×
Browse Products About Us Login / Sign Up Contact Us አማርኛ
African Law Archive
Logo
የፍርድ ቤት ውሳኔ 14974

      Sorry, pritning is not allowed

የመ / ቁ .14974
2. አቶ ዮሴፍ ገ / ሥላ ኣስሚደረግ ውል -
የፌዴራል ጠቅላይ ፍ / ቤት
ሰበር ሰሚ ችሎት ዳኞች፡- አቶ መንበረፀሐይ ታደሰ
አቶ ፍሥሐ ወርቅነህ ወ / ሮ ስንዱ ዓለሙ አቶ መስፍን ዕቁበዮናስ
ወ / ት ሂሩት መለሰ አመልካች፡ ማህሌት ገ / ስላሴ መልስ ሰጪ፡- 1. አቶ መንግስቱ
ስለ እንደራሴነት - ከገዛ ራስ ጋር
ፍጹም ስለ ሆነ እንደራሴነት -
ጥብቅ የሆነ ቅን ልቡና - የፍትሐብሔር ህግ ቁጥሮች 2188፣2189፣2208፣2209 ፡ በከሳሽነት ወይም በተከሳሽነት የሙግት ተካፋይ ስለመሆን
ስለ ወኪሎች - ስለ
ባለጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ሳይቀርብ መቅረት
ተከሳሽ በሌለበተ የተሰጠውን ውሳኔ
ስለማንሳት - የፍትሐብሔር ሥነሥርዓት ህግ ቁጥሮች 57 ፣ 78
2 ኛ መ /
ሰጭ የአመልካች ወኪል ሆኖ ከ 1 ኛ መ / ሰጭ ጋር በአመልካች ላይ
ባቀረበው ክስ በአመልካች ወኪልነቱ 2 ኛ መ / ሰጭ መልሶ ሰጥቶ ጉዳዩ ውሳኔ እንዲነሳ
ያቀረበችውን ጥያቄ የም / ሸ / ዞን ከፍተኛ ፍ / ቤት ወኪልሽ መልስ ሰጥቷል በሚል ውድቅ
በማድረጉና ጉዳዩን በይግባኝ ያለው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ / ቤት ሰበር ችሎት የአመልካችን
ጥያቄ ውድቅ በማድረጋቸው የቀረበ አቤቱታ
ው ሳ ኔ፡- የም / ሸ / ዞን ከፍተኛ ፍ / ቤት ፣ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ / ቤት የኦሮሚያ ሰበር ችሎት
የሰጡት ትዕዛዝ ተሽሯል ፡፡
1- አንድ ተወካይ ለወካዩ ፍጹም ታማኝ መሆን ያለበት ሲሆን በወካዩ ጥቅምና በራሱ
ጥቅም መካከል ግጭት ባለበት ጊዜ ለወካዩ የማሳወቅ ግዴታ አለበት ፡፡
2- አንድ ተወካይ በወካዩ ላይ ባቀረበው ክስ ወካዩን ወክሎ መከራከር አይችልም ::
የመ / ቁ 14974
ቀን ሃምሌ 28 ቀን 1997
ዳኞች 1. አቶ መንበረፀሃይ ታደሰ
2. አቶ ፍስሃ ወርቅነህ
3. ወ / ሮ ስንዱ አለሙ
4. አቶ መስፍን እቁበዮናስ
5. ወ / ት ሒሩት መለሰ
አመልካች :
ወ / ት ማህሌት ገ / ስላሴ
1 ) አቶ መንግስቱ ኃብ
2 ) አቶ ዮሴፍ ገ / ሥላሴ
