የሠ / መ / ቁ 22726
ታህሣሥ 19 ቀን 1999 ዓ.ም. ዳኞች 1. አቶ ከማል በድሪ
2. አቶ ፍስሐ ወርቅነህ 3. አቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ 4. አቶ መስፍን እቁበዮናስ
5. ወ / ት ሒሩት መለሠ አመልካች የቡና ተክል ልማት ድርጅት አልቀረቡም :: መልስ ሰጭ ፦ አቶ ሰብስብ ሀጂ አባቦንሳ ቀረቡ ።
ፍ ር ድ ጉዳዩ ለዚህ ችሎት የቀረበው መልስ ሰጭ አመልካች በሕገ ወጥ መንገድ ከስራ ያሰናበተኝ በመሆኑ ወደ
እንድመለስ ፤ ከአመልካች ጋር ባደረግነው ውል አመልካች
በጅማ ዩኒቨርሲቲ ለመማር ከማወጣው ወጭ ግማሹን ለመክፈል ግዴታ የገባ በመሆኑ በዚሁ
መሠረት የከፈልኩትንና ትምህርቱን ለማጠናቀቅ ወደ ፊት ከማወጣው ወጭ ግማሹን
እንዲከፍለኝ ይወሰንልኝ በማለት በጅማ ወረዳ ፍርድ ቤት ያቀረበውን ክስ ፍርድ ቤቱ
በመቀበል መልስ ሰጭ በሕገ ወጥ መንገድ ከሥራ የተሰናበተ በመሆኑ በአዋጅ ቁጥር
377/96 አንቀጽ 35 ፣ 39-41 እና 54 የተመለከቱት ክፍያዎች ተፈጽመውለት ከሥራ
እንዲሰናበት ፣ መልስ ሰጭ ለትምህርት የሚያወጣውን ወጭ ግማሽ አመልካች እንዲከፍለው
በሰጠውና የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍርጀ ቤትና የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ባጸናው ውሣኔ
ቅር በመሰ ት አመልካች የሰበር አቤቱታ በማቅረቡ ነው :: ጉዳዩ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ
በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት ግራ ቀ - ክርክራቸውን ለችሎቱ በቃል አሰምተዋል ፡፡
መልስ ሰጪ የተሰናበተው በሕጋዊ ነው ? በሕገ ወጥ መንገድ ? መንገድ የሚለውን
ነጥብ በሚመለከት አመልካች መልስ ሰጭ ወደተዛወረበት ቦታ ሄዶ ስራ ባለመጀመሩ በሕጋዊ
መንገድ ከሥራ ተሰናብቷል የሚል ሲሆን መልስ ሰጭ በበኩሉ በሥራ ላይ ያልነበርኩት
በሕመም ምክንያት ለመሆኑ ከሀኪም የተሰጠ የሕክምና እረፍት ማስረጃ አለኝ የእረፍት
ጊዜው እንደተጠናቀቀ ዝውውሩን በመቃወም ባቀረብኩት ቅሬታ ከአመልካች ጋር በአሰሪና
. ያ ያለባቸውን ግዴታ የመፈጸም ግዴታ እንዳለበትና አንድ ተዋዋይ ወገን እንዲፈጽም ግዴታ የሚጎም መልስ ሰጭ ለትምህርት የሚያወጣውን ወጭ ግማሽ አመልካች ሠራተኛ ጉዳይ አስማሚ ቦርድ ስንደራደር ስለነበር ነው በማለት ተከራክሯል ። ይህም መልስ ሰጭ የተሰናበተው በሕጋዊ ነው ? በሕገ ወጥ መንገድ ? መንገድ የሚለው ነጥብ ግራ ቀ ያቀረቡት ማስረጃ ተመዝኖ ውሣኔ የሚያገኝ ሲሆን ይህ ችሎት በዚሁ መሠረት የስር ፍርድ ቤቶች የሰጡትን ውጭ የሚመረምርበት የሕግ አግባብ የለም ። ስለሆነም የስር ፍርድ ቤቶች ስንብቱ ሕገ ወጥ ነው በሚል የሰጡትን ውሣኔ ይህ ችሎት ተቀብሎታል ፡፡
ችሎቱም አመልካች መልስ ሰጭ ለትምህርት የሚያወጣውን ወጭ ግማሽ አመልካች እንዲከፍለው የተወሰነው በአግባቡ ነው ? ወይስ አይደለም ? የማለውን የሕግ ነጥብ መሠረት ጉዳዩን መርምሯል ፡፡
