×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 19847

      Sorry, pritning is not allowed

* * ማንቦት 3 ቀን 1997 ዓ.ም. በሰጠው ውሣኔ የሕግ
ሰበር መ.ቁ. 19847
መጋቢት 22 ቀን 1998 ዓ.ም. ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
ኣቶ ፍስሐ ወርቅነህ አቶ አብዱልቃድር መሐመድ ወ / ሮ ሆሣዕና ነጋሽ
አቶ አሰግድ ጋሻው አመልካች፡- በኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር የሰሜን ቅርንጫፍ ጽ / ቤት ተጠሪ፡- አቶ ምንውየለት ውዴ
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል ፡፡
ፍ ር ድ
አመልካች ለሰበር ችሎት አቤቱታ ያቀረበው የምሥራቅ ጐጃም መስተዳድር ዞን
ከፍተኛ ፍ / ቤት በመዝ / ቁ . 6618
ስህተት ሰርቷል በማለት ነው ፡፡
ክርክሩ የተጀመረው በደብረማርቆስ ከተማ ወረዳ ፍ / ቤት ነው ፡፡ የአሁን ተጠሪ
ክስ የመሰረተው ከ 5 ዓመት በፊት በደብረማርቆስ ከተማ የሥነ ተዋልዶ ጤና
አገልግሎት ክሊኒክ ኃላፊ ሆኜ እንድሰራ ተመድቤ እንዳለሁ በተስማማሁበት ሁኔታ
አሰሪው መ / ቤት ለበርካታ አመታት ካገለገልኩበት የሥራ ቦታና ደረጃ ዝቅ በማድረግ
በደብረ ማርቆስ ሥነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት ክሊኒክ ሥር የቀበሌ ህብረተሰብ ጤና
አገልግሎት አስተባባሪ ሆኜ እንድሰራ የተመደብኩ ስለሆነ ከሥራ ቦታዬና ከደረጃ ዝቅ
ሊያደርገኝ የሚችልበት ምንም ዓይነት ምክንያት ስለሌለ ወደ መደበኛ ሥራ ቦታዬ
እንድመለስ ደመወዝ በአዲስ መዋቅር መሠረት እንዲከፈለኝ የሕክምና ፍቃድ እያለኝ
Arli እ .
ብለው 3. አይ መሆኑ . ኡ የተቆረጠ ደሞዝ እንዲመለስልኝ በማለት ነው ፡፡ የአሁንም አመልካች ቀርቦ የበኩሉን መቃወሚያና መልስ አቅርቧል ፡፡
ፍ / ቤቱም ተጠሪ በተመሣሣይ ደረጃና ደመወዝ የደብረማርቆስ ተዋልዶ ጤና ክሊኒክ የህብረት አቀፍ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት ሱፐር ይዘር ሆነው እንዲሰሩ የተመደቡት አቤቱታ ስላቀረቡ ካላቸው ችግር አንፃር መሆኑ በማስረጃ ተረጋግጧል ፡፡ የከሣሽም ጥቅም ቀርቷል ለማለት አልተቻለም በማለት የተጠሪን ክስ ውድቅ በማድረግ ወስኗል ፡፡
ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለደብርማርቆስ ከተማ ከፍተኛ ፍ / ቤት አቅርቧል ። ፍ / ቤቱም ግራ ቀኙን አከራክሮ አሠሪው መ / ቤት ሠራተኛውን ከክሊኒካል ኦፊሰርነት ወደ ሕብረተሰብ አቀፍ ሥነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት አስተባባሪነት ዝቅ
መደረጉ የሥራ ውላቸውን የጣሰ እና ከሠራተኛው ስምምነት ውጭ የተፈፀመ ተግባር
ሠራተኛው ከተቀጠሩበት የክሊኒካል ኦፊሰርነት የሥራ
መደብ ሊያስነሳቸው የሚችል በቂና
ምክንያት ስለሌለ ይህ ውሣኔ ከተሰጠበት ቀን
