ህዳር 7 ቀን 1998
መ / ቁ .14699
ዳኞች፡- 1. አቶ መንበረፀህይ ታደሰ
2. አቶ አብዱልቃድር መሐመድ 3. አቶ ተገኔ ጌታነህ 4. ወ / ሮ ሆሳዕና ነጋሽ
5 ወ / ት ሂሩት መለሰ አመልካች፡- የኢንጂነር ወርቁ መኮንን የአመልካች ወራሾች ተጠሪ፡- የቦሌ ክ / ከተማ ገቢዎች መምሪያ
ገቢን ለመፍጠር የሚወጣን ወጪ በትክክለኛ ሰነድ እንዲረጋገጥ ሕጉ ስለሚያስቀምጠው ሁኔታ የገቢ ግብር ደንብ ቁጥር 258 / s5
አንቀጽ 29
አመልካች ገቢ ለመፍጠር ወጪ ያደረጉት ገንዘብ በወጪነት ላይያዝ ግብር እንዲከፍሉበት የተወሰነ ሰመሆን ይኸው ገንዘብ በወጪነት እንዲያዝላቸው የጠየቁ ሲሆን የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤውም ወጪ ለመውጣቱ ማስረጃ የቀረበ በመሆኑ በወጪነት ሊያዝላቸው ይገባል በማለት ሲወስን ጉዳዮን በይግባኝ ያየው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ይህንኑ ውሳኔ ያፀናው ቢሆንም የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ግን የቀረቡት ማስረጃዎች በግብር ሕጉ በተደነገገው መሠረት ትክክለኛ ሰነዶች ስላልሆኑ በወጭነት ሊያዘ ስለማይገባ ግብር ይከፈልባቸው በማለት ውሳኔ በመሥጠቱ የቀረበ አቤቱታ :: ዉሳኔ፡- የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጠው ውሳኔ ተሽሯል ፡፡ 1. የገቢ ግብር ደንብ ቁጥር 258/55 አንቀጽ 29 « ትክክለኛ » ሰነዶች
እንዲቀርቡ የፈለገበት ዋነኛ ምክንያት ወጪዎች በቀጥታ ገቢን ለመፈጠር ስለመውጣታቸው በበቂ ሁኔታ ለማረጋገጥ እና ግብር ከፋዩ ሃሰተኛ ሰነድ በማቅረብ የግብር ግዴታውን እንዳይሸሽ ለመቆጣጠር እንጂ የሰነዶችን አዘገጃጀት ሥነ - ሥርዓት መሟላት አለመሟላት ለመቆጣጠር
አይደለም :: 2. ሰነዶቹ መ / ቤቱ እንዲሟሉ የሚፈልጋቸው ሥርዓቶች ባያማሉ እንኳ
ተቀባይነት የማያገኙበት ሕጋዊ ምክንያት የለም ፡፡
2 አቶ አብዱልቃድ ዘርዚት ወ / ሮ
ህዳር 7 ቀን 1998
መ / ቁ .34699 ዳኞች፡- 1. አቶ መ
3. አቶ ተገኔ ጌታነህ 4 ወ / ሮ ሆሳዕና ነጋሽ
5. ወ / ት ሃሩት መለሰ አመልካች፡- የኢንጂነር ወርቁ መካንን የአመልካች ወራሾች
ገነት ኤርሲዶ ቀረቡ ተጠሪ፡- የቦሌ ክ / ከተማ ገቢዎች መምሪያ - ነ / ፈጅ ገዛኸኝ ኢርኮ ቀረበ
ፍ ር ድ ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዳይ የጀመረው በግብር ይግባኝ | ሰሚ ጉባኤ ሲሆን አመልካች በይግባኝ አቤቱታቸው ገቢ ለመፍጠር ወጪ ያደረጉት ገንዘብ በወጪነት ሳይያዝ ግብር እንዲከፍሉፀት የተወሰነ በመሆኑ | ይኸው ገንዘብ በወጪነት እንዲያዝላቸው የጠየቁ ሲሆን ጉባኤውም ወጪ ለመውጣቱ ማስረጃ የቀረበ በመሆኑ በወጪነት ሊያዝላቸው