የሰበር መ / ቁ 22326
ቀን 16.2.99
መለስ ሰጭ የአዲቦ በሕግ ነጥብ በአደራ የተሰጠ ንብረት ለአደራ ሰጭው
ዳኞች፡ 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
2. አቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ 3. አቶ ጌታቸው ምህረቱ 4. አቶ መስፍን ዕቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሠ አመልካቾች፡ 1. ወ / ሮ ሸዋላንቺ ተክለሃይማኖት
2. አቶ አንተነህ ሙሉጌታ 3. ወ / ሮ መሠረት ሙሉጌታ
አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን
ፍ ር ድ
በዚህ ጉዳይ የቀረበው
የሚመለስበትን ጊዜ ነው ፡፡ የ 1 ኛ አመልካች ባለቤት የነበሩትና የ 2 ኛ እና 3 ኛ አመልካቾች
አባት የአስር አለቃ ሙሉጌታ ዳዲ በወንጀል ተጠርጥረው በመልስ ሰጭ በቁጥጥር ሥር
ሲውሉ ብር 9000 ( ዘጠኝ ሺ ) በመልስ ሰጭ በኤግዚቢትነት ተይዟል ። መልስ ሰጭ
ምርመራውን ጨርሶ ጉዳዩን ለ 0 ቃቤ ሕግ ካስተላለፈ በኋላ 0 ቃቤ ሕግ ጉዳዩ አያስከስስም
በማለት የተያዘው ገንዘብ ለባለመብቱ እንዲመለስ መጋቢት 25 ቀን 1983 ዓ.ም ለመልስ
ሰጭ ደብዳቤ ጽፏል ። አመለካቾች ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሐምሌ 21 ቀን
ባቀረቡት
ገንዘቡን ለመመለስ
ባለመሆኑ
የተጠቀሰውን ገንዘብ እንዲከፍል እንዲወሰንላቸው ጠይቀዋል ፡፡ ፍርድ ቤቱም መልስ ሰጭ
ያቀረበውን የይርጋ ክርክር በመቀበል በፍ / ብ / ሕ / ቁ 2782 ( 2 ) ፣ 2471 እና 1845
መሠረት ክሱ በይርጋ ይታገዳል በማለት ክሱን ውድቅ አድርጎታል ። ጉዳዩ በይግባኝ
የቀረበለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ብይኑን አጽንቶታል ፡፡
ከላይ የተመለከተውን ብይን በመቃወም አመልካቾች ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ
ተመርምሮ ጉዳዩ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ በተሰጠው ትእዛዝ መሠረት አመልካቾች እና
መልስ ሰጭ ክርክራቸውን ለችሎቱ በቃል አሰምተዋል ፡፡
ችሎቱም በአደራ የተሰጠ ንብረት ለአደራ ሰጭው የሚመለሰው
መቼ ነው ?
የሚለውን የሕግ ነጥብ መሠረት በማድረግ ጉዳዩን መርምሯል ፡፡
የፍትሐብሔር
ማስቀመጥ
የሚመሠረትባቸውን ሁኔታዎች ደንግጓል ። የአደራ ማስቀመጥ ሕጋዊ ግንነት አደራ ተቀባዩ
የሌላ ሰው ዕቃ ተቀብሎ በአደራ ጠባቂነት ለአደራ ሰጭው እንዲያስቀምጥለት በሚገባው
የውል ግዴታ ነው :: ከዚህ በተጨማሪ የፍ / ሕ / ቁ 2796 አንድ ሕጋዊ ሁኔታው በክርክር
ያለ ወይም የሚያጠራጥር ዕቃ በዕቃው ሕጋዊ ሁኔታ ላይ የተነሣው ጥርጣሬ ወይም ክርክር
በስምምነት ወይም በዳኞች እስኪፈታ ድረስ ዕቃው የተነሣው ጥርጣሬ ወይም ክርክር
ተጠቅሶ ለሶስተኛ ወገን ሲሆን በትእዛዝ የተቀመጠ አደራ ይባላል በማለት ይደነግጋል ።
በአደራ የተሰጠ እቃን በሚመለከት በትእዛዝ በተደረገ አደራ የትእዛዝ ባለአደራው
ዕቃውን የሚመልሰው በጉዳዩ ጥቅም ያላቸው ሁሉ ከተስማሙበት ወይም ዳኞች ካዘዙ
እንደሆነ በፍ / ብ / ሕ / ቁ 2798 በልዩ ሁኔታ ይደነግጋል ። ሆኖም በተመሣሣይ ጉዳይ ላይ
በልዩ ሁኔታ አስፈላጊ በሆነ አደራ ላይ ተፈፃሚ የሚሆን ልዩ ድንጋጌ በሕጉ
