ኣለመሆኑን የሚመለከት ነው ፡፡
የሰበር መ / ቁ 21086
ግንቦት 04 ቀን 1998 ዓ.ም.
ዳኞች፡- 1. አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
2. አቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ
3. አቶ ጌታቸው ምህረቱ
4. አቶ መስፍን እቁበዮናስ
5. ወ / ት ሂሩት መለሠ
አመልካች፡- የቀጨኔ ደብረ ሠላም መድኃኔአለም ቤ / ክርስትያን አስተዳደር
ተጠሪ፡- መምሬ ምስጋናው አስፋው
ፍ ር ድ
በዚህ ጉዳይ
ችሎት የቀረበው ክርክር የሃይማኖት ወይም የመንፈሳዊ
አገልግሎት የሚሰጡ ሠራተኞች ከሃይማኖት ድርጅቱ ጋር ያላቸው የሥራ ግንኙነት
በአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ የሚሸፈን መሆን
መልስ ሰጪ በአመልካች ቤ / ክርስትያን መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሰጡ ሲሆኑ
በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት ባቀረቡት ክስ ቤ / ክርስትያንዋ ያላግባብ ከሥራ
ስላሰናበተቻቸው ውዝፍ ደሞዝ ተከፍሏቸው ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ ጠይቀዋል ፡፡
ፍ / ቤቱም የቀረበለትን ጉዳይ በአዋጅ ቁጥር 377/96 መሠረት መርምሮ ተጠሪ
ውዝፍ ደሞዝ ተከፍሏቸው ወደ ሥራ እንዲመለሱ ወስኗል ፡፡
ይግባኝ ሰሚው ፍ / ቤትም ከላይ የተመለከተውን የሕግ ነጥብ ሳይመረምር
አልፎታል ፡፡
ፈዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ገልባጭ
ወሰነ የሕግ ስህተት አለበት ፡፡
በዚህ ጉዳይ ፌ / መጀመሪያ ደረጃ ፍ / ቤት መልስ ሰጪ ያቀረቡትን አመልካች በዚህ ችሎት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታም ተመርምሮ ጉዳዩ ለሰበር ችሎት እንዲቀርብ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት መ / ሰጪ ቀርበው መልስ ሰጥተዋል ፡፡
ይህ ችሎትም የሃይማኖት ወይም የመንፈሳዊ አገልግሎት የሚሰጡ ሠራተኞች ከሃይማኖት ድርጅት ጋር ያላቸው የሥራ ግንኙነት በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ይሸፈናል ? ወይስ አይሸፈንም ? የሚለውን የሕግ ነጥብ መሰረት በማድረግ አቤቱታ የቀረበበትን ውሣኔ መረምራል ፡፡
ይህ ችሎት በመዝገብ ቁጥር 18419 ግንቦት 4 ቀን 1998 በሰጠው ውሣኔ አግባብነት ያላቸውን የህጉን ድንጋጌዎች በመተርጎም አንድ የሃይማኖት አገልግሎት የሚሰጥ ሠራተኛ ከሃይማኖት ድርጅት ጋር ያለው የሥራ ግንኙነት በአሰራ እና ሠራተኛ አዋጅ የሚሸፈን አለመሆኑ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል ፡፡
በመሆኑም
ጥያቄ በአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ የሚሽፈን አይደለም በማለት ውድቅ ሊያደርገው ሲገባ
ጉዳዩን በዚህ ሕግ መሠረት አይቶ
ው ሣ ኔ
1. የፌ / መጀመሪያ ደረጃ ፍ /
ቤት በመ / ቁ 11456 በየካቲት 21 ቀን 1997 ዓ.ም
የሰጠው ውሣኔና የፌ / ከፍተኛ ፍ / ቤት በመ / ቁ . 37574 በሐምሌ 21 ቀን
1997 ዓ.ም. የተሰጠው ትዕዛዝ ተሽሯል ፡፡
2. ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻሉ ፡፡
3. መዝገቡ ተዘግቷል ፤ ይመለስ ፡፡
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ፡፡
ፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት
ትክክል ገልባጭ
You must login to view the entire document.