ወይስ የለውም ? የሚለውን የሕግ ነጥብ የሚመለከት ነው ፡፡
የሰበር መ / ቁ 23984
ቀን ሐምሌ 19/1998
ዳኞች፡- 1. አቶ ፍሥሐ ወርቅነህ
2. አቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ
3. አቶ ጌታቸው ምህረቱ
4. አቶ መስፍን እቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሠ
አመልካች፡- ግዮን ሆቴሉች ድርጅት ነ / ፈጅ ቀረበ
መለስ ሰጭ፡- ወ / ት አስቴር ጫኔ ጠበቃ ቀረቡ
ፍ ር ድ
በዚህ ጉዳይ ለሰበር
ችሉት የቀረበው ክርክር ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠርኩ
ይወሰንልኝ የሚል ዳኝነት በመጠየቅ የሚቀርብ ክስ የክስ ምክንያት / ause of action / አለው ?
የደሴ ከተማ ወረዳ ፍ / ቤት መ / ሰጭ ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠርኩ ይወሰንልኝ
በማለት ያቀረቡትን ክስ በመቀበል አከራክሮ ውጭ ሰጥቷል ፡፡ በውሣኔው ላይ ይግባኝ
የቀረበለት ይግባኝ ሰሚው ፍ / ቤትም ከላይ የተመለከተውን የሕግ ነጥብ ሣይመረመር
አልፎታል ፡፡
አመልካች በዚህ ችሎት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ጉዳዩ ለሰበር ችሎት
እንዲቀርብ በተሰጠው ትእዛዝ መሠረት መ / ሰጭ መልስ ሰጥቷል ፡፡
ችሎቱም ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠርኩ ይወሰንልኝ የሚል ዳኝነት በመጠየቅ
የሚቀርብ ክስ የክስ ምክንያት / cause of action / አለው ? ወይስ የለውም ? የሚለውን የሕግ
ነጥብ መሠረት በማድረግ አቤቱታ ያቀረበበትን ውጭ መርምሯል ፡፡
ይህ ችሎት በመ.ቁ 16273 ጥቅምት 22 ቀን 1998 በሰጠው ውጭ አግባብነት
ያላቸውን የሕጉን ድንጋጌዎች በመተርጎም አንድ ሰራተኛ ከውሉና ከአሰሪና ሠራተኛ ሕጉ
‹ ድ ቤት
አንፃር ሊያገኘው የሚገባና የቀረበት ጥቅም ካለ የቀረበለት ጥቅም እንዲሰጠው መጠየቅ / ክስ
ማቅረብ / የሚችል ሲሆን ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠርኩ ይወሰንልኝ ብቻ የሚቀርብን ክስ
የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሣኝ ቦርድም ሆነ የስራ ክርክር ችሎት ተቀብለው ሊያዩ
የሚችሉበት የሕግ ምክንያት የለም በማለት የሕግ ትርጉም ሰጥቷል ።
በዚህ ጉዳይም የደሴ ከተማ ወረዳ ፍ / ቤት መ / ሰጭ ያቀረቡትን ላልተወሰነ ጊዜ
እንደተጠቀርኩ ይወሰንልኝ በማለት ያቀረቡትን ክስ የክስ ሣክንያት የለውም በማለት ውድቅ
ማድረግ የነበረበት ሲሆን ጉዳዩን ተቀብሎ በማከራከር ውጭ በመስጠቱ መሠረታዊ የሕግ
ስህተት ፈጽሟል ፡፡
ው ሣ ኔ
የደሴ ከተማ ወረዳ ፍ / ቤት በመ.ቁ 10756 የሰጠው ውሣ የደ / ወሎ መስተዳድር
ዞን ከፍተኛ ፍ / ቤት በመ.ቁ 07370 የሰጠው ትእዛዝ / ውጫ / ተሽሯል ፡፡
በዚህ ችሎት ያወጡትን ኪሣራ የየራሣቸን ይቻሉ ፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል ፤ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ፡፡
ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ግልባጭ
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት