×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 15815

      Sorry, pritning is not allowed

የመ.ቁ 15815
ታህሣሥ 10 ቀን 1998 ዓ.ም
ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
አቶ ፍስሐ ወርቅነህ
አቶ አብዱልቃድር መሐመድ
ወ / ሮ ስንዱ ዓለሙ
አቶ መስፍን እቁበዮናስ
አመልካች፡- እርሲ እርሻ ልማት ድርጅት- ቃሲም ፈጂስ ቀረበ
ተጠሪ፡- አቶ ሰለሞን አበበ- አልቀረበም
የስራ ክርክር - ስለ ማኔጅመንት አባል የሆነ ሰው የስራ ስንብት ፣
ስለ ስራ ስንብት እና መመለስ ፣ የካሳ ክፍያ እና ማስጠንቀቂያ
የፍ / ብ / ህ / ቁ 2570 ፣ 2573 ፣ 2574 ፣ 2571
የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአሁን ተወሪን አመልካች ስራ ያባረረው ህጉን ተከትሎ ባለመሆኑ የተቋረጠበት ጥቅማ ጥቅም ተከፍሉት
ወደ ስራ ሲመለስ ይገባል በማለት በአርሲ ዞን ከፍ / ቤት የተሠጠውን ውሳንኔ በማፅናቱ የቀረበ አቤቱታ ፡፡ ው ሳ ኔ፡- የአርሲ ዞን ከፍ / ቤት የሰጠውና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ
ቤት ያጸናዉ ዉሳኔ ተሽራል ፡፡ 1 ኛ . በስራ አመራር ላይ ያሉ አባላት የስራ ውላቸው ቢቋረጥ የሚያገኙት
መፍትሔ በአሠሪ ሠራተኛ አዋጅ የሚሸፈኑ ሠራተኞች ከሚያገኙት
መፍትሔ የተለየ ነው ፡፡
2 ኛ . ዕኣመራር ላይ ያለው ሠው ያለበቂ ምክንያት ያለማስጠንቀቂያ ቢባረር
የሶስት ወር ደመወዝ ካሳ ይሠጠዋል እንጂ ወደ ስራ ሊመለስ አይችልም ::
ታህሣሥ 10 ቀን 1998 ዓ.ም
የመ.ቁ 15815
ዳኞች ፦ አቶ መንበረፀሐይ
አቶ ፍስሐ ወርቅነህ
ኣቶ ኣብዱልቃድር መሐመድ
ወ / ሮ ስንዱ ዓለሙ
አቶ መስፍን እቁበዮናስ
አመልካች ፦ እርሲ እርሻ ልማት ድርጅት- ቃሲም ፈጂስ ቀረበ
ተጠሪ፡ አቶ ሰለሞን አበበ- አልቀረበም
ፍ ር ድ
ይህ ክርክር የተጀመረው በኦሮሚያ አርሲ ዞን ከፍተኛ ፍ / ቤት ነው ።
ክሱን የመሠረተው ተጠሪው ሲሆን አቤቱታውም በኣጭሩ አመልካች በ 1989
ዓ.ም የወጣውን የማኔጅመንት መተዳደሪያ ደንብ ኣንቀጽ 37 ( 1 ) በመተላለፍ ከስራ ያሰናበተኝ በመሆኑ የቀረብኝ ጥቅማ ጥቅም ተከፍሉኝ ወደ ስራ እንድመለስ ይወሰንልኝ የሚል ነው ፡፡ ክሱ የቀረበለት ፍ / ቤትም ግራ ቀ፬ን
በጉዳዩ ከአከራከረ በኋላ የተጠሪ የስራ ስንብት ደንቡን ተከትሉ ያልተፈፀመ
ስለሆነ የተቋረጠበት ጥቅማ ጥቅም ተከፍሉት ወደ ስራ ሊመለስ ይገባል በማለት
ወስኗል ፡፡ ይህ ውሣኔም ጉዳዩን በይግባኝ ሳየው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ / ቤት
ፀንቷል ፡፡
በመቀጠል አቤቱታ የቀረበለት ይህ ችሉትም የግራ ቀኙን ክርክር
መርምሯል ፡፡
አንድ የማኔጅመንት
አባል የሆነ ሰው
ከሥራ ቢሰናበት ስንብቱ
ሥርዓቱን የተከተለ አይደለም በማለት ወደ ስራ እንዲመለስ መወሰንን ሕጉ
The ይቅዶዋል ? ወይስ አይፈቅደውም ? * የማየው Afy ዋዋሰጉ rq ምላሹፈታኝ
የሚገባው ነጥብ መሆኑንም ተገንዝቧል ፡፡
ተጠሪ ከአስተዳደሩ ክፍል የሚፈረጅ ሰራተኛ መሆኑ አላከራከረም ፡፡
ከስራ የተሰናበተውም በድርጅቱ የስራ አመራር ቦርድ በተሰጠ ውሣኔ መሆኑ
