የሰበር መ.ቁ .13223
ጥቅምት 9 ቀን 1998 ዓ.ም
ዳኞች፡- 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
2. አቶ ፍስሐ ወርቅነህ
3. ወ / ሮ ስንዱ ዓለሙ
4. ወ / ሮ ሆሳዕና ነጋሽ
5. አቶ አሰግድ ጋሻው
አመልካች፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
መልስ ሰጭ፡- አቶ አስፋ ኣበበ
ስለ ፍርድና ስለትዕዛዝ- የይግባኝ ሰሚ ፍ / ቤት የመጀመሪያ
ደረጃ ፍ / ቤት ውሳኔ ከሰጠበት ጉዳይ ውጭ ጭብጡን ለውጦ
ውሳኔ ስለሚሰጥበት ሁኔታ ይግባኝ ሰሚው ፍ / ቤት ተጨማሪ
ማስረጃ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ስለሚሰጥበት ሁኔታ፡- የፍትሐብሄር
ሥነ ስርዓት ህግ ቁጥር 182/2 } ፣ 342 ፣ 345 / 1 / ስ /
መልስ ሰጭ የጎንደር ስጋ ፋብሪካ ገንዘብ የሆነ ብር 486,312.00
ቅርንጫፍ በኩል እንዲከፈለው በማድረግ በፈጸመው ድርጊት ከስራ
ተሰናብቶ የወንጀል ጉዳዩ በሂደት ላይ የነበረ ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ
ፍ / ቤት መ / ሰጭ ወደ ስራ እንዲመለስ የሰጠው ውሳኔ በይግባኝ እየታየ
እያለ መ / ሳጭ በፈጸመው ድርጊት በወንጀል ተጠያቂ ተደርጎ ብር
የተቀጣ ቢሆንም ይኸው ክርክር የቀረበለት ይግባኝ ሰሚው
የከፍተኛው
አመልካች
የወንጀል
መዝገሱን በማስረጃነት
አላቀረበም በሚል ክርክሩን ውድቅ ስላደረገው የቀረስ አቤቱታ ፡፡
ውሳኔ፡- የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት
የሰጠውና የፌዴራል
ከፈተኛ ፍ / ቤት ያሻሻለው ውሳኔ ተሽሯል ፡፡
ይግባኝ ሰሚ ፍ / ቤት በተከራካሪ ወገኖች ባይቀርብለትም
ተገቢ በሆነ ጊዜ ማንኛውም አይነት ሰነድ ወይም
ምስክር ወይም ሌላ አይነት ማስረጃ በተጨማሪነት
እንዲቀርብ ማድረግ አለበት ፡፡
ይግባኝ ሰሚ ፍ / ቤት ይግባኝ የቀረበበትን ውሳኔ የሰጠው
ፍ / ቤት ከያዘው ጭብጥ ውጭ ጭብጡን ለውጦ ፍርድ
መስጠት ይችላል ፡፡
የመ.ቁ. 13223
ጥቅምት 9 ቀን 1998 ዓ.ም.
ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
አቶ ፍስሐ ወርቅነህ
ወ / ሮ ስንዱ ዓለሙ
ወ / ሮ ሆሳዕና ነጋሽ
አቶ አሰግድ ጋሻው
አመልካች፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
መንበረ አድማሱ ቀረበች
ተጠሪ፡- አቶ አስፋው አበበ - ቀረበ
ፍ ር ድ
የአሁን ተጠሪ የሥራ
ውሌን ከሕግ
አቋርጦታልና ውዝፍ ደመወዜን ከፍሎ ወደ ሥራ ይመልሰኝ ሲል
በአሁን አመልካች ላይ ክስ መስርቷል ፡፡ አመልካቹም ለሥራ ውሉ
መቋረጥ ምክንያት የሆነው ተጠሪው ሐሰተኛ ማሕተምና ፊርማ የያዘ
የማዘዣ ደብዳቤ ለባንኩ ቀርቦ ሳለ የበኩሉን ማጣሪያ ባለማድረግ
የጎንደር ስጋ ፋብሪካ ገንዘብ የሆነው ብር 486,312.00 ለአምጪው
በአሰሳ ንግድ ባንክ አማካኝነት እንዲከፈል ማድረጉ መሆኑን በመዘርዘር
ኪሣራ ላይ እንዲወድቅ አድርጓልና የሥራ ውሉ ያለማስጠንቀቂያ
መቋረጡ ተገቢ ነው ሲል መልሱን ሰጥቶ ተከራክሯል ፡፡
ክሱ የቀረበለት ፍ / ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ
የደብዳቤው ማህተምና ፊርማ ትክክለኛነት የሥራ ድርሻው በሆነ ሌላ
ሰው የተረጋገጠ መሆኑን ተጠሪ ይህን የመስራት ኃላፊነትም ሆነ ግዴታ
የሌለበት መሆኑን ፣ በባንኩ መመሪያም መሰረት ሰነዱን ከተጠራጠረ
