×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 14605

      Sorry, pritning is not allowed

የፌዴራል ጠቅላይ ፍ / ቤት
ሰበር ሰሚ ችሎት
የመ / ቁ .14605
ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
አቶ ፍሥሐ ወርቅነህ
አቶ አብዱልቃድር መሐመድ
አቶ መስፍን ዕቁበዮናስ
ወ / ት ሂሩት መለሰ
አመልካች፡- የኢትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት
መልስ ሰጪዎች፡- 1. ኮሜት ትራንስፖርት ድርጅት
2. ሸበሌ ትራንስፖርት ድርጅት 3. በከልቻ ትራንስፖርት ድርጅት 4. ወይራ ትራንስፖርት ድርጅት 5. አዲስ ሜካኒካል ድርጅት
6. አቶ ዮሐንስ ተስፋ
ስለ ማጓጓዝ ስራ
የአጓዥ ኃላፊነት - የተመዘገቡ ጓዞች ወይም ዕቃዎች የጠፉ ወይም
ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን
በተለያዩ ምክንያቶች ከኃላፊነት መዳን - የንግድ ህግ
ቁጥሮች 590 ፣ 591 ፡- ውል
ውልን ስላለመፈጸም
ከዐቅም በላይ የሆነ ነይል
የፍትሐብሔር ህግ ቁጥር 1792
አመልካች በፌ / መ / ደ / ፍ / ቤት ባቀረበው ክስ ከ 1 ኛ -5 ኛ በተጠቀሱት ተጠሪዎች
መኪና አቅሪቢነት ነጭ ጋዝ ናፍታ አስጭኖ ከአሰብ ወደ ባህር ዳር በሚጓጓዝበት ወቅት
መኪናው ተገልብጦ ዋጋው ብር 57 ዐ 89.78 / ሃምሳ አንድ ሺህ ሰማንያ ዘጠኝ ብር ከሰባ
ስምንት ሳንቲም / የሆነ ነዳጅ ስለፈሰሰ ይኸው ዋጋ ከ1-5 ያሉት ተጠሪዎች እንዲሁም
የመኪናው ባለንብረት 6 ኛ ተጠሪ በአንድነትና በነጠላ እንዲከፍሉት ያቀረበውን ጥያቄ
ፍ / ቤቱ ነዳጅ የፈሰሰው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት በመሆኑ ተጠሪዎች ኃላፊነት
የላባቸውም በማለት ውሳኔ በመስጠቱና ውሳኔውን የፌዴራል ከፍተኛ ፍ /
ቤትም
ው ሳ ኔ፡- የፌ / መ / ደ / ፍ / ቤት እና የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት የሰጡት ውሳኔ ተሽሯል ፡፡
1- አንድ አጓዥ በከፊል ወይም በሙሉ ዕቃዎች ወይም የተመዘገቡ ጓዞች ወይም
ጉዳት ሲያገኛቸው ወይም የማስረከቢያ ጊዜው ቢዘገይ በነላፊነት የሚጠየቅ ሲሆን
ከዚህ ኃላፊነት የሚድነው ዕቃው
የጠፋው ወይም ጉዳት
ረሰው ወይም የዘገየው
ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ወይም በዕቃው ውስጣዊ ጉድለት ምክንያት ወይም
በተቀባዩ ጥፋት ሲሆን ነው ፡፡
2- ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ተከስቷል የሚባለው ባለእዳው በአጓዡ / በቅድሚያ
በምንም መልኩ ሊየስበው ወይም ሊገምተው የማይችል ክስተት ሲፈጠር ነው ፡፡
3- ወደ መኪና ሮጦ የገባን ሰው ለማዳን በተወሰደ ርምጃ ምክንያት በመጓጓዝ ላይ
በነበረ ዕቃ ላይ የደረሰ ጉዳት ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ ተከስቷል የሚባል
የመ / ቁ 14605
ቀን ሐምሌ 29/1997

ትዮጵያ ነዳጅ ድርጅት አመልካች :
ዳኞች 1 አቶ መንበረፀሃይ ታደሰ
2 ) አቶ ፍስሃ ወርቅነህ
3 ) አቶ አብዱልቃድር መሃመድ
4 አቶ መስፍን እቁበዮናስ