ይገባል በማለት ወስኗል ፡፡ ጉዳዩን በይግባኝ ያየው የፌ / ከፍተኛ ፍ / ቤት ይህንኑ ውሣኔ ያፀናው ቢሆንም የፌ / ጠቅላይ ፍ / ቤት ግን ለድርጅቱ ወጥተዋል የተባሉት | ወጪዎችን ለማረጋገጥ የቀረቡት ማስረጃዎች በግብር ሕጉ ፅተደነገገው መሠረት ትክክለኛ የሆኑ ሰነዶች ስላልሆኑ በወጪነት ሊያዙ ስለማይገባ ግብር ይከፈልባቸው ሰማዕት ውሣኔ ሰጥተዋል ፡፡ የአሁኑ የሰበር የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ
በዚህ ውሣኔ ላይ ነው ፡፡ የአመልካች ቅሬታም የቀረቡት ሰነዶች ወጪዎቹ ገቢን ለመፍጠር የወው ወጪዎች ለመሆናቸው ለማረጋገጥ ብቃት ያላቸው ሰነዶች በመሆናቸው በወጪዎቹ ላይ ግብር እንዲከፈል መደረጉ የህግ ስህተት ነው የሚል ሲሆ ተጠሪ በበኩሉ ደረሰኞቹ በግብር ሕጉ መሠረት የተሰሩ ትክክለኛ ሰነዶች ስላልሆኑ ተቀባይነት ሲያገኙ አይገባም በማለት ተከራክሯል ፡፡
ከተመለከተው የግራ ቀኙ ክርክር ሊሆን ይህ ችሎ አመልካች ግብር እንዲከፈሉ የተሰጠው ውሣኔ የገቢ ግብርን ለማስከፈ የወሳውን አዋጅ መሠረት ያደረገ ነው ? ወይስ አይደለም ? የሚለው ነጥ ሊታይ የሚገባው ሆኖ አግኝተነዋል ፡፡
በገቢ ግብር አዋጁ መሠረት ግብር የተጣለበትን ገቢ የሚሰበስብ ማንኛውም ሰው በአዋጁ በተመለከተው መሠረት ከጠቅላላው ገቢ ላይ ገቢውን ለመፍጠር የወጡ ወጪዎች ከተቀነሱ በኋላ በሚገኘው የተጣራ ትርፍ ላይ ግብር የመክፈል ሃላፊነትና ግዴታ አለበት ፡፡ በመሆኑም ግብር ከፋይ ገቢን ለመፍጠር ያወጣውን ወጪ ትክክለኛነት ተቀባይነት ሳ ' ' ? የሚገባቸው ሰነዶች በማቅረብ ወጪዎቹን የማስረዳት ሸክም እዩት ፡፡ የግብር ሰብሳቢው ባለስልጣንም የሚቀርቡለትን ሰነዶች ወጪዎች በትክክል ለመፍጠር ለመሆናቸው የሚያስረዱ ትክክለኛ ሰነዶች ስለመሆናቸው የማረጋገጥ ሃላፊነት አለበት ፡፡ የቀረቡለት ሰነዶች ትክክለኛነት የማረጋገጥ ሃላፊነት የግብር ሰብሳቢው መ / ቤት እንደመሆኑ መጠን መ / ቤቱ የሰነዶቹን ትክክለኛነት ሊያረጋግጥ የሚገባው እንዴት ነው የሚለው በቀጣይነት መታየት ይኖርበታል ፡፡ የገቢ ግብር አዋጅ የወጣው ግብር ከፋዩ ግብር በተጣለበት ገቢ ላይ የሚፈለገውን ትክክለኛ ግብር እንዲከፍል ለማድረግ ነው ፡፡ ከላይ እንደተገለፀውም ግብር የሚከፈልበት ገቢ ገቢውን ለመፍጠር የወጣው ወጪ ከጠቅላላ ገቢው ላይ ከተቀነሰ በኋላ በሚገኘው ትርፍ ላይ ብቻ በመሆኑ ገቢን ለመፍጠር የወጡ ወጪዎች ሳይቀነሱ በጠቅላላው ገቢ ላይ ግብር እንዲከፈል ማድረጉ የአዋጁን አላማ የሚንድ ይሆናል ፡፡ በሌላ በኩል የቀረቡትን ሰነዶች በሙሉ መቀበሉም ግብር ሊከፈልበት የሚገባው ገቢ እንዲቀንስ የሚረዳ ስለሚሆን የሚቀርቡ ሰነዶች ትክክለኛነት በጥንቃቄ መረጋገጥ ይኖርባቸዋል ፡፡ በዚህም ምክንያት የገቢ ግብር ደንብ ቁጥር 258/55 አንቀጽ 29 ለባለስልጣኑ የሚቀርሱ የሂሣብ መዛግብት እና ሰነዶች ውስጥ የሚሰፍሩ ሂሳቦች ትክክለኛ በሆኑ ሰነዶች ቫውቸሮች / መደገፍ እንዳለባቸው ያዛል ፡፡ ይህ የአዋጁ ድንጋጌ V ትክክለኛ V ሰነዶች እንዲቀርቡ የፈለገበት ዋነኛ ምክንያት ወጪዎቹ በቀጥታ ገን ሰመፍጠር ስለመውጣታቸው በበቂ ሁናቴ ለማረጋገጥ እና ግብር ከፋዩ ሃሰተኛ ሰነድ በማቅረብ የግብር ግዴታውን እንዳይሽሽ ለመቆጣጠር እንጂ የሰነዶቹን አዘገጃጀት ሥነ - ሥርዓት መሟላት አለመሟላቱን ለመቆጣጠር ባለመሆኑ የሰነዶቹ ይዘት ሊታይ የሚገባው ከዚሁ የአዋጁ አላማ አንፃር ሊሆን ይገባል ፡፡ በመሆኑም ለመ / ቤቱ የቀረቡት ሰነዶች ወጪ ለመውጣቱ
የሚያሳዩ በቂ ሁኔታዎችን እስከያዙ ድረስ መ / ቤቱ ሰነዶቹ ሲዘጋጁ ሊሟሉ The ልፋልጋል የሚላቸው
ልጋል ያደጊቋቸው ስርዓቶች / ፎርማሊቲዎች ብቻ ሰነዶቹን ውድቅ ማድረግ ተገቢ አይሆንም ፡፡ በእርግጥ የሥርዓቶቹ
መውጣቱን ለማረጋገጥ
ማስረጃዎች ሲያደርጋቸው ይሆናል ፡፡ መ / ቤቱ እንዲሟሉ የማፈልጋቸው ሥርዓቶች ሳያሟሉ እንኳን ወጪ ለመውጣቱ ሊያረጋግጡ የሚችሉ በቂ ሁኔታዎችን እስካሳዩ ድረስ ተቀባይነት ሊያገኙ የማይችሉበት ህጋዊ ምክንያት አይኖርም ፡፡
ወደ ተያዘውም ጉዳይ ስንመለስ ኣመልካቹ የህንፃ ተቋራጭ ሲሆኑ የተጠየቁትም ለሚሰሩት የግንባታ ሥራ እንደሆነ
እንደሆነ ከመዝኀበ ተረድተናል ፡፡ ግብር የተጣለባቸው ይህንኑ ሥራ ኣከናውነው ገቢ አግኝተዋል በማለት ከሆነ አመልካች ግንባታውን ማከናወናቸው የተረጋገጠ ጉዳይ ለመሆኑ መረዳት ይቻላል ። ይህን የሥራ ዘርፍ ለማከናወን ደግሞ አሸዋ ፣ ድንጋይ የመሳሰሉት ጥሬ እቃዎች መጠቀማቸው እንደማይቀር አከራካሪ አይሆንም ፡፡ አከራካሪ ሊሆን የሚችለው ግብር የተጣለበትን የግንባታ ሥራ ለመስራት እቃዎች መገዛት አለመገዛታቸው ሳይሆን ግንባታውን ለመስራት ጥቅም ላይ የዋሉት ጥሬ እቃዎች መጠን እና ዋጋቸው ነው ፡፡ አመልካች ሥራቸውን ለማከናወን ከፍ ሲል የተጠቀሱትን ጥሬ እቃዎች የገዙት ከገጠር የአገሪቱ ክፍል ለመሆኑ የገለፁትን እውነታ ተጠሪ ክርክር እንዳላቀረበበት ከመዝገቡ ተመልክተናል ፡፡ በገጠር የሃገሪቱ ክፍል ለሚደረግ ሽያጭ ደግሞ ማህተም ያለው ደረሰኝ ማግኘት ከባድ በመሆኑ የወጣውን ወጪ ለማረጋገጥ የቀረበው ሰነድ ነጭ ወረቀት መሆኑን ኣመልካቹ ገልፀዋል ፡፡ ግብር ሰብሳቢው መ / ቤትም የቀረበለትን ሰነድ ውድቅ ያደረገውም ሰነዱ ማህተም ያልተደረገበት ነው በሚል ብቻ እንጂ ግብር የተጣለበትን ገቢ ለመፍጠር እነዚህ ጥሬ እቃዎች አልተገዙም ወይም ወጪው የተጋነነ ነው በማለት አለመሆኑን ከመዝገቡ ተረድተናል ፡፡ ተጠሪ በዚህ በኩል ያቀረበው ክርክር ሲኖር ኖሮ ከፍ ሲል እንደተባለው ጉዳዩ አከራካሪ ሊሆን ይችል ነበር ፡፡ በተጠሪ በኩል ግን እንደዚህ አይነት ክርክር አልቀረበም ፡፡ በእቃዎቹ ዋጋና መጠን ላይ ክርክር ሳይቀርብ ወጪ መውጣቱ በተረጋገጠ ጉዳይ ላይ ሰነዱ ማህተም የለውም በሚል ብቻ ሰነዱን ውድቅ : ማድረጉ ደግሞ በወጣ ወጪ ላይ ግብር እንዲከፈል የማድረግ ውጤት ስለሚኖረው ኣዋጁን የሚቃረን አፈፃፀም ይሆናል ፡፡
