ስለ ፋሎት የቀረበው
የሰበር መ / ቁ 22796
ቀን 24/4/99
ዳኞች 1. አቶ ከማል በድሪ
2. አቶ ፍስሐ ወርቅነህ
3. አቶ ዓብዱልቃድር መሐመድ
4. አቶ መስፍን እቁበዮናስ
5. ወ / ት ሒሩት መለሠ
አመልካች፡ ወ / ሮ ሐዋ አብዱላሂ
መልስ ሰጪ የሆሳዕና የመኖሪያ ቤት ሕብረት ሥራ ማኅበር
ፍ ር ድ
ጉዳዩ ለዚህ
ያስረክበኝ በሚል አመልካች ያቀረበችውን ክስ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት
በአዋጅ ቁጥር 147/91 አንቀጽ 46 እና 47 መሠረት ጉዳዩ የሚታየው በእርቅ ወይም
በሽምግልና ዳኝነት ስለሆነ ፍርድ ቤቱ ስልጣን የለውም በማለት ውድቅ በማድረግ በሰጠው
ውሣኔ ቅር በመሰ ት አመልካች የሰበር አቤቱታ በማቅረቧ ነው :: ጉዳዩ ለሰበር ችሎት
እንዲቀርብ በተሰጠው ትዕዛዝ መሠረት አመልካችና መልስ ሰጭ ክርክራቸውን ለችሎቱ
በቃል አሰምተዋል ፡፡
ይህ ችሎትም በአዋጅ ቁጥር 147/91 አንቀጽ 46 እና 47 መሠረት ጉዳይ
የሚታየው በእርቅ ወይም በሽምግልና ዳኝነት ስለሆነ ፍርድ ቤቱ ስልጣን የለውም በሚል ክሱ
ውድቅ የተደረገው በአግባቡ ነው ? ወይስ አይደለም ? የሚለውን የሕግ ነጥብ መሠረት
በማድረግ ጉዳዩን መርምሯል ፡፡
ከላይ እንደተመለከተው ለመልስ ሰጭ የከፈልኩት ገንዘብ ወይም ቦታ ያስረክበኝ
በሚል አመልካች ያቀረበችውን ክስ በስር ፍርድ ቤት ውድቅ የተደረገው አዋጅ ቁጥር
147/91 አንቀጽ 46 እና 47 መሠረት ጉዳዩ የሚታየው በእርቅ ወይም በሽምግልና ዳኝነት
የቀድሞ ሰራተኛ ተጠሪው ወራሾች ወ ' ን
እንደሆነ ተደንግጓል በሚል ነው :: በመሆኑም አዋጅ ቁጥር 147/91 አንቀጽ 46 እና 47
ለጉዳዩ አግባብነት ያላቸው መሆን አለመሆኑን መመርመር የስፈልጋል ፡፡
የአዋጅ ቁጥር 147/91 አንቀጽ 46 እና 47 በአዋጁ አንቀጽ 49 የተመለከቱት
ክርክሮች በእርቅና በሽምግልና ዳኝነት የሚያልቁ መሆኑን ይደነግጋል ፡፡ ክርክሩ በአዋጁ
አንቀጽ 49 ከተመለከቱት አይነቶች ውጭ ከሆነ አንቀጽ 46 እና 47 ለጉዳዩ አግባብነት
ያላቸው አይሆኑም ፡፡ በአንቀጽ 49 የተመለከቱት የክርክር አይነቶች በአባላት ፣ በቀድሞ
አባላትና በቀድሞ አባላት ወኪሎች ወይም በሞት በተለዩ አባላት ስም መብት የሚጠይቁ
ሰዎች መካከል የሚነሳ ክርክር ፤ በአባላት ፣ በቀድሞ አባላት ፣ በቀድሞ አባላት ወኪሎች ወይም
በሞት በተለዩ አባላት ስም መብት በሚጠይቁ ሰዎችና በማኀበሩ ስራ አመራር ኮሚቴ ፣
በማናቸውም ሹም ወኪሉ ወይም በማኀበሩ ሰራተኛ መካከል የሚነሳ ክርክር እና በማኅበሩ
ወይም በሥራ አመራር ኮሚቴ ወይም በማንኛውም የቀድሞ የስራ አመራር ኮሚቴ
በማንኛውም ሹም ወኪል ወይም ሰራተኛ ወይም የቀድሞ ሹም የቀድሞ ወኪል ወይም
ወኪሎቹ ወይም በሞት በተለዩ የማኅበሩ ሹሞች
ወኪሎች ወይም ሰራተኞች መካከል የሚነሱ ክርክሮች ናቸው ::
በዚህ ጉዳይ አመልካች የገንዘብ መዋጮውን ከከፈላችሁ
መዋጮ ባልከፈሉት
የመልስ ሰጭ ማኀበር አባላት ምትክ ተተክታችሁ ቤት ታገኛላችሁ ተብዬ ገንዘብ ከፍያለሁ
ባይ ናቸው :: አመልካች የማኅበሩ አባል ነኝ የማይሉ ሲሆን የማኅበሩ አባል ስለመሆናቸው
የተረጋገጠ ነገር የለም :: ይህም አመልካች ከከፈላችሁ መዋጮ ባልከፈሉት የመልስ ሰጭ
ማኀበር አባላት ምትክ ተተክታችሁ ቤት ታገኛላችሁ ተብዬ ገንዘብ ከፍያለሁ ፤ ስለሆነም ቤቱ
ይሰጠኝ ወይም የከፈልኩት ገንዘብ ይመለስልኝ በማለት በማኅበሩ ላይ የመሰረቱት ክስ ከላይ
በተመለከቱትና በአዋጅ ቁጥር 147/91 አንቀጽ 49 ከተመለከቱት ክርክሮች ውጭ መሆኑን
ያሳያል ፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ጉዳዩ በአዋጁ አንቀጽ 46 እና 47 የሚሸፈን አይሆንም ።
በመሆኑም ይህ ችሎት የስር ፍርድ ቤት አመልካች የቀረበችውን ክስ የፌዴራል የመጀመሪያ
ፍርድ ቤት በአዋጅ ቁጥር 147/91 አንቀጽ 46 እና 47 መሠረት ጉዳዩ የሚታየው
በእርቅ ወይም በሽምግልና ዳኝነት ስለሆነ ፍርድ ቤቱ ስልጣን የለውም በሚል ውድቅ
በማድረግ የሰጠው ትዕዛዝ መሠረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝቶታል ፡፡
ው ሣ ኔ
- ጉዳዩን ለማየት ፍርድ ቤት ስልጣን አለው በማለት ተወስኗል ፡፡
የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ክርክሩን ከቆመበት በማስቀጠል ውሣኔ እንዲሰጥ
ተመልሶለታል ፡፡ ይፃፍ ፡፡
የፌዴራል የመጀሪያ ደረጃ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ / ቁ 07967 መጋቢት 28 ቀን
1997 ዓ.ም. የሰጠው ትዕዛዝና የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ / ቁ 39013
ታህሣሥ 04 ቀን 1998 የሰጠው ትዕዛዝ ተሽረዋል ፡፡ ይፃፍ ፡፡
በዚህ ችሎት ያወጡትን ወጭና የደረሰባቸውን ኪሳራ የየራሳቸውን
ይቻሉ ፡፡
መዝገቡ ተዘግቷል ።
የማይነበብ የአምስት ዳኞች ፊርማ አለበት ፡፡
You must login to view the entire document.