5 ) ወ / ት ሒሩት መለሰ
ተጠሪዎች፡ 1. ኮሜት ትራንስፖርት ድርጅት
2. ሸበሌ ትራንስፖርት ድርጅት
3. በከልቻ ትራንስፖርት ድርጅት
4. ወይራ ትራንስፖርት ድርጅት
5. አዲስ ሜከኒከል ድርጅት
6. አቶ ዮሐንስ ተስፋ
ለአሁን አቤቱታ መነሻ የሆነው ፌ / መ / ደ / ፍ /
ቤት ጳጉሜ 3/1992 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ነው :: አመልካች በዚያ ፍ /
ቤት ከ 1 ኛ -5 ኛ ድረስ ባሉት ተጠሪዎች መኪና አቅራቢነት አመልካች 34993 ሊትር ነጭ ጋዝና ናፍታ አስጭኖ ከአሰብ ወደ ባህር ዳር በሚጓጓዝበት ወቅት መኪናው በመገልበጡ የተጫነው ነዳጅ በሙሉ ስለፈሰሰ የፈሰሰውን ነዳጅ ዋጋ ብር 51089.78 ( ምሳ አንድ ሺህ ሰማኒያ ዘጠኝ ብር ከሰባ ስምንት ሳንቲም ከነወለዱ አምስቱም ተጠሪዎች እንዲከፍሉ ፡፡ 6 ኛውም ተጠሪ የመኪናው ባለንብረት ስለሆነ በአንድነት እና በነጠላ በክሱ የተመለከተውን ገንዘብ ከነወለዱ እንዲከፍል ጠይቋል ፡፡
ምክንያት ስለሆነ የስር ፍ / ቤቶተ በ t
ፍርድ ቤቱም ግራ ቀኙን አከራክሮ ነዳጁ የፈሰሰው ከአቅም በላይ በሆነ ከፍተኛ ሃይል ስለሆነ ተጠሪዎቹ በሙሉ ለክሱ ሃላፊ አይደሉም በማለት የአመልካችን ክስ ውድቅ አድርጎታል ፡፡ ጉዳዩን በይግባኝ የተመለከተው የፌ / ከ / ፍ / ቤትም የስር ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አጽንቶታል ::
ሁኑ ይግባኝ የቀረበውም በዚሁ ውሳኔ ላይ ሲሆን የአመልካች ቅሬታ በአጭሩ ሲጠቃለል የስር ፍ / ቤቶች ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ » ን ሲተረጉሙ የህግ ስህተት ፈጽመዋል የሚል ነው :: ተጠሪዎችም ለቀረበው አቤቱታ መልስ አቅርበዋል ፡፡ ከ 1 ኛ - ኛ ያሉት ተጠሪዎች በአንድነት በ 17 / 10 / 96 በተጻፈ መልስ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ባላደራ ቦርድ በክሱ ይተካልን ፣ ይህ ቢታለፍ ነዳጁ የፈሰሰው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ነው ፣ በዚህ ሁኔታ አይደለም የፈሰሰው ከተባለም የቀድሞ የኢትዮጵያ ጭነት ማመላለሻ ኮርፖሬሽን ከአመልካች ጋር የማጓጓዣ ውል ስላልፈጸመ ለጥፋቱ ሃላፊ አይሆንም ፣ በተመሳሳይ ጉዳይ ጭነት ማመላለሻ ኮርፖሬሽን የግለሰብ ተሸከርካሪዎች ለሚፈጽሙት ጥፋት ሃላፊነት እንደሌለበት በመ / ቁ / 9678 እና በመ / ቁ 9679 በሰበር ችሎት ውሳኔ ተሰጥቷል የሚል ነው :: 6 ኛ ተጠሪ በበኩሉ በ 9 / 6 / 97 በተጻፈ መልስ ነዳጁ የፈሰሰው ከአቅም በላይ በሆነ
ውሳኔ እንዲጸናለት ጠይቋል ፡፡ አመልካችም በመልስ የስር ፍ / ቤቶች ውሳኔ እንዲሻርለት በመጠየቅ ተከራክራል ::
ከፍ ሲል የተገለጸው የግራ ቀኙ ክርክር ሲሆን ይህ ችሎትም መዝገቡን መርምሯል :: ከላይ እንደተመለከተው አመልካች ያቀረበው ክስ ውድቅ የተደረገው አደጋው የደረሰው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ነው በሚል ነው :: በመሆኑም ፣
1 ) አደጋው የደረሰው ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ ነው ? ወይስ አደለም ?
