×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 23647

      Sorry, pritning is not allowed

ይወሰንልኝ የሚል 6
የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ያ
ያንድ መ / ሰጭ ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠርኩ
የሰበር መ / ቁ 23647
ቀን ሰኔ 21 ቀን 1998
ዳኞች፡- 1.አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
2. ” ዓብዱልቃድር መሐመድ
3. ” ጌታቸው ምህረቱ
4. ” መስፍን ዕቁበዮናስ
5.ወ / ት ሂሩት መለሰ
አመልካች፡- የኢትዮጵያ ብረታብረት ማቅለጫ ፋብሪካ ጠበቃው ቀርቧል ፡፡
መልስ ሰጭ፡- አቶ ዓለማየሁ አሰፋ ቀርቧል
ፍ ር ድ
በዚህ ጉዳይ ለሰበር ችሎት የቀረበው ክርክር ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠርኩ
ዳኝነት በመጠየቅ የሚቀርብ ክስ የክስ ምክንያት / cause of atuion / አለው ?
ወይስ የለውም ? የሚለውን የሕግ ነጥብ የሚመለከት ነው ።
ይወሰንልኝ በማለት ያቀረቡትን ክስ በመቀበል አከራክሮ ውጭ ሰጥቷል ፡፡ በውሣው ላይ
ይግባኝ የቀረበለት ይግባኝ ሰሚው ፍ / ቤትም ከላይ የተመለከተውን የሕግ ነጥብ ሣይመረመር
አልፎታል ፡፡
አመልካች በዚህ ችሎት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ተመርምሮ ጉዳዩ ለሰበር ችሎት
እንዲቀርብ በተሰጠው ትእዛዝ መሠረት መ / ሰጭ መልስ ሰጥቷል ፡፡
ችሎቱም ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠርኩ ይወሰንልኝ የሚል ዳኝነት በመጠየቅ
የሚቀርብ ክስ የክስ ምክንያት / Cause of acnion / አለው ? ወይስ የለውም ? የሚለውን የሕግ
ነጥብ መሠረት በማድረግ አቤቱታ የቀረበበትን ውሣኔ መርምሯል ፡፡
ይህ ችሎት በመ.ቁ 16273 ጥቅምት 22 ቀን 1998 በሰጠው ውሣ አግባብነት
ያላቸውን የሕጉን ድንጋጌዎች በመተርጎም አንድ ሰራተኛ ከውሉና ከአሰሪና ሠራተኛ ሕጉ
ኗሪ - / E
አንፃር ሊያገኘው የሚገባና የቀረበለት ጥቅም ካለ የቀረበት ጥቅም እንዲሰጠው መጠየቅ / ክስ
ማቅረብ / የሚችል ሲሆን ላልተወሰነ ጊዜ እንደተቀጠርኩ ይወሰንልኝ ብቻ በሚል የሚቀርብን
ክስ የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድም ሆነ የስራ ክርክር ችሉት ተቀብለው ሊያዩ
የሚችሉበት የሕግ ምክንያት የለም በማለት የሕግ ትርጉም ሰጥቷል ፡፡
በዚህ ጉዳይም የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ወሣኝ ቦርድ መ / ሰጭ ያቀረቡትን ላልተወሰነ
ጊዜ እንደተቀጠርኩ ይወሰንልኝ በማለት ያቀረቡትን ክስ የክስ ምክንያት የለውም በማለት
ውድቅ ማድረግ የነበረበት ሲሆን ጉዳዩን ተቀብሎ በማከራከር ውጭ በመስጠቱ መሠረታዊ
የሕግ ስህተት ፈጽሟል ፡፡
ው ሣ ኔ
የአሰሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሣኝ ቦርድ በመ.ቁ 64/02/96 በ 20 / 3 / 98 የሰጠው
ውሣኔና የፌዴራል
ከፍተኛ ፍ / ቤት በመ.ቁ 43619 በ 20 / 5 / 98 የሰጠው ትእዛዝ
ተሽሯል ፡፡
ግራ ቀኙ በዚህ ችሎት ያወጡትን ኪሣራ የየራሣቸውን ይቻሉ ።
መዝገቡ ተዘግቷል ወደ መዝገብ ቤት ይመለስ ፡፡
ፌራ :: : : : : : : : ..
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት
ቀን 2 ፊ e- ሃ g

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?