የሰበር መ.ቁ. 15631 ታህሣስ 17 ቀን 1998 ዓ.ም.
ዳኞች፡- 1. መንበረፀሐይ ታደሰ
2. ሐጉስ ወለዱ 3. ዳኜ መላኩ 4. አሰግድ ጋሻው 5. ሂሩት መለሰ
አመልካቾች፡- 1 ኛ የሻረግ መንግሥቱ
2 ኛ . ሰገዴ መንግሥቱ ተጠሪ፡- እማሆይ የሻረግ ፈረደ
ስለ ይርጋ - የወራሽነት ጥያቄን ለማቅረብ ስለተወሰነው ጊዜ - የይርጋ ጥያቄ በፍርድ ቤት ተቀባይነት የማይኖርበት ሁኔታ የፍ / ብ / ህ / ቁ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ
ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመልካቾች ተጠሪዋ የሟች አባታችን የአቶ መንግሥቱ ዘወልዴን ቤት ሊያስረክቡን ይገባል በማለት ያቀረቡትን ክስ መርምሮ የሰሜን ጎንደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ በመሻር የጎንደር ወረዳ ፍርድ ቤት ክሱ ሰይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት ያፀናውን ውሳኔ በመቃወም የቀረበ አቤቱታ ፡፡
ዉሳኔ፡- በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሳኔ ፀንቷል ።
1. ውሎች ንብረትን በተመለተ በ 1675 መሠረት የሚደረግ ስምምነት
በመሆኑ በዚሁ መሠረት ትርጉም የሚሰጠው የውል ሰነድ ሳይኖር
በፍ / ብ / ህ / ቁ . 1845 ን በተመለከተ የሚሰጥ ውሳኔ የለም ፡፡ 2. የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለዕጅ / ባለይዞታ የሆነ ሰው የዚሁኑ ንብረት
ግብር ባለማቋረጥ 15 ዓመት ከከፈለ ሌላ ይገባኛል የሚል ሰው
ንበረፀሐይ ታደሰ
የሰበር መ.ቁ 15631
ታህሣስ 17 ቀን 1998 ዓ.ም. 2. ሐስ ወለዱ 3. ዳኜ መላኩ 4. አሰግድ ጋሻው 5. ሂሩት
አመልካቾች፡- 1 ኛ . የሻረግ መንግሥቱ
2 ኛ . ሰገደ መንግሥቱ ተጠሪ፡- እማሆይ የሻረግ ፈረደ መዝገቡ ተመርምሮ የሚከተለው ፍርድ ተሰጥቷል ፡፡
ፍ ር ድ በዚህ መዝገብ ለሰበር ለቀረበው አቤቱታ መነሻ የሆነው የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍ / ቤት በፍ / ይ / መ / ቁ . 364 በይግባኝ ደረጃ ቀርቦለት በነበረው ጉዳይ ሲያከራከር ቆይቶ የካቲት 16 ቀን 1996 ዓ / ም መረምሮ የሰሜን ጐንደር ከፍተኛ ፍ / ቤት የሰጠውን ውሣኔ በመሻር የአሁኑ አመልካቾች ተጠሪዋ የሟች አባታችን የአቶ መንግሥቱ ዘወልዴን ቤት ሊያስረክቡን ይገባል በማለት ያቀረቡት ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በሚል የሰጠው ውሣኔ ነው ፡፡ የክልሉ ጠቅላይ ፍ / ቤት በዚህ ውሣኔው ክርክሩን በመጀመሪያ ደረጃ ያየው የጐንደር ከተማ ወረዳ ፍ / ቤት ክሱ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1000 / 12 / እና 1845 መሠረት በይርጋ ቀሪ ሆኗል በሚል የወሰነው በሕጉ አግባብ ነው በማለት ኣጽንቶታል ።
አመልካቾች አባታችን አቶ መንግሥቱ ዘወልዴ ከሞቱ በኋላ በውርስ ሊተላለፍልን የሚገባውን ቤት የካቲት 8 ቀን 1962 ዓ / ም በተደረገ ስምምነት ተረክበን ተጠሪዋ ባይወልዱንም እናታችን ናቸው ብለን በማሰብ እንዲቀመጡበት ያደረግነውንና በአክብሮት ሣንጠይቃቸው የቆይነውን
ንብረት እንዲያስረክቡን በማለት ያቀረብነው ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በሚል * The በተሰጠው L ውሣኔ ri ሠረታዊ * የሕግ w ስህናት c ተፈጽሟል ch በማልብሰበር
አቤቱታ አቅርበዋል ፡፡ አመልካቾች ንብረቱን ሣንጠይቅ የቆየነው በቤተዘመድ ግንኙነት ምክንያት ተጠሪዋን በመፍራትና በማክበር ስለሆነ የይርጋውን ክርክር ሰፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1853 / 1 / መሠረት ሊቀበለው አይገባም ባዮች ናቸው ፡፡
አቤቱታው ተመርምሮ ጉዳዩ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ በመወሰኑ በአመልካቾች በኩል የቀረበው ማመልከቻ ለአሁኗ ተጠሪ እንዲደርሳቸው ተደርጐ ሐምሌ
ዓም የተፃፈ አቅርበዋል ፡፡ አመልካቾች በበኩላቸው የመልስ መልስ ሰጥተውበት ተከራክረዋል ።
በተጠሪዋ በኩል የቀረበው ክርክር ሲታይ አመለካቾች እኔን የእንጀራ እናታቸውን በማክበርም ሆነ በመፍራት መብታቸውን ሣይጠይቁ ቆይተዋል ሊባል ስለማይችል ፍ / ቤት ይርጋ አልቀበልም የሚልበት ምክንያት የለም
የሚል ይዘት ያለው ነው ፡፡
ችሎቱም የአሁኑ አመልካቾች ከ 1962 ዓ / ም በፊት የሞቱትን
የአባታችንን ቤት ይዘው የሚገኙት የአሁኗ ተጠሪ ሊያስረክቡን ይገባል በሚል ያቀረቡት ክሥ በይርጋ ቀሪ ሆኗል አልሆነም ፣ ፍ / ቤት ይርጋ
አልቀበልም የሚልበት የሕግ ምክንያት አለ ወይንስ የለም የሚለውን ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መርምሯል ፡፡
ክርክሩን በመጀመሪያ ደረጃ ያየው የጐንደር ከተማ ወረዳ ፍ / ቤትም ሆነ የክልሉ ጠቅላይ
ፍ / ቤት የአሁኑ
አመልካቾች ከአባታችን በውርስ ሊተላለፍልን የሚገባውን ቤት የአሁኗ ተጠሪ ምንም አይነት መብት ሣይኖራቸው ለማስረከብ ፈቃደኛ ባለመሆን ይዘው ስለሚገኙ ሊያስረክቡን ይገባል በሚል ያቀረቡትን ክስ በፍትሐብሄር ሕግ ቁጥር 1845 መሠረት በአሥር አመት ይርጋ ቀሪ ሆኗል ሰማዕት ሊወሰኑ የቻሉት የካቲት 8 ቀን 1962 ዓ / ም ተደርጓል የተባለውን ውል መነሻ በማድረግ ነው ። ከሰነዱ
እንደሚታየው ግን ቤቱን የአሁኗ ተጠሪ ለቀው ለሟቹ ለአቶ መንግሥቱ
የውልዴ ወራሾች ማሥረከባቸው እና ሌሎችን ንብረቶችም ስለመከፋፈላቸው
ከመገለጹ በቀር የሟቹ የአባታቸው ሚስት በቤቱ እየተጠቀመበት ይቆዩ ወይም ይኑሩበት የሚል ነገር የለውም ፡፡ ከዚህ ሌላ ቤቱ ሰሟች ሚስት ይዞታ ሥር ቆይቶ ወደፊት በዚህ ጊዜ ለወራሾች ያስረክባሉ የሚል የውል ቃል የለውም ፡፡ በሰነዱ ላይ የሰፈረው በሕግ የውል ትርጉም የሚሰጠው አይደለም ፡፡ ውል ማለት ደግሞ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1675 ላይ እንደተመለከተው ንብረታቸውን የሚመለከቱ ግዴታቸውን ለማቋቋም ወይም ለመለወጥ ወይም ለማስቀረት ባላቸው ተወዳዳሪ ግንኙነት በሁለት ወይም በብዙ ሰዎች መካከል የሚደረግ ሥምምነት ስለሆነ በዚሁ መሠረት የውል ትርጉም የሚሰጠው ነገር ሣይኖር ውል አለ የሚል መነሻ በመያዝ ይርጋን
