×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 22621

      Sorry, pritning is not allowed

የሰበር መ.ቁ 22621
ግንቦት 30 ቀን 1998
ዳኞች ፥ መንበረፀሐይ ታደሰ
ሐጉስ ወልዱ
ተገኔ ጌታነህ
መስፍን ዕቁበዮናስ
ሂሩት መለሰ
አመልካች፡- አቶ ዓለም ኃይሉ
ተጠሪ፡- አቶ ጥላሁን ሃይለሥላሴ
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል ፡፡
ፍ ር ድ
በዚህ መ
ክርክር የሚመለከት ነው :: ክርክሩ የተጀመረው በትግራይ ብ / ክ / መ / በቃፍታ ሑመራ ወረዳ
ፍ / ቤት ሲሆን ፤ ክርክሩ ሲጀመር ከሣሽ የነበረው አመልካች ነው አመልካች በተጠሪው ላይ
ክስ የመሠረተው ከሟች እናቱ ወ / ሮ ዝማም አብርሃ በውርስ የተላለፈለት ንብረት ( ቦታና
ቤት ) እንዲለቅለትና እንዲያስረክበው በመጠየቅ ነው ። ክሱ የቀረበለት የወረዳ ፍ / ቤትም
የሁለቱን ወገኖች ክርክር ከሰማ በኋላ ፣ አመልካች ያቀረበውን ክስ ውድቅ በማድረግ ውጭ
ሰጥቶአል ። ለሰጠው ውጭ ዋነኛ ምክንያት አድርጎ የጠቀሰው ከሣሽ ( አመልካች ) የሟች
ልጅ ቢሆንም ፤ ሟች በሕይወት እያሉ ባደረጉት ኑዛዜ ንብረቱ የእህታቸው ልጅ ለሆነው
ተከሣሽ ( ተጠሪ ) ያወረሱ በመሆኑ ኑዛዜው የሚሻርበት ምክንያት የለም ። የሚል እንደሆነም
ከውሣው ይዘት ለመገንዘብ ችለናል ፡፡ በዚህ ውሣኔ ላይ ይግባኝ የቀረበለት የከፍተኛ
ፍ / ቤትም ተመሣሣይ ምክንያት በመስጠት ውሣውን ያፀና ሲሆን ፣ የክልሉ ጠ / ፍ / ቤት
ደግሞ በስር ፍ / ቤቶች የተሰጠውን ውሣ በማሻሻል አከራካሪው ንብረት ለሁለቱም ይሁን
በማለት ወስኖአል ፡፡ አቤቱታው የቀረበውም በዚህ ላይ ነው ::
ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ትከክክል ግልባጭ
ረ / ሪና %
እንደሆነም ከም
መ " ውን ( መፅደቁን ) አይተናል ፡፡ አመልካች ለስር አቤቱታው በዚህ የፌዴራል ጠ / ፍ / ቤት ሰበር ችሉት እንዲታይ የተወሰነው ጉዳይ ቀድሞ በመሃከላችን ተጀምሮ በነበረው ክርክር በሁለታችንም ስምምነት በእርቅ አልቆ የመጨረሻ እልባት አግኝቶአል ፡፡ እርቁ ለፍ / ቤት ቀርቦ ተመዝግቦአል በማለት አመልካች ክርክሩን በየደረጃው ላዩት ፍ / ቤቶች ያቀረበው መቃወሚያ ተቀባይነት ሣያገኝ የመቅረቱ አግባብነት መመርመሩ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው :: በዚህ መሠረትም ነጥቡን አቤቱታ ከቀረበባቸው ውሣዎች እና ለጉዳዩ አወሳሰን ተገቢነት ካለው ሕግ ጋር አገናዝበን መርምረናል ፡፡
ከስር ጀምሮ ከተደረገው ክርክር ማየት እንደቻልነው ቀደም ሲል በአመልካች እና በተጠሪው መካከል በተያዘው ጉዳይ ማለትም የውርሱን ሃብት በሚመለከት በፍ / ቤት መዝገብ ተከፍቶ ክርክር ተደርጎአል ፡፡ ክርክሩ የተካሄደው ለአሁኑ አቤቱታ መነሻ የሆነውን ክርክር በመጀመሪያ ደረጃ የዳኝነት ስልጣኑ ባየው በቃፍታ ሑመራ ወረዳ ፍ / ቤት
