስምምነቱ መሠረት ስራውን በፈቃዱ ለለቀቀ ሰራተኛ መፈፀም የሚገባቸው ክፍያዎችና
ጥቅሞች አመልካች ለመ / ሰጭ ይክፈል በማለት የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት
ውሣን በማሻሻል ውሣኔ ሰጥቷል ፡፡
ከየካቲት የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት በሰጠው ውጭ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል አመልካች ያቀረበው አቤቱታ ተመርምሮ ጉዳዩ ለሰበር ችሉት እንዲቀርብ በተሰጠው ትእዛዝ መሠረት አመልካችና መ / ሰጭ ክርክራቸውን ለችሎቱ በቃል አቅርበዋል ፡፡
ችሎቱም የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጁ ቁጥር 42/85 ' ን'በመሻር የወጣው የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር 377/96 በፀናበት ጊዜ ለስራ ክርክር ሰሚ አካል ያልቀረበ የስራ ክርክር ፍፃሜ የሚያገኘው በአዋጅ ቁጥር 42/85 ነው ? ወይስ በአዋጅ ቁጥር 377/96 የሚለውን የሕግ ነጥብ መሰረት በማድረግ ጉዳዩን መርምሯል ፡፡
የአሰሪና ሰራተኛ አዋጅ ቁ .377 / 96 ቀደም ሲል ስለአሰሪና ሰራተኛ ጉዳዮች የተደነገገውን የአዋጅ ቁ . 42/85 በመሻር እንደወጣ የአዋጅ ቁ .377 / 96 አንቀጽ 190 ( 1 ) ይደነግጋል ። ሆኖም የዚሁ ሕግ አንቀጽ 188 ( 4 ) በማናቸውም የስራ ክርክር ሰሚ አካላት በመታየት ላይ ያሉ የስራ ክርክሮች ይህ አዋጅ ከመጽናቱ በፊት በነበረው ሕግ መሠረት በተጀመረበት ስርዓት ፍፃሜ ያገኛል በማለት ይደነግጋል ፡፡ አዋጅቁ .377 / 96 ከመጽናቱ በፊት በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳዮች የነበረው ሕግ ደግሞ የአዋጁ ቁ .42 / 85 ነው ። ከዚህ ድንጋጌ በግልጽ መረዳት የሚቻለው አዋጅ ቁ .42 / 85 የአዋጅቁ 377/96 በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበትና ከፀናበት
18 ቀን 1996 ዓ.ም ጀምሮ የተሻረ መሆኑ
እንደተጠበቀ ሆኖ የአዋጁ ቁ 377/96
የፀና ከሆነበት ከየካቲት 18 ቀን 1996 ዓ.ም
በፊት በማናቸውም የስራ ክርክር ሰሚ አካላት በመታዬት ላይ የነበሩ የስራ ክርክሮች በአዋጁ
ቁ . 377/96 ሣይሆን በአዋጅ ቁ . 42/85 ፍፃሜ እንደሚያገኙ ነው ::
ሆኖም የአዋጁ ቁ .42 / 85 ድንጋጌዎች የአዋጅ ቁ . 377/96 ከፀናበት የካቲት 18
ቀን 1996 ዓ.ም በኋላ በአዋጅ ቁ . 377/96 አንቀጽ 188 ( 4 ) መሠረት በአንድ ጉዳይ
ተፈፃሚ የሚሆነው ጉዳዩ ከየካቲት 18 ቀን 1996 ዓ.ም በፊት በስራ ክርክር ሰሚ አካላት
የቀረበ እንዲሆን ነው ። ይህንንም የአዋጅ ቁ . 377/96 አንቀጽ 188 ( 4 ) " በማናቸውም
የስራ ክርክር ሰሚ አካላት በመታየት ላይ ያሉ የስራ ክርክሮች ... "
በማለት በግልጽ
ከደነገገው መረዳት የሚቻል ነው ፡፡ የዚህ ድንጋጌ አቀራረጽ አዋጅ ቁ . 377/96 ካፀናበት
ተነ ረ 5፣5 s
ለለቀቀ ሰራተኛ መፈፀም የሚገባቸውን ክፍያዎችና ጥቅሞች መ / ሰጭ ይከፈላቸው በማለት
የካቲት 18 ቀን 1996 ዓ.ም በፊት በስራ ክርክር ሰሚ አካላት ያልቀረቡ የስራ ክርክሮችን
ለይቶ ያወጣ ነው ፡፡
በተሻረው የአዋጅ ቁ .42 / 85 ድንጋጌዎችም ሆነ በአዋጅ ቁ .377 / 96 ድንጋጌዎች
የስራ ክርክር ሰሚ አካላት የስራ ክርክር ችሎት እና የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሣኝ ቦርዶች
ናቸው ። በመሆኑም የአዋጅ ቁ .42 / 85 አዋጅ ቁ .377 / 96 ካፀናበት የካቲት 18 ቀን
1996 ዓ.ም በኋላ በአንድ ጉዳይ ተፈፃሚ የሚሆነው ጉዳይ ( የስራ ክርክሩ ) ከየካቲት 18
ቀን 1998 በፊት የስራ ክርክር ሰሚ አካላት ለሆኑት የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሣኝ ቦርድ