2 ) ካልሆነ ተጠሪዎች ለክሱ ሃላፊ ሊሆኑ ይገባልን ? የሚሉት ነጥቦች መታየት አለባቸው ::
የመጀመሪያውን ነጥብ በተመለከተ
አንድ አጓዥ በከፊል ወይም በሙሉ እቃዎች ወይም የተመዘገቡ ጓዞች ሲጠፉ ወይም ጉዳት ሲያገኛቸው ወይም የማስረከቢያው ጊዜ ቢዘገይ በሃላፊነት እንደሚጠየቅ የንግድ ህጉ ቁጥር 590 ሲያመለክት አጓዡ ከዚህ ሀላፊነት የሚድነው ደግሞ የጠፋው ወይም ጉዳት የደረሰው ወይም የዘገየው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ወይም በእቃው ውስጣዊ ጉድለት ምክንያት ወይም በላኪና በተቀባዩ ጥፋት ምክንያት ሲሆን እንደሆነ የን / ህ / ቁ 591 ያመለክታል ፡፡
ደርሷል የሚባለሥፍ
በመሆኑም አንድ አጓዥ የሚያጓጉዘው እቃ የጠፋ ወይም ጉዳት የደረሰበት ከሆነ ከሃላፊነት ለመዳን እቃው የጠፋው ወይም የተጎዳው ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ መሆኑን ወይም ከራሱ ከእቃው ጉድለት መሆኑን የማስረዳት ሸክም ያለበት ሲሆን ከምክንያቶቹ ውስጥም ከተያዘው ጉዳይ ጋር አግባብነት ያለው ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ የሚለው በመሆኑ ችሎቱም ይህ ሁኔታ ተከስቷል የሚባለው መቼ ነው የሚለውን ከህጉ ጋር በማገናዘብ ተመልክቷል ::
ህጉ ውስጥ « ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ » ማለት ምን ማለት እንደሆነ የተመለከተ ነገር ስለሌለ ትርጉሙን ለማወቅ ወደ ፍ / ብ / ህጉ በተለይም ደግሞ ስለውሎች በጠቅላላው ስለሚመለከቱ ድንጋጌዎች ማምራቱ የግድ ይሆናል ፡፡ በዚህ መሰረትም የፍ / ህ / ቁ 1792 ስንመለከት ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ አለ ወይም የለም የሚባለው መቼ እንደሆነ ያሳያል ፡፡ የዚሁ ድንጋጌ ንዑስ ቁጥር 1 ከአቅም በላይ የሆነ ሊመልሱት የማይቻል ሀይል
ባለእዳ ባላሰበው ነገር ድንገት ደራሽ ሆኖበት ግዴታውን እንዳይፈጽም ፍጹም መሰናክል በሆነ ዓይነት የሚያግደው ነገር ባጋጠመ ጊዜ መሆኑ ይገልጻል ።
ከንዑስ ቁጥር 2 ደግሞ በአእምሮ ግምት ባለእዳው ቀደም ብሎ ሊየስብበት የሚችል መሆኑ የታወቀ አንድ ድንገተኛ ደራሽ ነገር ወይም ለውሉ አፈጻጸም ከባድ የሆነ ወጪ በባለእዳው የሚደርስበት ቢሆን ከአቅም በላይ የሆነ ሃይል ነው ተብሎ እንደማይገመት መመለከት ይቻላል ፡፡
በመሆኑም በእነዚህ የሕጉ ድንጋጌዎች መሰረት ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ተከስቷል ሊባል የሚችለው ባለእዳው በቅድሚያ በምንም መልኩ ሊያስበው ወይም ሊገምተው የማይችል ክስተት ሲፈጠር ነው :: ነገር ግን ባለእዳው ሁኔታው ሊፈጠር ወይም ሊከሰት እንደሚችል ቀድሞ ሊገምት ወይም ሊያስብ እና ጥንቃቄ ሊያደርግበት የሚችል ከሆነ ሁኔታው ድንገተኛ ደራሽ ነገር ቢሆን እንኳን ከአቅም በላይ የሆነ ነገር ተብሎ እንደማይገመት ማየት ይቻላል ፡፡
በአጠቃላይ ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ሊባል የሚችለው ፈጽሞውኑ ሊቋቋሙት ወይም ሊቆጣጠሩት የማይቻል ወይም ማንኛውም ጠንቃቃ ሰው ሊገምተው እና ሊያስበው የማይቻለው ሁኔታ ነው :: በፍ / ብ / ህ / ቁ 1793 የተዘረዘሩት ምክንያቶችም ይህንኑ የሚያሳዩ ናቸው ::
ወደ ተያዘው ጉዳይም ስናመራ የስር ፍ / ቤቶች ተጠሪዎችን ከሃላፊነት ነጻ ያደረጓቸው ነዳጁ የፈሰሰው ወደ መኪናው ሮጦ የገባን ሰው ለማዳን በተወሰደ እርምጃ ስለሆነ ከአቅም በላይ በሆነ ድንገተኛ ደራሽ አደጋ ነው በማለት ነው :: ነገር ግን አንድ የመኪና አሽከርካሪ መኪና በሚያሽከረክርበት ወቅት በመንገዱ ድንገት ሰው ሊገባበት እንደሚችል ፣ የተለያዩ
