×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 22795

      Sorry, pritning is not allowed

ያቀረበችውን ክስ የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በአዋጅ
የሰበር መ / ቁ 22795
ዳኞች፡ 1. አቶ ከማል በድሪ
2. አቶ ፍስሐ ወርቅነህ
3. አቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ
4. አቶ መስፍን ዕቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሠ
አመልካች ወ / ሮ ፋጡማ አብዱልሐይ
መልስ ሰጭ፡- የሆሣዕና የመኖሪያ ቤት ሕብረት ሥራ ማህበር
ፍ ር ድ
ጉዳዩ ለዚህ ችሎት የቀረበው ለመልስ ሰጭ የከፈልኩት ገንዘብ ወይም ቦታ
ያስረክበኝ በሚል አመልካች
ቁጥር 147/91 አንቀጽ 46 እና 47 መሠረት ጉዳዩ የሚታየው በእርቅ ወይም በሽምግልና
ዳኝነት ስለሆነ ፍርድ ቤቱ ስልጣን የለውም በማለት ውድቅ በማድረግ በሰጠው ውሣኔ ቅር
በመሰ ት አመልካች የሰበር አቤቱታ በማቅረቧ ነው ። ጉዳዩ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ
በተሰጠው
ትእዛዝ መሠረት አመልካችና መልስ ሰጭ ክርክራቸውን ለችሎቱ በቃል
አሰምተዋል ፡፡
ይህ ችሎትም በአዋጅ ቁጥር 147/91 አንቀጽ 46 እና 47 መሠረት ጉዳዩ
የሚታየው በእርቅ ወይም በሽምግልና ዳኝነት ስለሆነ ፍርድ ቤቱ ስልጣን የለውም በሚል ክሱ
ውድቅ የተደረገው በአግባቡ ነው ? ወይስ አይደለም ? የሚለውን የሕግ ነጥብ መሠረት
በማድረግ ጉዳዩን መርምሯል ፡፡
ከላይ እንደተመለከተው ለመልስ ሰጭ የከፈልኩት ገንዘብ ወይም ቦታ ያስረክበኝ
በሚል አመልካች ያቀረበችውን ክስ በስር ፍርድ ቤት ውድቅ የተደረገው አዋጅ ቁጥር
147/91 አንቀጽ 46 እና 47 መሠረት ጉዳዩ የሚታየው በእርቅ ወይም በሽምግልና ዳኝነት
እንደሆነ ተደንግጓል በሚል ነው :: በመሆኑም አዋጅ ቁጥር 147/91 አንቀጽ 46 እና 47
ለጉዳዩ አግባብነት ያላቸው መሆን አለመሆኑን መመርመር ያስፈልጋል ፡፡
የአዋጅ ቁጥር 147/91 አንቀጽ 46 እና 47 በአዋጁ አንቀጽ 49 የተመለከቱት
ክርክሮች በእርቅና በሽምግልና ዳኝነት የሚያልቁ መሆኑን ይደነግጋል ፡፡ ክርክሩ በአዋጁ
አንቀጽ 49 ከተመለከቱት አይነቶች ውጭ ከሆነ አንቀጽ 46 እና 47 ለጉዳዩ አግባብነት
ያላቸው አይሆኑም :: በአንቀጽ 49 የተመለከቱት የክርክር አይነቶች በአባላት በቀድሞ
አባላትና በቀድሞ አባላት ወኪሎች ወይም በሞት በተለዩ አባላት ስም መብት የሚጠይቁ
ሰዎች መካከል የሚነሣ ክርክር በአባላት በቀድሞ አባላት ፣ በቀድሞ አባላት ወኪሎች ወይም
በሞት በተለዩ አባላት ስም መብት በሚጠይቁ ሰዎችና በማህበሩ ስራ አመራር ኮሚቴ
በማናቸውም ሹም በወኪሉ ወይም በማህበሩ ሰራተኛ መካከል የሚነሣ ክርክር እና በማህበሩ
ወይም በስራ
አመራር ኮሚቴ
ወይም በማንኛውም የቀድሞ የስራ አመራር ኮሚቴ
በማንኛውም ሹም ወኪል ወይም ሰራተኛ ወይም የቀድሞ ሹም የቀድሞ ወኪል ወይም
የቀድሞ ሰራተኛ ተጠሪው ወራሾች ወይም ወኪሎቹ ወይም በሞት በተለዩ የማህበሩ ሹሞች
ወኪሎች ወይም ሰራተኞች መካከል የሚነሱ ክርክሮች ናቸው ::
በዚህ ጉዳይ አመልካች የገንዘብ መዋጮውን ከከፈላችሁ
መዋጮ ባልከፈሉት
የመልስ ሰጭ ማህበር አባላት ምትክ ተተክታችሁ ቤት ታገኛላችሁ ተብዬ ገንዘብ ከፍያለሁ
ባይ ናቸው :: አመልካች የማህበሩ አባል ነኝ የማይሉ ሲሆን የማህበሩ አባል ስለመሆናቸው
የተረጋገጠ ነገር የለም :: ይህም አመልካች ከከፈላችሁ መዋጮ ባልከፈሉት የመልስ ሰጭ
ማህበር አባላት ምትክ ተተክታችሁ ቤት ታገኛላችሁ ተብዬ ገንዘብ ከፍያለሁ ስለሆነም ቤቱ
ይሰጠኝ ወይም የከፈልኩት ገንዘብ ይመለስልኝ በማለት በማህበሩ ላይ የመሠረቱት ክስ ከላይ
በተመለከቱትና በአዋጅ ቁጥር 147/91 አንቀጽ 49 ከተመለከቱት ክርክሮች ውጭ መሆኑን
ያሣያል ። ይህ ከሆነ ደግሞ ጉዳዩ በአዋጁ አንቀጽ 46 እና 47 የሚሸፈን አይሆንም ።
በመሆኑም ይህ ችሎት የስር ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረበችውን ክስ የፌዴራል የመጀመሪያ
ደረጃ ፍርድ ቤት በአዋጅ ቁጥር 147/91 አንቀጽ 46 እና 47 መሠረት ጉዳዩ የሚታየው
በእረቅ ወይም በሽምግልና ዳኝነት ስለሆነ ፍርድ ቤቱ ስልጣን የለውም በሚል ውድቅ
በማድረግ የሰጠው ትእዛዝ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝቶታል ፡፡
ው ሣ ኔ
- ጉዳዩን ለማየት ፍርድ ቤት ስልጣን አለው በማለት ተወስኗል ፡፡
- የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ክርክሩን ከቆመበት በማስቀጠል ውጭ እንዲ
ሰጥ ተመልሶለታል ፡፡ ይፃፍ ፡፡
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ.ቁ 08046 ኅዳር 22 ቀን 1997
ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝና የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ.ቁ 35632
ታህሣሥ 04 ቀን 1998 የሰጠው ትእዛዝ ተሽረዋል ፡፡ ይፃፍ ፡፡
ግራ ቀ - በዚህ ችሎት ያወጡትን ወጭና የደረሰባቸውን ኪሣራ የየራሣቸውን
ይቻሉ ፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል ።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?