አቤቱታው መነሻ የሆነው ተጠሪ በፌ / መ / ደረጃ ፍ / ቤት ያቀረቡት ክስ
የሰበር መ.ቁ .19738
ዳኞች፡- 1- አቶ መንበረፀሀይ ታደሰ
2- አቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ
3- አቶ ጌታቸው ምህረቱ
4- አቶ መስፍን እቁበዮናስ
5- ወ / ት ሂሩት መለሰ
አመልካች፡- የኢት / ልማት ባንክ
ተጠሪ፡- ተፈሪ ነጋሺ
ፍ ር ድ
ነው ፡፡ ተጠሪ ለፍ / ቤቱ ባቀረቡት ክስ ገንዘብ አጉድለዋል በማለት ያላግባብ ከሥራ
ስለታገዱ የተቋረጠ ደሞዛቸው ተከፍሏቸው ወደ ስራ እንዲመለሱ ጠይቀዋል ፡፡ ጉዳዩን
ያየው ፍ / ቤትም እምነት ማጉደል የሥራ ውል ለማቋረጥ እንጂ ለእግድ ምክንያት
አይሆንም በማለት ተጠሪ ወደ ሥራ ለመመለስ ካመለከቱበት ቀን ጀምሮ ያለው ደሞዝ
ተከፍሏቸው ወደ ስራ እንዲመለሱ ወስኗል ፡፡ የፌ / ከፍተኛ ፍ / ቤትም ይህንኑ ውሣኔ
አፅንቷል ፡፡
የአሁኑ የሰበር አቤቱታም የቀረበው በዚሁ ውሣኔ ላይ ነው ፡፡ ይህ ችሎትም
እምነት ማጉደል ከስራ ለማገድ የሚያበቃ ምክንያት መሆን አለመሆኑን ለመመርመር
አቤቱታውን ለሠበር ችሎት በማስቀረብ የግራ ቀኙን የፁሁፍ ክርክር መርምሯል ፡፡
የሥር ፍ / ቤት አመልካች ተጠሪን ለማገድ በቂ ምክንያት አልነበረውም ያለው
ተጠሪ ፈፅመውታል የተባለው የእምነት ማጉደል ተግባር በአ / ቁ 42/85 አንቀፅ 18
ፌዶራል ጠቅላይ ፍ t ደ ናት
ቀን 13- 3 ቀን
= አላማ አኳያ ነው ፡፡
በእርግጥ
እንቀፅ 18 ፤ ያምራ መሠረት የእግድ ምክንያት ሣይሆን በአዋጁ አንቀፅ 27 / 1 / ሐ / ከሥራ የማሠናበቻ ምክንያት ነው በሚል ነው ፡፡ በመሆኑም አንድ ሠራተኛ ከስራ ሊታገድ የሚችለው ከፍ ሲል በተጠቀሰው አንቀፅ ሥር የተዘረዘሩት ሁኔታዎች አንዱ ወይም ሌላኛው ሲሟሉ ብቻ ነው ወይ ? የሚለውን መመርመሩ ተገቢ ይሆናል ፡፡ በአዋጅ ቁጥር 42/85 አንቀጽ 17 / 1 / ሥር ከሥራ ውል የሚመነጨ መብትና ግዴታዎች ለተወሠነ ጊዜ ሊታገድ የሚችል መሆኑ የተመለከተ ሲሆን የመታገድም ውጤት በእግዱ ጊዜ ሠራተኛው ሥራ
መስራቱን አሠሪው ደግሞ ደሞዝና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች መክፈሉ የሚቆም እንጂ የሥራ ውሉን ማቋረጥም ሆነ ማስቀረት አለመሆኑ በንዑስ ቁጥር / 2 / ሥር ተገልጿል ፡፡ በመሆኑም የድንጋጌው አላማ የሠራተኛን የሥራ ውል ማቋረጥ ሣያስፈልግ ሠራተኛው
የማይችልባቸው ሁኔታዎች ሲያጋጥሙ ሁኔታዎቹ እስኪወገዱ ሠራተኛውን
ከደሞዝ አግዶ ማቆየት ነው ፡፡ ስለሆነም አንቀፅ 18 መታየት ያለበት ከዚህ ለጊዜው ለማገድ የሚቻልባቸው በቂ ምክንያቶች ተዘርዝረው ተቀምጠዋል ፡፡ ነገር ግን
ከፍ ሲል ከተገለፀው የአዋጁ ድንጋጌ አኳያ ስንመለከተው የሥራ ውል ለማገድ በቂ
የሚሆኑ ምክንያቶች በአንቀፁ ስር ተዘርዝረው በተቀመጡት ብቻ ተወስኖ የሚቀር ነው
ለማለት አይቻልም ፡፡ ምክንያቱም የአንድን ሠራተኛ የሥራ ውል ማቋረጥ ሳያስፈልግ
ሠራተኛው ለተወሠነ ጊዜ በሥራ ገበታው ላይ እንዳይገኝ የሚያስገድዱ የተለያዩ
ምክንያቶች ሊያጋጥሙ ይችላሉ ፡፡ ከነዚህም ውስጥ በተለይ የሠራተኛውን የሥራ ውል
ያለማስጠንቀቂያ
ሊያቋርጥ
ምክንያት የተገኘ
ቢሆንም እንኳን
የሠራተኛውን የሥራ ውል በቀጥታ ከማቋረጥ ይልቅ ሁኔታው እስኪጣራ የስራ ውሉ
ለጊዜው አግዶ ማቆየቱ አስፈላጊ ሊሆን የሚችልበት አጋጣሚ ነው ፡፡ ስለዚህም የስራ
ውሉን ያለማስጠነቀቂያ ለማቋረጥ በሚያበቃ ምክንያት ባጋጠመ ጊዜ ሁሉ ሠራተኛውን
ፈያ.ረል ሓይ ፍርድ