ጀምሮ ወደ መደበኛ የሥራ ቦታቸው የክሊኒክ ኦፊሰርነት ሥራቸው እንዲመለሱና
ለቦታው የተመደበውን ጥቅም እንዲያገኙ ፣ በይግባኝ ባይና በመልስ ሰጭ መካከል ያለው
የሥራ ውል ለአልተወሰነ ጊዜ የተደረገ የሥራ ውል ነው በማለት ወስኗል ፡፡
አመልካች ግንቦት 5 ቀን 1997 ዓ.ም. በተፃፈ ማመልከቻ ለሰበር ችሎት
ያቀረበው አቤቱታ ይህን ውሣኔ በመቃወም ነው ፡፡ ፍሬ ቃሉም ሲጠቃለል የተጠሪ
የሥራ መደብ የተቀየረው በአመልካች ድርጅት በተደረገው አጠቃላይ የመዋቅር ለውጥ
ምክንያት ነው ፣ በመዋቅር ለውጥ ምክንያት የሥራ ውልን በማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ
እንደሚቻል በአዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ 28 / 1 / ተገልጿል ፡፡ በአንቀጽ 28 / 2 / ሐ
መሠረት የአሠራር የመዋቅር ለውጥ ሲደረግ የሠራተኞችም ቅነሳም እንደሚከተል ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት Ar / ት / የኔ_
። } } ዓባጭ
እንደማላሟላ ለማረጋገጥ S
ወይንም በሕግ ካልሆነ በስተቀር በአንዱ ወገን ፍላጐት ብቻ የሚሰረዝ አይደለም ፣
ተደንግጓል ፣
በአመልካች ድርጅት
ውስጥ የመዋቅር ለውጥ መደረጉን
ካለመካዳቸውም በላይ ለበታች ፍ / ቤቶች የመዋቅር ለውጡ ሰነዶች ቀርበው ከፋይሎቹ
ተያይዘዋል ፡፡ ተጠሪና አመልካች በየአመቱ ሲፈራረሙ የነበረው በጊዜ ተገድቦ የተደረገው
የሥራ ውል ግልፅና ለትርጉም የተጋለጠ አይደለም የከፍተኛ ፍ / ቤት ተጠሪና አመልካች
ያላቸው የሥራ ግንኙነት ላልተወሰነ ጊዜ የተደረገ የሥራ ውል ግንኙነት ነው ያለው
ዐብይ የሕግ ስህተት ነው ፡፡ ስለዚህ የሰበር ችሎት የዞኑ ከፍተኛ ፍ / ቤት ውሣኔ በመሻር
የወረዳውን ፍ / ቤት ውሣኔ እንዲያፀድቅልን ውሉም በሁለቱ ተዋዋዮች በተደረገው
መሠረት ነው እንዲልልን የሚል ነው ፡፡
አቤቱታው በሰበር ችሎት ሊታይ ይገባል ተብሎ ተጠሪ መልስ እንዲሰጥ
በታዘዘው መሠረት ሐምሌ 27 ቀን 1997 ዓ.ም. የተፃፈ መልስ አቅርቧል ፡፡ ፍሬ ቃሉም
ከክሊኒክ ኦፊሰርነት የሚያስፈልገውን ዝርዝር መስፈርት ለማሳየት እና ተጠሪ ያንን
የቀረበ መዋቅር የለም ፡፡ የተጠሪ የቀድሞው የሥራ መደብ
በአዲሱ መዋቅር ተሰርዟል አልተባለም ፡፡ ይህ የሥራ ውል በተዋዋይ ወገኖች ስምምነት
ስለዚህ ተጠሪው ወደ ተቀጠርኩበት ወደ ክሊኒክ ኦፊሰርነት የስራ መደብ እንድመደብ
የከፍተኛ ፍ / ቤት መወሰኑ የህግ ስህተት ሰለሌለው እንዲፀና ፤ እንዲሁም ሥራው ያለ
እና በአዲሱ መዋቅርም የተካተተና የሚቀጥል ነው ፡፡ ስለዚህ የተጠሪ የሥራ ውል
ላልተወሰነ ጊዜ የተደረገ ውል ነው ተብሎ መወሰኑም የህግ ስህተት ስለሌለበት እንዲፀና
የሚል ነው ፡፡
በዚህ ጉዳይ ታይቶ መወሰን ያለበት ጭብጥ አመልካች ተጠሪውን ከተቀጠረበት
የክሊኒካል ኦፌሰርነት የሥራ መደብ ወደ ጤና አገልግሎት አስተባባሪነት መድቦ
እንዲሠራ ማድረጉ ተገቢ ነው ? ወይስ አይደለም የሚለው ነው ፡፡
ፌዴራል ( ነ ፡፡ ያ ፍርድ ቤት
3r ) .
ተደን የዚህም ድንጋጌ ይዘት አንድ አሠሪ ከድርጅቱ ይህ ክርክር የተጀመረው አዋጅ ቁጥር 42/85 በአዋጅ ቁጥር 377/96 ከመተካቱ በፊት ስለሆነ የሚታየው በአዋጅ ቁጥር 42/85 መሠረት ነው ፡፡ በዚሁ አዋጅ በአንቀጽ 28 / 1 / መ መሠረት ሠራተኛው የያዘው የሥራ መደብ በበቂ ምክንያት ሊሰረዝና ሠራተኛውን ወደ ሌላ ሥራ ማዛወር የማይቻል ሆኖ ሲገኝ በማስጠንቀቂያ የሥራ ውል መቋረጥ እንደሚቻል ተመልክቷል ፡፡ ይህ ድንጋጌ የሥራ መደብ መሰረዝ የሥራ ውል ማቋረጫ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ያመለክታል ፡፡ በተዘዋዋሪም በድርጅቱ መዋቅር ለውጥ ምክንያትም የሥራ መደቡ መስፈርት ሲለወጥና በቦታው የተመደበው ሠራተኛ መስፈርቱን የሚያሟላ ሆኖ ሲገኝ አሰሪው ሰራተኛው ችሎታውና ሥልጠናው ወደሚያሟላ ቦታ መድቦ ማስራት እንደሚችል ያስገነዝባል ፡፡ በዚሁ አንቀፅ በንዑስ ቁጥር 2 መሠረትም ከድርጅቱ ድረጅታዊ አቋም ወይም የሥራ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ የሠራተኛ ቅነሳ የሚያስከትል ሁኔታ ሲከሰት የሥራ ውልን በማስጠንቀቂያ ለማቋረጥ እንደሚቻል
ድርጅታዊ አቋም ጋር በተያያዘ የሥራ ውልን ማቋረጥ ከቻለ በተደረገው የመዋቅር
ለውጥ መሠረት ሠራተኛ የሥራ መስፈርቱን ወደሚያሟሉበት የሥራ መደብ አዛውሮም
ማሰራት ይችላል ወደሚል መደምደሚያ ያደርሳል ፡፡ በአጠቃላይ አንድ ድርጅተ
የመዋቅር ለውጥ ቢያደርግና ሠራተኛን ከነበረበት በለውጡ መሠረት መስፈርቱን ወደ
ሚያሟላበት የስራ መደብ ላይ መድቦ ቢያሰራው ዝውውሩ ሕገ ወጥ ነው ለማለት
አይቻልም ፡፡
ወደያዝነው ጉዳይ ስንመጣ ተጠሪ በሥራ ውል የተቀጠረው በክሊኒክ ኦፌሰርነት
ነው ፡፡ ሆኖም በአመልካች ድርጅት የመዋቅር ለውጥ የተደረገ መሆኑን በዚህም ሳቢያ
የክሊኒክ ኦፌሰርነት የስራ መደብ የሚያስፈልገው መስፈርትም መለወጡ አልተካደም ፡፡
ተጠሪው በተደረገው … ልውጣመሠረት የክሊኒከ ኦፌሰርነት የሚጠይቀውን መስፈርት
ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ግፊባጭ
' ለገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ፡፡ አሟላለሁ የሚል ክርክር የለውም ፡፡ አዲሱን የሥራ መስፈርት የሚያሟላ ከሆነ ደግሞ አመልካች ድርጅት ተጠሪን ችሎታውና ሥልጠናው ወደ ሚያሟላበት የሥራ መደብ አዛውሮ እንዲሰራ ማድረጉ ተገቢ ነው ፡፡
የደብረማርቆስ ዞን ከፍተኛ ፍ / ቤት ተጠሪው በአዲሱ መስፈርት ወደ ማያሟላበት የክሊኒክ ኦፊሰርነት የሥራ መደብ ተመልሶ እንዲሠራ መወሰኑ በአመልካች ድርጅት የተደረገውን አጠቃላይ የመዋቅር ለውጥ ያላገናዘበ በመሆኑ ስህተት ነው ፡፡
ው ሣ ኔ 1. ተጠሪ ወደ ቀድሞው የክሊኒካል ኦፊሰርነት የሥራ መደብ መመለስ
የለበትም ፡፡ 2. የደብረ ማርቆስ ዞን ከፍተኛ ፍ / ቤት በመዝ / ቁ 6618 ግንቦት 3 ቀን 1997
የሰጠው ውሣኔ በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕግ ቁ . 348 / 1 / መሠረት ተሽሯል ፡፡ 3. ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ በየራሳቸው ይቻቻሉ ፡፡ የውሣኔው ግልባጭ ለስር
ፍ / ቤት ይተላለፍ ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ፡፡
ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ግልባጭ
85.3 ፃእ

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?