በተመሳሳይ ለመኪና የሰሌዳ ቁጥር ከመስጠቱ በፊት የሻንሲ ቁጥር
ያልተመዘገበበት ደረሰኝ መሆኑን መዝገብ ያመለክታል ፡፡ በዚህ ደረሰኝ ላይ
የሰፈረው የሻንሲ ቁጥር የአመልካች መኪና ለመሆን ማረጋገጡን ግብር ሰብሳቢው መ / ቤትም አይከራከርም ፡፡ መታየት ያለበት ደግሞ የቀረበው ሰነድ ለአመልካች መኪና ጥገና የተደረገ መሆኑን ማረጋገጡ እንጂ
እንጂ የግድ የመኪናው ሰሌዳ ቁጥር መፃፉ ሊሆን አይገባም ፡፡ የሻንሲ ቁጥሩም ቢሆን ከታርጋ ቁጥሩ የበለጠ መኪናው የአመልካች መኪና ለመሆኑ የማረጋገጥ ብቃት አለው ። በመሆኑም ደረሰኙ ጥገና የተደረገላት መኪና የትኛው መኪና ለመሆኑ ማረጋገጥ እየቻለ የታርጋ ቁጥሩ ባለመግለጹ ብቻ ገቢን ለመፍጠር የወጣው ወጪ ላይ ግብር እንዲከፈል ማድረጉ የሕግ ስህተት ነው ፡፡ ለነዳጁ የወጣውን ወጪ በተመለከተም ከዚህ የተለየ አይደለም ፡፡ ነዳጅ ለመቀዳቱ በተሰጠው ደረሰኝ ላይ የተመዘገበው የመኪናው ታርጋ ቁጥር የአመልካች መኪና ታርጋ ቁጥር ላለመሆኑ የቀረሽ ክርክር ሳይኖር የባለቤቱ ስም ባለመፃፉ ብቻ ስነዱ ወድቅ ሊደረግ የሚገባባት ምክንያት የለም ፡፡ በአጠቃላይ ገቢን ለመፍጠር የሚወጣን
በትክክለኛ ሰነድ እንዲረጋገጥ ሕጉ የሚያዘው ግብር ከፋዩ የተጣለበትን ግብር የመክፈል ግዴታውን ሳይወጣ እንዳይቀር ለመቆጣጠር በመሆኑ ሰነዶቹ በበቂ ሁኔታ ወጪ መውጣቱን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ነገሮች ከያዙ በሰነድ አዘጋጃጀት የተለያዩ ፎርማሊቲዎች ባለመሟላታቸው ብቻ ሰነዱን ማድረጉ ፣ ከፍ ሲል እንደተገለፀው ፣ ውጤቱ ከግብር ሕጉ በመውጣት ግብር እንዲከፈልበት ባልተጠየቀ ገንዘብ ላይ ግብር እንዲከፈል ማድረግ ቤት የቀረቡትን ሰነዶች የተለያዩ ስርዓቶች / ፎርማሊቲዎች / ሳለማሟላታቸው ብቻ ውድቅ ማድረጉ የሕግ ስህተት
ው ሣ ኔ
የጠቅላይ ፍ / ቤት በመ / ቁ . 13065 በጥር 26 ቀን 1996 የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል ፡፡
የፌ / ከ / ፍ / ቤት በመ / ቁ .783 በሐምሌ 16 ቀን 1995 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ እና የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ ሰግ / ይ / መ / ቁ . ወ -17 በየካቲት 8 ቀን 1992 ዓ.ም. የሰጠው ውሣኔ ፀንቷል ፡፡
ግራ ቀኙ ወጪ እና ኪሣራ ይቻቻሉ ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ፡፡
You must login to view the entire document.