×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 16378

      Sorry, pritning is not allowed

በነበረፀሐይ ታደሰ 2. አቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ
የሰ / መ / ቁ .16378 ታህሣስ 17 ቀን 1998 ዓ.ም 8. ኦቶ ተገኔ ጌታነህ 4. አቶ ዳኜ መላኩ
5. አቶ መስፍን ዕቁስዮናስ ኣመልካች፡- የ 10 ዓለቃ ጌታቸው ባዩ ተጠሪ፡- በቤ / ጉ / ክ / መ / ማህበራዊ ዋስትና ባለስልጣን ቅ / መ / ቤት
ስለ ጡረታ መብት የመንግስት ሠራተኛ ጡረታ ከወጣ በኋላ ሌላ የመንግሥት መስሪያ ቤት ተቀጥሮ ስለመስራት - ድንጋጌ ቁጥር 46/53 እና አዋጅ ቁጥር 209/55 አንቀጽ 30 ( 2 )
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ / ቤት አንድ የመንግስት ሠራተኛ ጡረታ ከወጣ በኋላ ተመልሶ በመንግስት መስሪያ ቤት በመቀጠር ደመወዝና የጡረታ አበል በጣምራ ከወሠደ የጡረታ እበሉን መመለስ አለበት ማለት የአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍ / ቤት የሠጠውን ውሳኔ በመሻሩ የቀረበ አቤቱታ ። ውሳኔ፡- የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ / ቤት
ውሳኔ ተሻሽሏል ። 1- አንድ የመንግስት
ተከፈለው ከሆነ በሌላ የመንግስት መስሪያ ቤት ተቀጥሮ ደሞዝ እና የጡረታ አበል አጣምሮ መቀበል አይቻልም ፡፡ 2- አንድ የመንግስት ህይራተኛ
እየተከፈለው በሌላ በመንግስት መስሪያ ቤት
ደመወዝ ከወሰደ ከጡረታ አበሉ ወይም ከወሰደዉ ደመወዝ
በመጠን የሚያነሰዉን ይመልሳል ፡፡
የመ / ቁ .16378
ታህሣሥ 17 ቀን 1998 ዓ.ም
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ
አብዱልቃድር መሐመድ
ተገኔ ጌታነህ
ዳኜ መላኩ
መስፍን ዕቁበዮናስ
አመልካች የ 10 አለቃ ጌታቸው ባዩ ቀረበ
ተጠሪ፡ ሰቤ / ዝ / ክ / መ / ማህበራዊ
ባለሥልጣን
ቅ / መ / ቤት ነገረፈጅ አቶ ፈርተውሃል ኃይለጊዮርጊስ ቀረበ ፡፡
መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል ፡፡
ፍ ር ድ
በዚህ መዝገብ ለሰበር የቀረበው ክርክር አንድ የመንግሥት ሠራተኛ
ጡረታ ከወጣ በኋላ ተመልሶ በመንግሥት መሥሪያ ቤት በመቀጠር ደመወዝና
የጡረታ አበል በጣምራ መውሰድ ይችላል አይችልም ፣ ሁለቱን በጣምራ ወስዶ
ከተገኘ የጡረታ አበሉን ለመመለስ ይገደዳል አይገደድም የሚለውን ጉዳይ
የሚመለከት ነው ፡፡
ክርክሩን በመጀመሪያ ደረጃ ያየው የአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍ / ቤት የአሁኑ
አመልካች ጡረታ ከወጣ በኋላ ተመልሶ በሌላ የመንግሥት መሥሪያ ቤት
በመቀጠር ደመወዝና የጡረታ አበል በጣምራ ሲወስድ የቆየ መሆኑ ቢረጋገጥም
ደመወዙንም ሆነ የጡረታ አበሉን የሚመልስበት የሕግ ምክንያት የለም በማለት
የወሰነውን
የቤንሻንጉል
መንግሥት
ፍ / ቤት
በፍ / ሥ / ሥ / ሕ / ቁ .348 ( 1 ) መሠረት በመሻር ቀደም ሲል በሥራ ላይ በቆየው የጡረታ አዋጅ ቁጥር 209/55 አንቀጽ 30 / 2 / መሠረትም ሆነ
በኋላ ተሻሽሉ , በወጣው አዋጅ ቁጥር 345495 , አንቀጽ 46 / 3 / መሠረት
እንድ የመንግሥት ሠራተኛ ጡረታ ከወጣ በኋላ እንደገና በመንግሥት
መሥሪያ ቤት በመቀጠር ደመወዝ ማግኘት ከጀመረ የጡረታ አበል እና