ተመልክተናል ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ክርክሩ በፍ / ቤት ውሣኔ ከማግኘቱ በፊት ተከራካሪ ወገኖቹ በ 30 / 7 / 87 በተደረገ የዕርቅ ስምምነት ለክርክራቸው እልባት መስጠታቸውና የእርቅ ስምምነቱም በመዝገብ ቁ 60/87 በ 6 / 8 / 87 ዓ.ም በፍ / ቤቱ ተቀባይነት አግኝቶ ፍ / ቤቶች መቃወሚያውን ያቀረበው ይህን መሠረት በማድረግ ነው ፡፡
የእርቅንና
የግልግልን
ስምምነት
ስለመመዝገብ
በሚመለከት
የተደነገገው
የፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕግ ቁ 277 በንዑስ ቁጥር ( 1 ) እንዳመለከተው ክርክሩ በመሰማት ላይ
ባለበት ጊዜ ተከራካሪዎቹ ወገኖች ነገሩን በእርቅ በመጨረስ የተስማሙ እንደሆነ ፍ / ቤቱ
እርቁን ተቀብሎ በማፅደቅ ከመዝገቡ ጋር እንዲያያዝ ያደርጋል ። የእርቅ ስምምነቱ ተጽፎና
ተፈርሞ መቅረብ እንዳለበትና ፍ / ቤቱም እርቁን ተቀብሎ ከማፅደቁና ከመመዝገቡ በፊት
ሕግንና ሞራልን የማይቃወም መሆኑን ሊረዳው እንደሚያስፈልግ ድንጋጌው ያመለክታል ።
በመጨረሻም ፍ / ቤቱ እርቁን ከመዝገቡ
ጋር ካያያዘው በኋላ በተካራካሪዎቹ ወገኖች
አመልካችነት በእርቁ መሠረት እንዲፈፀም ትእዛዝ ወይም ፍርድ እንደሚሰጥ በንዑስ
ቁ ( 2 ) ተደንግጎአል ፡፡ እንግዲህ ከዚህ መገንዘብ የሚቻለው ክርክሩ በተከራካሪ ወገኖች
ፈራፊ ! : * ይ ፍርድ ትት
ትክክል ግልባ »
ቀን 2 ሱረቱ ጥ s
ስምምነት በእርቅ ከተቋጨ እና ፍ / ቤቱም ተቀብሉ በማፅደቅ ከመዘገበው እንደማንኛውም
የመጨረሻ ውሣ ያገኘ ክርክር እንደሚቆጠር ነው ። በተያዘው ጉዳይም አመልካች እና
ተጠሪ በመረጡአቸው ስድስት ሰዎች አስማሚነት ( አስታራቂነት ) ክርክራቸው በእርቅ
የጨረሱ በመሆናቸው በዚህ ጉዳይ ሁለተኛ ክርክር ሊያካሂዱ አይችሉም ፡፡ አመልካች
ተጠሪን የከሰሰው ቀደም ሲል በተደረገው የእርቅ ስምምነት መሠረት ሊፈጽምለት ባለመቻሉ
ሲሆን ፣ ይህ ደግሞ ከአፈፃፀም ክስ ተለይቶ የሚታይ አይደለም ። በመሆኑም ተጠሪ በእርቁ
ስምምነት መሠረት የአመልካች ድርሻ የሆነውን ቤት ልቀቅ ሲባል የቀድሞውን ( እኔም
የኑዛዜ ወራሽ ነኝ የሚለውን ክርክር ማንሣት አይችልም ( የፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕግ ቁ 5 ( 1 ) ) ።
የስር ፍ / ቤቶችም የተጠሪን ክርክር መቀበላቸው ትክክል አይደለም ፡፡ ሲጠቃለል አቤቱታ
ው ውሣዎች መሠረታዊ የሕግ ስህተት ያለባቸው ሆነው ተገኝተዋል ፡፡
ው ሣ ኔ
1. በወረዳ ፍ / ቤት ፣ በከፍተኛ ፍ / ቤት ፣ በጠ / ፍ / ቤት የተሰጡት እና በመጨረሻም
በትግራይ ብ / ክ / መ / ጠ / ፍ / ቤት ሰበር ችሎት በመ.ቁ 10871 በጥቅምት 21 ቀን 98 ዓ.ም
በተሰጠው ትእዛዝ መሠረታዊ
ስህተት የለባቸውም የተባሉት ውሣኔዎች በሙሉ
በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕግ ቁ . 348 ( 1 ) መሠረት ተሽረዋል ።
2. ወጪና ኪሣራ በተመለከተ ግራ ቀኝ ወገኖች የየራሣቸውን ይቻሉ፡ ። ውጫው
ለሥር ፍ / ቤት ይተላለፍ ፡፡
መዝገቡ ይመለስ ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
ፌደራል :: ተላይ ፍ . ሴት ትንንም ግልባ ! »
ቀን ? ፉ / e- %

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?