×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 20219

      Sorry, pritning is not allowed

33606 ሚያዝያ 18 ቀን 1997 ዓ.ም በሠጠው ውጭ ላይ ነው ::
የሠ / መ / ቁ 20219
ዳኞች አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
አቶ አብዱልቃድር መሐመድ
አቶ ጌታቸው ምህረቱ
አቶ መስፍን ዕቁበዮናስ
ወ / ት ሂሩት መለሠ
አመልካች ቶሎሣ ፈርጋሳ
መልስ ሰጪ ፦ ፊንፊኔ የደን ልማት ገበያ ድርጅት
መዝገቡን መርምረን እንደሚከተለው ፈርደናል ፡፡
ፍ ር ድ
አቤቱታው ሊቀርብ የቻለው የፌ / መ / ደ ፍ / ቤት ሐምሌ 28 ቀን 1996 ዓ.ም
በመ / ቁ 19626 በሰጠው ውሣኔ እና የፌዴ / ከ / ፍ / ቤትም ውሣኔውን በመሻር በመ / ቁ
ለአቤቱታው
አመልካች
ለፌዴ / መ / ደ / ፍ / ቤት ያቀረበው
ክስ ሲሆን የክሱ
ይዘትም አመልካች በእቃ
ሠራተኝነት ተቀጥሬ በመሥራት ላይ እያለሁ የሠሌዳ ቁጥር 4-19847 ኢኢ የሆነውን
ተሽከርካሪ ለሥራ ሚያዝያ 15 ቀን 1994 ዓ.ም ለሥራ ጉዳይ ይዘህ ከወጣህ በኋላ
ከቆመበት ቦታ ላይ በመሠረቁ የድርጅቱን ንብረት ሆነ ብለህ እንዲጠፋ ያደረክ ስለሆነ
ከየካቲት 11 ቀን 1996 ዓ.ም ጀምሮ ከሥሪ ተሠናብተሃል በማለት ያሠናበተኝ ሕገ ወጥ
ነው ፤ በመሆኑም ወደ ሥራ እንድመለስ እና ውዝፍ ደመወዜም ይከፈለኝ ሲል ጠይቋል ይህ
ክስ የቀረበለት ፍ / ቤት ግራ ቀኙ በጉዳዩ ያቀረቡበትን ክርክር እና ማስረጃ ከሠማ በኋላ
አሠሪው በከሳሽ ላይ መውሠድ የነበረበት እርምጃ በሠራተኛው የተሠራ ጥፋት በተፈፀመ
በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ መሆን ነበረበት ። ይህ በይርጋ ከአለፈ በኋላ ምንም እርምጃ
ሊወስድ አይችልም ስለዚህ ወደ ሥራው ይመልሠዋል በማለት ወስኗል ።
ይህ ውጭ በይግባኝ የቀረበለት የፌዴ / ከ / ፍ / ቤት የሥር ፍ / ቤት በይርጋ ጉዳይ
በተከራካሪዎች ያልተነሳ ስለሆነ የሕግ አግባብነት የለውም በማለት ሽሮታል ።
አመልካች ጥፋቱ ተፈፀመ ከተባለ አንድ አመት ጊዜ በላይ በኋላ የሥራ ውሌ
ሊቋረጥ አይችልም በማለት አቤቱታውን ለዚህ ፍ / ቤት አቅርቧል ፡፡ ተጠሪው ደግሞ
ባቀረበው የቃል ክርክር አመልካች በመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት በቀረበው ክርክር የይርጋ
ጥያቄን አንስተው አልተከራከሩም ፍ / ቤቱ በራሱ ተነሳሽነት የይርጋ ጊዜን አንስቶ ለመወሰን
አይችልም በማለት ሲከራከር አመልካች በበኩሉ እኔ የይርጋ ክርክርን ባልጠቅስም የጊዜ
ገደቡን ጠቅሼአለሁ በማለት ተከራክሯል ፡፡
ይህም ችሎት አመልካች ያቀረበውን የሠበር አቤቱታ እና የግራ ቀኙን ክርክር መነሻ
በማድረግ በአሠሪ እና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27 / 2 / የሠፈረውን
ያለሥራ ማስጠንቀቂያ መብት የጊዜ ወሠን ፍ / ቤቱ ሊያነሳው ይችላል ? ወይንስ አይችልም
የሚለውን ጭብጥ ይዞ ምላሽ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ አግኝቶታል ፡፡
አመልካች በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 27 ንዑስ ቁጥር 2 ላይ የተደነገገውን
አሠሪው ያለማስጠንቀቂያ ውሉን የሚያቋርጥበትን የጊዜ ወሠን ይርጋን ከሚመለከቱ
ድንጋጌዎች ጋር አንድ እንደሆኑ በመቁጠር ፍርድ ቤት ይህንን የጊዜ ወሠን በራሱ
አነሳሽነት ሊያነሳው አይችልም በማለት ተከራክሯል ፡፡ በዚህ መዝገብ የተያዘው የጊዜ ወሠን
ጉዳይ በፍ / ብ / ሕጉ አንቀጽ 1845 / ወይንም በሌሎች በርካታ አንቀፆች / ከሠፈረው የይርጋ
ደንብ ጋር የተለየ ነው ፡፡ የይርጋ ደንብ አንድ ክስ በፍ / ቤት ቀርቦ በሥረ ነገር እንዳይታይ
የሚከለክል ሲሆን የጊዜ ወሠን ሕጉ ደግሞ አንድ አሠሪ ሠራተኛውን
አዋጁ አንቀጽ
27 / 1 / ከ'ሀ '
እስከ ' ተ '
የተዘረዘሩትን ምክንያቶች በመጥቀስ ያለማስጠንቀቂያ የሥራ
ውሉን ለማቋረጥ ያለውን መብት የሚመለከት ነው : አሠሪው ምክንያቶቹን በመጥቀስ
ሠራተኛውን ለማሠናበት ወይንም ውሉን ለማቋረጥ የአንድ ወር ጊዜ ተሠጥቶታል ሲባል
o ወሰነው የይርጋ ክርክር የለም ፡፡ የፍ / ብ / ሕ / ቁ 1856
በሌላ አንፃር የማቋረጫ ምክንያቶቹን ጠቅሶ የሥራ ግንኙነቱን ለማቋረጥ ከፈለገ በአንድ ወር
ጊዜ ውስጥ እንዲፈጽመው የጊዜ ገደብ የሚጥል አስገዳጅ ሕግ ነው :: ይህ ሕግ በአሠሪው
ላይ እንደዚህ ዓይነት ግዴታ ከጣለ ደግሞ ሠራተኛው ምክንያቱ ተገልፆለት የሥራ ውሉ
አንዲቋረጥ ከተፈለገ በ 1 ወር ጊዜ ውስጥ ሊገለጽለት መብት አለው ። በመሆኑም ሕጉ
በአሠሪው እና በሠራተኛው መካከል ስራ የሚቋረጥበትን የጊዜ ወሠንን በተመለከተ
የመብት እና ግዴታ ግንኙነት ፈጠረ እንጂ አሠሪው ከሠራተኛው ጋር ያለውን የሥራ
ግንኙነት ከፍ ብሉ
በተጠቀሰው
ሕግ ላይ ከተዘረዘሩት ምክንያቶች መሠረት ያለ
ማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ ቢፈልግ ጉዳዩን ለፍ / ቤት የሚቀርብበትን የጊዜ ገደብ የሚያመለክት
አይደለም ። በመሆኑም ፍ / ቤቱ የጊዜ ወሠኑን በተመለከተ የመብት እና ግዴታ ክርክር
የሚመለከት በሚሆንበት ጊዜ የቀረበውን ክስ ይዘት መርምሮ በሥረ ነገር ውጭ መስጠትን
የሚከለክል አይደለም ፡፡ በፍ / ብ / ሕጉ ውስጥ የሠፈረውን ይርጋ ተከሳሹ ወገን ካላነሣው
ፍርድ ቤቱ በራሱ ሊያነሳ እንደማይችል በፍ / ብ / ሕ / ቁ 1856 መደንገጉ ግልጽ ነው ። ነገር
ግን ይህ ችሎት ከመዝገቡ ለመረዳት እንደቻለው የአሁን አመልካች ከሥር ፍ / ቤት ጀምሮ
ሲከራከር የነበረው የጊዜ ወሠኑ ካለፈ በኋላ ከሥራዬ ልሠናበት አይገባኝም በማለት ነው ፡፡
በመሆኑም ፍ / ቤቱ በራሱ ተነሳሽነት
ድንጋጌ ተፈፃሚነቱ ለይርጋ ድንጋጌዎች እንጂ በአሠሪና በሠራተኛው መካከል ላለው
ግንኙነት የሥራ ውል ማቋረጥ የፈለገ ወገን ያለማስጠንቀቂያ ውሉን ለማቋረጥ ያለውን
የጊዜ ወሠን የሚመለከት አይደለም ፡፡ ሰለዚህ የተጠሪ ድርጅት ይርጋን ከሥራ ውል
ማቋረጫ የጊዜ ወሠን ጋር በማመሣል የይርጋ ሕግ ለሥራ ውል ግንኙነት ማቋረጫ
የጊዜ ወሠን ሕግ ላይ ተፈፃሚ መሆን ይገባዋል በማለት ያቀረበው ክርክር የሕጉን መንፈስ ፣
ዓላማና ግልጽ ይዘት ያልተከተለ በመሆኑ ተቀባነት የለውም ፡፡
አሁን በቀረበልን ጉዳይ የተጠሪ መስሪያ ቤት አመልካችን በድርጅቱ ንብረት ላይ
ጉዳት እንዲደርስ ያደረግክ ስለሆነ በሚል ምክንያት ከሥራው ያሠናበተው የአንድ ወር ጊዜ
ካለፈ በኋላ እንደሆነ ፍ / ቤቱ ተረድቶአል ። ስለሆነም የፌዴራሉ መጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት
የሠጠው ውሣኔ በአግባቡ በመሆኑ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ / ቤት የውል ማቋረጫ ምክንያት
እንደ ይርጋ ሕግ በመቁጠር በሥር ፍ / ቤት ሊነሳ አይገባም በማለት የሠጠው ውሣ
መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ሆኖ በመገኘቱ ተሽሯል ፡፡
ው ሣ ኔ
1 ኛ / የፌ / መ / ደ / ፍ / ቤት በመ / ቁ 19626 የተሠጠው
ውሣኔ ፀንቶ የፌ / ከ / ፍ / ቤት
በመ / ቁ 33606 የሰጠው ውሣ ተሽሮአል ፡፡
2 ኛ / ግራ ቀኙ በዚህ ፍ / ቤት ያወጡት ወጪ ይቻቻሉ ።
መዝገቡ ተዘግቷል ፡፡ ይመለስ ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?