×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 20212

      Sorry, pritning is not allowed

በወረዳው ፍ / ቤት ተሰጥቶ የነበረውን ወ 4
የሰ / መ / ቁ 20212
ግንቦት 29 ቀን 1998
ዳኛች ፦ 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
2. ዓብዱልቃድር መሐመድ
3. አቶ ጌታቸው ምህረቱ
4. አቶ መስፍን እቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሰ
አመልካች ወ / ሮ አብረኸት ተክሉ
ተጠሪ፡ አቶ ገዛኢ ገ / ፃዲቅ
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል ፡፡
ፍ ር ድ ፣
ይህ ጉዳይ
ለዚህ ችሎት ሊቀርብ የቻለው የክልሉ ሰበር ሰሚ ችሎት ለክርክሩ
ምክንያት የሆነው ቤትና ቦታ አመልካች ከባለቤቷ ጋር ያፈራችው የጋራ ሀብት ነው በማለት
• ሣኔ በመሻሩ ነው ። የሥር ፍ / ቤት ውሣኔ ለዚህ
ሰበር ሰሚ ችሉት እንዲቀርብ ከተወሰነ በኋላ የግራ ቀኙ ክርክር ተሰምቷል ።
የሥር ፍ / ቤት የወረዳ ፍ / ቤቱን ውሣኔ ለመሻር መሠረት ያደረገው የአሁኑ ተጠሪ
ክርክር የተነሣበትን ቤትና ቦታ አስመልክቶ በውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ / ቤት የተረጋገጠ
የሽያጭ ምዝገባ አቅርቧል በሚል እንደሆነ ከውሣው መረዳት ችለናል ፡፡ በዚህ መዝገብ
ከአጠቃላዩ ሁኔታ መረዳት የቻልነው ዋነኛ ነገር አሁን አከራካሪ በሆነው ቦታ ላይ የአሁኗ
አመልካች ቀደም ሲለ ከባለቤቷ ጋር 125 ካ.ሜ ቦታ ገዝተውና ቤት ሠርተው ሲኖር
መቆየታቸውን ፣
በመካከላቸው በተፈጠረው አለመግባባት እንዲለያዩ ሲወሰን ንብረትን
አስመልክቶ አሁን ክርክር ካስከተለው ቦታ ላይ የሚገኘውን ቤትና ቦታ በጋራ እንዲካፈሉ
በ 6 / 11 / 94 ውጭ በማኀበራዊ ፍ / ቤት ተሰጥቶ ይህም በይግባኝ ፀድቆ ያደረገ መሆኑንም
ተገንዝበናል ፡፡ የአሁኑ ተጠሪ የሥነ ሥርዓት ሕጉ በሚፈቅደው አግባብ የክርክሩ ተካፋይ
ፌደራል ( 3፦49 X !! .. ት
ተ ie 2 ፡12
ሆኖ ፍርዱን ያስለወጠበት ሁኔታ አለመኖሩንም ይህ ችሉት በሚገባ ተረድቷል ። የአሁኑ
ተጠሪ ከዚህ ሁሉ ሕጋዊ ክንዋኔ በኋላ ቀደም ሲል በ 1984 በቃል ስምምነት ብቻ ከወ / ሮ
ፈቴን 125 ካ.ሜ. ቤትና ቦታ ገዝቼ ማዘጋጃ ቤቱ ስሙን አላዞርም ስላለኝ በድጋሚ
ስምምነት በ 1995 ተደርጎ ጠቅላላ ስፋቱ 240 ሜ.ካ የሆነ ቦታና ቤት ገዝቻለው ብሉ
በውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ / ቤት ውሉን አስመዝግቦ ተገኝቷል መባሉ ብቻ ቀደም ሲል
125 ካ.ሜ. ቦታና ቤት ላይ በሕግ አግባብ ሥልጣን በተሰጠው ማኀበራዊ ፍ / ቤት ተሰጥቶ
የነበረውን ፍርድ የሚያሽር ሆኖ አላገኘነውም ፡፡
በመሆኑም የክልሉ ጠቅላይ ፍ / ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ይህን መሠረታዊ የሕግ ነጥብ
በማለፍ የአሁኑ ተጠሪ 240 ካሜትር ቤትና ቦታ ብቸኛ ባለቤት ነው በማለት የሰጠው
ውጭ መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ብለናል ፡፡
ው ሣ ኔ
የትግራይ
ክልል ጠቅላይ ፍ / ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በ 26 / 8 / 97 በመዝገብ ቁጥር
02108 የሰጠው ውሣ በከፊል ተሻሽሏል ።
የአሁኗ ተጠሪ አከራካሪ ከሆነው 240 ካሜትር ቦታ ውስጥ 125 ካሜትር ቦታ
ላይ ያረፈው ቤትና ቦታ ከባለቤቷ ጋር በጋራ ያፈራችው ንብረት ነው ብለናል ።
ይህ ውሣኔ የአሁኑ ተጠሪ በቀረው ቦታ ላይ ያለውን መብት የሚነካ አይሆንም ።
ግራ ቀኙ ወጪና ኪሣራ ይቻቻሉ :: መዝገቡ ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ፡፡
ፌዴራል : ! : P ደ ፍርደ : ! .. ; የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ፡፡

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?