በሚመለከት
ተፈፃሚ . የሚሆነው
ስለውሎች
በጠቅላላው
የፍትሐብሔር ሕጉ ክፍል
ክፍል ተጽፎ የሚገኘው በፍ / ብ / ህ / ቁ . 1845 ላይ የተመለከተው የአሥር ኣመት ጊዜ ነው ብሉ መወሰን ትክክል አይደለም ፡፡
በአሁኑ አመልካቾች በኩል የቀረበው የካቲት 8 ቀን 1962 ዓ / ም የተፃፈው
ሰነድ ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1845 ጋራ በተያያዘ የሚያስነሣው የይርጋ ጥያቄ ስለሌለ በዚህ ጉዳይ የተጠቀሰው የይርጋ ሕግ አግባብነት የለውም ፡፡
በሌላም በኩል የአሁኗ ተጠሪ ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት ሲከራከሩ የነበሩት የካቲት 8 ቀን 1962 ዓ / ም ተፃፈ የተባለውን ሰነድ መነሻ በማድረግ ብቻ ሣይሆን ቤቱ ከ 1943 ዓ / ም ጀምሮ ባለማቋረጥ ግብር እየከፈልኩበት ንብረቴ ሆኗል ፣ ከሃያ ሰባት አመት በላይ በስሜ ስገብርበት ቆይቼ የቤቱ የቦታ ይዞታም ሆነ የሴቱ ባለቤትነት ሥም በሥሜ ሊሆን ችሏል በሚል ምክንያት ጭምር ሲሆን እነዚህ የተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች መሆናቸውን ከመዝገቡ ለመረዳት ተችሏል ፡፡ ከእነዚህ ፍሬ ነገሮች በመነሣት ሲታይ የፍትሐብሔር ሕግ 1168 / ህ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለእጅ / ባለይዞታ / የሆነ ሰው የዚሁኑ ንብረት ግብር
ባለማቋረጥ 15 ዓመት በሥሙ ከከፈለ የዚሁ ሀብት ባለቤት ይሆናል
ስሚል ደንግጐ ይገኛል ፡፡ ሕጉ ይርጋ አዘል ስለሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት
ባለእጅ [ ባለይዞታ የሆነው ሰው የዚህን ንብረት ግብር ባለማቋረጥ ለ 15 ዓመት በሥሙ ከከፈለ ሌላ ይገባኛል የሚል ሰው እንዲሰጠው ሊጠይቀው አይችልም ። በሕጉ ለባለይዞታው መብቱ ይረጋለታል ፡፡ የአሁኗ ተጠሪም ለክርክሩ መነሻ የሆነው ሴት ባለይዞታ በመሆን የዚሁኑ ንብረት ግብር
ባለማቋረጥ ከ 15 ዓመት በላይ በሥማቸው ሲከፍሉ ስለቆዩ በሕጉ የዚሁ ህብት ባለቤት ሆነዋል ፡፡ የአሁኑ አመልካቾች እባት ከ 1962 ዓ / ም በፊት
የሞቱ ስለሆነ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በተጠሪዋ ይዞታ ሥር የቆየውን ቤት ከሃያ ስምንት አመት በኋላ እንዲያስረክቧቸው ያቀረቡት ክሥ በይርጋ ቀሪ አይሆንም በሚል የሚያቀርቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም ፡፡