የመጋጨት ወይም የመገልበጥ አደጋ ሊያጋጥመው እንደሚችል ቀደም ብሎ ሊገምት ወይም ሊያስብ የሚችለው ነገር ነው :: የመኪና አሽከርካሪ በሚያሽከረክርበት ጊዜ በመንገዱ ላይ ድንገት ሰው ሊገባ ወይም ድንገተኛ አደጋ ሊያጋጥም ይችላል ብሎ ፈጽሞ አያስብም ተብሎ አይገመትም :: በመሆኑም 6 ኛ ተጠሪ መኪናውን ሲያሽከረክር ድንገት ሰው ሮጦ ወደ መንገዱ መግባቱ ብቻ ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ መኖሩን አያሳይም :: ስለዚህም የስር ፍ /
ቤቶች ለነዳጁ መፍሰስ ምክንያት የሆነውን አደጋ ከአቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ነው በማለት የሰጡት ትርጉም የህግ ስህተት ያለበት ነው ::
ሁለተኛውን ነጥብ በተመለከተ
ከፍ ሲል እንደተገለጸው አንድ አጓዥ በከፊል ወይም በሙሉ እቃዎች ወይም የተመዘገቡ ጓዞች ሲጠፉ ወይም ጉዳት ሲያገኛቸው በሃላፊነት ይጠየቃል ፡፡ ከሃላፊነቱ ነጻ ከሚሆንባቸው ምክንያቶች አንደኛው ደግሞ አደጋው ወይም ጉዳቱ የደረሰው ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ መሆኑ ነው ፡፡ በተያዘው ጉዳይ 6 ኛ ተጠሪ አጓዥ መሆኑ ክርክር አልተነሳበትም ፡፡ ከላይ እንደተገለጸው ደግሞ አደጋው የደረሰው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት አይደለም ፡፡ ስለዚህም 6 ኛ ተጠሪ ለጉዳቱ በን / ህ / ቁ 590 መሰረት ሃላፊ ነው :: ከ 1 ኛ -5 ኛ ያሉትን ተጠሪዎችን ሃላፊነት ስንመለከት ተጠሪዎቹ አደጋው የደረሰው ከአቅም በላይ በሆነ ሁኔታ ነው የማይባል ከሆነ የፈረሰው የኢትዮጵያ ጭነት ማመላለሻ ኮርፖሬሽን እቃውን ለማጓጓዝ ከአመልካች ጋር ያደረገው ውል ስለሌለ ሃላፊነት የለብንም ሲሉ ተከራክረዋል :: ይሁን እንጂ በስር ፍ / ቤት የፈረሰው ድርጅት የእቃ ላኪ ኮሚሲዮን ውል የፈረመ መሆኑ ተረጋግጧል ፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ የእቃ ላኪ ኮሚሲዮኑ እቃ አጓዡ ያለበት መብት እና ግዴታ ያለበት በመሆኑ ( ፍ / ህ / ቁ / 2252 ( 3 ) ) ተጠሪዎቹ ለደረሰው ጉዳት በአንድነት እና በነጠላ ሃላፊ ሊሆኑ ይገባል ::
ከ 1 ኛ -5 ኛ ያሉት ተጠሪዎች በተጨማሪ ያነሱት ክርክር በተመሳሳይ ጉዳይ ጭነት ማመላለሻ ኮርፖሬሽን የግለሰብ ተሽከርካሪዎች ለሚፈጽሙት ጥፋት ሃላፊነት እንደሌለበት ቀደም ሲል ተወስኗል የሚል ሲሆን እንደዚህ አይነት ውሳኔ ተሰጥቶ እንኳን ቢሆን በተያዘው ጉዳይ ተመሳሳይ ውሳኔ እንዲሰጥ የሚያስገድድ አይሆንም ::
በመጨረሻም እነዚሁ ተጠሪዎች ወደ አክስዮንነት የተቀየርን ስለሆነ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ባለአደራ ይከራከር ሲሉ የጠየቁ ቢሆንም ቦርዱ በሃላፊነታቸው መጠን እዳቸውን የመክፈል ግዴታ ካለበት በአፈጻጸም ጊዜ እንዲተካ ሊጠይቁ የሚችሉ በመሆኑ ጥያቄያቸው በዚሁ ታልፏል ፡፡
ተጠሪዎች በአንድነት እና በነጠላ ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ክስ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ ዘጠኝ በመቶ ወለድ ጋር ለአመልካች ይክፈሉ ::
አመልካች በክርክሩ ወቅት ለደረሰበት ወጪ እና ኪሳራ ዝርዝሩን በስር ፍ / ቤት አቅርቦ ያስወስን ፡፡
የፌ / መ / ደ / ፍ / ቤት በመ / ቁ 349/87 በ 3 / 13 / 92 ዓ.ም እና የፌ / ከ / ፍ / ቤት በመ / ቁ 2317/93 በ 143 / 96 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔዎች ተሽረዋል ::
መዝገቡ ተዘግቷል ፧፧ ለመ / ቤት ይመለስ ::

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?