በስር ውሣ ተመልክቷል ፡፡ እንዲሁም በአስተዳደር መተዳደሪያ ደንቡ መሠረት
ተጠሪ ፈፅሞታል የተባለው ጥፋት አስቀድሞ በኮሚቴ ከዚያ ዶግም 8 ይገባኝ በስራ አመራር ቦርድ ታይቶ ውሣኔ ሊያገኝ ሲገባው ተጠሪው በቀጥታ በቦርዱ
ከስራ እንዲሰናበት መወሰኑ በደንቡ የተቀመጠውን ሥርዓት የጠበቀ አይደለም
በሚል ምክንያት ከፍ ሲል የተጠቀሰው ውጭ በስር ፍርድ ቤቶች መስጠቱን
መዝቡ ያስረዳል ፡፡
በመሠረቱ የስር ፍርድ ቤቶች ለውጭያቸው መሠረት ያደረጉት
የአስተዳደር መተዳደሪያ ደንቡን
የአስተዳደር መተዳደሪያ አንድ የአመራር አባል ጥፋት ፈጽሟል ቢሰኝ የጥፋቱ
መፈፀም አለመፈፀም ተጣርቶ እርምጃ የሚወሰድበት ሥርዓት የተቀመጠበት
ደንብ መሆኑንም ከውጭያቸው መንፈስ መረዳት ይቻላል ፡፡ ፍርድ ቤቶቹ
ተጠሪ ከስራ የተሰናበተበትን ሁኔታ ከደንቡ ጋር በማገናዘብ ስንብቱ በደንቡ
የተመለከተውን
ኣይደለም
ማጠቃለያ
መድረሣቸውም ከፍ ሲል ተጠቅሷል ፡፡ እንግዲህ የተጠሪ የስራ ስንብት ደንቡን
የተመሠረተ መሆን
አለመሆኑን ለመለየት የክርክሩን
ፍሬ ነገር ማጥራት
ያስፈልጋል ። ይህ ደግሞ የዚህ ችሉት የስራ ድርሻ ባለመሆኑ የስር ፍርድ
ቤቶች ስንብቱ ደንቡን የተከተለ አይደለም ሲሉ በፍሬ ነገሩ ረገድ የደረሱበትን
መደምደሚያ ይህም ችሉት ተቀብሉታል ፡፡
በሌላ በኩል ግን በአስተዳደር መተዳደሪያ ደንቡ መሠረት ያልተፈፀመ የስራ ስንብት ለሰራተኛው ወደ ስራ የመመለስን መፍትሔ ሊያሰጠው የመቻል አለመቻሉ ጉዳይ የሕግ ጥያቄን የያዘ ነውና በዚህ ችሉት ሊዳኝ ይባዋል ። ከመዝገቡ መረዳት እንደሚቻለው የስር ፍ / ቤቶች ተጠሪ ወደ ስራ እንዲመለስ ይወስኑ እንጂ ይህንኑ እንዲወስኑ ያስቻላቸው የደንቡን አንቀጽ በውሣኔያቸው
የተሰናበተን
የመመለስ
አላረጋገጡም ። እንዲሁም ተጠሪ የአስተዳደር መተዳደሪያ ደንቡ ከስርዓት ውጭ የተናበተ የአመራር ኣባል ወደ ስራ ይመለስ ዘንድ የሚፈቅድ ነው ሲል ያቀረበው ርክር የለም ። ይህ ደግሞ ፍርድ ቤቶቹ ተጠሪ ወደ ስራ ይመለስ ሲሉ ለደረሱበት መደምደሚያ በደንቡ የተፈቀደ መፍትሄን መነሻ አለማድረጋቸውን ለማመላከት ይበቃል ፡፡ ፍርድ ቤቶቹ ያስደገፉት ሕግ ሣይኖር የደረሱበት ይህን ይህ ማጠቃለያም አሳማኝነት የሚጎድለው ሆኖ አግኝተነዋል ።
ስለሆነም ጉዳዩ ለክርክሩ ኣግባብነት ከአለው የፍ / ብ / ሕጉ ድንጋጌዎች አኳያ ሊመረመር የሚገባው መሆኑን አምነንበታል ። በመሠረቱ ተጠሪ የስራ አመራር አባል በመሆኑ ከአመልካች ጋር የፈፀመው ያልተወሰነ ጊዜ የሰራ
ከሁለቱ በአንዳቸው የሁለት ወር ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ሊቋረጥ እንደሚችል ከፍ / ብ / ሕ / ቁ 2570 እና 2571 ላይ መረዳት ይቻላል ። ውሉን ያቋረጠበት በቂ ምክንያት ለሰራተኛው የሦስት ወር ደመወዙን የመክፈል ግዴታ እንዳለበት በዚሁ ሕግ
አንቀጽ 2573 እና 2574 ላይ ተደንግጎ ይገኛል ፡፡ እነዚህ ድንጋጌዎች እንደ
ተጠሪ ያሉ የስራ አመራር አባላት የፈፀሟቸው የስራ ውሉች ያለበቂ ምክንያት እንኳ ሊቋረጡ እንደሚችሉ የሚያስገነዝቡ ናቸው ። የስራ ውሉ መቋረጥ
በአሰሪው በኩል በቂ ምክንያት ያልተሰጠበት ከሆነም ሰራተኛውን ወደ ስራ