የፍ / ብ / ሕ / ቁ የውሎችን በሚመለከት የተቋቋሙ
ባቋቋሟቸው ሰዎች ላይ ሕግ ናቸው " በማለት ይደነግጋል ፡፡ ይህ ተዋዋይ ወገኖቹ በውሉ
በውሉ ያለበትን ግዴታ ነው :: በዚህ ጉዳይ አመልካችና መልስ ሰጭ ባደረጉት ውል
እንዲሸፍን ተስማምተዋል ፡፡ በዚሁ መሠረት አመልካች የተሰወነ ክፍያ ፈጽሟል ። ሆኖም
ውሉ መልስ ሰጭ ከሥራ ከተሰናበተ በኋላም ለትምህርት የሚያወጣውን ወጭ ግማሽ
እንዲከፍል በአመልካች ላይ ግዴታ ይጥላል ? ወይስ አይጥልም ? የሚለው ነጥብ መመለስ
ይኖርበታል ፡፡ በአመልካችና በመልስ ሰጭ መካከል ባለው
ውል በዚህ ነጥብ ላይ ግልጽ
ስምምነት አልተደረገም ፡፡ በመሆኑም በፍ / ብ / ሕ / ቁ 1734 / 1 / መሠረት የተዋዋዮች ሀሣብ
ምን እንደነበር ለማወቅ መፈለገ ይገባል ፡፡ መልስ ሰጪ ራሳቸው በዚህ ችሎትም ሆነ በሥር
ፍርድ ቤቶች ባቀረቡት ክርክር አመልካች ለትምህርት የሚያወጣውን ወጭ ግማሽ ለመክፈል
የተስማሚው የድርጅቱ ሰራተኛ በመሆናቸው መሆኑንና ሌሎች የድርጅቱ ሰራተኞችም
በተመሣሣይ መንገድ ተጠቃሚ እንደሆኑ ገልጸዋል ፡፡ ይህም አመልካች ሰራተኛ ካልሆነ ሰው
ጋር ተመሣሣይ ግዴታ ውስጥ እንደማይገባና እሳቸውም ቢሆኑ የድርጀቱ ሰራተኛ ባይሆኑ
አመልካች ወደ ውሉ እንደማይገባ ያመለክታል ። በዚሁ መሠረት አመልካች ሰራተኛው
የድርጅቱ ሰራተኛ መሆኑ ካቆመበት ጊዜ በኋላም ተመሣሣይ ግዴታ እንዲኖርበት ይስማማል
ለማለት አይቻልም :: ስለሆነም አመልካች ከሠራተኛ ባደረገው ውል መሠረት ለትምህርት
' ኣካች
መልስ ሰጭ ከሥራ ከተሰናበቱበት ቀን በኋላ ለትምህርት የሚያመጣውን የሚያወጣውን ወጪ ለመተካት ግዴታ የሚኖርበት ሠራተኛው የድርጅቱ ሰራተኛ ሆኖ እስከቀጠለበት ጊዜ ብቻ ነው ማለት ነው ::
በሥር ፍ / ቤት አመልካች እንዲከፍል የተፈረደበት መልስ ሰጪ ለትምህርት የሚያወጣውን ወጭ ግማሽ አመልካች እንዲከፍለው ነው :: ይህም መልስ ሰጭ ከሥራ ከተሰናበተበት ቀን በፊት ለትምህርት የከፈለውን እንዲሁም ከሥራ ከተሰናበተበት ቀን በኋላ ትምህርቱን ለመጨረስ ለትምህርት የሚከፍለውንም የሚጨምር ነው :: በመሆኑም ከላይ በተመለከተው መሠረት መልስ ሰጭ ከሥራ ከተሰናበተ በኋላም ለትምህርት የሚያወጣውን ወጭ ግማሽ እንዲከፍል የተሰጠው ውሣኔ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል ።
ው ሣ ኔ
ወጭ ግማሽ መክፈል የለበትም በማለት ወስኗል ፡፡
የጅማ ወረዳ ፍርድ ቤት በመ / ቁ 03315 ግንቦት 26 ቀን 1997 የሰጠው ውሣኔና
የጅማ ዞን ከፍተኛ ፍ / ቤት በመ / ቁ 07112 ጥቅምት 18 ቀን 1998 ዓ.ም.
የሰጠው ትዕዛዝ እና የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በመ / ቁ 35900 ጥር 10 ቀን
1998 ዓ.ም. የሰጠው ትዕዛዝ ተሻሽሏል ።
አመልካችና መልስ ሰጭ በዚህ ችሎት ያወጡትን ወጭና የደረሰባቸውን ኪሣራ
የየራሳቸውን ይቻሉ ፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ፡፡
You must login to view the entire document.