አልተቀመጠም ፡፡ በመሆኑም ከላይ እንደተመለከተው በፍ / ብ / ሕ / ቁ
አስፈላጊ በሆነ አደራ በአደራ የተሰጠው እቃ ስለሚመለስበት ሁኔታ ስለ አደራ በጠቅላላ
የተደነገጉት ድንጋጌዎች ተፈፃሚ ይሆናሉ ፡፡
የፍ / ብ / ሕ / ቁ 2781 / 2 / አደራ ተቀባዩ ለአደራ ማስቀመጥ የተወሰነው የውሉ
የጊዜ ውጭ ሲደርስ ዕቃውን ለአደራ ሰጭው ሊመልስለት ይገባል በማለት ይደነግጋል ፡፡
በዚህ ድንጋጌ መሠረት በውል ዕቃው የሚመለስበት ጊዜ የተወሰነ እንደሆነ አደራ ተቀባዩ
የሚመልሰው
የፍ / ብ / ሕ / ቁ 2786 ( 1 ) ለአደራ ተቀባዩ
ጥቅም ሲባል አደራ የተቀመጠውን እቃ
ስለመመለስ በውሉ ላይ የተወሰነ ጊዜ ከሌለ በቀር አደራ ሰጭው እንደጠየቀ እቃው
ገንዘቡ እንዳይጠፋ በማሰብ ነው !
ሊመለስለት ይገባል በማለት ይደነግጋል ፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሠረት ደግሞ በውል እቃው
የሚመለስበት ጊዜ ያልተወሰነ እንደሆነ ወይም በውል እቃው የሚመለስበት ጊዜ የተወሰነ
ቢሆንም ጊዜው የተወሰነው ለአደራ ተቀባዩ ጥቅም ካልሆነ ( ለአደራ ሰጭው ጥቅም ከሆነ
የተደረገው ወይም ለማንኛውም ወገን ጥቅም ተብሎ ያልተደረገ እንደሆነ ) አደራ ሰጭው ለዕ
ቃው መመለሻ የተወሰነው ጊዜ ካለፈ በኋላም በማንኛውም ጊዜ ዕቃው እንዲመለስለት
ከጠየቀ አደራ ተቀባዩ የተወሰነው ጊዜ አልፏል በሚል ዕቃውን አልመልስም የማለት መብት
የለውም ፡፡
በዚህ የሕግ ክፍል የአደራ ማስቀመጥ ውል በማናቸውም ፎርም ሊከናወን የሚችል
ስለመሆኑ
በቁጥር 2892
ላይ ተመልክቷል ፡፡ በያዝነው
መልስ ሰጭ ክርክር
ያስነሣውን ገንዘብ የተቀበለው የ 1 ኛ አመልካች ባለቤት የነበሩትንና የ 2 ኛ እና የ 3 ኛ
አመልካቾች አውራሽ ( አባት ) በእስር ባዋለበት ወቅት በወንጀል ድርጊት የተገ ነው በሚል
:: ይህም ገንዘቡን የተቀበለው አስፈላጊ በሆነ አደራ እንደሆነ
ያሣያል፡፡በዚህ ሁኔታ ከላይ እንደተመለከተው ገንዘቡ በፍ / ብ / ሕ / ቁ .2804 እና 2787 ( 1 )
መሠረት አደራ ሰጭው ዕቃው ( ገንዘቡ ) እንዲመለስለት በጠየቀ ጊዜ የሚመለስለት ነው ::
ጥያቄው የቀረበው በየትኛው ጊዜ ቢሆን ጥያቄው በይርጋ የሚታገድበት የሕግ አግባብ
የለም ፡፡ በመሆኑም በጉዳዩ የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የአመልካቾች ጥያቄ በአስር
ዓመት ይርጋ ይቋረጣል በማለት የሰጠውና የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያፀናው ውሣኔ
መሠረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል ፡፡
ው ሣ ኔ
• ይህ ችሉት መልስ ሰጭ በአደራ የተቀበለውን ብር 9000 ( ዘጠኝ ሺህ ብር )
ለአመልካቾች እንዲመልስ ወስኗል ፡፡
የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በመ / ቁ 170 ሰኔ 10 ቀን 1996 ዓ.ም
የሰጠውና የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ / ቁ 33491 ጥቅምት 11 ቀን
1998 የሰጠው ትእዛዝ ተሽሯል ፡፡
- ግራ ቀ በዚህ ችሎት ያወጡትን ወጪና የደረሰባቸውን ኪሣራ የየራሣቸውን
ይቻሉ ፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል ።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት