አለመሆናቸውን
የሰበር መ / ቁ 23881
ዳኞች፡- 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
2. አቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ 3. አቶ ሐጎስ ወልዱ 4. አቶ መስፍን እቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሠ አመልካች የኢት / ንግድ ባንክ ነ / ፈጅ ቀረቡ ተጠሪ አቶ አብደላ ተጂ አልቀረበም
መዝገቡ የተቀጠረው ክሱን ለመስማት ሲሆን ተጠሪ አልቀረበም :: አመልካች በ 2 / 10 / 98 በተፃፈ የቃለ መሐላ ማመልከቻ ተጠሪ መጥሪያውን ለመቀበል ፈቃደኛ
ገልፆ መጥሪያውን መልሷል ፡፡
ት ዕ ዛ ዝ
ተጠሪ ክስ በሚሠማበት ቀን ስላልቀረቡ ጉዳዩ በሌሉበት ይታያል ፡፡
በኩል የአመልካች ነ / ፈጅ ሲያስረዱ ተበዳሪ / ከፋይ ሲመጣ መጀመሪያ
የሚከፈለውን ገንዘብ ልክ ይሞላና ለተቀባዩ ይሠጣል ተቀባዩ ገንዘቡን ያረጋግጣል ፡፡
የተቀበለውን ገንዘብ በኖት በኖት ለያይቶ ይፅፋል ማለትም ባለመቶ ኖት ፣ ባለሃምሣ ኖት
ወዘተ ብዛቱን ለይቶ ይፅፋል ፡፡ በተያዘው ጉዳይ ደረሰኙ ላይ ያለውን የገንዘብ መጠን
የሞሉት ተጠሪ ናቸው ፡፡ በዛ ላይ ተጠሪው ቀሪ ዕዳ አለባቸው ፡፡ ቀሪ ሂሣብ የለባቸውም
በማለት ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ / ቤት የገለፀው በራሱ ነው ብለዋል ።
ይህ ችሎትም የሰበር አቤቱታ የቀረበበትን የውሣኔ አግባብ ካለው የሕጉ ድንጋጌ
አኳያ መርምሯል ፡፡
የቀረበውም ሰ .
ፍ ር ድ
ለሠበር አቤቱታው መነሻ የሆነውን ውሣኔ የሠጠው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ / ቤት
ተጠሪ በአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍ / ቤት ባቀረቡት ክስ ከአመልካች ባንክ ለተበደሩት
ብድር ከከፈሉት ገንዘብ ውስጥ ብር 6000 የከፈሉበት ደረሠኝ ላይ በቁጥር 600 ብር
በአሃዝ 6000 ብር ተብሎ በመፃፉ ባንኩ 600 ብር ብቻ እንደከፈሉ በመቁጠር ቤታቸውን
በሃራጅ ሊሸጠው ስለሆነ ሽያጩ እንዲታገድላቸው ጠይቀዋል ፡፡ ፍ / ቤቱም ተጠሪ የከፈሉት
ገንዘብ ብር 6000 ቢሆንም ቀሪ እዳ ስላለባቸው ባንኩ ቤታቸውን እንዳይሸጥ ሊያግድ
የማይችል መሆኑን ገልፆ በዚህ በኩል የቀረበውን የተጠሪውን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል ።
የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ / ቤትም ተጠሪ የከፈሉት ብር 6000 ከመሆኑም ሌላ ቀሪ እዳ
የሌለባቸው በመሆኑ ቤታቸው ሊሸጥ አይገባም በማለት ወስኗል ፡፡ የአሁኑ የሠበር አቤቱታ
ውሣኔ ላይ ነው ::
ይህ ችሉትም በባንክ ሥራ የሂሣብ አሠራር ስህተት ሲፈፀም ውጤቱ ምንድነው
የሚለውን
ለመመርመር
አቤቱታው
እንዲቀርብ
ተጠርተው
ባለመቅረባቸው ጉዳዩ በሌሉበት ታይቷል ፡፡
ከፍ ሲል እንደተገለፀው ተጠሪ ለአመልካች ለከፈሉት ገንዘብ የተሰጣቸው ደረሠኝ
ላይ በአሃዝና በቁጥር የተገለፀው የገንዘብ መጠን ልዩነት ያለው ቢሆንም ሁለቱም ፍ / ቤቶች
6000 ብር ተብሎ በአሃዝ የተፃፈውን ደረሰኝ ባንኩ ራሱ ያዘጋጀው በመሆኑ ሰነዱም