የመመለስ መፍትሄ የሚያስገኘለት ሣይሆን ካሣ ተቀብሉ ይስናበት ዘንድ የሚፈቅዱለት ናቸው ። ይህም የሚያሣየን በሥራ አመራር ላይ የሚገኙ ሰዎች የሥራ ውላቸው ቢቋረጥ የሚያገኙት ሕጋም መፍትሄ ( remedy ) ሌሎቹ በአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ የሚሸፈኑ ሰራተኞች ከሚያገኙት መፍትሄ የተለየ መሆኑን ነው ። ፍርድ ቤቶች ለአንድ መብቴ ተነካ ለሚል ወገን የሚሰጡት መፍትሄ ደግሞ በሕጉ ላይ የተመሠረተ መሆን ይኖርበታል ። ከተጠቀሱት
ለመገንዘብ እንደሚቻለው የሥራ አመራር
የሥራ አመራር ላይ ያለ ሰው ሰማይፈቅደው ምክንያት እንኳን ከሥራ ቢሰናበት ፍርድ ቤት ወደ ሥራው እንዲመለስ ለማድረግ የሚያስችለው የሕግ - ድጋፍ የለውም ። ሕጉ የሰጠው
መብት ካሳ መቀበል ብቻ ነው :: * The Afrie ቲያያዘው aw ቱዴይ hi መሪ ብርድ www ው ¥¥¥ idu ስራ aw ሕወሰናበቱ e . እንጂ
አመልካቹ የሁለት ወር ማስጠንቀቂያ በመሰበት የስራ ውሉኝ ያቋረጠው
መሆኑን አልተረጋገጠም ። እንዲሁም ተጠሪው ለስንብቱ ምክንያት የተደረጉትን መስሪያ ቤቱን በቅንነት ለማገልገል ፈቃደኛ አይደለም፡ የበታች ሰራተኞችን ይንቃል ትእዛች እይቀበልም ... ወዘተ በሚል በአመልካች የተጠቀሱትን ጥፋቶች መፈፀም አለመፈፀሙም በስር ፍርድ ቤቶች አልተረጋገጠም ። በሌላ በኩል ግን የሥር ፍርድ ቤቶች የተጠሪ የስራ ስንብት የአስተዳደር መተዳደሪያ ደንቡን ተመስርቶ የተፈፀመ አይደለም የሚል ማጠቃለያ ላይ የደረሱ ሲሆን ይህም ችሉት ፍርድ ቤቶቹ በጉዳዩ ፍሬ ነገር የደረሱበትን የተጠቀሰውን ማጠቃለያ ተቀብሉታል ። እነዚህ በጉዳዩ የሚታዩት ፍሬ ነገሮች ተዳምረው ሲመሆኑም አመልካች የተጠሪን
ለማቋረጥ በቂ ምክንያት አልነበረውም ለማለት ያህል መሆናቸውንም አምኖበታል ፡፡ ይህም ተጠሪው ማስጠንቀቂያ ያልተሰጠው በመሆኑ ምክንያት . የሁለት ወር ደመኻ የስራ ስንብቱ በበቂ ምክንያት ያልተደገፈ በመሆኑ ምክንያት ደግሞ ቢበዛ የሦስት ወር ደመወዝ በካሣ መልክ እንዲያገኝ የሚያስችለው እንጂ ወደ ስራ እንዲመለስ የሚያደርገው እይደለም ። ስለሆነም የስር ፍርድ ቤቶች ተጠሪው ወደ ስራ እንዲመለስ የሰጡት ውጭ ከፍ ሲል ከተጠቀሱት የፍትሐብሔሩ ድንጋጌዎት ጋር ያልተጣጣመ ነው ።
ው ሣ ኔ
1. የተጠሪ የስራ ውል መቋረጥ በፍ / ብ / ሕ / ቁ .2570 ( 1 ) የተደገፈ ነውና
ወደ ሥራ ሊመለስ አይገባም ፡፡ 2. ይሁን እንጂ አመልካች የተጠሪን የስራ ውል ያቋረጠበት በቂ
ምክንያት ስለሌለው በፍ / ብ / ሕ / ቁ .2573 እና 2574 መሠረት
የሦስት ወር ደመወዝ በካሣ መልክ እንዲከፈለው ተወስኗል ፡፡ 3. በተጨማሪም የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ
ያልተሰጠው በመሆኑ በፍ / ብ / ሕ / ቁ 257 0 ( 2 ) እና 2571 መሠረት
የሁለት ወር ደመወዙ እንዲከፈለው ተወስኗል ፡፡ 4. የእርሲ ዞን ከፍተኛ ከፍተኛ ፍ / ቤት በመ.ቁ. 38/95 የኦሮሚያ
ጠቅላይ ፍ / ቤት ደግሞ በመ.ቁ. 2339/95/016 ግንቦት 3 ቀን
1995 ዓ.ም የሰጠት ውሣኔ ተሽሯል ፡፡
የማይነበብ የኣምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ።

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?