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ብይን የተሰጠው በም / ሸ / ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲሆን የአሁኑ ተጠሪዎች የአሁኗን አመልካች ጨምሮ ሶስት ሰዎች ላይ ክስ መስርተው ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ የአሁኗ አመልካች በሌለሁበት የተሰጠው ውሳኔ ተነስቶ ወደ ክርክሩ ልግባ በማለት በፍ / ሥ / ሥ / ህ / ቁ 78 መሰረት ታመለክታለች :: ፍርድ ቤቱም የአመልካች አቤቱታ ለአሁኖቹ ተጠሪዎች አንዲደርሳቸው አድርጎ ተጠሪዎቹም በክርክሩ ወቅት ለአመልካቿ ወኪል መጥሪያ ደርሶ መልስ የሰጠች ስለሆነ አቤቱታው ውድቅ ሊደረግ ይገባል በማለት
ተቃውመዋል ::
ጉዳዩን በመጀመሪያ ያየው የም / ሸ / ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ህዳር 17/1995 ዓ.ም በዋለው ችሎት በፍ / ሥ / ሥ / ህግ ቁጥር 78 መሰረት አንድ ሰው ክርክሩ ውስጥ ገብቶ መከራክር የሚችለው በሌለበት እና ሳይከራከር ውሳኔ ወይም ትእዛዝ ወይም ብይን ሲሰጥ ነው ፡፡ አመልካች ግን በተወካይዋ በኩል መጥሪያ ደርሷት መልስ ሰጥታ የተከራከረች በመሆኑና ውክልናው የተነሳ ለመሆኑም የቀረበ ነገር ስለሌለ አቤቱታዋ ተቀባይነት የለውም በማለት የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ አድርጓል :: ጉዳዩኑ በይግባኝ ያየው የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ውሳኔው ስህተት የለውም በማለት ይግባኙን በፍ / ሥ / ሥ / ህግ ቁጥር 337 መሰረት
የዘጋው ሲሆን የዚሁ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎትም ውሳኔው መሰረታዊ የህግ ስህተት የለውም ሲል የአመልካችን አቤቱታ ውድቅ አድርጓል ፡፡
የአሁኑ አቤቱታም የቀረበው በዚሁ ብይን ላይ ሲሆን የአመልካቹዋ ዋና ቅሬታም ፣ 2 ኛ ተጠሪ ራሱ ክስ አቅራቢ እራሱ መልስ ሰጪ ሆኖ ያቀረበው ክርክር ከህጉ መንፈስ ውጪ ነው የሚል ነው ::
ተጠሪዎች ለቀረበው አቤቱታ መልስ እንዲሰጡ ተጠርተው ስላልቀረቡ ጉዳዩ በሌሉበት ተይቷል ፡፡
ይህ ችሎትም መዝገቡን መርምሯል ፡፡ ከመዝገቡ የስር 2 ኛ ከሳሽ የአሁኑ 2 ኛ ተጠሪ ) የአመልካች ( የስር 3 ኛ ተከሳሽ ወኪል መሆኑ ፣ ይህንን ውክልናም በመጠቀም በአመልካቿ ላይ በመሰረተው ክስም በአመልካች ስም መከላከያ መልስ መስጠቱን መረዳት ይቻላል ፡፡ በመሆኑም አንድ ተወካይ በወኪሉ ላይ በመሰረተው ክስ በወካዩ ስም መልስ ሊያቀርብ ይችላል ወይ ? አቅርቦስ ከሆነ ክርክሩ ወካዩ እንዳቀረበው ሊቆጠር ይችላል ወይ ? የሚሉት ነጥቦች የህግ ትርጉም የሚያስፈልጋቸው ሆነው ተገኝተዋል ::