በሰው ማስረጃ ሊስተባበል ስለማይችል ተጠሪ የከፈሉት ይህንኑ ገንዘብ ነው ሲሉ የኦሮሚያ
ጠቅላይ ፍ / ቤት በተጨማሪ ይኸው የገንዘብ መጠን ደግሞ ሲቀነስ ተጠሪ ቀሪ እዳ
አይኖርባቸውም በማለት ቤታቸው እንዳይሸጥ ወስኗል ።
በዘወትር የሂሣብ አሠራር በአንዳንድ አጋጣሚዎች የሂሣብ ስሌት ወይም የቁጥር
አፃፃፍ ስህተት ሊፈጠር የሚችል መሆኑ አሌ የሚባል አይደለም ፡፡ ይህ አይነቱ ስህተት
በሚፈጠርበት ጊዜ ግን ስህተቱ ሊታወቅ የሚችለው አስፈላጊው ማስረጃ ሁሉ ቀርቦ ሂሣቡ
ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ግልባጭ
ቀን // - / - 5
ተጣርቶ ከቀረበ በኋላ ነው :: ማንኛውም ፍሬ ነገር ሕጉ በሌላ አኳኋን እንዲረጋገጥ ወይም
እንዲስተባበል ገደብ ካላበጀለትም በቀር በየትኛውም ዓይነት ማስረጃ ሊረጋገጥ ወይም
ሊስተባበል የሚችል በመሆኑ የሂሣብ ስህተት መፈጠሩን ማስረዳት የሚችል በቂ ማስረጃ
ሁሉ ሊቀረብ ይችላል ፡፡
በተያዘውም ጉዳይ ለተጠሪ የተሠጠው ደረሰኝ ላይ በቁጥርና በአሃዝ በተገለፀው
የገንዘብ ልክ በአፃፃፍ ስህተት ምክንያት ልዩነት በመፈጠሩ ተጠሪ የከፈሉትን ትክክለኛ
የገንዘብ መጠን ማወቁን አስቸጋሪ አድርጎታል ፡፡ በዚህም ምክንያት በደረሰኙ ላይ ከተገለፁት
ሁለት የተለያዩ የገንዘብ መጠኖች ውስጥ በትክክል የተከፈለውን ገንዘብ ለማወቅ ይቻል
ዘንድ አግባብነት ያለው ማስረጃ ሁሉ ቀርቦ ሊታይ ይገባል ፡፡ የሥር ፍ / ቤቶች ግን ደረሰኙ
በሌላ ማስረ
ሊስተባበል እንደማይችል አድርገው በአመልካች የውስጥ ተቆጣጣሪ ኦዲተሮች
ተጠሪው ብር 600 ( ስድስት መቶ ) ብቻ የከፈሉ መሆኑ ተረጋግጦ የቀረበውን ያለበቂ
ምክንያት ሣይቀበሉት ቀርተዋል ፡፡ ፍ / ቤቶች የቀረበላቸውን ማስረጃ መቀበልም ሆነ ውድቅ
ማድረግ ያለባቸው
ሕጋዊ ምክንያት ሲኖራቸው ብቻ ነው :: ነገር ግን የሥር ፍ / ቤቶች
በአሃዝ የተፃፈው
በቁጥር ከተፃፈው
የበለጠ ተቀባይነት ያገኘበትን ሕጋዊ ምክንያት
ካለመግለፃቸውም ሌላ በኦዲተሮች ተረጋግጦ የቀረበውን ማስረጃ ያለበቂ ምክንያት ውድቅ
በማድረግ ተጠሪ የከፈሉት ብር 6000 ( ስድስት ሺህ ) ነው ሲሉ የደረሱበት መደምደሚያ
ሕጉን መሠረት ያላደረገ ነው ፡፡
ው ሣ ኔ
1 / የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ / ቤት በመ / ቁ 25807 በ i8 / 04 / 98 የሰጠው ውሣኔ
ተሽሯል ፡፡
2 / የአርሲ ዞን ከፍተኛ ፍ / ቤት በመ / ቁ 04442 በ 26 / 07 / 97 የሰጠው
ውጭ ተሻሽሏል ፡፡
3 / ተጠሪ የከፈሉት ብር 600 ( ስድስት መቶ ) በመሆኑና ቀሪ ዕዳ ያለባቸው
በመሆኑ ባንኩ ቤታቸውን በጨረታ እንዳይሸጥ ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት
ፌዴ ... እንተላ ናርድ ቤት
ትክል ግልባጭ
ቀን //// W
የለውም ፡፡ በመሆኑም ጨረታው ሊቀጥል ይገባል ፡፡
4 / ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ ፡፡ መዝገቡ ተዘግቷል ፡፡
ለመ / ቤት ይመለስ ፡፡
ነ r ተ ትክክል ግልባጭ
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
ተ.ወ ፊርማ
You must login to view the entire document.