ሊወሰድ አይችልም ፣
የጡረታ አበሉ
ይቆያል ፣ ስለዚህ 10 ኣለቃ ጌታቸው ባዩ ሲቀበል የቆየውን የጡረታ አበል
መመለስ ይገባዋል በማለት ወስኗል :: አመልካች ከየካቲት 1 ቀን 1986 ዓ.ም
ጀምሮ እስከ ታህሣሥ 30 ቀን 1993 ዓ.ም ድረስ ያለአግባብ ሲቀበል ቆይቷል
የተባለው የጡረታ አበል በአጠቃላይ
ብር 9000 ሲሆን
የክልሉ ጠቅላይ
ፍ / ቤትም እንዲመልስ የወሰነው ይህንኑ ገንዘብ ነው ፡፡
የሰበር አቤቱታው በዚህ ምክንያት የቀረበ ነው ። አመልካች ሲቀበል
የቆየውን የጡረታ አበል መመለስ አለበት በሚል በተሰጠው ውሣኔ መሠረታዊ
የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት ነው ለሰበር አቤቱታ ያቀረበው ።
አቤቱታው
ተመርምሮ ጉዳዩ ለሰበር ችሉት እንዲቀርብ በመወሰኑ
በአመልካች በኩል የቀረበው ማመልከቻ ለኣሁኑ ተጠሪ እንዲደርሰው ተደርጉ
የማህበራዊ
በጽሑፍ መልስ ሰጥቶበት
ተከራክሯል ፡፡
በማህበራዊ ዋስትና ባለሥልጣን በኩል የቀረበው w ክር ጠቅለል ባለ መልኩ ሲታይ አንድ የጡረታ መብቱ የተከበረለት ሠራተኛ እንደገና በመንግሥት መሥሪያ ቤት ደመወዝ በሚያስገኝ ሥራ ላይ ከተቀጠረ የጡረታ ሕጉ የጡረታ አበሉ ወዲያውኑ የሚቋረጥ መሆኑን ይደነግጋል ፡፡ አመልካች ጡረታ ከወጣ በኋላ እንደገና በመንግሥት መሥሪያ ቤት ደመወዝ በሚያስገኝ ሥራ ላይ እንደተቀጠረ ለማህበራዊ ዋስትና ባለሥልጣን መሥሪያ ቤት በማሣወቅ ያጡረታ
አበሉ እንዲቋረጥ ማድረግ ሲገባው ደብቆ ደመወዝና የጡረታ አበል ያለአግባብ
በጣምራ ሲቀበል ቆይቷል ፡፡ መሥሪያ ቤቱ ኣመልካች ጡረታ ከወጣ በኋላ እንደገና በመንግሥት መ / ቤት ደመወዝ በሚያስገኝ ሥራ ላይ መቀጠሩን የሚያውቅበት እንዲያቋርጥ ለማድረግ አይችልም ፡፡ የጡረታ አበሉን ሲከፍለው የቆየው ደመወዝ ማግዐቱን እያወቀ አይደለም ፡፡ አመልካች በሕግ የጡረታ አበል ስለመቋረጡ አላውቅም የሚለው
መከላከያ መልስ ሊሆነው አይችልም ፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍ / ቤት በጉዳዩ ላይ
ይዘት ያለው ነው ።
የ … ችርጽ ስራ አቆየበት የመንግሥት መሥሪያ
ችሉቱም አንድ የመንግሥት ሠራተኛ ጡረታ ከወጣ በኋላ እንደገና ተመልሶ ደመወዝ በሚያስገኝ የመንግሥት ሥራ ሊቀጠር ከቻለ ደመወዝና የጡረታ አበል አጣምሮ ሊቀበል ይችላል አይችልም ፤ የአሁኑ አመልካች ጡረታ ካወጣ በኋላ ደመወዝ በሚያስገኝ የመንግሥት ሥራ ተቀጥሮ ከደመወዝ ጉን ሲቀበል የቆየውን የጡረታ አበል ለመመለስ ይገደዳል ኣይገደድም የሚለውን ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መርምሯል ።
የኣሁኑ አመልካች ቀደም ሲል ሲሰራ ከቆየበት የመንግሥት መሥሪያ ከታህሣሥ 1 ቀን 1985 ዓ.ም ጀምሮ በጡረታ እንዲገለል ተደርጉ የተወሰነላትን የጡረታ አበል ማግኘት ከጀመረ በኋላ ከየካቲት 1 ቀን 1986 ዓ.ም ጀምሮ ደመወዝ በሚያስገኝ ሌላ የመንግሥት ሥራ ተቀጥሮ እስከ ታህሣሥ 30 ቀን 1993 ዓ.ም ድረስ በመሥራት ደመወዝና የጡረታ አበል አጣምሮ ሲቀበል የቆየ መሆኑ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ነው :: ከሣሽ የሆነው የአሁኑ ተጠሪ ተከሣሹ የእሁኑ አመልካች ደመወዝና የጡረታ አበል አጣምሮ ሲቀበል : የቆየው ያለአግባብ ስለሆነ የጡረታ አበሉን ሊመልስ ይገባል በሚል የከሰሰው በታህሣሥ ወር 1994 ዓ.