ክል ግልባ »
Q -- ሁ -- የፅ
የግድ ከሥራ ማሠናበት እንጂ የሥራ ውሉን ለተወሠነ ጊዜ ማገዱ ህገወጥ ነው
የሚባል ከሆነ ህጉ ለሠራተኛው የሚያደርገውን ጥበቃ ከሚያጠብ በቀር ጠቀሜታ
አይኖረውም ፡፡ በማጣራቱ ሂደት የተገኘው ውጤት ሠራተኛውን ከሥራ የሚያሠናብት
ቢሆን እንኳን ሠራተኛው ላይ የተለየ የመብት መጣበብ የሚያስከትልበት አይሆንም
ምክንያቱም ቀድሞውኑም ቢሆን ከሥራ የመሠናበት እርምጃ ሊወሠድበት የሚያበቃ
ምክንያት ነበርና ነው ፡፡ ውጤቱ ሠራተኛውን የሚጠቅምም ከሆነ ሠራተኛው ሣራውን
ሊቀጥል የሚችልበት እድል ይፈጥርለታል ፡፡
በመሆኑም የሥር ፍ / ቤት በአ / ቁ .42 / 85 አንቀፅ 18 ሥር ከተዘረዘሩት ምክንያቶች
ውጪ በሌላ ምክንያት የሥራ ውል ታግዶ ሊቆይ አይችልም በማለት የደረሠበት
መደምደሚያ ህጉን ያላገናዘበ ነው ፡፡
በሌላ በኩል ግን ተጠሪ ከስራ ከታገዱ በኋላና ክርክሩ በሂደት ላይ እያለ ከሥራ
የተሠናበቱ መሆኑን ተረድተናል ፡፡ ከፍ ሲል እንደተገለፀው ምንም እንኳን የሥራ ውሉን
ያለማስጠንቀቂያ የሚያቋርጥ ሁኔታ ቢፈጠርም የስራ ውሉ ከመቋረጡ በፊት ሁኔታው
እስኪጣራ ውሉን ለጊዜው አግዶ ማቆየቱ የአዋጅን አንቀፅ 18 ባይቃረንም ማጣራቱ
ከተደረገ በኋላ ውጤቱ የሥራ ውሉን ለማቋረጥ የሚያስተል ከሆነ ውሉ የማይቋረጥበት
ምክንያት አይኖርም ፡፡
በተያዘውም ጉዳይ ከእግዱ በኋላ የተጠሪ የሥራ ውል
ስለመቋረጡ ለፍ / ቤቶቹ ተገልጿል ፡፡ በመሆኑም ክስ የቀረበበት ምክንያት በመቋረጡ
መዝገቡን በፍ / ሥ / ሥ / ህ / ቁ .280 መሠረት ሊዘጉት ወይም ክርክሩ እንዲቀጥል ካደረጉም
ተጠሪ ክሣቸውን በማሻሻል ክርክራቸውን እንዲለውጡ በማድረግ የፍ / ሥ / ሥ / ህ / ቁ .1
ተመልክቷል / ጉዳዩን ሊወስኑ ሲገባ የእግዱ አብቅቶ ተጠሪ ከስራ በተባረሩበት ሁኔታ
እግዱ ህገ - ወጥ ነው በማለት ተጠሪ ወደ ስራቸው እንዲመለሱ መወሠናቸው ተገቢ ሆኖ
አላገኘነውም ፡፡
ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ነቱ ግልባ
ቀን 13 -1 -52
ለመ / ቤት ይመር /
ከዚህ በተጨማሪም ተጠሪ ሥራ ሣይሠሩ ለቆዩበት ጊዜ ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፈላቸው ተወስኗል ፡፡ ሆኖም በአ / ቁ .42 / 85 አንቀፅ 54 / 1 / ውዝፍ ደመወዝ ሊከፈል የሚገባው ለተሠራ ሥራ ብቻ መሆኑ በመ / ቁ 8159 ትርጉም ተሠጥቶበታል ፡፡ ስለዚህ ውዝፍ ደሞዝ እንዲከፈል የተሠጠውም ውሣኔ የአዋጁን ድንጋጌ ያላገናዘበ ነው ፡፡
ው ሣ ኔ 1- የፌ / መ / ደረጃ ፍ / ቤት በመ / ቁ .31 / 93 በ 21 / 9 / 94 ውሣኔ እና
የፌ / ከፍተኛ ፍ / ቤት በመ / ቁ .00586 በ 29 / 07 / 97 የሰጠው ውሣኔ ተሽረዋል ፡፡ 2- አመልካች ተጠሪን ከሥራ ያሠናበተው በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም
የሚለውን ነጥብ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ የመሠለውን እንዲወስን ጉዳዩ ለፌ / መ / ደረጃ ፍ /
ቤት ተመልሷል ፡፡ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ ፡፡ መዝገቡ ተዘግቷል ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
ፈያራል ( በቅላይ ፍርድ
ተክል ግልባታ
ን ገፅ --የኝ
You must login to view the entire document.