አመልካቾች ክስ ሣናቀርብ የቆየነው ተጠሪዋ የሟቹ አባታችን ሚስት በመሆናቸው በመፍራትና በማክበር በመሆኑ ፍ / ቤት ይርጋውን ሊቀበለው አይገባም በሚል ያነሱትን ክርክር በተመለከተም በእርግጥ ፍ / ቤት ይርጋን አልቀበልም የሚልባቸው ምክንያቶች አሉ ፡፡ እነዚህ ምክንያቶች በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1853 የተዘረዘሩት ሲሆኑ ከእነዚህ መካከል ባለገንዘቡ የሚፈልገውን ያልጠየቀበት ምክንያት ባለዕዳውን የመፍራትና የማክበር ስሜት መኖር ኣንዱ ነው ፡፡ አመልካቾች ከሃያ ስምንት አመት
በላይ ተጠሪዋ ሴቱን እንዲያስረክቡን ሣንጠይቅ የቆየነው የአማታችን ሚስት ስለሆኑ እንደ እናት ስለምናያቸው የመፍራትና የማክበር ስሜት አድሮብን ነው ይበሉ እንጅ የክልሉ ጠቅላይ ፍ / ቤት አመለካቾች ኣባታቸው ከሞቱ ሰኋላ የአባታችንን ንብረት አካፍይን ወይም አስረክቢን የሚል ጥያቄ አንስተው ሽማግሌዎች ሰብስበው የካቲት 8 ቀን 1962 ዓ / ም በተፃፈ ሰነድ በተደረገ እርቅ ንብረት መከፋፈላቸው መገለጹና በዚሁ ሰነድ አማካኝነት ቤቱን ተረክበን ነበር ማለታቸው ሲታይ ከዚህ በኋላ ሣይጠይቁ የቆዩት ተጠሪዋን በመፍራትና በማክበር ምክንያት ነው ለማለት አይቻልም በሚል
ሣይቀበላቸው ቀርቷል ፡፡ በአመልካቾች ስኩል ተጠሪዋን የመፍራትና
የማክበር ስሜት ነበረ አልነበረም ለሚለው ፍ / ቤት መፍራትም ሆነ ማክበር
ልፋ እያ *
እልነበረም የሚል ድምዳሜ ላይ ከደረሰ ወደ ፍሬ ነገር ጥያቄ ስለሚያመዝን በሰበር ደረጃ ሊመረመር አይችልም ፡፡ በሰበር ደረጃ ሊታይ የሚችለው የሥር ፍ / ቤት የመፍራትና የማክበር አረጋግጦ አልቀበልም ለማለት የሚያስችል የሕግ ምክንያት አይደለም በሚል ወስኖ ሲገኝ ነው ፡፡ ስለዚህ እመልካቾች ያቀረቡት ክስ በይርጋ ሕግ ቀሪ መሆነ ቢረጋገጥም ፍ / ቤት ይርጋውን አልቀበልም የሚልበት የሕግ ምክንያት አለ በሚል ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም ፡፡
ከፍ ሲል እንደተገለፀው የክልሉ ጠቅላይ ፍ / ቤት የካቲት 8 ቀን 1962 ዓ / ም በተፃፈው ሰነድ በአመልካቾችና በአሁኗ ተጠሪ መካከል ቤቱን በሚመለከት የተደረገ የውል ስምምነት እንዳለ አድርጉ በመመልከት መነሻ በማድረግ ለተነሣው የይርጋ ጥያቄ የሚመለከተው የይርጋ ሕግ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1845 ላይ የተመለከተው የአሥር አመት ጊዜ ነው ማለቱ የተሣሣተ ሆኖ ቢታይም ክሱ ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1168 አንፃር ሲመረመር በይርጋ ቀሪ ከመሆን የሚድን - ሆኖ ስላልተገኘ በውጤቱ የሚያመጣው ለውጥ የለም ፡፡ ክሱ ስይርጋ ቀሪ ሆኗል ተብሎ መወሰኑ ተቀባይነት የሚሰጠው ነዉ ፡፡
ው ሣ ኔ 1. በኣሁኑ አመልካቾች በኩል የቀረበው ክሥ በይርጋ ቀሪ መሆኑ
ስለተረጋገጠ
በፍ / ሥ / ሥ / ህ / ቁ 348 / 1 / መሠረት ፀንቷል ። 2 በዚህ መዝገብ በተደረገው ክርክር ምክንያት የደረሰውን ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሣቸውን ይቻሉ ፡፡
ጉዳዩ ስለተወሰነ መዝገቡ ተዘግቷል ፡፡ ይመለስ ፡፡ * The African Law Archive * የማይነበብ.የአምስትዳኞችፊርማ . አለት ፡፡
You must login to view the entire document.