ወይም ስራ ክርክር ችሎት የቀረበ እንደሆነ ብቻ ነው ::
በዚህ ጉዳይ በአመልካችና በመ / ሰጭ መካከል የነበረው የስራ ውል በመ / ሰጭ
ፈቃድ የተቋረጠው መስከረም 4 ቀን 1996 ዓ.ም ሲሆን መ / ሰጭ የስራ ክርክሩን
ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት ስራ ክርክር ችሎት ያቀረቡት መጋቢት 7 ቀን 1996
ዓም ነው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት መ / ሰጭ የስራ ክርክሩን ለፌዴራል የመጀመሪያ
ደረጃ ፍ / ቤት ባቀረቡበት ወቅት በአዋጅ ቁ . 377/96 የተሻው የአዋጅ ቁ 42 / 85'ን '
በጉዳዩ ተፈፃሚ በማድረግ በአዋጁ እና በሕብረት ስምምነቱ መሠረት ስራ ውሉን በፈቃዱ
የወሰነው መ / ሰጭ ከስራ በተሰናበቱበት መስከረም 4 ቀን 1996 ዓ.ም የአዋጅ ቁ 42/85
ስራ ላይ ነበር በሚል ነው ፡፡ ሆኖም ከላይ እንደተመለከተው በአንድ ለስራ ክርክር ሰሚ አካል
በቀረበ የስራ ክርክር ተፈፃሚ የሚሆነው የአዋጅ ቁ
ወይስ የአዋጅ
ቁ 377 / 96 የሚለውን የሚወስነው የአዋጅ ቁ 42/85 መሠረት ሲሆን ከየካቲት 18 ቀን
1996 ዓ.ም በኋላ ለስራ ክርክር ሰሚ አካል የቀረበ ጉዳይ ግን በአዋጅ ቁ 377 / 96
መሠረት ፍፃሜ ይገኛል ። መ / ሰጭ ክሱን ያቀረቡት ከየካቲት 18 ቀን 1996 ዓ.ም በኋላ
መጋቢት 7 ቀን 1996 ዓ.ም በመሆኑም የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት በጉዳዩ የአዋጅ ቁ
42/85 ድንጋጌዎች ተፈፃሚ ያደረገው በአግባቡ ሆኖ አልተገኘም ፡፡
የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት ለመ / ሰጭ እንዲከፈል ውጭ ከሰጠባቸው ክፍያዎች
መካከል የአዋጅ ቁ 377/96 ከአዋጅ ቁ 42/85 ልዩነት የሚያደርገው የስራ ስንብት
ፈ ፥ : ÷ . . ' , £ ታ ሴት
ክፍያን በሚመለከት ነው :: በአዋጅ ቁ 42/85 አንቀጽ 39 በአዋጁ መሠረት የስራ ውሉ
የተቋረጠበት ሰራተኛ የስራ ስንብት ክፍያ እንዲከፈለው ይደነግጋል ፡፡ በአዋጁ መሠረት
የስራ ውል ከሚቋረጥባቸው ሁኔታዎች አንዱ ሰራተኛው ማስጠንቀቂያ በመሰጠት የስራ
ውሉን በፈቃዱ የሚያቋርጥበት ሁኔታ ነው ። የአዋጅ ቁ . 377/96 አንቀጽ 39 ( 1 )
መሠረት የስራ ውሉ የተቋረጠ ሰራተኛ የስራ ስንብት ክፍያ የሚያገኘው የስራ ውሉ
በአንቀጽ ከፊደል ተራ ሁ - ረ በተመለከቱት ሁኔታዎች የተቋረጠ እንደሆነ ብቻ ነው :: በዚህ
ጉዳይ የመ / ሰጭ የስራ ውል የተቋረጠበት ሁኔታ በድንጋጌው በተቀመጡት ሁኔታዎች
የሚጠቃለል አይደለም ። በመሆኑም የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት የአዋጅ ቁ 42 / 85'ን '
በማድረግ
ውጭ መ / ሰጭ የስራ ስንብት ክፍያ እንዲከፈላቸው
የሚያደርግ ነው ። ሆኖም በጉዳዩ ተፈፃሚ በሚሆነው የአዋጅ ቁ 377/96 አንቀጽ 39 ( 1 )
መሠረት መ / ሰጭ የስራ ስንብት ክፍያ ሊከፈላቸው የሚገባ አይደለም ፡፡ በዚሁ ምክንያት
የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት ውሣኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል ።
ው ሣ ኔ
ይህ ችሎት መ / ሰጭ
ስንብት ክፍያ የማግኘት መብት የላቸውም በማለት
ወስኗል ። ይፃፍ ።
- የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት በመ / ቁ 37953 ህዳር 12 ቀን 1998 ዓም
የሰጠው ውሣ ተሻሽሏል ፡፡
ግራ ቀኙ በዚህ ችሉት ያወጡትን ውጭ የየራሣቸውን ይቻሉ ::
- መዝገቡ ተዘግቷል ፡፡ ይመለስ ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
ይራል ብቅ ይ ፍርድ ቤት
You must login to view the entire document.