ገንዘቡን ከመክፈሉ በፊት አውጪውን ማማከር ያለበት ከፋዩ የአሰላ ባንክ
እንጂ ተጠሪው የሚገኝበት የባንኩ የመስቀል አደባባይ ቅርንጫፍ
አለመሆኑን በመግለጽ የተጠሪው የሥራ ውል የተቋረጠው ከሕግ ውጭ
ነውና የሥራ ውሉ ከተቋረጠበት ጊዜ ጀምሮ ውሣኔው እስከተሰጠበት
እለት ድረስ ያለው ውዝፍ ደመወዝ ተከፈሎት ወደ ሥራው ሊመለስ
ይገባል በማለት ወስኗል ፡፡
ከዚህ ውሣኔ ላይ አመልካቹ ይግባኝ ተጠሪው ደግሞ መስቀለኛ
ይግባኝ አቅርበው በፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት የተከራከሩ ሲሆን የከፍተኛ
ፍ / ቤትም ተጠሪ የሦስት ወር ደመወዝ ብቻ ተከፍሎት ወደ ሥራ ይመለስ
ሲል የስር ፍርዱን አሻሽሎታል ፡፡
በመቀጠል አመልካች ውሣኔው መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት
የተፈፀመበት ነው ሲል አቤቱታውን ለዚህ ችሎት አቅርቧል ፡፡ ተጠሪም
መልሱን ሰጥቶ ተከራክራል ፡፡
ይህም ችሎት ከቀረበለት ክርክር በመነሳት በጉዳዩ ሊታይ
የሚገባው ነጥብ ተጠሪ ፈጽሞታል በተባለው ተግባር በወንጀል ጥፋተኛ
ተሰኝቷል ? ወይስ አልተሰኝም ? የሥራ ውሉስ መቋረጥ በሕግ የተደገፈ
ነው ? ወይስ አይደለም ? የሚለው መሆኑን ተገንዝቧል ፡፡
“ በወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ መገኘትና በጥፋቱም ምክንየት ለያዘው
ሥራ ብቁ ሆኖ አለመገኘት
* የሥራ ውልን ያለማስጠንቀቂያ ሊያቋርጥ
የሚችል ምክንያት መሆኑ በኣዋጅ ቁ . 42/85 አንቀጽ 27 / ቀ / ላይ
ተደንግጋል ፡፡ ወደ ተያዘው ጉዳይ ፍሬ ነገር ስንመለስ አመልካች ተጠሪው
በፈፀመው ጥፋት በመ.ቁ. 4176/88 በወንጀል ተከስሶ የጥፋተኛነት ውሣኔ
ተሰጥቶበት ብር 500.00 ተቀጥቷል ሲል ተከራክሯል ። ይህ ክርክር
የቀረበለት የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት ደግሞ አመልካቹ በተጠቀሰው
W ዝገብ በማስረጃነት ሊያቀርብ
አልቻለም በሚል ክርክሩን ውድቅ ማድረጉን በውሣኔው አመልክቷል ፡፡
በመሰረቱ አንድ ይግባኝ ሰሚ ፍ / ቤት በራሱ አስተያየት ተገቢ ሆኖ
ሲያገኘው ማናቸውም አይነት ሰነድ ወይም ምስክር ወይም ሌላ አይነት
በተጨማሪነት
ይቀርብለት
እንዲችል
በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕ / ቁ .345 ስልጣን ተሰጥቶታል ፡፡ እንዲሁም አንድ ፍ / ቤት
ለውሣኔው አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው በእራሱ አነሳሽነትም ሆነ በተከራካሪዎቹ
ጠያቂነት በሌላ ፍ / ቤት የሚገኝ ሰነድ ፣ የጽሁፍ ማስረጃ ወይም ፍርድ
የተሰጠበት
እንዲቀርብለት
እንደሚችል
በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕ / ቁ .145 / 1 / ላይ ተመልክቷል ፡፡ በተጨማሪም ይግባኝ ሰሚ
ፍ / ቤት የስር ፍ / ቤት ለውሣኔው መሠረት በአደረገው ምክንያት ሳይገደብ
ጉዳዩን ራሱ በተረዳው አይነት ጭብጥ ስውጦ ፍርድ ሊሰጥ እንደሚችል
ከፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕ / ቁ . 342 እና 182 / 2 / ላይ መገንዘብ ይቻላል ፡፡ ከፍ ሲል
እንደተመለከተው ይህን ጉዳይ በይግባኝ ያየው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት
ተጠሪው በወንጀል ተከስሶ የተቀጣ ስለመሆኑ ክርክሩ በአመልካች ቀርቦለታል ፡፡ እንዲህ ከሆነ ደግሞ ክርክሩን ከአዋጅ ቁ . 42/85 አኳያ
የተሰጠበትን የጥፋተኛነት ውሣኔ ይዘት አሊያ
ፈልጋል ፡፡ ይህንንም ሊመረምረው እና ውሣኔውንም ለመስጠት ተጠሪው በወንጀሉ ጉዳይ
ጉዳዩ ከሥራ ውሉ
መቋረጥ ጋር ያለውን ተያያዥነት እንዲያየው ያስፈልጋል ፡፡ ይህንንም
ለማድረግ በአመልካች ቁጥሩ የተጠቀሰለትን የወንጀል መዝገብ ከሚገኝበት
ፍ / ቤት ሰራሱ አነሳሽነት ጭምር ሲያስቀርበው ይገባል ፡፡ ይሁን እንጂ
ፍ / ቤቱ ይህንን አላደረገም ፡፡ ይልቁንም ተጠሪው ሰወንጀል ስለመቀጣቱ
ክርክሩ ቢቀርብም መዝገቡ በማስረጃነት ሊቀርብ አልቻለም ሲል ነጥቡን
አልፎታል ፡፡ በወንጀሉ ጉዳይ የተሰጠው ውሣኔ የሥራ ክርክሩን ጉዳይ
ለመወሰን የግድ አስፈላጊ መሆኑ እየታየም ፍ / ቤቱ በወንጀሉ ክስ
የተሰጠውን ፍርድ በእራሱ አነሳሽነት አስቀርቦ አለማየቱ የክርክሩን
በተጠቀሱት
የፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕጉ
ድንጋጌዎች
አለማስደገፉንና በውጤቱም መሠረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት መፈፀሙን
ያረጋግጣል ፡፡
በሌላ በኩል ግን ይህ ችሎት ተጠሪው ግብረ አበር
ተገቢውን ማጣራት ሳያደረግ መጠኑ ከላይ የተጠቀሰው የፋብሪካው ገንዘብ
በአሰላ ቅርንጫፍ አማካኝነት ለሌላው ተከሣሽ እንዲከፈል አድርጓል
በሚል ከሌሎች ተከሣሾች ጋር በከባድ አታላይነት ወንጀል በፌዴራል
ከፍተኛ ፍ / ቤት ተከሶ ፍ / ቤቱ ተጠሪውን በወ / መ / ሕ / ቁ . 412 / 1 / መሠረት
ጥፋተኛ በማድረግ ብር 5 ዐዐ .00 የቀጣው መሆኑን እና ይህም ፍርድ
በተጠሪው አማካኝነት ይግባኝ
በቀረበለት የፌዴራል ጠቅላይ ፍ / ቤት
ስመ.ቁ. 3885 መጽናቱን አረጋግጧል ፡፡ እንዲሁም የፌዴራል ጠቅላይ
ፍ / ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አመልካቹ በመቁ . 6928 ፍርዱ መሰረታዊ
የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ሲል ያቀረበውን አቤቱታ
በአለመቀበል መዝገቡን የዘጋው መሆኑን ተገንዝቧል ፡፡
ይህ በወንጀሉ ጉዳዩ የተሰጠው ፍርድ ተጠሪው ጥፋተኛ መሰኘቱን ብቻ
ሳይሆን ጥፋተኛ የተሰኘው ከሥራው ጋር በተያያዘ ሁኔታ ፈጽሞታል
በተባለ ወንጀል መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው ፡፡ የተረጋገጠበት ጥፋትም
በስራው ለመቀጠል ብቃት የሌለው መሆኑን ለማሳየት የሚሰቃ ነው ፡፡
እንደውም የሥራ ውል መቋረጥ ሰኣዋጅ ቁ . 42/85 አንቀጽ 27 / ቀ /
መደገፉን የሚያረጋግጥ ነው ፡፡ ይህ በመሆኑም አቤቱታው በቀረበበት
ውሣኔ ተጠሪው የሦስት ወር ደመወዝ ተከፍሎት ወደሥራ እንዲመለስ መወሲኑ የሕግ ድጋፍ የሌለው ነው ፡፡
© ጠር o ሆነ ምክንያት
ው ሣ ኔ
1 ኛ የተጠሪ የሥራ ውል የተቋረጠው ሕጋዊ
በመሆኑ ወደ ሥራ ሊመለስ አይገባም ፡፡
2 ኛ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት በመ.ቁ. 21/88 ፧
የፌዴራል ከፍተኛ ፍ / ቤት ደግሞ በመ.ቁ. 6222
ተጠሪ ውዝፍ ደመወዝ ተከፍሎት ወደ ሥራ
እንዲመለስ የሰጡት ውሣኔ በፍ / ብ / ሥ / ሥ / ሕ / ቁ .
348 / 1 / መሠረት ተሽራል ፡፡
You must login to view the entire document.