አንድ ባለጉዳይ ፍ / ቤት መቅረብ የማይፈቅድ ከሆነ ነገሩን ለማስረዳት ፣ ለመከራከር ፣ ለሚጠየቀው ሁሉ በቂ መልስ ለመስጠት የሚችል ሰው በዋናው ባለጉዳይ ተተክቶ በነገረ ፈጅነት ፣ በወኪልነት ፣ በጠበቃነት ሊከራከር እንደሚችል በፍ / ሥ ሥ / ህግ ቁጥር 57 ስር ተገልጿል ፡፡ በመሆኑም አንድ ባለጉዳይ በሚከሰስበትም ሆነ በሚከስበት ጉዳይ ፍ / ቤት መቅረብ ካልፈለገ ወይም ካልቻለ እሱን በመወከል እንዲከራከር ለሌላ ሰው ውክልና መስጠት የሚችል ሲሆን ይህም ውክልና የሚሰጠው ስለውክልና የሚመለከቱትን የፍ / ብሄር ህጉ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ ነው፡፡በመሆኑም አንድ ወኪል የውክልናውን ስራ በሚፈጽምበት ጊዜ እነዚህን የህጉን ድንጋጌዎች በመከተል ይሆናል :: ወኪሉም ከተሰጠው የውክልና ስልጣን ክልል ሳይወጣ በህጉ መሰረት የሚፈጽማቸው ተግባራት ወካዩ ራሱ እንደሚፈጽማቸው ተደርገው ይቆጠራሉ የፍ / ህ / ቁ 2189 ( 1 ) ፡፡ በመሆኑም አንድ ወኪል ስለሌላው ሰው ሆኖ በፍ /
ቤት ክርክር እንዲያቀርብ በተሰጠው የውክልና ስልጣን መሰረት የሚያቀርበው ክርክር ባለጉዳዩ እንዳቀረበው ተደርጎ ይቆጠራል :: ይህ አጠቃላይ መርህ ሲሆን አንድ ሰው ስለሌላ ሰው ሆኖ ክርክር እንዲያቀርብ የውክልና ስልጣን ተሰጥቶት እንኳን ቢሆን ወኪሉ ራሱ ወካዩን በከሰሰበት ጉዳይ ግን በወካዩ ስም ክርክር ሊያቀርብ ይችላል ወይ ? የሚለው ነጥብ ውክልናን ከሚመለከቱ አጠቃላይ የህጉ ድንጋጌዎች እና ከህጉ አላማ ጋር አገናዝቦ ማየቱ ተገቢ ነው ::
ውክልና ማለት ተወካይ የሆነ ሰው ወካዩ ለሆነው ሌላ ሰው እንደራሴ ሆኖ አንድ ወይም ብዙ ህጋዊ ስራዎች በወካዩ ስም ለማከናወን የሚገባበት ውል ነው ( ፍ / ህ / ቁ 2198 ) ፡፡ በመሆኑም አንድ ተወካይ የውክልና ስራ በሚፈጽምበት ጊዜ የወካዩን ህጋዊ ሁኔታዎችን የመለወጥ ስልጣን ተሰጥቶታል :: ይሕም በመሆኑ ተወካዩ ለወካዩ ፍጹም ታማኝ የመሆን እና
የወካዩን ጥቅም ሙሉ ለሙሉ የማስጠበቅ ግዴታ ተጥሎበታል :: ስለሆነም ተወካዩ ስራውን በሚከናውንበት ጊዜ ቅድሚያ ሊሰጥ የሚገባው የወካዩን ጥቅም ብቻ በመሆኑ የጥቅም ግጭት ባለበት ሁኔታ ተወካዩ በስራው አፈጻጸም ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል :: ምክንያቱም የጥቅም ግጭት በሚፈጠርበት ጊዜ አንድ ተወካይ ከራሱ ጥቅም ይልቅ የወካዩን ጥቅም ሊያስቀድም ይችላል ተብሎ አይታሰብም :: ስለዚህም ተወካዩ የራሱን ጥቅም የሚመለከት ጉዳይ ሲያጋጥመው ሁኔታውን ለወካዩ ሳያሳውቅ እና ሳይስማማ ስራውን እንዳይፈጽም ይከለከላል :: ሥለወኪልነት የተደነገጉትን የፍ /
ብር ድንጋጌዎች ስንመለከትም ተወካዩ ከወካዩ ጋር በሚኖረው ግንኙነት ጥብቅ የሆነ ቅን ልቦና ሊኖረው እንደሚገባ እና የውክልና ስልጣኑን የሚያስቀሩ ምክንያቶች ወይም መሻሻል የሚያስፈልጋቸው ነገሮች ሲገኙ ለወካዩ ማሳወቅ እንዳለበት ( ፍ / ብ / ህ / ቁ 2208 ) ፣ ተወካዩ ስራውን የሚፈጽመው በተለይ ለወካዩ ጥቅም ሊሰጥ በሚችል መንገድ ብቻ መሆን እንዳለበት ( ፍ / ብ / ህ / ቁ 2209 ( 1 ) ) ፣ እንዲሁም ተወካዩ በራሱ ስም ከወካዩ ጋር የሚያደርገው ውል ወካዩ ካላጸደቀው በቀር ሊፈርስ እንደሚችል ( የፍ / ህ / ቁ 2188 ) ስር መደንገጋቸው ተወካዩ ለወካዩ ፍጹም ታማኝ መሆን እንዳለበት እና ለወካዩ ጥቅም ብቻ መስራት እንዳለበት ፣ የጥቅም ግጭት ባለበት ጊዜ ሁሉ ሁኔታውን ለወካዩ የማሳወቅ ግዴታ እንዳለበት የሚያስገነዝቡ ናቸው :: በመሆኑም አንድ ተወካይ የጥቅም ግጭት ባለበት ጊዜ ለወካዩ ሳያሳውቅ የሚያከናውነውን ስራ ወካዩ ሊቃወመው የሚችል መሆኑን እና በዚህ ሁኔታ የተከናወነውም ስራም ወካዩ ካላጸደቀው በቀር ወካዩ ራሱ እንደፈጸመው ሊቆጠር እንደማይገባ ከውክልና ግንኙነት አጠቃላይ አላማ እና ከፍ / ብ / ህጉ ድንጋጌዎች መገንዘብ ይቻላል ፡፡
ወደተያዘው ጉዳይ ስንመለስም የአሁኑ 2 ኛ ተጠሪ አመልካች የስር 3 ኛ ተከሳሽ ላይ የመሰረተው ክስ በወኪሉ እና በተወካዩ መሃከል ግልጽ የጥቅም ግጭት ፈጥሯል ፡፡ 2 ኛ ተጠሪም ራሱ ከሳሽ ሆኖ የቀረበበትን ጉዳይ ለአመልካች የገለፀላት መሆኑ እና አመልካቿም ተጠሪው ያቀረበውን መልስ የተስማማችበት ለመሆኑ የተረጋገጠ ነገር የለም ፡፡ አመልካቿ እንዲያዉም ወኪሏ የሰጠውን መልስ ተቃዉማዋለች :: በመሆኑም 2 ኛ ተጠሪ ራሱ በመሰረተው ክስ ለአመልካች ሳያሳውቅ ያቀረበው መከላከያ መልስ ስለወኪልነት የሚመለከቱትን መርሆች እና የህጉ ድንጋጌዎች የሚቃረን በመሆኑ አመልካች በወኪሏ በኩል ክርክር አቅርባለች ማለት አይቻልም :: በዚህም ምክንያት አመልካች በወኪሏ በኩል መልስ ሰጥታ የተከራከረች በመሆኑ በሌለሁበት የተሰጠው ውሳኔ ተነስቶ ወደ ክርክሩ ልግባ በማለት ልትጠይቅ አይገባም በማለት የተሰጠው ብይን የህግ ስህተት አለበት ::
አመልካች በሌለችበት የተሰጠው ውሳኔ ተነስቶ ወደ ክርክሩ ገብታ ፍ /
ቤቱ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የመሰልውን ይወስን ፡፡ የም / ሽ / ዞን ከፍተኛ ፍ /
ቤት በመ / ቁ -13 / 95 በ 17 / 3 / 95 ዓ.ም ፣ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ / ቤት በመ / ቁ 464/95 በ 20 / 6 / 95 ዓ.ም ፣ የኦሮሚያ ፍ / ቤት በመ / ቁ 532/95 በ 3/5/96 ዓ.ም. የሰጡት ትዕዛዞች ተሽረዋል ::
መዝገቡ ተዘግቷል :: ለመ / ቤት ይመለስ ፡፡

You must login to view the entire document.

Enter your email address and password to login.
Please enter a valid email address
Please enter your email address
Please enter your password
Password must be at least 8 characters long
Forgot your password?