ም ነው ፡፡ ይኼው ከተረጋገጠ በዚህ ጉዳይ ተፈፃሚ የሚሆነው በኋላ የወጣው አዋጅ ቁጥር 345/95 ሣይሆን በወቅቱ ድርጊቱ በተፈፀመበት ጊዜ በሥራ ላይ የነበረው ድንጋጌ ቁጥር 46/53 እና ይህንኑ ድንጋጌ በከፊል በማሻሻል የወጣው አዋጅ ቁጥር 209/55 ነው የተጠቀሰው ድንጋጌ አንቀጽ 30 / 2 / የመንግሥት ሠራተኛ ጡረታ ከወጣ በኋላ ተመልሶ ደመወዝ በሚያስገኝ የመንግሥት ሥራ ከተቀጠረ ከደመወዙ እና ከጡረታ አበሉ እንዱን መምረጥ አለበት ይላል ፡፡ ከዚህ ሕግ ድንጋጌ መረዳት የሚቻለው ደመወዝና የጡረታ አበል አጣምሮ መቀበል መሆኑን ነው ፡፡ ከሁለቱ አንዱን የመምረጥ
የመምረጥ መብት የተሰጠው ለሠራተኛው ነው ፡፡. በሕግ ከተፈቀደለት የጡረታ
የጡረታ አበል ከተቀጠረበት የመንግሥት ሥራ ከሚያገኘው ደመወዝ የበለጠ ይጠቅመኛል የሚለውን የመምረጥ
ስለተሰጠው በሚያስገኝ የመንግሥት ሥራ እንደተቀጠረ በአካባቢው
የማህበራዊ ባለሥልጣን
ሥሪያ ቤት በማሣውቅ ምርጫው እንደሆነ መግለጽ ይኖርበታል ፡፡ የበለጠ የሚጠቅመኝ አዲሱ ደመወዝ ነው ካለ የጡረታ አበሉ
እንዲቋረጥ ማድረግ አለበት ። አንድ የመንግሥት ሠራተኛ ጡረታ ከወጣ በኋላ
ራሱ ወይም ቀጣሪው መሥሪያ ቤት ለማህበራዊ ዋስትና ባለሥልጣን ካላሣውቀ
በቀር ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የሚያውቅበት መንገድ ስለሌለ ተከታትሉ የጡረታ አበሉን ማቋረጥ ነበረበት የሚለው ከጡረታ ሕጉ አኳያ ሲታይ ተቀባይነት የለውም ፡፡
ጡረታ የወጣው ሰው ደመወዝ በሚያስገኝ የመንግሥት ሥራ ተቀጥሮ አዲስ ደመወዝ እና የጡረታ አበል አጣምሮ ሲቀበል የቆየ መሆኑ ከተረጋገጠ በሕጉ ምን ይደረጋል ? የሚለው ሲመረመር ሕጉ ደመወዙን ወይም የጡረታ እበሉን ይመልሣል የሚል ድንጋጌ ባይኖረውም ሕጉ ደመወዝና የጡረታ አበል አጣምሮ መቀበል ኣይቻልም ከተባለ አጣምሮ ሲቀበል የቆየውን በሕግ ያልተፈቀደለትን ገንዘብ የማይመልስበት ምክንያት የለም ፡፡ የአሁኑ ተጠሪ አመልካች ከደመወዝ ጎን ለጉን ሲቀበል የቆየውን የጡረታ አበል እንዲመልስ ጠይቋል ፡፡ ሆኖም ኣመልካች በወቅቱ በሕጉ በተሰጠው ከኣዲሱ ደመወዝ እና የጡረታ አበል አንዱን የመምረጥ መብት ስላልተጠቀመ ሊመልስ የሚገባው ሲቀበል ከቆየው ደመወዝና የጡረታ አበል አነስተኛ ሆኖ የተገኘውን ገንዘብ ነው :: በሕጉ ላይ በተገለፀው መሠረት ሊመርጥ ሲችል ኖሮ ከሁለቱ ከፍ ያለውን ገንዘብ ይመርጣል ተብሎ ይገመታል ፡፡ ከተቀጠረበት ሥራ የሚያገኘው ደመወዝ ዝቅተኛ ሆኖ የጡረታ አበሉ ከፍተኛ ከሆነ የጡረታ እበሉን ትቶ የሆነውን ደመወዝ ይመርጣል ለማለት ያስቸግራል ። ፍትሐዊም የሚሆነው አጣምሮ ሲቀበል ከቆየው ደመወዝና የጡረታ አበል መካከል ዝቅተኛ የሆነውን እንዲመልስ ማድረግ ነው ፡፡
ው ሣ ኔ . በዚህ
በፍ / ሥ / ሥ / ሕ / ቁ 348 ( 1 ) መሠረት ተሻሽሉ የአሁኑ አመልካች ከየካቲት 1 ቀን 1986 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሣሥ 30 ቀን 1993 ዓ.ም ድረስ አጣምሮ ሲቀበል ከቆየው ደመወዝ እና የጡረታ አበል መካከል አነስተኛ ሆኖ የተገኘውን እንዲመልስ ወይም ለተጠሪው
እንዲከፍል ተወስኗል ፡፡ 2. በዚህ መዝገብ በተደረገው ክርክር ምክንያት የደረሰውን ወጪና ኪሣራ
ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ ፡፡ የዚህ ውሣኔ ግልባጭ ይተላለፍ ።
መዝገቡ ተዘግቷል ፡፡ ይመለስ ።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ::

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?